ቅዱሳት መጻሕፍት
7.38K subscribers
1.33K photos
61 videos
331 files
784 links
በዚህ ቻናል

👉ቅዱሳት መጻሕፍት ይጠናሉ::
👉መጽሐፍ ቅዱሳዊ ትምህርቶች ይቀርባሉ::
👉 ለቅዱሳት መጽሐፍት ጥናት የሚያግዙ መጻሕፍት ይለቀቃሉ።

⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

@Holy_scriptures
Download Telegram
.       ──•◈•─────•◈•─
                   🌼 የዕለቱ ጥቅስ  🌼
        ──•◈•─────•◈•─
“የክብር አባት የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እርሱን በማወቅ የጥበብንና የመገለጥን መንፈስ እንዲሰጣችሁ እለምናለሁ።”
ኤፌሶን 1፥17



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
8🙏5
ቅዱሳት መጻሕፍት
#እምነት                  ክፍል-17 የእምነት አይነቶች 1. የሚያድን እምነት ይህ እምነት በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ድነትን የሚያስገኝ ነው። “ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤” (ኤፌሶን 2፥8) 2. ትንሽ እምነት ደካማ ወይም የሚናወጥ እምነት፤ ብዙ ጊዜ በፍርሃት ወይም በጥርጣሬ በጭንቀት ቅርቃር ውስጥ የሚገባ ነው። …
#እምነት


                 ክፍል-18


እምነታችንን እንዴት ማሳደግ እንችላለን?


1. የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት እና በማሰላሰል

" እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።" (ሮሜ 10፥17)

ራሳችንን ለእግዚአብሔር እውነት ባጋለጥን መጠን በእግዚአብሔር መታመናችን እና እምነታችን እየጎለበተ ይሄዳል።

2. በጸሎት ወይም እግዚአብሔር እምነታችን እንዲጨምርልን በመለመን።

“ሐዋርያትም ጌታን፦ እምነት ጨምርልን አሉት።” ( ሉቃስ 17፥5 )

እምነት የሚያድገው በትሕትና በእግዚአብሔር ስንታመን ነው።

3. ፈተናዎችን በመቋቋም

“ወንድሞቼ ሆይ፥ የእምነታችሁ መፈተን ትዕግሥትን እንዲያደርግላችሁ አውቃችሁ፥ ልዩ ልዩ ፈተና ሲደርስባችሁ እንደ ሙሉ ደስታ ቍጠሩት” ( ያዕቆብ 1፥2-3 )

ተግዳሮቶች እምነታችንን ያሰፋሉ፤ የእምነታችንን እውነተኛነት ያረጋግጣሉ እና ጠንካራም ያደርጉታል። ያልተፈተነ እምነት የእድገት ደረጃው አይታወቅም።

4. በኅብረት እና በመበረታታት

"ይህንም ማለቴ በመካከላችን ባለች በእናንተና በእኔ እምነት አብረን በእናንተ እንድንጽናና ነው።" ( ሮሜ 1፥12)

እርስ በርሳችን በክርስቶስ ስንገነባ እምነታችን ያድጋል።

5. እምነትን በተግባር በማዋል (ታዛዥነት)

"ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።” ( ያዕቆብ 2፥26 )

ያመነውን ነገር መተግበር እምነታችንን ያጠናክራል።


ይቀጥላል...




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
17
.       ──•◈•─────•◈•─
                   🌼 የዕለቱ ጥቅስ  🌼
        ──•◈•─────•◈•─
“ለእነዚያ ደግሞ እንደ ተነገረ ለእኛ የምስራች ተሰብኮልናልና፤ ዳሩ ግን የሰሙት ቃል ከሰሚዎቹ ጋር በእምነት ስላልተዋሐደ አልጠቀማቸውም።”
ዕብራውያን 4፥2




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6👍1
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3
የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ክርስትና.pdf
935.5 KB
👉ርዕስ፦ የመጽሐፍ ቅዱሳዊ ክርስትና
የጥናት መምሪያና ማብራሪያ
ጸሐፊ፦ ዶ/ር ዊልበር አዶኖቫን
🗣ትርጉም፦ ግርማዊ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
7
.       ──•◈•─────•◈•─
                   🌼 የዕለቱ ጥቅስ  🌼
        ──•◈•─────•◈•─
“ስለዚህም ምክንያት ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፥”
2ኛ ጴጥሮስ 1፥5



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
14
ከሰማይ እውቀት መጉደል



ከሰማያዊ እውቀት መጉደል የሚያመጣውን መምታታት፣ የሚፈጥረውን የማስተዋል እጦት፣ የሚጥለውን የጉዳት ጠባሳ፣ የሚያስቀረውን መለኮታዊ ጸጋ፣ ተመትቶ ማንከስ ወይም ተቆርጦ መንገድ ላይ መቅረትን ለመገንዘብ በግልጽ ከአይሁድ የህይወት ተሞክሮ በማየት መማር እንችላለን፡፡ ሰማያዊ እውቀት ምንድነው? የእውቀቱ መታጣት እንዴት አስከፊ ቢሆን ነው የዚህን ያህል ጉድለትና ጥፋት የሚያስከትለው? የምንል ልንኖር እንችላለን፡፡ ቅድሚያ በዘኊ.24:15-16 ላይ የሚገኘው በለአም የተባለ ሰው ስለ መለኮታዊ እውቀት ያስተዋለውን ነገር እንመለከታለን፡-

”የቢዖር ልጅ በለዓም እንዲህ ይላል፥ ዓይኖቹም የተከፈቱለት ሰው እንዲህ ይላል፤ የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማ፥ የልዑልንም እውቀት የሚያውቅ፥ ሁሉን የሚችል የአምላክን ራእይ የሚያይ፥የወደቀው፥ ዓይኖቹም የተከፈቱለት እንዲህ ይላል።…”

ከላይ ባለው ጥቅስ መሰረት ሰማያዊ እውቀት መለኮታዊ እውቀት/የልዑል እውቀት እንደሆነ እንመለከታለን፡፡ እውቀት የሚባል የሰው ልጅ ነፍስ ልታስተውለው የተገባ ይህ መለኮታዊ እውቀት አስፈላጊነቱ ከፍ ያለ ነው፡፡ ነፍሳችን አምላኩዋን ታውቅ ዘንድ ከፈጠራት ከርሱ የተላለፈ ትእዛዝ በመሆኑ እርሱን ባለማወቅዋ የሚከተላት ጥፋትና እጦት እስከ ሞት የሚያደርሳት ነው፡፡ በለአም ግን የእግዚአብሔርን ቃል ሲሰማ የልዑልን እውቀት እንዳወቀ ዓይኖቹም ሲከፈቱለት ሁሉን የሚችል የአምላክን ራእይ እንዳየ ይመሰክራል፡፡ ነቢዩም በኢሳ.43:10 የእግዚአብሄርን ድምጽ እንዲህ ያስተላልፋል፡-

”ታውቁና ታምኑብኝ ዘንድ እኔም እንደሆንሁ ታስተውሉ ዘንድ፥ እናንተ የመረጥሁትም ባሪያዬ ምስክሮቼ ናችሁ ይላል እግዚአብሔር፤ ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም ከእኔም በኋላ አይሆንም።”

ሰው ላለመፍራት ዋስትናው ምንድነው? ቃሉ በግልጽ እንደሚለን እርሱን ማወቅ ነው፤ እውቀቱም ምድራዊ ሳይሆን መለኮታዊ ነው፡፡ ነፍስን ከዘላለም ህይወት ያጎደላት ያለማስተዋል ዋና ከአምላክዋ የመለየትዋ ችግር ከሆነ እርሱን በማወቅ መንቃትና ከእርሱ ጋር ዳግም መገናኘት በሆነላት ወቅት መዳንን ትጎናጸፋለች ማለት ነው፡፡
እግዚአብሄር ለእስራኤላውያን አትፍሩ እኔ አምላካችሁ ነኝ ሲል ያጽናናቸዋል፡፡ እነዚህ ህዝቦች በእግዚአብሄር ተመርጠው ሳለ በሆነ ወቅት ከእርሱ ኮብልለው በባእድ አማልክት ስር ሲወድቁና ለጠላቶቻቸው ተላልፈው ሲሰጡ እጅግ ተስፋ ያጡና የተጠቁ ሆነው ይኖሩ ነበር፡፡ እግዚአብሄርም ይሄን አይቶ እኔን እወቁና ወደ እኔ ተመለሱ እንጂ የሚያስፈራችሁ አንዳች ጠላት ሊኖር አይችልም የሚል ዋስትና ሲሰጣቸው እንመለከታለን፡፡ እኛም ብንሆን ከሰማይ እውቀት ጎድለን ያለተስፋና ያለአምላክ ሆነን በባእድ አምላክ የጨለማ ጥላ ድንጉጥ ከመሆን እርሱን በማወቅና በማመን ዋስትናውን ማግኘት አለብን፡፡

የእስራእል መዳን የተቋጠረበት እውቀት
እግዚአብሄር ድምጹን ልኮ ህዝቡን ባስተማራቸው ዘመን ሁሉ እርሱን የሚያውቁበትን መንገድ ገልጦላቸው ነበር፡፡ በየዘመናቱ በተነሱት ትውልዶች ውስጥ ግን መለኮታዊውን ትምህርት የሚበርዙ አሳሳቾች መነሳታቸው ስላልቀረ እግዚአብሄር ከነዚያ አሳቾች ህዝቡን ነጻ ያወጣ ዘንድ ነቢያትን አስነስቶ ሰማያዊውን እውቀት ደጋግሞ ልኮአል፡፡ በይሁዳ ነገሥታት በዖዝያንና በኢዮአታም በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን የአሞጽ ልጅ ኢሳይያስ ተነስቶ መለኮታዊውን እውቀት ለህዝቡ ያውጅ ነበር። እግዚአብሔር ተናግሮአልና ሰማያት ስሙ፥ ምድርም አድምጪ… ሲልም ተናግሮአል፡፡(ኢሳ.1:1) ህዝቡም የእግዚአብሄርን ነገር ያስተውል ዘንድ መመልከት የነበረበት፣ እንዲሁም ማወቅና ማመን ያለበት የእግዚአብሄር ነገር ምን እንደነበር ሲያሳይ እንዲህ ይል ነበር፡-

• የእግዚአብሄር ምክርና ብርቱ እጅ ከጠላትና ከፈተና ያድናቸው ዘንድ እንዳለው ሊያውቁና ሊያምኑ ይገባል

ኢሳ.43:1-3 ”አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ። በውኃ ውስጥ ባለፍህ ጊዜ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፥ በወንዞችም ውስጥ ባለፍህ ጊዜ አያሰጥሙህም፤ በእሳትም ውስጥ በሄድህ ጊዜ አትቃጠልም፥ ነበልባሉም አይፈጅህም። እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር መድኃኒትህ ነኝ፤ ግብጽን ለአንተ ቤዛ አድርጌ፥ ኢትዮጵያንና ሳባንም ለአንተ ፋንታ ሰጥቻለሁ።”

ህዝቡ በዚህ እወቀት ሲገነቡ እርሱ የአባታቸው የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር መድኃኒታቸው መሆኑን ስለሚያምኑ አባቶቻቸውን በረዳበት ክንድ እነርሱም መረዳት እንደሚችሉ ያስተውላሉ፡፡

• እግዚአብሄር ህዝቡን እንደሚወድ ሊያውቁ የተገባ ነው

ኢሳ.43:4 ”በዓይኔ ፊት የከበርህና የተመሰገንህ ነህና፥ እኔም ወድጄሃለሁና ስለዚህ ሰዎችን ለአንተ አሕዛብንም ለነፍስህ እሰጣለሁ።”

እግዚአብሄር እንደሚወዳቸው እንዲያውቁ የሚያስፈሩና የሚያስደነግጡዋቸው ነገስታቶችን ማርኮ ከእግራቸው በታች ሊያደርግ እንዳለው በማመልከት ተናግሮአቸዋል፡፡

• እግዚአብሄር ከህዝቡ ጋር እንደሆነና ለህዝቡ ምርኮን ሁሉ እንደሚመልስ ሊያውቁ ይገባል

ኢሳ.43:5-7 ”እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ ዘርህንም ከምሥራቅ አመጣዋለሁ፥ ከምዕራብም እሰበስብሃለሁ። ሰሜንን፡- መልሰህ አምጣ፥ ደቡብንም፡- አትከልክል፤ ወንዶች ልጆቼን ከሩቅ ሴቶች ልጆቼንም ከምድር ዳርቻ፥ በስሜ የተጠራውን ለክብሬም የፈጠርሁትን፥ የሠራሁትንና ያደረግሁትን ሁሉ አምጣ እለዋለሁ።”

ይቀጥላል...



ምንጭ፦ tsionvoice.com




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
6
በዮሐንስ ራእይ መልእክት ከተጻፈላቸው 7ቱ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ከጌታ ዘንድ አንድም ሙገሳ ወይም አድናቆት ያልተነገረው ቤተክርስቲያን የቱ ነው?
Anonymous Quiz
12%
ሀ. ትያጥሮን
53%
ለ. ሎዶቅያ
13%
ሐ. ጴርጋሞን
11%
መ. ሰርዴስ
11%
ሠ. ሰምርኔስ
🤯1
.       ──•◈•─────•◈•─
                   🌼 የዕለቱ ጥቅስ  🌼
        ──•◈•─────•◈•─
“ከሳሙኤልም ዘንድ ለመሄድ ፊቱን በመለሰ ጊዜ እግዚአብሔር ሌላ ልብ ለወጠለት፤ በዚያም ቀን እነዚህ ምልክቶች ሁሉ ደረሱለት።”
1ኛ ሳሙኤል 10፥9



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🙏71👍1
ቅዱሳት መጻሕፍት
#እምነት                  ክፍል-18 እምነታችንን እንዴት ማሳደግ እንችላለን? 1. የእግዚአብሔርን ቃል በመስማት እና በማሰላሰል " እንግዲያስ እምነት ከመስማት ነው መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።" (ሮሜ 10፥17) ራሳችንን ለእግዚአብሔር እውነት ባጋለጥን መጠን በእግዚአብሔር መታመናችን እና እምነታችን እየጎለበተ ይሄዳል። 2. በጸሎት ወይም እግዚአብሔር እምነታችን እንዲጨምርልን…
#እምነት


                 ክፍል-19

በእምነት እና በጸጋ መካከል ያለው ግንኙነት

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ፣ ጸጋ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች የማይገባቸውን በነጻ እንዲሁ የሰጠበትን የሚገልጽ ቃል ነው፤ በጌታችን እና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በነጻ የተሰጠ ስጦታ ነው። እምነት ግን ያንን ጸጋ ለመቀበል የሰው ምላሽ ነው።

1. ጸጋ እንደ እግዚአብሔር ስጦታ

ጸጋ ከእግዚአብሔር የተገኘ እንጂ በሥራ ወይም በሰው ጥረት የሚገኝ አይደለም። የሰውን ልጅ ለማዳን እግዚአብሔር በራሱ ፍላጎት እና ተነሳሽነት የሚሰጠው ነው (ኤፌሶን 2፥8-9)።

2. እምነት እንደ ምላሽ

እምነት ሰዎች የእግዚአብሔርን ጸጋ የሚቀበሉበት እና ከእግዚአብሔር አሳብ ጋር የሚስማሙበት መንገድ ነው። ያለ እምነት አንድ ሰው የጸጋን ጥቅሞች ሙሉ በሙሉ መቀበል ወይም ማግኘት አይችልም (ሮሜ 5፥1-2)።

3. የጸጋ እና የእምነት ግንኙነት

ጸጋ የመዳንን ስጦታ ይሰጣል፣ እምነት ደግሞ መዳንን የምንቀበልበት መንገድ ነው። ጸጋው ምንጭ ነው፤ እምነት መሳሪያ ነው።
ሐዋርያው ጳውሎስ “እንዲያው በጸጋው ይጸድቃሉ” (ሮሜ 3፥24) እና ደግሞ “በእምነት ከጸደቅን” (ሮሜ 5፥1) በማለት ይህን አጽንዖት ሰጥቷል። እነዚህ አባባሎች በአንድነት መጽደቅ፣ በጸጋው በእምነት በኩል መሆኑን ያሳያሉ።

4. እምነት ጸጋን አይተካም።

እምነት መዳንን አያገኝም ጸጋው ያቀረበውን በቀላሉ ይቀበላል እንጂ። ጆን ካልቪን ጠቅለል አድርጎ እንዳስቀመጠው፣ እምነት የጸጋን ስጦታ ለመቀበል እንደ ተዘረጋ ባዶ እጅ ነው።

በቀጣይ ስለጸጋ እና እምነት በአርሜንያን እና በሉተራን አመለካከት መሠረት እንመለከታለን።


ይቀጥላል...


ምንጭ፦
Calvin, J. (1960). Institutes of the Christian religion (J. T. McNeill, Ed.; F. L. Battles, Trans.). Westminster John Knox Press.

Grudem, W. (1994). Systematic theology: An introduction to biblical doctrine. Zondervan.




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍54🔥1🤯1
ከወንጌላት ውስጥ በአረማዊ (አይሁዳዊ ባለሆነ) ሰው እንደተጻፈ የሚታመነው መጽሐፍ የቱ ነው?
Anonymous Quiz
12%
ሀ. ማቴዎስ
17%
ለ. ማርቆስ
63%
ሐ. ሉቃስ
8%
መ. ዮሐንስ
3🔥1
.       ──•◈•─────•◈•─
                   🌼 የዕለቱ ጥቅስ  🌼
        ──•◈•─────•◈•─
“የእምነታችን ጀማሪና ፍጹም አድራጊ የሆነውን ኢየሱስን እንመልከት፤ እርሱ በፊቱ ስላለው ደስታ መስቀሉን ታግሦ፣ የመስቀሉንም ውርደት ንቆ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአል።”
ዕብራውያን 12፥2 (አዲሱ መ.ት)




ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
10
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
3
Mere_Christianity_a_revised_and_amplified_edition,_with_a_new_introduction.pdf
772.4 KB
"Mere Christianity" ሲኤስ ሊዊስ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ካደረጋቸው ተከታታይ የቢቢሲ የሬዲዮ ንግግሮች የተወሰደ ሲሆን ተጠቃሽ የክርስቲያን እቅበተ-እምነት ስራ ነው። በውስጡም፣ ሌዊስ የክርስትናን ዋና እምነቶች ያብራራል እና ይሟገታል። “ብቸኛው” ወይም ሁሉም ቤተ እምነቶች የሚጋሩት አስፈላጊ ክርስትና ክፍል ላይ ትኩረት ያደረገ መጽሐፍ ነው። አላማው ለአንድ ቤተ እምነት መሟገት ሳይሆን በእግዚአብሔርና በኢየሱስ ክርስቶስ ለማመን የሚያስችል ምክንያታዊ መሠረት ማቅረብ ነው።


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
5
.       ──•◈•─────•◈•─
                   🌼 የዕለቱ ጥቅስ  🌼
        ──•◈•─────•◈•─
“የጌታውንም ፈቃድ አውቆ ያልተዘጋጀ እንደ ፈቃዱም ያላደረገ ያ ባሪያ እጅግ ይገረፋል፤”
ሉቃስ 12፥47



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍71
#እራሳችንን_እንመርምር


መንፈሣዊ ነገርን መመርመር ሥጋዊነት ወይስ መንፈሣዊነት?

“ሁሉን ነገር ፈትኑ፤ መልካም የሆነውን ያዙ፤”
1ኛ ተሰሎንቄ 5፥21 (አዲሱ መ.ት)

“ሁለት ወይም ሦስት ነቢያት ይናገሩ፤ ሌሎቹ ደግሞ የተነገረውን በጥንቃቄ ይመዝኑ።”
1ኛ ቆሮንቶስ 14፥29 (አዲሱ መ.ት)



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
4
ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
👍3
የብሉይ_ኪዳን_የጥናት_መምሪያና_ማብራሪያ.pdf
21.8 MB
ርዕስ፦ የብሉይ ኪዳን መምሪያና ማብራሪያ
1ኛ መጽሐፍ
ጸሐፊ፦ ቲም ፌሎስ


ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🔥64
.       ──•◈•─────•◈•─
                   🌼 የዕለቱ ጥቅስ  🌼
        ──•◈•─────•◈•─
“በአፉ ነገር ላይ ዓመፅ አድርጌአለሁና እግዚአብሔር ጻድቅ ነው። እናንተ አሕዛብ ሁሉ፥ እባካችሁ፥ ስሙ መከራዬንም ተመልከቱ፤ ደናግሎቼና ጐበዛዝቴ ተማርከው ሄዱ።”
ሰቆ. 1፥18



ወደ ቻናሉ ለመ🀄️🀄️ል፦ @Holy_scriptures
🙏43
ከሚከተሉት ሰዎች፣ ቅዱሳት መጻሕፍት ጸሐፊዎች ለግለሰብ ከላኩት መልእክት ውስጥ የማይገኘው የቱ ነው?
Anonymous Quiz
8%
ሀ. ፊሊሞና
29%
ለ. ቴዎፍሎስ
3%
ሐ. ቲቶ
5%
መ. ጢሞቴዎስ
56%
ሠ. መልስ የለም
2