ቅዱሳት መጻሕፍት
7.91K subscribers
1.5K photos
61 videos
365 files
855 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
.       ──•◈•─────•◈•─
                 የዕለቱ ጥቅስ 
        ──•◈•─────•◈•─
“እንግዲህ ከወዴት እንደ ወደቅህ አስብ ንስሐም ግባ የቀደመውንም ሥራህን አድርግ፤ አለዚያ እመጣብሃለሁ ንስሐም ባትገባ መቅረዝህን ከስፍራው እወስዳለሁ።”
ራእይ 2፥5



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤11
በቅዱሳት መጻሕፍት ካሉት ወንጌላት መካከል የብሉይ ኪዳን ትንቢት መፈጸም ላይ ትኩረት የሚያደርገው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
16%
ዮሐንስ
15%
ሉቃስ
6%
ማርቆስ
64%
ማቴዎስ
👍6❤2
Audio
ርዕስ፦ የቅዱስ አውግስቲን ኑዛዜ
ክፍል፦ 9
ምንጭ፦ @Reading_Life_1


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤1
የይሁዳ መልእክት ጥናት.pdf
302.9 KB
ርዕስ፦ የይሁዳ መልእክት ጥናት

በኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኢየሱስ ታቦር ማኅበረ ምእመናን የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ዝግጅት አገልግሎት ቡድን የተዘጋጀ

ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study
.       ──•◈•─────•◈•─
                 የዕለቱ ጥቅስ 
        ──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ፥ ይራራልህም፤”
ዘኍልቁ 6፥25


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🥰9🙏5👍2❤1
በቅዱሳት መጻሕፍት ካሉት ወንጌላት ውስጥ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደስቅዩ(እንደተሰቃየ) አገልጋይ የሚያስተዋውቀን መጽሐፍ የቱ ነው
Anonymous Quiz
15%
ዮሐንስ
31%
ሉቃስ
41%
ማርቆስ
13%
ማቴዎስ
❤7👍1
ቅዱሳት መጻሕፍት
በክርስትና ብስለት ማደግ "እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ  ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ እንደግ፤"          ኤፌ. 4፡15 መንፈሳዊ ብስለት ይጠበቅብናል ወይ? •ኤፌ. 4:11-13 "እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፣ ሌሎቹም ነቢያት፣ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፣ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤ ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፣ ሙሉ…
...የቀጠለ
በክርስትና ብስለት ማደግ


ወዴት ነው የምናድገው? የእድገታችን መለኪያው ማን ነው?

"…እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ 
ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ 
እንደግ፤" ኤፌ. 4:15

በመካከላችን ምሳሌ የሚሆኑ ሰዎችና ማህበራት ቢኖሩም…

• "እኔ ክርስቶስን እንደምመስል…"1ቆሮ. 11፡1

• "…እኛንና ጌታን የምትመስሉ ሆናችሁ" 1ኛ ተሰ. 1፡6

• "በይሁዳ የሚኖሩትን በክርስቶስ ኢየሱስ ያሉትን የእግዚአብሔርን ማኅበሮች የምትመስሉ ሆናችኋልና" 1ተሰ. 2፡14

• ሮሜ. 8፡29 "ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፣ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና፤"

ይህን ጉዞ መቼ ጀመርን? መቼስ ይጠናቀቃል?

• ጌታ ኢየሱስን በተቀበልን ጊዜ ወደዚህ ብስለት የምናደርገው ጉዞ ይጀመራል።

• ፊሊ. 3፡12-14 "አሁን እንዳገኘሁ ወይም አሁን ፍጹም እንደ ሆንሁ አይደለም፥ ነገር ግን ስለ እርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ የተያዝሁበትን ያን ደግሞ እይዛለሁ ብዬ እፈጥናለሁ።
ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍ ከፍ 
ያለውን የእግዚአብሔርን መጥራት ዋጋ እንዳገኝ ምልክትን እፈጥናለሁ።"

መንፈሳዊ ብስለት ያልሆነው ነገር ምንድን ነው?

1. መንፈሳዊ ብስለት የእድሜ ጉዳይ አይደለም።

• መንፈሳዊ እድገት ጊዜ፣ ጥረት፣ ወዘተ የሚጠይቅ ጉዳይ መሆኑ የሚስተባበል አይደለም። ማንም ሰው በአንድ ምሽት በሳል አይሆንም (ሉቃ. 2፡52)።

• ማስጠንቀቂያ፦ ሆኖም ግን በጌታ ቤት ረጅም አመታት አስቆጥሮ ሳይበስሉ መክረም ይኖራል። በእግዚአብሔር ቤት 50 እና 60 አመት ያስቆጠሩ መንፈሳዊ ሕጻናት ይኖራሉ። መንፈሳዊ ብስለት በእግዚአብሔር ቤት ጊዚያትን ከመቁጠር ያለፈ ነው።

• ዕብ. 5፥12 "ከጊዜው የተነሳ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ቃላት መጀመሪያ ያለውን የሕፃንነትን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ እንደ ገና ያስፈልጋችኋልና፤ 
የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም።"

2. መንፈሳዊ ብስለት ውጫዊ ጉዳይ አይደለም።

አንዳንድ ሰዎች በውጫዊ ይዘታቸው (ንግግራቸው) በሳል መንፈሳዊያን ሊመስሉ ይችላሉ። መንፈሳዊ ብስለት የኑሮ ጉዳይ እንጂ የንግግር ጉዳይ አይደለም። የመለወጥ እንጂ የመምሰል ጉዳይ አይደለም::

• ሉቃ. 11፡39-42 "ጌታም እንዲህ አለው፦ አሁን እናንተ ፈሪሳውያን የጽዋውንና የወጭቱን ውጭ ታጠራላችሁ፥ ውስጣችሁ ግን ቅሚያና ክፋት ሞልቶበታል እናንት ደንቆሮዎች፥ 
የውጭውን የፈጠረ የውስጡን ደግሞ አልፈጠረምን? ነገር ግን በውስጥ ያለውን ምጽዋት አድርጋችሁ ስጡ፥ እነሆም፥ ሁሉ ንጹሕ ይሆንላችኋል።…"

3. መንፈሳዊ ብስለት የክንውን ጉዳይ አይደለም።

• የአገልግሎት ቦታና የሃላፊነት ብዛትም የብስለት መለኪያዎች አይደሉም።

• ብስለት እውቀት የማከማቸት ጉዳይም አይደለም።

• ሉቃ. 11፡52 "እናንተ ሕግ አዋቂዎች፥ የእውቀትን መክፈቻ ስለ ወሰዳችሁ፥ ወዮላችሁ ራሳችሁ አልገባችሁም የሚገቡትንም ከለከላችሁ።"

4. በመንፈሳዊ ስጦታዎች መሞላት፣ በመንፈሳዊ ስጦታዎች ማገልገል/መጠቀም ማለት አይደለም።

• መንፈስ ቅዱስን መግለጥ፣ ጥበብን መናገር፥ እውቀትን መናገር፣ የመፈወስ ስጦታ፥ ተአምራትን ማድረግ፣ ትንቢትን መናገር፥ መናፍስትን መለየት፥ በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ በልሳኖች 
የተነገረውን መተርጎም…….የመንፈሳዊ ብስለት መለኪያዎች አይደሉም።

ንጽጽር

• 1ቆሮ. 1፡7 "እንደዚህ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን መገለጥ ስትጠባበቁ አንድ የጸጋ ስጦታ እንኳ አይጎድልባችሁም፤"

• 1ቆሮ. 3፡1-3 "እኔም፥ ወንድሞች ሆይ፥ የሥጋ እንደ መሆናችሁ፥ በክርስቶስም ሕፃናት እንደ መሆናችሁ እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ ልናገራችሁ አልቻልሁም። ገና ጽኑ መብል ለመብላት አትችሉም ነበርና ወተት 
ጋትኋችሁ፤ ገና ሥጋውያን ናችሁና እስከ አሁን ድረስ ገና አትችሉም። ቅናትና ክርክር ስለሚገኝባችሁ ሥጋውያን መሆናችሁ አይደላችሁምን?"


ይቀጥላል...


ምንጭ:- tsegaewnet.files.wordpress.com



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤5
Audio
👉ርዕስ፦ የካታኮምቡ ሰማዕት
🗣ትርጉም፦ በአማረ ማሞ
መካነ ኢየሱስ ሥነ ጽሑፍ ክፍል።
📻ሙሉ ትረካ
⏱️አጠቃላይ የሚፈጀው ሰዓት፦ 3:49:45


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል👉 @TME_bible_study
👍5❤1
.       ──•◈•─────•◈•─
                 የዕለቱ ጥቅስ 
        ──•◈•─────•◈•─
“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በመንገድ ላይ ቁሙ ተመልከቱም፥ የቀደመችውንም መንገድ ጠይቁ፤ መልካሚቱ መንገድ ወዴት እንደ ሆነች እወቁ፥ በእርስዋም ላይ ሂዱ፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ እነርሱ ግን፦ አንሄድባትም አሉ።”
ኤርምያስ 6፥16



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤10🙏2
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በትንቢተ ኢሳይያስ "አማኑኤል" ስለሚባለው ልጅ ምልክት እንዲጠይቅ የተነገረ የይሁዳ ንጉሥ ማን ነው?
Anonymous Quiz
9%
ምናሴ
39%
ሕዝቅያስ
28%
አካዝ
23%
ኢዮሳፍጥ
❤4
AI_in_Church_Haylat_032026.pdf
199.1 KB
"ለቤተክርስቲያን የቀረበ መልእክት: AI በአማኞች ልብ ውስጥ እያደረገ ያለው ድምፅ አልባ ወረራ" በዶ/ር ኃይለልዑል ጥበቡ

በዚህ አጭር ጽሁፍ ሰው ሰራሽ አስተውሎት(AI) ለቤተ ክርስቲያን ይዞ የመጣውን ጋሬጣ በማጋራት ፥ ለቤተ ክርስቲያን መጋቢያን አማራጭ መፍትሄ በማቅረብ ቤተ ክርስቲያን በኋላ ይዞ የሚመጣውን እኩይ ነቅሶ በማውጣት በንቃትና በማስተዋል ቴክኖሎጂን እንድትጠቀም ይመክራሉ። ዶ/ር ኃይለልዑል ጥበቡ በአሜሪካ በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ የAI ፕሮፌሰር ሲሆኑ፣ በዘርፉም የዶክትሬት (PhD) ዲግሪ አላቸው።


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
.       ──•◈•─────•◈•─
                 የዕለቱ ጥቅስ 
        ──•◈•─────•◈•─
“ስትሄድም ይመራሃል፤ ስትተኛ ይጠብቅሃል፤ ስትነሣ ያነጋግርሃል።”
ምሳሌ 6፥22


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤13👏1
#እራሳችንን_እንመርምር


“የሎጥን ሚስት አስቡአት።”
ሉቃስ 17፥32

የእግዚአብሔር መንግሥት በሙላት ልትመጣ ነው። ጌታችንም ይህን ታላቅ መምጣቱን ሲያወሳ መጠንቀቅና መትጋት እንደሚገባ ሊያሳስበን የሎጥን ሚስት እንደምሳሌ ይጠቅስልናል። እርሷ ለዚህ ነገር ለምን እንደማስጠንቀቂያ ተጠቀሰች? እስቲ ከእርሷ ጋር ሕይወታችንን እያስተያየን እራሳችንን እንመርምር።


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤8👍3
.       ──•◈•─────•◈•─
                 የዕለቱ ጥቅስ 
        ──•◈•─────•◈•─
“ከክፉ የጎልማሳነት ምኞት ግን ሽሽ፥ በንጹሕም ልብ ጌታን ከሚጠሩ ጋር ጽድቅን እምነትን ፍቅርን ሰላምን አጥብቀህ ተከተል።”
2ኛ ጢሞቴዎስ 2፥22



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤14
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ በነቢዩ ኢሳይያስ “በፊትህ እሄዳለሁ ተራሮችንም ትክክል አደርጋለሁ፥ . . .” ተብሎ ትንቢት የተነገረለት ንጉሥ ማን ነው?
Anonymous Quiz
10%
ኢየሱስ
24%
ዘሩባቤል
50%
ቂሮስ
2%
ሴዴቅያስ
14%
ሕዝቅያስ
❤3👍1
ቅዱሳት መጻሕፍት
https://www.youtube.com/watch?v=vPCNlfNURzA ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
ስለሲኦል ምንነት ጳውሎስ ፈቃዱ የተነተነበት ነው። ይዩትና ከመጽሐፍ ቅዱስና ከቤተክርቲያንዎ አስተምህሮ አንጻር ይፈትሹት። በነገራችን ላይ ይህንን አሳብ እራሱ በጻፈው "የተሰቀለው" በሚለው መጽሐፍ ውስጥ በስፋት ማንበብ ትችላላችሁ
ቅዱሳት መጻሕፍት
...የቀጠለ በክርስትና ብስለት ማደግ ወዴት ነው የምናድገው? የእድገታችን መለኪያው ማን ነው? "…እውነትን በፍቅር እየያዝን በነገር ሁሉ  ወደ እርሱ ራስ ወደሚሆን ወደ ክርስቶስ  እንደግ፤" ኤፌ. 4:15 በመካከላችን ምሳሌ የሚሆኑ ሰዎችና ማህበራት ቢኖሩም… • "እኔ ክርስቶስን እንደምመስል…"1ቆሮ. 11፡1 • "…እኛንና ጌታን የምትመስሉ ሆናችሁ" 1ኛ ተሰ. 1፡6 • "በይሁዳ የሚኖሩትን…
...የቀጠለ
በክርስትና ብስለት ማደግ


መንፈሳዊ ብስለት ምንድን ነው?

•መንፈሳዊ ብስለት ክርስቶስን በባሕሪው መምሰል ማለት ነው።

•መንፈሳዊ ብስለት የጸባይ፣ የዐመል፣ የባሕሪይ ጉዳይ ነው ATTITUDE and CHARACTER. 

•የባሕሪይ ለውጥ እንጂ የዕውቀት ክምችት ጉዳይ አይደለም።

•1ቆሮ. 4፡16 "እንግዲህ እኔን የምትመስሉ ሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ።"

•1ቆሮ. 4፡9-13 "ለዓለም ለመላእክትም ለሰዎችም መጫወቻ ሆነናልና፤ እግዚአብሔር እኛን ሐዋርያቱን ሞት እንደ ተፈረደባቸው ሰዎች ከሁሉ ይልቅ የኋለኞች እንዳደረገን ይመስለኛልና። እኛ ስለ ክርስቶስ ሞኞች ነን እናንተ ግን በክርስቶስ ልባሞች ናችሁ፤ እኛ ደካሞች ነን እናንተ ግን ኃይለኞች ናችሁ፤ እናንተ የከበራችሁ ናችሁ እኛ ግን የተዋረድን ነን። እስከዚህ ሰዓት ድረስ እንራባለን፥ እንጠማለን፥ እንራቆታለን፥ እንጐሰማለን፥ እንንከራተታለን፥ በገዛ እጃችን እየሠራን እንደክማለን፤ ሲሰድቡን እንመርቃለን፥ ሲያሳድዱን እንታገሣለን፥ ክፉ ሲናገሩን እንማልዳለን፤ እስከ አሁን ድረስ የዓለም ጥራጊ የሁሉም ጉድፍ ሆነናል።"

• ፊሊ. 3፡10-11 "የክርስቶስንና የትንሳኤውን ሃይል እንዳውቅ፣ በስቃዩ ተካፋይ እንድሆንና፣ በሞቱም እርሱን እንድመስል እመኛለው።"

እንዴት ነው በመንፈስ እየበሰልን የምናድገው?

1. የማደግ ጥልቅ ፍላጎት

ሀ) ለማደግ ካልፈለግን አናድግም፤ ለመሄድ ካልተነሳን አንደርስም።

•መዝ. 34፡10 "…እግዚአብሔርን የሚፈልጉት ግን ከመልካም ነገር ሁሉ አይጐድሉም።"

•መዝ. 105፡4 "እግዚአብሔርን ፈልጉት ትጸናላችሁም ሁልጊዜ ፊቱን ፈልጉ።"

•ሶፎ. 2፡3 "…እግዚአብሔርን ፈልጉ ጽድቅንም ፈልጉ፥ ትሕትናንም ፈልጉ …"

•ማቴ. 6፡33 "ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥት ጽድቁንም ፈልጉ፥ … "

•ማቴ. 7፡7 "ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል።"

•ዕብ. 2፡14 "ከሰው ሁሉ ጋር ሰላምን ተከታተሉ ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፥ ያለ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና።"

ለ) አንዳንድ ሰዎች መንፈሳዊ ሕጻንነትን ይፈልጉታል

•ሃላፊነት የሌለበት በመሆኑ

•ሁሉ ስለሚመግባቸው/ቁጭ ብሎ መመገብ ምቹ ስለሆነ

•ማስተማር፣ መገሰጽ፣ ወዘተ ስለማይጠበቅባቸው


ሐ) አንዳንዶች ደግሞ የማደግ ጎዞ ጀምረው ቀድሞ የነበራቸውን የእድገት ፍላጎት በጉዞ መሃል ያጣሉ

•በእሳት ጀምረው ይቀዘቅዛሉ፣ በቅንአት ጀምረው ይዝላሉ፣ ማመቻመች፣ መሃል ሰፋሪ መሆን፣ ግዴለሽነት
የዚህ መቀዛቀዝ ምልክቶች ናቸው::

•ራዕ. 2፡4 "ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና።"

•ራዕ. 3፡15-16 "በራድ ወይም ትኩስ እንዳይደለህ ሥራህን አውቃለሁ። በራድ ወይም ትኩስ ብትሆንስ መልካም በሆነ ነበር። እንዲሁ ለብ ስላልህ በራድም ወይም ትኩስ ስላልሆንህ ከአፌ ልተፋህ ነው።"

መ) ሌሎች ደግሞ፣ በደረሱበት የእድገት ደረጃ ይረካሉ::

•ፊሊ. 3፡12-14 "አሁን እንዳገኘሁ ወይም አሁን ፍጹም እንደ ሆንሁ አይደለም፥ ነገር ግን ስለ እርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ የተያዝሁበትን ያን ደግሞ እይዛለሁ ብዬ እፈጥናለሁ። ወንድሞች ሆይ፥ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቈጥራለሁ፤ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ፤ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ፥ በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍ ከፍ ያለውን የእግዚአብሔርን መጥራት ዋጋ እንዳገኝ ምልክትን እፈጥናለሁ።"

•ራዕ. 3፡17-18 "ሀብታም ነኝና ባለጠጋ ሆኜአለሁ አንድም ስንኳ አያስፈልገኝም የምትል ስለ ሆንህ፥ ጐስቋላና ምስኪንም ድሀም ዕውርም የተራቆትህም መሆንህን ስለማታውቅ፥ ባለ ጠጋ እንድትሆን በእሳት የነጠረውን ወርቅ፥ ተጐናጽፈህም የራቁትነትህ ኃፍረት እንዳይገለጥ ነጭ ልብስን፥ እንድታይም ዓይኖችህን የምትኳለውን ኵል ከእኔ ትገዛ ዘንድ 
እመክርሃለሁ።"

•ጴጥሮስ ኢየሱስን ሊክድ የማይችልበት መንፋዊ ከፍታ ላይ እንደደረሰ ተሰማው

•1ቆሮ. 10፡12 "ስለዚህ እንደ ቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ።"

•ክርስቲያኖች ከማያድጉበት ምክንያቶች አንዱ፣ የማደግ አስፈላጊነት ስለማይታያቸው ነው።

•ጌታን ለማገልገል በውስጥህ የሚቀጣጠል የፍላጎት እሳት አለ?

•ልትደርስባቸው ያስቀመጥቃቸው ግቦች አሉህ?


ይቀጥላል...


ምንጭ:- tsegaewnet.files.wordpress.com


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤3👍3
.       ──•◈•─────•◈•─
                 የዕለቱ ጥቅስ 
        ──•◈•─────•◈•─
“በወንጌልም ማኅበረተኛ እሆን ዘንድ ስለ ወንጌል ሁሉን አደርጋለሁ።”
1ኛ ቆሮንቶስ 9፥23


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
❤8🔥5
በቅዱሳት መጻሕፍት ውስጥ ኢየሱስ ስለሚወለድበት ከተማ (ቤተልሔም) ትንቢት የተናገረው ነቢይ ማን ነው?
Anonymous Quiz
53%
ኢሳይያስ
22%
ሚክያስ
12%
ሚልክያስ
7%
ኤርምያስ
6%
ኢዩኤል
❤3
ቅዱሳት መጻሕፍት
...የቀጠለ በክርስትና ብስለት ማደግ መንፈሳዊ ብስለት ምንድን ነው? •መንፈሳዊ ብስለት ክርስቶስን በባሕሪው መምሰል ማለት ነው። •መንፈሳዊ ብስለት የጸባይ፣ የዐመል፣ የባሕሪይ ጉዳይ ነው ATTITUDE and CHARACTER.  •የባሕሪይ ለውጥ እንጂ የዕውቀት ክምችት ጉዳይ አይደለም። •1ቆሮ. 4፡16 "እንግዲህ እኔን የምትመስሉ ሁኑ ብዬ እለምናችኋለሁ።" •1ቆሮ. 4፡9-13 "ለዓለም…
...የቀጠለ
በክርስትና ብስለት ማደግ


እንዴት ነው በመንፈስ እየበሰልን የምናድገው?

2. መንፈሳዊ ምግብ

•አንድ ሕጻን ያለበቂ ምግብ ማደግ አይችልም። እንዲሁ ያለ እግዚአብሔር ቃል መንፈሳዊ ሕይወታችን ሊያድግ አይችልም።

•ማቴ. 4፡4 "ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም…"

•1ጴጥ. 2፡2-3 "…ለመዳን በእርሱ እንድታድጉ አሁን እንደ ተወለዱ ሕፃናት ተንኰል የሌለበትን የቃልን ወተት ተመኙ።"

• መዝ. 1፡1-2 "ምስጉን ነው በክፉዎች ምክር ያልሄደ፥ በኃጢአተኞችም መንገድ ያልቆመ፥ በዋዘኞችም ወንበር ያልተቀመጠ። ነገር ግን በእግዚአብሔር ሕግ ደስ ይለዋል፥ ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል።"

•2ጢሞ. 3፡16-17 "የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት 
በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።"

•ኤፌ. 6፡17 "የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።"

• ቆላ. 3፡16 "የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ።"

•ይህን ምግብ በበቂ ለማግኘት መጽሐፍ ቅዱስ ማጥናት እና በክርስቲያናዊ ስብሰባዎች ላይ
መገኘት ያስፈልጋል::

ለእግዚአብሔር ቃል ያለህን አፕታይት/ፍላጎት ለመለካት የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልስ

•በዚህ ሳምንት ምን ያህሉን ሰአት ቲቪ በማየት አጠፋህ?

•ምን ያህሉን ጊዜ አዝናኝ ጋዜጣዎችን ወይም መጽሔቶችን በማንበብ አጠፋህ?

•ምን ያህሉን ጊዜ ሶሻል ሚዲያዎችን በመጠቀም፣ ከሰው ጋር የባጥ የቆጡን ስታወራ አሳለፍክ?

•ምን ያህል ሰአት መጽሐፍ ቅዱስህን ለማጥናት ተጠቀምክ?


3. ልምምድ

•አትሌቶችና ልምምድ ያለውን ትልቅ ዋጋ ጠንቅቀው ያውቃሉ።

•ክህሎትን ለማዳበር ያልተቁዋረጠ ልምምድ ማድረግ የግድ ነው። ምሳሌ፣ ባስኬት ቦል

•ሕጻናት ለመቆም አበክረው መለማመድ ይኖርባቸዋል።

•ልምምድ ለመንፈሳዊ እደገት ወሳኝ ነው።

•1ጢሞ. 4፡7-8 "ነገር ግን ለዚህ ዓለም ከሚመችና የአሮጊቶችን ሴቶች ጨዋታ 
ከሚመስለው ተረት ራቅ። እግዚአብሔርን ለመምሰል ግን ራስህን አስለምድ። ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።"

• ዕብ. 5፡14 (አ.መ.ት.) "ጠንካራ ምግብ ግን መልካሙንና ከክፉውን ለመለየት ራሳቸውን ላስለመዱ፣ ለበሰሉ ሰዎች ነው።"

• ለማስተማር፣ ለመዘመር፣ መጽሐፍ ቅዱስን በአግባቡ ለመረዳት፣ ለመጸለይ፣ ወዘተ ልምምድ ይጠይቃል።

4. ጊዜ እና ትዕግስት

•እድገት ጊዜን ይጠይቃል፣ ሂደት ነውና። የሂደት ጉዞ ደግሞ ያለ ትዕግስት የሚሞከር ጉዞ አይደለም::

•ግብህ ላይ በአንድ ለሊት ለመድረስ አትመኝ። ሕጻናት በአንድ ለሊት ሙሉ ሰው አይሆኑምና። ግብ የብዙ ልምምድ እና ትዕግስት ድምር ውጤት ነው።

•ያዕ. 1፡4 (አ.መ.ት.) "ምንም የማይጎድላችሁ ፍጹማንና ምሉዓን እንድትሆኑ ትዕግሥት ሥራውን 
ይፈጽም።"

• ዕብ. 10፡36 "የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ መጽናት ያስፈልጋችኋልና።"

• መክ. 3፡1 "ለሁሉ ዘመን አለው፥ ከሰማይ በታችም ለሆነ ነገር ሁሉ ጊዜ አለው።"

• መክ. 3፡11 "ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው …።"



ይቀጥላል...


ምንጭ:- tsegaewnet.files.wordpress.com



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️ላ🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍4❤1