ጤናማ ህይወት በእግዚአብሔር ቃል
183 subscribers
33 photos
1 video
3 files
13 links
እንግድህ፡... አንተ፥በክርስቶስ ፥ኢየሱስ፥ባለው ፥ፀጋ፥ በርታ። ብዙ ሰዎች፥ የመሰከሩለትን፤ ከእኔም ደግሞ፥የሰመሀውን፤ሌሎቹን፥ሊያስተምሩ፥ለሚችሉ፥ለታመኑ፥ሰዎች፥አደራ፥ስጥ።
2ጢሞቴዎስ 2፥1-2
Download Telegram
ኢዲ አሚኒን እወደዋለሁ

(በእሳትና በስደት ውስጥ የወንጌልን አሸናፊነትን የሚያሳይ ድንቅ ታሪክ)

ክፍል ሶስት

ደራሲ፡ አቡነ ፊስቶ ኪቬንጌሪ

ትርጉም፡ ገለታው ፈንታ

አዘጋጅ፡ @Bito45tesfu44

ለትረካ እንዲመች የተወሰነ ማስተካከያ ተደርጎበታል።

°°°°°°°°°°°°°°°°
አቡነ ፊሰቶ ለተሰበሰቡት ምዕመን ‹‹ ትርምስ በበዛበት በሞላው ዩጋንዳ በሚገኙ ቀበሌዎችና ከተሞች ተስፋ የሚጣልበትና የብርታት ምንጭ ሊሆን የሚችለው ጌታ ብቻ ነው፡፡ ፍራቻ በተሞላችና ተስፋ ባጣች ሀገር የእግዚአብሔርን ፍቅር እርስ በእርስ ከመለዋወጥ በስተቀር ሌላ መፍትሄ የለም፡፡›› አሉ

በብዙ ትርምስ ውስጥ ያሉት እንአቡነ ፊስቶ ከአዲሱ ፕሬዝዳንት ተዓምር መጠበቃቸውን አላቆሙም፡፡ በዚህ ሁሉ ላይ በእንቅርት ላይ ጆር ደግፍ እንዲሉ በቤተክርስቲያን ሽማግሌዎች መካከል ሰላም ጠፋ መከፋፈላቸውም ገሃድ እየሆነ መጣ፡፡ ይህም ወሬ ለአዲሱ ፕሬዝዳንት ለኢድ አሚን ጆሮ ደረሠ።

      አስቸኳይ በተጠራው የቤተክርስቲያን ስብሰባ ላይ አንድ ዲያቆን ‹‹ወደድንም ጠላንም ከቤተክርስቲያን የመለያ ጊዜ አኹን ነው አብረን መሆን የምንችልበት አቅም የለንም መለየት አለብን›› አለ

አንደኛውም ካህን ‹‹ከህብረቱ ጋር ምንም አይነት ንግግር ማድረግ እንደማይፈልጉ›› አሳወቀ

በዲያቆናትና በካህናት የተከፋፈለች ቤተክርስቲያን በዩጋንዳ መታየት ጀመረ ይህም ነገር ለፕሬዝዳንት ኢድ አሚን ጆሮ የደረሰ ሲሆን ኢድ አሚንም ምላሽ ለመስጠት አልዘገዩም የሚገርምና ማስጠንቀቂያ አዘል አጭርና ግልፅ መልዕክት ላኩ መልዕክቱም እንዲህ የሚል ነበር ‹‹እኔ የዩጋንዳ ፕሬዝዳንት ኢድ አሚን በምድሬ ዩጋንዳ በካህናትና በዲያቆናት መካካል የተከፈለች ቤተክርስቲያን እንድትኖር ፈፅሞ አልፈቅድም፡፡››

ከዚህ ከኢድ አሚንን መልዕክት በኋላ ህዳር 26 1971 ስብሰባ ተጠራ። በቤተክርስቲያን መካከል የተከሰተው መከፋፈል ላይ ብዙ ተነጋገሩ በሚያሳዝን ሁኔታ እርስ በእርስ ከመተያየት ውጪ ለልዩነታቸው መፍትሄ ሳያገኙ እስከ ህዳር 28 ድረስ ዘለቁ፡፡ ከህዳር 28 በኋላ ግን እግዚአብሔር አምላክ ከፊልጵስዩስ ውስጥ መልዕክትን ሰጣቸው፡፡ እያዳንዳቸው ለመብታቸውና ለክብራቸው እየተጋደሉ መሆናቸውን አወቁ፡፡ ይህም ስጋዊ ትግል በዓለም ያለውን ከፍታ ቦታ በመመኘት የመነጨ መሆኑ ግልፅ ነበር፡፡ ክርስቲያን ለራሱ ክብርና መብት መታገል ሲጀምር ለህይወት እንቆቅልሹ መፍትሄን አያገኝም መፍትሄ ያለው ክብሩን ሁሉ ትቶ ወደ ታች የወረደውን ‹‹ሰው›› የሆነውን ‹‹ክርስቶስን›› በማሰብና በመመልከት ውስጥ ነው፡፡ ‹‹እርሱ በእግዚአብሔር መልክ ሲኖር ሳለ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን እንደሚገባ ነገር አድርጎ አልቆጠረውም ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ በሰውም ምሳሌ ሆኖ ራሱን ባዶ አደረገ፡፡ በምስሉም እንደ ሰው ተገኝቶ ራሱን አዋረደ፡፡ ለሞትም ይኸውም የመስቀል ሞት እንኳን የታዘዘ ሆነ፡፡›› ከዚህ ቃል በላይ ማንነታቸውን ሊያሳይ የሚችል አልነበረም ይህ ቃል አጥንታቸው ድረስ ዘልቆ ስብርብራቸውን አወጣ፡፡ መሳታቸውን ተገነዘቡ ቃሉ ከሁለት በኩል ከተሳለ ሰይፍ በላይ አጥንትን ጅማትን ዘልቆ እንደሚገባ አሳያቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ታላቅ ለውጥ ሆነ፡፡

አቡነ ኢሪካ ሳባቲ እና ሌሎች ዘጠኝ የቤተክርስቲያን መሪዎች ሀጢአታቸውን ተንበርክከው ተናዘዙ፡፡ የመንፈስ ቅዱስ እሳትም በሃይል ወርዶ ሁላቸውንም ጎበኘ፡፡
((እኔም የምመኘው ይህንን ነው የቤተክርስቲያን መሪዎች አገልጋዮች የተባሉ ሁሉ ያለምንም ዕፍረት ሀጢአታቸውን ተናዘው ዳግም እንደገና መንፈስ ቅዱስ እንዲጎበኘን ነው፡፡ ለራሱ መብትና ክብር የሚሟገት አገልጋይና መሪ የበዛበት ዘመን አኹን ይህ ያለንበት ዘመን አይደለምን?)))

ቤተክርስቲያን ወደ አንድነቷ ከተመለሰች በኋላ ፕሬዝዳንት ኢድ አሚን ፈገግ እያሉ

‹‹ቤተክርስቲያናችሁን ከመከፋፋል አዳንኩላችሁ›› አሉ!

ይህን የሰሙት አቡነ ኢሪካ ሳባቲ
‹‹ቤተክርስቲያናችንን ከመከፋፋል ያዳናት ክብሩን ጥሎ ወደ መሬት የወረደው ክርስቶስ ኢየሱስ እንጂ ኢድ አሚን አይደለም፡፡›› ብለው መለሱ ለአንድ ሀገር መሪ እንዲህ አይነት ድፍረት የተሞላበት መልስ መስጠት እጅግ ከባድ ቢሆንም አቡነ ኢሪካ ግን ትክክል ነበሩ! ፕሬዝዳንት ኢድ አሚን በቁጣ ይናገራሉ ብለው የቤተክርስቲያን መሪዎች ለአቡነ ኢሪካ ፈርተው ሲጠብቁ ፕሬዝዳንት ኢድ አሚን የሚያስገርም ግብዣ አደረጉ ……….

በፕሬዝዳንት ኢድ አሚን የተደረገው ግብዣ የሚያስገርም ነበረ ‹‹ወንጌልንና የጌታን ፍቅር ለዩጋንዳ የጦር ሰራዊት በሙሉ እየተዘዋወሩ እንዲሰብኩ፡፡ ለዚህም ይረዳቸው ዘንድ እነ አቡነ ፊስቶ በጦር ሰራዊቱ አዛዦች ታጅበው በሠራዊቱ መኪናዎች መንቀሳቀስ ጀመሩ፡፡ በዚህ የወንጌል ዘመቻ አንዳንድ ወታደሮች የነፍሳቸው መድህን አድርገው ክርስቶስ ኢየሱሰስን ተቀበሉ፡፡»

የቤተክርስቲያን መሪ የነበሩት አቡነ ዋኒ በዚህ በ1972 እና 1973 ለሠራዊቱ በተደረገው የወንጌል ዘመቻ ላይ እንዲሳተፉ ከኢዲ አሚን መንግስት ጥሪ ቀርቦላቸውም ነበር።

በ1972 በጋ ላይ የምስራቅ አፍሪካ ‹‹ወንድሞች መነቃቂያ›› ተብሎ የተሰየመውን ጉባኤ ለመካፈል የዩጋንዳ ክርስቲያኖች ጓዛቸውን ሸክፈው ወደ ታንዛኒያ ለማምራት ተነሱ፡፡ ይህ ጉባኤ በ1940 ጀምሮ በየዓመቱ የሚደረግ ከ5000 እስከ 25000 ሰው የሚሳተፍበት ብዙዎች ከብዙ ወንድሞችና እህቶች ጋር ተገናኝተው በብዙ ናፍቆት ውስጥ ሆነው ጌታን የሚያመልኩበት ተወዳጅ ጉባኤ ነው፡፡

በጊዜው በታንዛኒያና በዩጋንዳ መንግስት የነበረው መቃቃር የተነሳ እያንዳንዱ ወደ ጉባኤው የሚያመራ ሰው ከወታደራዊው ኮሚሳሪያት ፅ/ቤት የመውጫ ፍቃድ ይዟል፡፡ የጉባኤው ተሳታፊዎች ወደ ታንዛኒያ ለመሄድ በታላቅ ጉጉት ውስጥ ሳሉ ያልታሰበ ነገር ተከሰተ ቁጥራቸው የበዛ ወታደሮች መሳሪያቸውን አንግተው በአዛዦቻቸው ጩኸት እየታጀቡ ወደ ታንዛኒያ ለመሄድ ወደ ተሰናዱት ሰዎች መጡ፡፡

ተጓዦቹን ሁሉ ከከበቡ በኋላ ወደ ወታደራዊው እስር ቤት እንዲሄዱ  አስገደዶቸው፡፡ አቡነ ፊስቶን ጨምሮ ሰማኒያ የሚያህሉ ክርስቲያኖች ወደ ወህኒ ቤት ወረዱ፡፡


ይቀጥላል

(((  )))) በአዘጋጁ የተጨመረ


ለሌሎች እንዲደርስ ቻናሉን ሼር ማድረግ አይርሱ



@senpareAdisketemaFGC
ኢዲ አሚኒን እወደዋለሁ

(በእሳትና በስደት ውስጥ የወንጌልን አሸናፊነትን የሚያሳይ ድንቅ ታሪክ)

ክፍል አራት

ደራሲ፡ አቡነ ፊስቶ ኪቬንጌሪ

ትርጉም፡ ገለታው ፈንታ

አዘጋጅ
@Bito45tesfu44

ለትረካ እንዲመች ጥቂት ማስተካከያዎች ተደርገውበታል

°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
ከወታደሮች አንዱ

‹‹ይህ ሁሉ ህዝብ ወደ ጠላት አገር ታንዛኒያ እንዴት ይሄዳል›› በማለት ነገሩን ለማሟቅ ሞከረ አንደኛውም ተቀብሎት

‹‹ምናልባት የሽምቅ ተዋጊዎችን ለመቀላቀል ይሆናል መታሰር አለባቸው›› እያለ መዘላበዱን ተያያዘው

ከዚህ ድርጊት በኋላ ብዙ ክርስቲያኖች ወደ እስር ቤት ተወስደው ታጎሩ። በእስር ቤቱ ውስጥ ምንም መቀመጫ እስከማይገኝ ድረስ አጨናነቁት። በዮጋንዳ እንደተለመደው ሁሉም ክርስቲያን እስረኞች ሳር ጎዝጉዘው ተቀመጡ። ብዙም ሳይቆይ ከእስር ቤቱ ውስጥ በሚገኝ በአንደኛው ማዕዘን በኩል ዝግ የዓለ የዝማሬ ድምጽ መሰማት ጀመረ። ድምጹም

«ክብር ክብር ሃሌሉያ
ክብር ለበጉ ይሁን» የሚል ነበረ።

ወዲያውም ሁሉም እስረኛ ዝማሬውን እየተቀባበለ መዘመር ቀጠሉ፤ አብዛኞቹ ክርስቲያኖች በድንገተኛው እስር ምክንያት ፍርሃት ገብትዋቸው ስለነበር ለነፍሳቸው ንስሃ ሲገቡ ተስተውሎ ነበር። ይሁን እንጂ እየቆየ ሲመጣ የምስጋናው መዝሙር በኮሪደር ሳይቀር ተጋጋለ፤ የብዙ ክርስቲያኖች አይኖች በእንባ ተሞሉ። ሌሎች ደግሞ የመፈታት ተስፋ በፊታቸው መታየት ጀመረ።

አንዱ እስረኛ ለሌላው ጌታ እንዴት ግሩም ሰላም እንደሰጠው ይመሰክራል፤ ሁሉም እስረኛ እግዚአብሔርን ያመሰግናል፤

ከእስር ቤት ከነበሩት ክርስቲያኖች አንዱ

«ታንዛኒያ ወደ ሚደረገው የመነቃቂያ ጊዜ እንሄዳለን ብለን አስበን ነበር፤ ነገር ግን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ መነቃቃትን እዚሁ እስር ቤት አደረገልን።» አለ

ክርስቲያኖቹ ምንም እንኳን በእስር ሁለት ቀን ቢቆዩም የኢድ አሚን ወታደሮች ከዝማሬው የተነሳ አይተውት የማያውቁትን ደስታ ይለማመዱት ነበር። ክርስቲያን ታሳሪዎች በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተሞልተው ለሚጠብቅዋቸው ወታደሮች የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝነት ይሰብኩላቸው ነበር። አንዳንድ ወታደሮች ከደስታቸው የተነሳ ለታሰሩት ክርስቲያኖች ለስላሳ መጠጥን ይገዙላቸው ነበር። አብዛኞቹ ወታደሮች እንዴት ንስሃ እንደሚገቡና ጌታን እንደሚቀበሉ የዕጠይቁ ነበር።

የቤተክርስቲያን መሪዎች ተሰባስበው ወደ ታንዛኒያ ለመሄድ የተሰጠውን የመውጫ ፍቃድ ለታላላቅ ባለስልጣናትና ለፕሬዝዳንት ኢዲ አሚንን ጭምር በማሳየት የታሰሩ ክርስቲያኖችን ለማስፈታት ላይ ታች ይሯሯጡ ጀመር። በመጨረሻም ድካማቸው ፍሬ አፍርቶ ባለስልጣኖቹ «እነዚህስ ታዛዥ ዜጋዎች ናቸው።» በማለት የታሰሩት እንዲፈቱና ጉዞኣቸውን ወደ ታንዛኒያ እንዲቀጥሉ ትዕዛዝ ሰጡ።

ክርስቲያኖቹ እንዲፈቱ መታዘዙን የሰሙት ወታደሮች፤ የወህኒ ቤት ዘበኞችና ቤተሰቦቻቸው በእስር ሁለት ቀን ብቻ የቆዩትን ክርስቲያኖችን ለመሰናበት በእስር ቤቱ ደጃፍ በሰልፍ ቆመው ታዩ። ምክንያቱም በክርስቲያኖቹ ላይ ያዩት የፍቅርና የመፈታት ተስፋ ለልባቸው መደነቅ ሆኖ ነበር። በተጨማሪም ታስረው የነበሩት ክርስቲያኖች የሞት ጽዋ እንኳን ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ወታደሮቹ ገምተው ስለነበር «ይፈቱ» ሲባል ትልቅ ደስታ ተሰምቷተቸዋል። በእርግጥም በዚያን ዓመት እንኳን ወደዚያ እስር ቤት ከገቡት እስረኞች የመፈታት እድል የገጠማቸው በጣም ጥቂቶቹ ነበሩ፤ ሌሎቹ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ እዚያው ተቀብረው ነበርና።

መስከረም በገባ የመጀመሪያው ሳምንት እንደተለመደው ፕሬዝዳንት አሚን በጣም የሚያስደንቅ መግለጫ በሬዲዮ ሰጡ። ቢግዳዲ በዚሁ አለምን ባሸበረ መግለጫቸው ወደ 50 ሺህ የሚደርሱ የእንግሊዝ ፓስፖርት የያዙ የኤሽያ፤ የፓኪስታንና የህንድ ዜጎች ከዮጋንዳ እንዲወጡ አዘዙ። ማንኛውም ከአገር የሚወጣ ዜጋ ይዞ መውጣት የሚፈቀድለት 140 የአሜሪካ ዶላር ብቻ መሆኑን በጥብቅ አሳሰቡ። ከሁሉ የሚገርመው ግን ሃማሳው ሺው ህዝብ ከዮጋንዳ እንዲወጣ የተሰጠው ጊዜ ሶስት ወር ብቻ መሆኑ ነበር። ቢያንስ በቀን 555 ሰው ዮጋንዳን መልቀቅ አለበት።

ክርስቲያኖች የተፈጸመው ድርጊት ድንገተኛ እና የሰውን መብት የሚጋፋ ነው በማለት ኮንነውታል።
የፕሬዝዳን ሐጂ ኢድአሚን ነገር በዚህ አላበቃም በሙኒክ ኦሎምፒክ በእስራኤል የኦሎምፒክ ልዑክ ላይ «በጥቁሩ መስከረም» ሽብር ቡድን የተፈጸመውን የሽብር ድርጊትና ጨካኙ ሂትለር ስድስት ሚሊዮን አይሁዶችን መግደሉን አሞገሱ፤ ለታላቁ ሂትለርም የመታሰቢያ ሃውልት እሰራለታለሁ ሲሉ ተናገሩ። እስራኤላውያን በሙሉ የአረብን ይዞታ ለቀው ወደ ታላቅዋ ብሪታኒያ መፍለስ አለባቸው ሲሉ አሳሰቡ።

ከዚህ ጊዜ በኋላ ኢዲ አሚን በሬዲዮ መናገር ሲጀምሩ «ደግሞ ዛሬ ምን ይሉ ይሆን? የሚቀጥለው ምንድን ነው?» በማለት የብዙዎች ልብ መንጠልጠል ጀመረ . . . . . . ይቀጥላል
Forwarded from YOSEF GOD'S
የሲዖል ጉብኝት ተከታታይ ትረካ

ይህ ቀጥለን የምናቀርበው ታሪክ በ1961ዓ.ም በአሜሪካ ሀገር ውስጥ በሜሪ ካትሪን በተባለች ሴት በልዩ መገለጥ ለ40 ተከታታይ ምሽቶች የተደረገ እውነተኛ የሲዖል ጉብኝት ነው።
በደንብ ይነበብ

#ክፍል -1

የካቲት 1961ዓ.ም ነበር ቤት ሆኜ እየፀለይኩ ነበር:: ሳምንቱን ሙሉ በመንፈስ ሆኜ በጌታ ፊት እየፀለይኩ እየቃተትኩ ባለሁበት ጊዜ ነበር ጌታ የተገለጠልኝ:: ከምፀልይባቸው ቀናት በአንዱ ቀን ማታ በድንገት ክፍሉ በብርሀን ተሞላ ልክ እንደ ኳስ የሚሽከረከሩ የብርሀን ነፀብራቆች ክፍሉን ሞሉት። በጣም አይን ይማርኩ ነበር። አንድ ድምፅ መናገር ጀመረ " እኔ ኢየሱስ ክርስቶስ ነኝ ጌታሽም አምላክሽም። የኔ የሆኑ ቅዱሳን ወደ እውነቴ እንዲመለሱ እና የጨለማው አለም እውነት መሆኑ ፍርዴም የማይቀር መሆኑን አሳይሻለው። ነፍስሽንም ወደ ሲዖል እወስዳታለው ያሳየሁሽን ነገር ፅፈሽ ትመዘገቢያለሽ።እኔ ህያው ብቻዬን አምላክ ነኝ።ከኔ በላይ ማንም የለም::" አለኝ:: ምናገረው ጠፋኝ ተርበተበትኩ ጌታ አጠገቤ መሆኑ ግን ልዩ ዉበት ደስታ እና ሀሴት በውስጤ ሲሞላ ይታወቀኝ ነበር::

.....በድንገት ነፍሴ ከስጋዬ ወጥታ ከጌታ ጋር ከፍ አለች:: ስጋዬን ከአልጋዬ ተመለከትኩት ባለቤቴ እና ልጆቼ ተኝተዋል:: ጌታም የዉስጥ ስሜቴን ተረድቶ ምንም አይሆኑም አይዞሽ ብሎ አበረታኝ::
....ከሰማይ በላይ ከፍ አልን ምድር ኳስ ሆና ታየችኝ። በጣም ብዙ ረጃጅም ዋሻዎችን አየሁ ጌታንም ምንድን ናቸው? ብዬ ጠየኩት እርሱም "እነዚህ የሲዖል መግቢያ ደጆች ናቸው በነርሱ አርገን ወደ ውስጥ እንገባለን::" አለኝ::
በፍጥነት ወደ ዋሻዎቹ ገባን ያለማቋረጥ የሚሽከረከሩ ይመስሉ ነበር:: ጥልቅ የሆነ ጭለማ ዋሻዎቹን ዉጧቸው ነበር በዋሻዎቹ የነበረው ሽታ አቅሜ ከሚቆጣጠረው በላይ አስቀያሚ ነው። ጥቋቁርና አስቀያሚ በጉም የተሸፈነ ሰውነት ያላቸው ፍጡራን ከዋሻው ግርግዳ ጋር ተጣብቀው ነበር። አፋቸውን ከፍተው ሲጮሁ እጅግ በጣም የሚያስቀይም ሽታ ከአፋቸው ወጣ:: ጌታንም እነዚህ ምንድን ናቸው ብዬ ጠየኩት::" እነዚህ ወደ ምድር በሰይጣን ትዕዛዝ ለመላክ ተራቸውን የሚጠብቁ መንፈሶች ናቸው::" አለኝ።
.... ወደ ዋሻው ጠልቀን ስንገባ መንፈሶቹ እኛን ለመያዝ ጥረት አደረጉ ግን ከጌታ ሀይል የተነሳ መቅረብ አቃታቸው። አየሩ በጣም የሚቀፍ ሽታ ይሸት ነበረ:: ማንኛውንም ነገር አደርግ ነበር ማሽተት መስማት ማየት አፌ ውስጥ ሳይቀር አጣጥም ነበር::
.... ወደ ሲዖል መግቢያ ዋሻው መውጫ በተቃረብን ቁጥር ታላቅ ጩኸት እየተሰማ መጣ የአስቀያሚው ሽታ መጠንም እጅግ ጨመረ ውስጤ ሞት ፍርሀት እና ሀጥያት በተደጋጋሚ ይሰማኝ ነበረ:: ከቅድሙ የበለጠ የበሰበሰ የሞተ እንስሳ አይነት ሽታ በአየሩ ገነነ:: ሽታው ከሁሉም አቅጣጫ ይመጣ ነበረ::
.....በድንገት አንድ ነገር ከጭንቅላቴ በላይ ሲሄድ ተሰማኝ...የ ዋሻው ሙሉ ብርሀኑ ጥቁር ቢሆንም ግራጫ የሚመስል ብርሀን በዙርያችን ነበር:: ቀና ብዬ የተሰማኝን ስመለከት ትልቅ ዘንዶ ከበላያችን የዋሻውን ጣራ እየተሳበ ይሄድ ነበር:: በጣም ብዙ እባቦች በየቦታው ይርመሰመሱ ነበር። ጌታም እንዲህ አለኝ
"አሁን ወደ ሲዖል ግራ እግር ክፍል እንገባለን በዛም ትልቅ ምሬት ሐዘን ፤ አስፈሪ ጩኸት እና በጣም አስፈሪ ነገሮችን ትመለከቻለሽ። ከአጠገቤ ሁኚ በምንጓዝበት ሁሉ ጥንካሬን እሰጥሻለው:: ወደ ሲዖልም እንሄዳለን የምታያቸው ነገሮች በምድር ይሄን ለሚያነቡ ማስጠንቀቂያ ይሆናል::ብዙዎችም በዚህ ፁህፍሽ ይድናሉ የምታዪው እውነት ነው::አትፍሪ እኔ ከአንቺ ጋራ ነኝ::" አለኝ:: ...ወደ ዋሻው መጨረሻ ተቃረብን። ከዋሻውም ወደ ሲዖል ወረድን:: በምችለው ቃላት ያየሁትን ለመግለፅ እሞክራለው።

ይቀጥላል
እባካችሁን የሲዖልን እውነትነት ለምታውቋቸው ወደ ሲኦል ለሚንደረደሩ ላኩላቸው።
ለምታውቋቸው ሁሉ ሼር አድርጉ...
ወደዚህ ቻናል እንዲገቡ ጋብዙ
Forwarded from YOSEF GOD'S
ክፍል ሁለት
የሲዖል ጉብኝት ተከታታይ ትረካ
እውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ መፅሐፍ

በጥልቅ ጨለማ ተዋጥን። ከጨለማው በተጨማሪ አስቀያሚ ሽታ አካባቢውን ሞላው። ካለንበት ዋሻ ዳር ከግርግዳው ጋር የተጣበቁ ህይወት ያላቸው ፍጡራን ነበሩ። መጥፎ መናፍስት ለመሆናቸው ነጋሪ አያስፈልግም ነበር። ሰውነታቸውን ስመለከት የጥቁርና ግራጫ ቀለም ውህድ መሆኑን አስተዋልኩ። ፍጡራኑ ወደኛ ለመጠጋት እየሞከሩ ጮኹ። ፍጡራኑ ለመንቀሳቀስ ቢሞክሩም ከዋሻው ግርግዳ ጋር እንደተጣበቁ ስለነበር አልቻሉም። ከሰውነታቸው እጅግ የሚቀፍ ሽታ ይመጣ ነበር። ደግመው በጣም የሚቀፍ ጩኸት ሲያሰሙ ጥጉር ጉም የመሰለ ነገር ሰውነታቸውን ይሸፍነው ነበር። "ጌታ ሆይ እነዚህ ምንድናቸው ? " ብዬ ጠየኩ ጌታም መለሰልኝ። " እነዚህ ወደ ምድር በሰይጣን ትዕዛዝ ለመላክ ተራቸውን በመጠባበቅ ላይ ያሉ የተዘጋጁ መናፍስት ናቸው" አለኝ። ከዋሻው አልፈን ለመሄድ ስንሞክር መናፍስቱ እያስካኩ መጮህ ቀጠሉ። ሊነኩንም ሞከሩ ግን ከጌታ ሀይል የተነሳ አልቻሉም ነበር። አየሩ በጣም በቆሻሻ ሽታ የተሞላ ነበር እውነት ለመናገር ጌታ አጠገቤ መሆኑና መገኘቱ ነው ያበረታኝ። ሁሉም የስሜት ህዋሶቼ ይሰሩ ነበር። ማየት ፤ መስማት ፤ ማሽተት ፤ መዳሰስ እና ማጣጣም ጭምር እችል ነበር። የአካባቢው አስቀያሚ ሽታ ህመም ሲፈጥርብኝ ይሰማኛል።...
ከዋሻው ወጥተን ወደ ቀጣዩ ስንሄድ ታላቅ ጩኸት ተቀበለን በአካባቢው የምሬት ለቅሶ ፣ ጩኸትና ምሬት ብቻ ጎልቶ ይሰማል። የሚሰማኝ ስሜት ሞት ፣ ፍርሀትና ፣ የሀጥያት ስሜት ነበር። ከበፊቱ የከፋው ሽታ አየሩ ላይ ጎላ። የሚበሰብስ ስጋ አይነት ነበር በአካባባው ከሁሉም ስፍራ የሚመጣ ይመስል ነበር ሽታው። በምድር ሳለሁ እንደዚህ አይነት ለቅሶ ሰምቼ አላውቅም ነበር። ሲዖል በእርሱ ተሞልቷል። ከበላያችን አየሩን ሰንጥቆ የሚገባ ጥቂት ጭላንጭል ብርሀን ለግርግዳዎቹ ግራጫ ቀለም ሰጥቷቸዋል። ለማየት ግን የሚከብድ ጨለማ ነበር። በድንገት ከፊት ለፊቴ ካለው መሬት አንዳች ነገር እንዳለ ተሰማኝና አጎነበስኩ ትልቅና አስቀያሚ እባብ መሬቱን እየተሳበ እየሄደ ነበር። አትኩሬ ስመለከት በየቦታው የሚርመሰመሱ እባቦች ነበሩ ጌታ እንዲህ አለኝ። " አሁን ወደ ሲዖል የግራ እግር ክፍል እንገባለን ታላቅ ሀዘንና ምሬት መግለፅ የማይቻል አስፈሪ ነገሮችን ትመለከቻለሽ ከጎኔ ሁኚ አጠነክርሻለሁ እጠብቅሻለሁ። የምትመለከቺው ነገር ማስጠንቀቂያ ይሆናሉ። በምትፅፊው መፅሐፍ ለብዙዎች መዳን ምክንያት ይሆናል። የምትመለከቺው ነገር እውነት ነው። አትፍሪ እኔ ከአንቺ ጋር ነኝ።" አለኝ። ከዚህኛውም መተላለፊያ በስተመጨረሻ ወደ ታች ወጣን። ጌታ በሰጠኝ ቅደምተከተል እናገራለሁ። ከአካባቢው በላይ የሚበሩ መናፍስት ይታያሉ። እያረፉ እየበረሩ ድምፅ ያወጣሉ። ከአንድ ጥግ ደብዘዝ ያለ ብርሀን ያለው መንገድ ተመለከትኩ ከጌታ ጋር አብረን በርሱ መሄድ ጀመርን። መንገዱ ላይ ደረቅ ዱቄታማ ቆሻሻ ይታያል። ጥቂት እንደተጓዝን ወደ መጨረሻው መግቢያ የመሰለ ነገር ተመለከትኩ። አንዳንድ ያየኋቸውን ነገሮች ለመግለፅ በጣም ያስቀይማሉ። ይሄን በምፅፍበት ወቅት ብዙ ነገሮች አልገቡኝም ነበር ግን ጌታ ሁሉን ስለሚያውቅ በዚያ ያየሁትን ነገር እንድረዳ አግዞኛል። በጣም ማሳሰብ የምፈልገው ዋና ነገር ወደዚህ ስፍራ በፍፁም እንዳትመጡ ነው። የሀዘን የህመምና የዘልአለም ስቃይ ቦታ ነው። የሰው ልጅ ነፍስ ለዘልአለም በህይወት ትቆያለች። ነፍሳችሁ ማለት ደግሞ እናንተ ራሳችሁ ናችሁ። ነፍሶች ደግሞ ወደ ሲዖል ወይም መንግስተ-ሰማያት ብቻ ነው የምትሄደው። በሲዖል እንደምድር መዝናኛ ፓርቲ የለም ፣ ፍቅር የለም ፣ ርህራሄና እረፍት አይታሰብም ከምታስቡት በላይ የስቃይ ስፍራ ነው።
በመግቢያው አልፈን ወደ ሲዖል የመጀመርያ ክፍል ወደ ግራ እግሩ ገባን።
እየሱስ ያድናል!!!
በአዲሱ አመት እየሱስን ስጦታ እንስጥ!
Forwarded from YOSEF GOD'S
የሲዖል ጉብኝት ተከታታይ ትረ
ክፍል-3
የሲዖል የግራ እግር

ወደ ሲዖል የግራ እግር ክፍል ስንገባም አስቀያሚ ሽታ አየሩ ላይ ሰፍኖ ነበር። ጌታም " በዚህ በሲዖል የግራ እግር ብዙ ጉድጓዶች አሉ የመጣንበት መተላለፊያ ወደ ሲዖል የተለያዩ ክፍሎች ቢወስደንም እዚ ጥቂት እንቆያለን። የምታያቸው ነገሮች ሁሌ ከአንቺ ጋር ይቀራሉ። አለም ስለ ሲዖል መኖር ማወቅ አለበት ብዙ ሀጥያተኞች እና ጥቂት ክርስቲያኖችም ጭምር ሲዖል እውነት መኖሩን አያምኑም። አንቺ ይሄን እውነት ለነርሱ እንድትየግሪ መርጬሻለሁ። የማሳይሽ ሁሉም ነገር እውነት ነው።" አለኝ።
ጌታ ለኔ የሚታየኝ ሙሉ በሰው ቅርፅ ሆኖ ግን ሙሉ ለሙሉ ብርሀን ሆኖ ነበር። ብርሀኑ ከፀሀይ በጥንካሬ ይልቃል። አልፎአልፎ በስጋ ይታየኝ ነበር። አብዛኛው ጊዜ ግን በመንፈስ ነበር። በድጋሚ እንዲህ አለኝ። " ልጄ እኔ የምናገረው አባቴ የሚለውን ነው። አባቴና እኔ ደግሞ አንድ ነን። መዋደድና ይቅር መባባል የሚገባ ነገር ነው። ተከተይኝ አሁን" አለኝ።
ከበላያችን እየጮኹ የሚበሩ መናፍስት ነበሩ። ስንሄድ ከጌታ እየራቁ ይበሩ ነበር። " ጌታ ሆይ ቀጥሎ የማየው ምንድነው?" አልኩት። ቅድም እንዳልኩት ሙሉ የስሜት ህዋሶቼ ይሰሩ ነበር። በኋላ እንደተረዳሁት በሲዖል ያሉ ነፍሶችም ሁሉም የስሜት ህዋሳቸው ይሰራ ነበር። ፍርሀት አካባቢውን ሞልቶታል። የምረግጣቸው እያንዳንዱ እርምጃዎቼ ከበፊቱ ይልቅ እያስፈሩኝ መጡ። የምንገባበት በር ያለማቋረጥ ሲዘጋና ሲከፈት አየሁ። ሲከፈት መናፍስት እየጮኹ ወደ ውስጥ ይገቡ ነበር። ሰውነቴን ተመለከትኩ ለመጀመርያ ጊዜ በመንፈስ ቅርፅ መሆኔን ተረዳሁ። የመንፈሴ ቅርፅ የሰውነቴን ቅርፅ ይመስል ነበር።
በየቦታው በእሳት የተሞሉ ጉድጎዶች ይታያሉ። የአንዱ ጉድጓድ ርዝመት 3ጫማ ስፋቱ ደግሞ 4ጫማ ይሆናል። የጉድጓዶቹ ቅርፅ ክብና ጎድጎድ ያለ ነበር። ጌታም ተናገረኝ " በሲዖል የግራ እግር ክፍል ይሄን የመሰሉ ብዙ ጉድጓዶች አሉ። ጥቂቶቸቹን አሳይሻለሁ አለኝ። ከጌታ ጋር ቆምኩና ወደ አንዱ ጉድጓድ ተጠጋን። በጉድጓዱ ውስጥ ያለው ፍም ቀይ ቀለም ነበረው። ከፍሙ መሀል የጠፋና ሲዖል የገባ የሰው ነፍስ ነበረ። እሳቱ እየተፍለቀለቀ የነፍሱን መላ አካል ይሸፍን ነበር። ነፍሱን ስመለከት አፅም የመሰለ ሰውነት ነበረው። " ጌታ ሆይ ለምን እንዲወጡ አትፈቅድላቸውም? እንዴት ነው ህያው ፍጡር በዚህ ስፍራ ማየት የሚያሳዝነው" ብዬ አለቀስኩ። ከጉድጎዱ ያለው ነፍስ " ጌታ ሆይ ምህረት አድርግልኝ" አለ። ከድምጿ ሴት መሆኗን ተገነዘብኩ። በጣም አሳዘነችኝ ብችል ኖሮ ከፍሙ ጎትቼ ባወጣት ደስ ባለኝ ነበር። የሰውነቷ አጥንቶች ውስጥ ጥቁር ጉም የመሰለ ነገር ተሸፍኗል። ከአጥንቶቿ ጫፍና ጫፍ የበሰበሰ ስጋ የመሰለ ነገር ተንጠልጥሎ ነበር። አይኖቿ በነበሩበት ቦታ ባዶ ቀዳዳ ይታያል። ፀጉር የሚባል አልነበራትም። ከፍሙ መሀል ለቅሶዋ ጨመረ " ጌታ ሆይ ከዚህ መውጣት እፈልጋለሁ አለች።ወደ ጌታ አጥብቃ መለመን ጀመረች። በጣም ታሳዝን ነበር። ወደ ጌታ ዞሬ ስመለከት ፊቱ ላይ ጥልቅ ሀዘን ይታይ ነበር። ወደኔ ተመለከተና " ልጄ እዚህ ያለሽው ለአለም ሀጥያት ሞት እንደሚያመጣና እንድትናገሪ ነው። ሲዖል መኖሩንም እንድታሳውቂ ነው።" አለኝ። ወደ ሴቲቱ ስመለከት እሳቱ ሳያቃጥላቸው በላይዋ ላይ ትሎች ይርመሰመሱ ነበር። ጌታም "ትሎቹን ታውቃለች መኖራቸውም በሰውነቷ ውስጥ ድረስ ይሰማታል።" አለኝ።"ጌታ ሆይ ምህረት አድርግላት" ብዬ አለቀስኩ። ከሴትየዋ የሚወጣው ምሬትና ለቅሶ ያሳዝን ነበር። አንዴ ጠፍታለች። ከሲዖል መውጫ አልነበራትም። "ጌታ ለምን እዚህ መጣች?" ስለው። ፍርሀቴን ተመልክቶ ጌታ "ነይ" ብሎኝ አልፈን ሄድን

ይቀጥላል
Forwarded from YOSEF GOD'S
የሲዖል ጉብኝት ተከታታይ ትረካ



ክፍል-4
የሲዖል የግራ እግር

የምንሄድበት ረጅም መንገድ በየጫፉ ካሉት ፍም የተሞሉ ጉድጓዶች ይነከርና ይወጣ ነበር። የሰዎች ለቅሶና ጩኸት ከየቦታው ይሰማኝ ነበር። በጭራሽ ፀጥታ እና ርጋታ ኖሮ አያውቅም። በአየሩ የገነነው የሞተና የሚበሰብስ ስጋ ሽታ ያስጠላ ነበር። ከጌታ ጋር ወደ ቀጣዩ ጉድጓድ ሄድን በዚህኛውም ጉድጓድ እንደበፊቱ በአጥንት ቅርፅ የተመሰለ ነፍስ ነበረ። " ጌታ ሆይ ማረኝኝ! " ብሎ ሲጮህ ወንድ መሆኑን ተረዳሁ። በጣም አሳዛኝ የሆነ ልመና ማሰማት ጀመረ " ጌታዬ ሆይ እባክህ ይቅር በለኝና ከዚህ ልውጣ ለአመታት በዚህ ስፍራ ተሰቃየሁኮ ፣ እባክህ እባክህ ልውጣ" ብሎ አለቀሰ። የጌታን ፊት ዞሬ ስመለከት በእንባ ርሶ ነበር። ሰውየው ቀጠለ " ጌታ ሆይ የእስካሁኑ ቅጣት ለሀጥያቴ አይበቃም? ከሞትኩ እንኳን አርባ አመት አለፈኝኮ።" አለው። ጌታም እያዘነ እንዲህ አለው " በህይወት የሚኖረው በእምነት ነው። የትኛውም የማያምንና ፌዘኛ ከእሳት ባህር የድርሻውን ያገኛል። አንተ በኔና በእውነቴ አላመንክም ነበር። ብዙ ጊዜ ሰዎቼን በመላክ ትክክለኛውን መንገድ ላሳይህ ሞከርኩ አንተ ግን አትሰማቸውም ነበር። ብዙ ጊዜ ቀለድክባቸው ወንጌሌን ገፋህ። በመስቀል የሞትኩት ላንተ ነበር። አንተ ግን በኔ ቀለድክብኝ። በኔ አምነህ ሀጥያትህን አልተናዘዝክም ነበር። አባቴ ለመዳን ብዙ እድልን ሰጠህ ብትሰማ ኖሮ...." አለው። ሰውየውም " አውቃለሁ ጌታ ሆይ! አውቃለሁ! ግን አሁን ንስሀ እገባለሁ አሁን እገባለሁ.." ብሎ አለቀሰ። ጌታ " አሁን እንኳን ረፍዶብሀል። ምክንያቱም ፍርድህ ተፈፅሟልና።" አለው። ሰውየው መናገሩን ቀጠለ። " ጌታ ሆይ የኔ ከምላቸው ቤተሰቦቼ አንዳንዶቹ ወደዚህ መምጣት ጀምረዋል እባክህ የቀሩትን ሄጄ በአንተ አምነው ንስሀ እንዲገቡ እንድነግራቸው ፍቀድልኝ። እባክህ ሳይረፍድብኝ በምድር ሳሉ ልንገራቸው። ወደዚህ እንዲመጡ አልፈልግም።" አለ።
ጌታም መለሰለት " ለነሱ ሰባኪዎቼ ፣ አስተማሪዎቼ ፣ አባቶችና ፣ የወንጌል አገልጋዮች አሉላቸው። እነርሱ ይነግሯቸዋል። በዘመናዊ መገናኛ መንገዶችም ጭምር ስለኔ ይሰማሉ። በኔ አምነው እንዲድኑ ሰራተኞቼን ወደነርሱ እልካለሁ። ለነርሱ ሞቼ መነሳቴን ሰምተው ግን ካላመኑ አላስገድዳቸውም። " አለው። በዚህ ጊዜ ሰውየው በጣም ተናደደ። መራገምና መሳደብ ጀመረ። ከአፉ ፀያፍ ቃላት ይወጡ ነበር። ሰውነቱን እሳቱ እያለበሰው ሲሄድ ሳይ ዘገነነኝ ከአጥንቶቹ ተንጠልጥለው የቀሩ የመሰሉ ስጋዎች ወድቀው ወደ ፍሙ መግባት ጀመሩ። " እንዴት ዘግናኝ ነገር ነው የማየው ጌታ ሆይ።" ብዬ ወደ ጌታ ፊቴን አዞርኩና አለቀስኩ። ጌታም እንደዚህ አለኝ። " በጣም ብወዳቸውም የሲዖል መኖር ግን እውነት ነው። የምታይው ገና ጅማሬውን ነው።ብዙ ታያለሽ። በአለም ላሉ እንዲህ ብለሽ ንገሪልኝ። ' ሲዖል በእርግጥም አለ። ወንዶችና ሴቶች ሁሉ በኔ አምነው ንስሀ መግባት ይኖርባቸዋል።' እንሂድ" አለኝ።
በቀጣዩ ጉድጓድ ሰውነቷ ከቀደሞቹ አነስ ያለች ሴት አየሁ። እድሜዋን እንዴት ማወቅ እንደቻልኩ ባላውቅም አስራስምንት አመት ይሆናታል። ከሰውነቷ የቀረው በጉም የተሸፈነ አጥንቷ ብቻ ነበር። በርሱ ላይ የበፊቶቹን የመሰሉ ትሎች ይርመሰመሱ ነበር። "ልጄ የመጣሽው ለዚህ ነው። ማወቅና መናገር ያለብሽ መንግስተ-ሰማያትም ሆነ ሲዖል በእርግጥም እንዳሉ ነው።እንሂድ" አለኝ።ወደ ልጅቷ ዞሬ ሳይ ሀዘኔ በረታብኝ እጇን እንደሚፀልይ ሰው አድርጋ አጣምራ ነበር።ማልቀሴን ማቅም አቃተኝ። በሲዖል ያሉ ነፍሶች ሁሉ እንደኔ ሁሉም እንደሚሰማቸው አሰብኩ። ጌታ ያሰብኩትን አውቆ " አዎ ልጄ። ሰዎች ወደ ሲዖል ሲመጡ ምድር የነበራቸውን አስተሳሰብና ትዝታ ይዘው ነው የሚመጡት። ቤተሰቦቻቸውን ጓደኞቻቸውን ያውቃሉ።ያስታውሳሉ። በምድር እኔን ችላ ያሉበትንም ጊዜ ያስታውሳሉ። ሁልጊዜ ትዝታቸው ከነርሱ ጋር ይኖራል። አሁን ረፍዷል እንጂ በኔ አምነው ንስሀ ቢገቡ ኖሮ...." አለኝ።

ይቀጥላል
Forwarded from YOSEF GOD'S
የሲዖል ጉብኝት ተከታታይ ትረካ

🔹ክፍል-5
የሲዖል የግራ እግር

መጀመርያ ያየኋት ትልቅ ሴት ከኋላ ታየችኝ አሁን ሳያት ያስተዋልኩት ግን አንድ እግር ብቻ እንዳላት ነበር። በአጥንቶቿ ቀዳዳዎች ይታዩኛል። "...ምንድነው ጌታ ሆይ ?" ብዬ ጠየቅኩ። ጌታም " በምድር ሳለች ካንሰር በሚባለው በሽታ በጣም ታማሚ ነበረች። ህይወቷን ለማዳን ቀዶ ጥገና ተደርጎላት ነበር። ከተደረገላት በኋላ ግን ለአመታት መራር ሴት ሆና አረጀች። ብዙ የኔ ሰዎች ሊፀልዩላት ይመጡ ነበር። ትፈወሻለሽ ሲሏት " እግዚአብሔር ራሱ ነው ይህንን ያደረገብኝ " ብላ ታባርራቸውና ወንጌሌንም ታጥላላ ነበር።ንስሀ አልገባችም ነበር። ቀድሞ ታውቀኝ ነበር ኋላ ላይ ግን ጠላችኝ። እግዚአብሔር አያስፈልገኝም ፈውሱንም አልፈልግም ትል ነበር። ስለምናት ጀርባዋን ሰጠችኝ። አልፈልግህም አለችኝ። መንፈሴ ወደኔ እንድትመጣ አጥብቆ ለመናት አትሰማም ነበር። ኋላ ሞተችና ወደዚህ ስፍራ መጣች።
ሴትየዋን ጥቂት ስንጠጋት " ጌታሆይ አሁንስ ይቅር አትለኝም? በምድር ሳለሁ ንስሀ ባለመግባቴ እባክህ ጌታ ይቅርታ አድርግልኝ።" እያለች አለቀሰች። " ምናለ ድሮ ንስሀ ገብቼ ቢሆን ኖሮ። አሁንማ በጣም ረፈደብኝ። ግን ጌታዬ ከዚ አውጣኝ እባክህ ካወጣኸኝ አገለግልሀለሁ ጥሩ እሆናለሁ......የእስካሁኑ ስቃዬ አይበቃም ጌታ ሆይ እባክህ"
".....ወይኔ ለምን እስኪረፍድብኝ ድረስ ቆየሁኝ ለምን መንፈስህ እስኪተወኝ ከአንተ ራቅኩ....."
ብላ አለቀሰች። ጌታም መለሰላት " በኔ አምነሽ ንስሀ ገብተሽ እንድታገለግይኝ በተደጋጋሚ ብዙ እድል ነበረሽ።...." በጌታ ፊት ሀዘን እየተነበበ ተመልሰን ከሷ ርቀን ሄድን።ፍርሀት ብቻ ነው የሚሰማኝ ለቅሶ፣ሰቆቃ፣እና ሞት በአካባቢው ሰፍኗል። ከጌታ ጋር መሄዴ ነው ጥንካሬ የሆነኝ እንጂ አልችለውም ነበር። ከሷ በጣም ርቀን እንኳ ለቅሶና ልመናዋ ይሰማ ነበር። እባካችሁ ማናችሁም አሁን በሀጥያት የምትኖሩ እስኪረፍድባችሁ አትጠብቁ እባካችሁ የእግዚአብሔር መንፈስ ገና ሳይርቃችሁ ወስኑ።
በቀጣዩ ጉድጓድ የተንበረከከች ሴት ትታያለች ከፍሙ መሀል አንዳች ነገር የምትፈልግ ይመስል መሬቱን ትጭራለች። እንደቀደሟ ሴት አጥንቷ በቀዳዳዎች የተሞላ ነበር። የተቀደደና የተቃጠለ ቀሚስ መሳይ ነገር በሰውነቷ ይታያል።ጭንቅላቷ ላይ ፀጉር አልነበረም። አይኖቿና አፍንጫዋ በነበረበት ቦታ የማየው ባዶ ቀዳዳ ብቻ ነበር። የተንበረከከችባቸው ጉልበቶቿ ስር እሳት በጥቂቱ ይነዳል። በእጆቿ መሬቱን በጫረች ቁጥር ሰውነቷ ላይ ተቃጥለው የተንጠለጠሉት ስጋ መሳይ ነገሮች ይረግፋሉ። ድንገት ቀና ብላ ስታየን " ጌታ ሆይ ጌታ ሆይ መውጣት እፈልጋለሁ ..." ብላ እየተንደረደረች ወደ ጉድጓዱ ጫፍ ለመውጣት ታገለች። ልትወጣ መስሎኝ ነበር ነገርግን ከፊት ለፊት አንድ ክንፎቹ የተዛነፉ አጋንንት ወደሷ እየተንደረደረ መጥቶ ገፈተራት። አጋንንቱ ቀለሙ ጥቁር ቡኒ ነበር። መላ ሰውነቱ በፀጉር ተሸፍኖ ነበር። አይኖቹ ከጭንቅላቱ ዳርና ዳር በጣም ተራርቀዋል። የሰውነቱ መጠን አንድ ትልቅ ድብ ይመስል ነበር። ሲገፈትራት የወደቀችውን ዘግናኝ አወዳደቅ እየተሳቀቅኩ ተመለከትኩ። አጠገቤ አድርጌያት አቅፌ ጌታ እንዲምራትና እንድትወጣ ተመኘሁ። ጌታ ሀሳቤን አውቆ እንዲህ አለኝ። " ልጄ አባቴ ተናግሮ ፍርዷ ተፈፅሟል። ገና ልጅ እያለች ጀምሮ ነበር ንስሀ ገብታ በኔ አምና እንድታገለግለኝ ስጠራት የነበረው። የ16አመት ልጅ እያለች ወደሷ ሰዎቼን ልኬ ' እወድሻለሁ ህይወትሽን ለኔ ስጭኝ። ተከተይኝ ለተለየ አላማ ጠርቼሻለው። አልኳት እርሷ የምትለኝ ግን "አንድ ቀን አገለግላለሁ ጌታ ሆይ። አሁን ጊዜ የለኝም። አሁን ጊዜዬ ለመዝናናትና ለጨዋታ ነው እንጂ ቤተክርስቲያንም አንተን ላገለግልህ ጊዜ የለኝም። ነገ አገለግልሀለሁ ነገ " አለችኝ። " የቀጠረችው ነገዋ ሳይመጣ ግን ረጅም ጊዜ አሳለፈች"

ይቀጥላል


ከዘልአለም ሞት በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ያድናል!
Forwarded from YOSEF GOD'S
የሲዖል ጉብኝት ተከታታይ ትረካ

የቀደሙ ክፍሎች ቻናሉ ውስጥ አሉ

ክፍል-6
የሲዖል የግራ እግር

ወጣቷ ሴት አሳዛኝ ልመና ማሰማቷን ቀጠለች። " ነፍሴ በታላቅ ስቃይ ውስጥ ናት።ከዚህ መውጫ አጣሁ ጌታዬ ከአንተ በላይ የአለምን ፈልጌ መሄዴን አውቃለሁ። ዝናና ሀብትን ፈለግኳቸው አገኘዃቸውም። የፈለኩትንና ያማረኝን ነገር መግዛት ቻልኩ። ቆንጆና ጥሩ ልብስ የምትለብስ ሴት መሆን ቻልኩ። በራሴ ላይ እንደፈቀድኩ አዛዥ የነበኩት ራሴ ነበርኩኝ።ከሞትኩኝ በኋላ ግን ያገኘዋቸውን ዝናና ሀብት ይዤ መምጣት አልቻልኩም። ጌታዬ ሆይ ቀንና ሌት ያለማቋረጥ ነፍሴ ተሰቃየች እባክህ ጌታ ሆይ ከዚህ እንድወጣ አድርገኝ እባክህ።" አለች። ልጅቷ ወደ ጌታ ፊቷን አድርጋ መለመኗን ቀጠለች " የኔ ውድ ጌታ ምናለ ሰምቼህ ቢሆንስ ኖሮ? ለዘልአለም ገና ሲቆጨኝ ይኖራል። እኔማ .....ዝግጁ ስሆን አገለግልሀለሁ ብዬ ነበር። አንተ የትም የማትሄድ ቆመህ የምትጠብቀኝ መስሎኝ ነበር።በሀብቴና በውበቴ ሰዎችን እንደተጠቀምኩባቸው አንተንም በአንድ መንገድ እንዴት እንደምጠቀምብህ ነበር የመሰለኝ። አንተ ግን ንስሀ እንድገባና ወደ አንተ እንድመለስ ዘመኔን ሙሉ ስትለምነኝ ነበር። በምትፈልገኝ ሰአት አልፈልግህም አልኩህ። ለሰይጣን ራሴን ሰጠሁ....በኔ ተጠቅሞ ሀሳቡን መፈፀም ጀመረ። ጌታዬ አንተን ትቼ የእሱን ሀሳብ ማገልገል ጀመርኩ። በመጨረሻም የምኖረውን ሀጥያት ከአንተ ከአምላኬ በላይ ወደድኩት ወዳንተ ለመመለስ አቃተኝ። ቀንና ሌት ያገኘሁትን ሀብት እንዴት ራሴን ሀያል ለማድረግ እንደምጠቀመው ማሰብ ነበር። እንደዛም ሆኜ አልተውከኝም ስትለምነኝ ነበር።ግን ላንተ ነገ ይመጣል ብዬ ተስፋ አድርጌ ችላ አልኩህ። አንድ ቀን በመኪና ከሹፌሬ ጋር ስንሄድ አቅጣጫውን ስቶ አንድ ቤት ሰብሮ ገባ። ህይወቴ እንደዋዛ አለፈችና ወደዚህ መጣሁ። ጊዜ አለኝ ስል ሞትኩኝ። ....ጌታ ሆይ እባክህ በቃሽ በለኝና ከዚህ ልውጣ እባክህ ጌታ ሆይ።" ብላ እያለቀሰች አጥንት ብቻ የሆኑት እጆቿን ወደ ጌታ ዘረጋች። ጌታ እንባው በጉንጮቹ እየወረደ " ፍርድሽ ተፈፅሟል" ብሏት ወደ ቀጣዩ ጉድጓድ አለፍን።በውስጤ ማልቀስ ማቆም አቃተኝ። በሲዖል ያለው ስቃይ እውነት አስከፊ ነው። " ጌታ ሆይ በሲዖል የማየው ሰቆቃ በጣም አሳዛኝ ነው። ነፍሶች ወደዚ ከመጡ ተስፋ የላቸውም.." ይሄን ስል ነፍሶቹ ለዘለዓለም በዚ ስፍራ እንደሚቆዩ ሲታወሰኝ ሀዘኔ በረታብኝ። ጌታም " ጊዜ እየሄደ ነው። ነገ ወደዚህ ስፍራ እንመለሳለን።"አለኝ። ወዳጄ ሆይ በሀጥያት ኑሮ ውስጥ ከሆንክ ወይ ከሆንሽ እባክህ እባክሽን ህይወትሽን ለዘልአለም ሊያድን በሚችለው በኢየሱስ ክርስቶስ ንስሀ ግባና እመን። ዳግም ተወልጃለሁ ብላችሁ ግን ከጌታ ራሳችሁን ላዞራችሁ እባካችሁ ንስሀ ግቡና ወደ ጌታ ኢየሱስ ፊት ተመለሱ።መልካም ኑሮ ኑሩ። ለእውነት ብቻ ምንጊዜም ቁሙ። እባካችሁ ሳይረፍድባችሁ እንድትነቁ እለምናችኋለሁ። ይህንን ካደረጋችሁ ከጌታ ኢየሱስ ጋር በመንግሥተ-ሰማያት በደስታ ትኖራላችሁ። ጌታም እንዲህ አለኝ። " ሲዖል ሰውነት አላት።ልክ በሰው ቅርፅ የተመሰለ ሰውነት። በጀርባው በምድር ላይ የተኛን ሰው ትመስላለች። በውስጧም ሰፊ ክፍሎች አሏት። አስታውሺ በምድር ያሉ ሰዎች ሲዖል መኖሯን በእርግጥም ማወቅ አለባቸው። በሲዖል እጅግ በጣም ብዙ ነፍሶች አሉ።በፍርድ ቀንም ሲዖልና ሞት ወደ እሳት ባህር ይጣላሉ። ይህም ሁለተኛው ሞት ይሆናል።"

ምዕራፍ-3 | የሲዖል የቀኝ እግር

ሲዖል ሄጄ በመጣሁ በማግስቱ ቀን ላይ ለመተኛት ብሞክርም እንቅልፍ የሚባል በአይኖቼ ሊዞር አልቻለም። አይኖቼን ለቅፅበት ስጨፍን የማየው የሲዖልን ነፍሶች ሰቆቃ ብቻ ነበር።ጆሮዎቼ ያለማቋረጥ የሲዖልን የስቃይ ጩኸት ያስተጋባሉ። ልክ እንደተቀረፀ ፕሮግራም እያንዳንዷ ያየኋትን ነገር አዕምሮዬ ያለማቋረጥ ይደጋግመው ነበር።ምግብ በአፌ ለማድረግ ይቀፈኝ ነበር። በሄድኩባቸው ምሽቶች ቀን ስመለስ ያየሁትን ነገር እንደ አስፈሪነቱ ለመፃፍ ቃላት ማግኘቱ ትልቅ ችግር ነው የሆነብኝ። እነሆ ሁለተኛውም ቀን መሸና ጌታ በድጋሚ ተገለጠልኝ። " ዛሬ የሲዖልን የቀኝ እግር ክፍል አሳይሻለሁ። ስለምወድሽ ከአንቺ ጋር ነኝና አትፍሪ።" አለኝ። በጌታ ፊት ላይ መራር ሀዘን ይስተዋል ነበር። አይኖቹ በፍፁም ፍቅርና ርህራሄ ተሞልተው ነበር። በሲዖል ያየኋቸው ነፍሶች አንዴ ለዘላለም ቢጠፉም ጌታ ግን ለዘልአለም እንደሚወዳቸው ተረዳሁ። ጌታ እንዲህ አለኝ። " ልጄ አባቴ ለልጆቹ ያሻቸውን እንዲመርጡ ፈቃድን ሰጥቷቸዋል እግዚአብሔርን ወይም ሰይጣንን ያገለግላሉ። አየሽ እግዚአብሔር ሲዖልን ያዘጋጀው ለፈጠራቸው ሰዎች አልነበረም። ለሰይጣንና ለመላዕክቱ ነበር። ሰይጣን ግን ብዙዎችን እያታለለ እንዲከተሉት ያደርጋል።"

ይቀጥላል
ወንድም እህቶቼ ይሄ ታሪክ የተፈፀመ ነው የተፃፈ ልብ ወለድ አይደለም። እውነተኛ ታሪክ ነው...ክርስቲያኖች በምድር ላይ የመኖራችን ምክንያት ለሌሎች ሰዎች ላላመኑ ሁሉ ነው። ህይወት እየሱስ ነው!!!


ከዘልአለም ሞት በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ያድናል!
Forwarded from YOSEF GOD'S
የሲዖል ጉብኝት ተከታታይ ትረካ

🔸ክፍል-7
የሲዖል የቀኝ እግር

ጌታ ይህን ካለኝ በኋላ ሀዘን ፊቱ ላይ ይነበብ ነበር። በድጋሚ እንዲህ አለኝ። በሚመጡት ቀናት የበለጠ ሲዖልን ሳሳይሽ ያልኩሽን ነገር አስታውሺ በሰማይም በምድርም ሀይል የኔ ነው። ብቻሽን የተውኩሽ የሚመስልሽ ሰአቶች ይመጣሉ ግን አልተውሽም። በሲዖል ያሉ ነፍሶችን ስንጎበኝ የሚያዩንም የማያዩንም ጊዜ ይኖራል።የትም ብንሄድ ግን እኔን ለመከተል አትፍሪ።" አለኝ። አብረን መሄዳችንን ቀጠልን ለቀናት በውስጤ የሰቀቀን እንባዬን ማቆም አልቻልኩም በማየው ነገር ነፍሴ በጣም አዝና ነበር። ወደ ሲዖል የቀኝ እግር ክፍል ደረስን። ከፊታችን የተቃጠለና የደረቀ የመሰለ መንገድ ተዘርግቷል። በአካባቢው ካለው ቆሻሻ አየር በተጨማሪ የሚበሰብስ ስጋ ሽታ ይበልጥ ገኖ ነበር። አንዳንዴ ሽታውን መቆጣጠር ሲያቅተኝ ውስጤን ሲያቅለሸልሸኝ እና ሲያመኝ ይታወቀኛል። በዚህ ስፍራ ከሩቅ ከሚታዩት ፍም የተሞሉ ጉድጓዶች በቀር ብርሀን አልነበረም። ከጌታ የሚመነጨው ብርሀን አካባቢውን ማየት እንድችል አድርጎኛል። ከላያችን መናፍስት አየር ላይ እንደቆሙ ቀና ስል አየሁ። በተለያየ መጠንና ቅርፅ ነበሩ። ከመካከላቸው ተለቅ የሚለው ለሌሎቹ ትዕዛዝን ሲሰጣቸው ተመለከትኩና ምን እንደሚል ለመስማት ከጌታ ጋር ቆምኩ። ጌታም "..በዚህ ስፍራ ከምናያቸው ከነዚህ መናፍስት በተጨማሪ የማይታዩን እንደ የበሽታ መንፈስ የመሳሰሉም አሉ።.." አለኝ። "ሂዱ!" ብሎ ትልቁ መንፈስ ለሌሎቹ ተናገራቸው። "...ሂዱ! መጥፎ የተባሉትን ሁሉ በምድር ስሩ ቤተሰቦችን እየከፋፈላችሁ በትኗቸው! ደካማ ክርስቲያኖችን የበለጠ አታሏቸው! በቻላችሁት ሁሉ የምታገኙትን በሙሉ ወደ ተሳሳተው መንገድ ምሩ! ስትመለሱ ሽልማታችሁን ታገኛላችሁ! ግን አስታውሱ ኢየሱስ ክርስቶስን በሙሉ ልባቸው አዳኝ አድርገው የተቀበሉ ሰዎችን ተጠንቀቋቸው በውስጣቸው እናንተን ማስወጣት የሚችል ሀይል አላቸው።..ሂዱ! ከእናንተ በፊት የሄዱም አሉ ሌሎችም እናንተን ይከተሏችኋል። እኛ የጨለማው ንጉስ የአየር ላይ አለቃ አገልጋዮች ነን! ..." መናፍስቱ ከሲዖል በፍጥነት እየበረሩ ሲወጡ የሲዖል የቀኝ እግር በር በፍጥነት ተከፍቶአሳልፎአቸው በፍጥነት ተመልሶ ተዘጋ። የተቀሩት መናፍስት እኔና ጌታ በመጣንበት ዋሻ የሚመስል መንገድ ወጥተው ሄዱ። እነዚህ ያየኋቸው መናፍስት ምን ይመስሉ እንደነበር ለመግለፅ ልሞክር...ትዕዛዝ ሲሰጣቸው የነበረው ትልቅና ሙሉ እድገቱን የጨረሰ ድብ ይመስል ነበር። ጭንቅላቱ የለሊት ወፍ ይመስላል። አይኖቹ በጣም ተራርቀው በጭንቅላቱ ላይ ይታያሉ። ሙሉ ፊቱን ከሸፈነው ፀጉር መሀል አራት ረዘም ያሉ የላይና የታች ጥርሶች ወጥተው ነበር። የሰውነቱ ቀለም ሙሉ ለሙሉ ቡናማ ነበር። ሁለተኛው መንፈስ አካሉ የጦጣ አይነት ቅርፅ ነበረው።እጆቹ ረጃጅም ሆነው እንደበፊቱ መንፈስ ሰውነቱ በፀጉር የተሸፈነ ነበር። ፊቱ አነስ ያለ ሆኖ አጭር አፍንጫ የሚመስል ነገር ከመሀሉ ይታያል። በየትኛውም የጭንቅላቱ ቦታ አይኖች ማየት አልቻልኩም ነበር። ሌላኛው ተለቅ ያለ ጭንቅላት ከትልቅ ጆሮዎች ጋር ነበሩት። የሰውነቱ ቀለም ይሄም ቡናማ ሲሆን መጠኑ ተለቅ ያለ ፈረስ ያክላል። እነዚህን መናፍስት ስመለከት ከእይታዬም ከእነርሱ ከሚመጣው አስቀያሚ ሽታም ውስጤ ታሞ ነበር.....በኋላ ጌታ ነግሮኝ እንደተረዳሁት እነዚህን ጨምሮ ሌሎች በየስፍራው ያየኋቸው መናፍስትን ሲያዙ የነበሩት ትልልቆቹ መንፈሶች ትፅዛዛቸውን የሚቀበሉት በቀጥታ ከሰይጣን ነበር። ጌታን እየተከተልኩ ጉዞአችንን ቀጠልን። እየሄድን እያለ ሌሎች መናፍስት ሳያዩን በአጠገባችን አልፈው ወደ አንድ ጉድጓድ ሄዱ....እኔና ጌታም አንድ ፍም የያዘ ከሌላ ጉድጎድ ጋር ስንደርስ ቆምን። የቆምንበት አጠገብ ያለው ጉድጓድ ውስጥ አንድ ተለቅ ያለ አጥንት ያለው ሰው ከፍሙ መሀል ነበረ። ወንጌል ለመመስከር ሲሞክር ይሰማኛል። በመገረም ወደ ጌታ በጥያቄ ተመለከትኩ።
ጌታም ሁሌ ሀሳቤን ቀድሞ ያውቅ ስለነበር እንዲህ አለኝ። " በምድር ይኖር ሳለ ወንጌልን ይሰብክ የነበረና በአንድ ወቅት እውነትን ይናገር የነበረ ሰው ነው።" አለኝ። ታድያ ይሄ ሰው ሲዖል ምን ይሰራል ስል አሰብኩ።...

ክፍል ፦8 ይ
ጥላል

ከዘልአለም ሞት በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ያድናል!
Forwarded from YOSEF GOD'S
የሲዖል ጉብኝት ተከታታይ ትረካ


🔸ክፍል-8
የሲዖል የቀኝ እ
ግር

የሰውየው ቁመት 6ጫማ ወይም 1ሜትር ከ80 የሚሆን ይመስላል። በፍሙ የተቃጠሉት አጥንቶቹ ግራጫ ቀለም ነበራቸው። የተወሰነ ልብስ መሳይ የተቀዳደደ ነገር ሰውነቱ ላይ አይቼ እንዴት በፍሙ እንዳልተቃጠለ አስቤ ገረመኝ። ከአጥንቶቹ ጥቂት ተቃጥለው የተንጠለጠሉ ስጋዎች ነበሩ በጭንቅላቱ ላይ እሳት ይታየኝ ነበር። ይሄንን እየተመለከትኩ ሳለ ከሰውየው ጠንካራና አስቀያሚ ሽታ ወደኔ መጣ....ሰውየው በእጆቹ መፅሐፍ-ቅዱስ እንደያዘ ሰው አድርጎ ስለ ኢየሱስ ሞትና ትንሳኤ የተፃፉ የመፅሐፍ-ቅዱስ መፀሐፍቶችን ይናገራል። ከምዕራፍ ምዕራፍ ከመፅሐፍ መፅሐፍ እየቀያየረ ይሰብካል። እኔ የሚናገረው ጥሩ መስሎኝ ነበር። ጌታም እሱን " ሰላም... እረፍ " ሲለው ሰውየው በዚ ጊዜ ተረጋግቶ መጮኹን አቆመና በቀስታ ወደ ጌታ ተመለከተ። ድምፁን ቀስ አድርጎ በልመና "...ጌታ ሆይ አሁን ወጥቼ እውነትን ለሰዎች እናገራለሁ። አሁን ወጥቼ ስለዚህ ስፍራ ለሰዎች አወራለሁ።አውቃለሁ በምድር ሳለሁ ሲዖል መኖሩን አላምንም ነበር። አንተም ተመልሰህ ትመጣለህ ብዬም አስቤ አላውቅም.....ሰዎች ይሄን መስማት እንደማይፈልጉ ከተረዳሁ ጀምሮ ሰዎች እንዲቀበሉኝ ስል እውነትህ ላይ ውሸትን ቀላቀልኩ። ዘራቸውና ቀለማቸው ከኔ የሚለዩ ሰዎችን አልወድም ነበር። ብዙዎችም በኔ ምክንያት አንተን እንዲርቁህ አደረግኩ ስለ መንግስተ-ሰማይ እና ሲዖል የራሴን ህግ አወጣሁ....ብዙዎች በአንተ ላይ እንዲያምፁና ቅዱሱን ቃልህን አቃለው አንዲያዩት አደረግኩ....ከደሀው ገንዘቡን እያታለልኩ ወሰድኩ.... ጌታ ሆይ እባክህ አሁን ከዚህ ልውጣ! በትክክል ማድረግ ያለብኝን ሁሉ አደርጋለሁ።....ከቤተክርስቲያን ገንዘብ መውሰዴን አቆማለሁ።....,ንስሀ ገብቼ ሁሉም ከኔ በዘርም በቀለምም የሚለዩ ሰዎችን እወዳለሁ።...እባክህ ጌታ ሆይ።.." ጌታም እንዲህ አለው። "...አንተ ቅዱሱን ቃሌን አሳስተህና አበላሽተህ ስትናገር ብቻ አልነበረም የነበረው...እውነትን እንደምታውቅ ትዋሽ ነበር።..ግን ከእውነት ይልቅ የምድር ህይወት እርካታ በልጦብህ ነበር። ራሴ ጎብኝቼህ ወደ እውነቴ ልመልስህ ሞክሬ ነበር።ግን አልሰማኸኝም ነበር። በራስህ መንገድ ሄድክ ክፉውንም አለቃህ አድርገህ ሾምክ። እውነት የቱ እንደነበር ተረድተህ ግን ንስሀ ገብተህ ወደኔ አልተመለስክም ነበር። ሁሌ ከአንተው ጋር ነበርኩ። እየጠበቅኩህም ነበር። ንስሀ እንድትገባ ስለምንህ ነበር አንተ ግን አልገባህም ነበር....እናም አሁን ፍርድህ ተፈፅሟል."
ሀዘን በጌታ ፊት ላይ አይ ነበር። ሰውየው ምድር ሳለ ጌታ ብሎት የነበረውን ቢሰማ እዚ ባልተገኘ ነበር። እባካችሁ ሰዎች ጌታ የሚላችሁን ስሙ።.....ጌታ መልሶ ለሰውየው መናገር ቀጠለ። "...እውነትን መናገር ነበረብህ እውነትን ብትናገር ኖሮ ብዙዎችን በእግዚአብሔር ቃል ወደ ቅድስና በመለስክ ነበር። ቃሌም የሚለው ሁሉም የማያምን በዲን እና በእሳት ከሚቃጠል ባህር የድርሻውን ያገኛል ነው። የመስቀሉን መንገድ ታውቅ ነበር።የቅድስናንም መንገድ ታውቅ ነበር። እውነት መናገር እንደነበረብህም እንደዛው ነገር ግን ሰይጣን ልብህን በውሸት ስለሞላው ወደ ሀጥያት ሄድክ። በትህትና ንስሀ መግባት ነበረብህ....ቃሌ እውነት ነው! ቃሌ በውስጡ ውሸት የለውም።....አሁን በጣም ረፍዶብሀል....በጣም ረፍዷል።." በዚህ ጊዜ ሰውየው እጆቹን አወናጭፎ ጌታን መራገም
ጀመረ። በሰቀቀን ተሞልቼ ከጌታ ጋር ወደ ቀጣዩ ጉድጓድ ሄድን። ሰባኪው ከኋላ ተቆጥቶ ያለማቋረጥ ሲራገም ይሰማኛል።

ይቀጥ
ላል...

ከዘልአለም ሞት በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ያድናል!
Forwarded from YOSEF GOD'S
የሲዖል ጉብኝት ተከታታይ ትረካ

🔸ክፍል-9
የሲዖል የቀኝ እግር

ወደ ሌሎች ጉድጓዶች ስንሄድ በምናልፍበት መንገድ ሁሉ ያሉ ነፍሶች እጆቻቸውን እየዘረጉ ወደ ጌታ በልመና ምህረትን ይጠይቁ ነበር። የሁሉም እጆች አጥንት ብቻ ሆነው በእሳቱ ከመቃጠል የተነሳ ጠቁረዋል። ስጋ ፣ደምና አካል የሚባል የላቸውም። በአለም የምትኖሩ ሆይ እባካችሁ በኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ላይ ስራ አምናችሁ ንስሀ ካልገባችሁ ወደዚህ ስፍራ መምጣታችሁ አይቀርም። ከመርፈዱ በፊት ወስኑ።ወደ ቀጣዩ ጉድጓድ ስንሄድ አካሌም መንፈሴም ተሰብሮ መራመድ እንኳን አቅቶኝ ነበር። ያለማቋረጥ የምሰማው ለቅሶ ውስጤን በሰቀቀን ሞላው። በዚህ በደረስንበት ጉድጓድ ውስጥ ያለችው ነፍስ ከፍሙ መሀል ተቀምጣ ትታያለች። መላ አካሏ በበሰበሰ ስጋና በትሎች ተሞልቷል። እሳቱ እየተፍለቀለቀ ሰውነቷን ያቃጥላል። ወደ ጌታ አጥንት ብቻ የሆነው እጆቿን ዘረጋችና "...ጌታ ሆይ እባክህ አሁን ከዚህ ልዉጣ...አሁን ልቤን ለአንተ እሰጥሀለሁ ...ስለ ምህረትህ ምስክር እሆናለሁ ለሌሎች እናገራለሁ.....እባክህ ልውጣ አለች። ጌታም " ቃሌ እውነት ነው። ቃሌም ደግሞ የሚለው ሁሉም ሀጥያተኛ በኔ አመነው ንስሀ ካልገቡ እዚህ ስፍራ ከመምጣት ማምለጥ አይችሉም። የፈሰሰው ደሜ ለሀጥያት ሁሉ ምህረትን ያስገኛል። እኔም ወደኔ የሚመጡትን ይቅር ለማለት ታማኝ ነኝ። ወደኔ የመጡትን ከራሴ አለያቸውም።" ወደ ሴትየዋ ዘወር ብሎ " ወደኔ ተመልሰሽና ንስሀ ገብተሽ ቢሆን ኖሮ ይቅር እልሽ ነበር።" ሴትየዋም ጌታን " ጌታ ሆይ ከዚህ የምወጣበት ምንም አይነት መንገድ የለም?.." አለችው። " ለአንቺ ንስሀ እንድትገቢ ብዙ እድሎች ተሰጥተውሽ ነበር ግን ልብሽን

አደነደንሽ። ቃሌ የማይታዘዙት ከእሳት ባህር ድርሻ አላቸው እንደሚል ታውቂያለሽ።.."አላት።
ጌታ ፊቱን ወደኔ አዙሮ..." ይህች ሴት ከብዙ ወንዶች ጋር በሀጥያት የተሞላ ዝሙት ትፈፅም ነበር። ለብዙ ቤተሰብ መበታተንም ምክንያት ነበረች። ይሄን ሁሉ እያደረገች እሷን እወዳት ነበር የመዳን መንገዴን ላሳያት ወደሷ ሄድኩ። ከክፉ ስራዋ እንድትመለስና ንስሀ እንድትገባ ብዙ ሰራተኞቼን ወደሷ ላኩኝ። ግን ንስሀ አትገባም ነበር። በጣም ወጣት እያለች ወደሷ ሄድኩኝ አልሰማችኝም። ብዙ ስህተትንም ሰራች ቢሆንም ግን ወደኔ ተመልሳ ቢሆን ኖሮ ይቅር እላት ነበር። ግን ሰይጣን በውስጧ ገባ የበለጠ መራር ሆነች። ማንንም ይቅር ማለት አትፈልግም ነበር። ወደ ቤተክርስቲያን ወንዶችን ፍለጋ ትሄድ ነበር። የምታገኛቸውንም እያማለለች ትወስድ ነበር። ወደኔ ተመልሳ ቢሆን ኖሮ ግን ሙሉ ሀጥያቷን በደሜ አጥቤ አነፃት ነበር። በግማሽ ልቧ እኔን ማገልገል ትፈልግ ነበር ነገር ግን እግዚአብሔርም ሰይጣንንም በአንድ ጊዜ ማገልገል አይቻልም። ሁሉም ሰው ማንን እንደሚያገለግል መምረጥ አለበት።
"..ጌታ ሆይ እባክህ ጥንካሬን ስጠኝ የማየውን ነገር መቋቋም አልቻልኩም..."ብዬ አለቀስኩ።
ጌታም " አይዞሽ ተረጋጊ" አለኝ።
" እባክህ ጌታ ሆይ እርዳኝ...ሰይጣን አለም ሲዖል መኖሩን እንዲያውቅ አይፈልግም ...ጌታ ሆይ እንዲ ይሆናል ብዬ በህልሜም አስቤ አላውቅም ነበር... ውዴ ኢየሱስ መች ነው የሚያበቃው ሲዖል....."
" ልጄ ሲዖል መች እንደሚያበቃ አባቴ ያውቃል። አይዞሽ ተረጋጊ። .." ሲለኝ ጥንካሬ ተሰማኝ። እኔና ጌታ ባለፍንባቸው ጉድጓዶች ሁሉ ያሉትን ነፍሶች ስቤ አውጥቼ ወደ ጌታ እግር ስር ባደርጋቸው ደስ ባለኝ ነበር።...በልቤም መቼም ልጆቼ ወደዚህ ስፍራ እንዲመጡ አልፈልግም ስል አሰብኩ። በመጨረሻም ጌታ "...ልጄ አሁን ወደ ቤትሽ እንመለሳለን ነገ ምሽት ተመልሰን ወደ ሲዖል እንመጣለን አለኝ።....

ይቀጥ
ላል
Forwarded from YOSEF GOD'S
የሲዖል ጉብኝት ተከታታይ ትረካ

🔸ክፍል-10
የሲዖል የቀኝ እግር

ወደ ቤት ስመለስ ስራዬ ማልቀስ ብቻ ሆነ። በቀኑ ሰአት ደግሞ ያየሁትን የሲዖልን ሰቆቃ ማስታወስ ብቻ። በየዕለቶቼ የማገኛቸውን ሰዎች ለሁሉም ስለ ሲዖል እውነት መሆን እና ሲዖል ከሚያስቡት በላይ መሆኑን እነግራቸው ነበር። የሲዖል ስቃይ ከሚያስቡት በላይ እንደሆነም ጭምር.....ይሄንን እያነበባችሁ ያላችሁ እባካችሁ እለምናችኋለሁ ለሀጥያታችሁ በፈሰሰው በኢየሱስ ደም አምናችሁ ንስሀ ግቡ። ብቻውን የሚያድናችሁን ጌታ ጥሩት....እባካችሁ ልባችሁ እያወቀ ነገን አትጠብቁ ነገ ላይመጣ ይችላልና። ጊዜ ከምታስቡት በላይ ስለሚፈጥን ቶሎ ተንበርከኩና ንስሀ ግቡ....እርስበርስ መልካም ተደራረጉ። እባካችሁ ለጌታ ስትሉ ይቅር ተባባሉ። የተቀየማችሁት ሰው ካለ ይቅር በሉት...የቱም ቂም ሲዖል እንድትገቡ ሊያደርጋችሁ አይገባም።ጌታ ይቅር እንዳለን ይቅር በሉ። ጌታ ምንም ያህል አስቸጋሪ ልብ ቢኖረንም በደሙ አንፅቶ ይጠብቀናል። ወላጆች ልጆቻችሁን ልጆችም ቤተሰባችሁን ውደዱ...የቤተክርስቲያን ጌታ " በኔ በማመን ንስሀ ግቡና ዳኑ " ይላል።

ምዕራፍ-
4 | ተጨማሪ ጉድጓዶች

በቀጣዩም ምሽት ጌታና እኔ ወደ ሲዖል የቀኝ እግር ተመልሰን ሄድን። ባለፈውም እንዳስተዋልኩት ዛሬም ጌታ በሲዖል ያሉትን ነፍሶች እስከ ዘልአለም እንደሚወድ ተረዳሁ። ለኔም ጥልቅ ፍቅሩ ተሰማኝ ጌታ አሁን በአለም ያላችሁ ሁላችሁንም ሰዎች ይወዳል። እንዲህ አለኝ "ልጄ ማንም እንዲጠፋ የኔም የአባቴም ፈቃድ አይደለም።ሰይጣን ብዙዎችን እያታለለ የራሱ ያደርጋል። ግን እግዚአብሔር ይቅር ባይ ነው። የፍቅር አምላክ ነው። በዚህ በሲዖል ያሉት ነፍሶች ሁሉ ወደርሱ መጥተው ንስሀ ቢገቡ ኖሮ ይቅር ይባሉ ነበር።..." ጌታ ይሄንን ሲናገር ፊቱ ላይ ሀዘን አይ ነበር። ስንሄድ ብዙ ጉድጓዶች ነበሩ ከሁሉም እጆቻቸውን እየዘረጉ ጌታን ይጣራሉ... በዚያ ያለው ሀዘን ፣ ተስፋ መቁረጥ ፣ እና እሳቱ ሲሰማቸው እያዘንኩ አይ ነበር። ሀዘናቸውን ሳይ የማልቋቋመው ሰቀቀን ፈጠረብኝ...." ምናለ ሰምተው እዚህ ባልመጡ ኖሮ" ስል አሰብኩኝ። በሲዖል ያሉ ነፍሶች ሁሉም ስሜቶች እንዳሏቸውና በፊት የተነገራቸውን ነገር በሙሉ እንደሚያስታውሱ ተረዳሁ። ከዚህ ለመውጣት ለዘልአለም ባይቻልም ጌታን ሲያዩ ግን ተስፋ እያደረጉ ምህረትን ይለምኑ ነበር። ጥቂት ተጉዘን ከአንድ ጉድጓድ አጠገብ ቆምን። ይሄኛውም እንደበፊቶቹ ያለ ነበር። በውስጡ ዃላ ላይ ሴት መሆኗን ያወቅኳት ነፍስ ነበረች። ጌታ ከፍሙ እንዲያወጣት ለመነችው። ሴቲቷን በፍቅር አይኖች እያያት እንዲህ አላት። " በምድር ሳለሽ ወደኔ እንድትመጪ ስለምንሽ ነበር።ልብሽን በኔ እንድትቀይሪ ለመንኩሽ ግን አልሰማሽም። ብዙ ጊዜ ወደ አንቺ መጣሁ ጎበኘሁሽ ፍቅሬን ነገርኩሽ ወደኔ በመንፈሴ ሳብኩሽ..."እሺ ጌታ ሆይ" አልሽ። "በከንፈርሽ እሺ እከተልሀለሁ.... እወድሀለሁ"አልሽ ግን የልብሽ እውነት እርሱ አልነበረም። ልብሽ የት እንደነበር አውቃለሁ። መልዕክተኞቼን ወደ አንቺ ልኬ ንስሀ እንድትገቢና እንድትመለሺ ስነግርሽ ነበር።....ግን አትሰሚም ነበር። ሌሎችን እንድታገለግይ ላደርግ ነበር ለሌሎች እኔን እንዲያውቁ እንድትናገሪ ነበር ያሰብኩሽ።...አንቺ ግን ከኔ በላይ የአለምን ፈለግሽ። ስጠራሽ አትሰሚም ንስሀ ሳትገቢም በጣም ብዙ ቆየሽ።ሴትየዋም እንዲህ አለች። "ታሰሰታውሳለህ ጌታ ሆይ ሁሌ ቸርች እሄድ ነበር....ጥሩ ሰው ነበርኩ። የአንተው ቤተክርስቲያን አባል ነበርኩ። በህይወቴ ጥሪህ ምን ያህል ዋጋ እንደሚያስከፍለኝም አውቅ ነበር። ዋጋም ከፍያለሁ...." አለች። "..አሁንም በውሸት እና በሀጥያት እንደተሞላሽ ነው። ጠራሁሽ ግን አትሰሚኝም ነበር። እውነት ነው የቤተክርስቲያን አባል ነበርሽ ግን ቤተክርስቲያን መሄድሽ ብቻ መንግስተ-ሰማያት እንድትገቢ አያደርግሽም። ሌሎች በቃሌ ላይ እንዲያምፁ አደረግሽ።....የጎዱሽንም ይቅር ማለት ፈፅሞ አትፈልጊም ነበር። ከክርስቲያኖች ጋር ስትሆኚ የምትወጂኝ እና የምታገለግይኝ ታስመስይ ነበር። ከነርሱ ስትለዪ ግን ትዋሺ፣ ትሰርቂና፣ታጭበረብሪ ነበር።ለክፉ መናፍስት እድልን ሰጠሽ እነርሱም መንታ ህይወትሽ ተመቻቸው አብረውሽም መኖር ጀመሩ።ነገር ግን ብቸኛው ጠባቡና ትክክለኛው መንገድ የቱ እንደነበር ታውቂ ነበር። አንቺ ግን ሁለት ምላስ ነበረሽ የኔ በሆኑ ክርስቲያን ወንድሞች እና እህቶችሽ ላይ በሀሜት ታወሪ ነበር። ደግሞም ራስሽን ከነርሱ በላይ ቅዱስ እንደሆንሽ እያሰብሽ ሰዎችን ከላይ ብቻ እያየሽ አማኝ መሆናቸውን ዘንግተሽ ፈረድሽባቸው። በአፍሽ እወድሃለሁ ብትይም ልብሽ ከኔ ሩቅ ነበር። የኔን መንገድ እያወቅሽ ልትቀልጂ ሞከርሽ ሁሉንም ግን እኔ አውቃለሁ። መንፈሴ የሚልሽን መስማት አልቻልሽም ነበር። ንስሀ ገብተሽ በትህትና አገልግለሺኝ ቢሆን እዚህም ባልመጣሽ ነበር።እኔንና ሰይጣንን እኩል ማገልገል አይቻልም....."አላት።ጌታ ወደኔ ዞሮ በመጨረሻው ዘመን ብዙዎች ከእምነት ፈቀቅ ይላሉ። በዚህም ለክፉ መናፍስት እየተጋለጡ ሀጥያትን ማገልገል ይጀምራሉ።ከነርሱ ተለዩና ውጡ መንገዳቸውንም አትከተሉ አብራችኋቸውም አትሂዱ። የለያችሁ ሁኑ።
ከሴትየዋ ርቀን ስንሄድ መሳደብ ጀመረች በታላቅ ድምፅም እየጮኸች መራገም ጀመረች።....ከሷ ራቅን ሰውነቴን በጣም ሲደክመኝ ይታወቀኛል።

ክፍል
፦11 ይቀጥላል

ከዘልአለም ሞት በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ያድናል!!!
Forwarded from YOSEF GOD'S
የሲዖል ጉብኝት ተከታታይ ትረካ

🔸ክፍል-11
ተጨማሪ ጉድጓ
ዶች

በቀጣዩ ጉድጓድ የነበረውም አጥንት እንደ ሌሎቹ ይመስል ነበር። ወደ ጉድጓዱ ስንቀርብ የበለጠ የሞት ሽታ ይሸተኝ ነበር። እዚህ ለምን እንደመጣ ነፍሱ ጥያቄ ሆነብኝ። ከፍሙ መሀል ያለው ነፍስ ወደ ጌታ መናገር ሲጀምር ሴት መሆኗን አወቅኩ ከመፅሐፍ-ቅዱስ የተለያዩ ጥቅሶችን ትናገር ነበር። " ምን እያደረገች ነው?" ብዬ ጌታን ጠየኩት። ጌታም "ስሚ።" አለኝ።
"...ኢየሱስ እውነት ነው። መንገድ ነው ህይወት ነው ካለሱ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ አይቻልም። ኢየሱስ የአለም ብርሀን ነው። ወደ ኢየሱስ ኑ እርሱ ህይወት ይሰጣችዃል ትድናላችሁ።.." ይህንን ስትናገር በአካባቢው ያሉ ነፍሶች ይሰሟት ነበር። አንዳንዶቹ በቁጣ እየሰደቧትና እየረገሟት እንድታቆም ይነግሯታል። አንዳንዶቹ ነፍሶች ደግሞ ' ተስፋ አለን በእውነት?.." ብለው በተስፋ መቁረጥ ይጠይቋታል። ታላቅ ለቅሶ እና ምሬት በአካባቢው ይሰማል። ሴቲቷ ምን እያደረገች እንደሆነ አልገባኝም ነበር። " ለምን ይቺ ሴት ወንጌልን በሲዖል ትሰብካለች ስል አሰብኩ።ጌታም ሀሳቤን አውቆ እንዲህ አለኝ። " ልጄ ይህች ሴት በ30አመቷ ነበር የወንጌል ምስክር እንድትሆን እና የቃሌ አገልጋይ እንድትሆን የጠራዃት። የተለያዩ ሰዎችን ለተለያየ አገልግሎት እጠራለሁ ግን ማንኛውም ወንድ ወይም ሴት መንፈሴን ካልፈለጉት ከነርሱ አወጣለሁ። አዎ። ጥሪዬን ለአመታት መልሳ ነበር። በኔም እውቀት አድጋ ነበር።ድምፄንም መስማትን ተለማምዳ ነበር።ብዙ መልካም ነገሮችንም አድርጋ ነበር። ቃሌን ዘወትር ታጠና ያለማቋረጥም ትፀልይ ነበር። ብዙ ፀሎቶቿ ተመልሰውላትም ነበር። ብዙ ሰዎችን የቅድስና መንገድን አስተማረች።በቤቷም ታማኝ ነበረች። አመታት አልፈው አንድ ቀን ባለቤቷ ከሌላ ሴት ጋር እንደማገጠ አወቀች።ባለቤቷ ወደርሷ መጥቶ ይቅርታ እንድታደርግለት ጠየቃት እርሷ ግን አልፈቀደችም። መራር ሴት ሆነች ትዳሯን ከመፍረስ ማዳን አልቻለችም ነበር። በእርግጥ ባሏ ትልቅ ሀጥያት ሰርቷል። ተሳስቷል። ግን ሴቲቱ ቃሌን ታውቅ ነበር። ይቅር ማለት ምን እንደሆነ ታውቃለች። ይቅርታ ባለቤቷ ደጋግሞ ቢጠይቃትም ልታደርግለት አልቻለችም።ቁጣ በርሷ ስረሰ ሰደደ አብዝቶም አደገ። ጉዳይዋን ወደኔም ይዛ አልመጣችም ነበር። በየቀኑ በመራርነቷ እና በቁጣዋ ቀጠለችበት። እርሷም አለች "..እኔ እግዚአብሔርን ለማገልገል በዚህ እሯሯጣለሁ በዚ ደግሞ ባለቤቴ በኔ ለመወስለት ይሯሯጣል።እና አንተ ይሄ ልክ ነው ትላለህ?..."አለችኝ። እኔም "ልክ አይደለም። ግን ወደ አንቺ መጥቶ ይቅርታን ጠየቀሽ። እንደማይደግመውም ቃል ገባልሽ።ልጄ በራስሽ ላይ እያመጣሽ ያለውን ተመልከቺ።" አልኳት።እርሷም መልሳ " እኔ አይደለሁም እኔ ንፁህ ነኝ። እሱ ነው በሀጥያት የተሞላው" አለችኝ።ልትሰማኝ አልቻለችም። ጊዜ የበለጠ ሲሄድ መፀለይና መፅሐፍቅዱስን ማጥናቷን ተወች። በባሏ ብቻ ሳይሆን በአጠገቧ ባሉት ሰዎች ሁሉ ቁጡ ሆነችባቸው። ጥቅሶችን ትጠቅሳለች ግን ይቅር ማለት አልቻለችም። በጭራሽ አትሰማኝም ልቧም የበለጠ እየከፋ ሄደና ታላቅ ሀጥያት ወደርሷ ገባ።ፍቅር ተሞልቶ የነበረው ልቧ በጭካኔ ተሞላ። አንድ ቀንም ከቁጣዋ የተነሳ ባለቤቷን እና ውሸማውን ገደለቻቸው። ሰይጣን መላ ማንነቷን ተቆጣጥሮትም ራሷንም አጠፋች።

በሲዖል ለዘልአለም የተተወችውን ነፍስ ከፍሙ መሀል ከስቃይዋ ጋር አየኋት።ለጌታ በአሳዛኝ ድምፅ ስትለምን ሰማኋት። "...አሁን ይቅር እለዋለሁ...አሁን እተወዋለሁ ጌታ እታዘዝሀለሁ ብቻ ከዚህ ቦታ ልውጣ .....አየኸኝ ጌታ ወንጌል እዚህ ስሰብክ አየኸኝ...ከአንድ ሰአት በዃላ ክፉ መናፍስት ወደዚህ ይመጣሉ። ስላንተ እዚ በማውራቴ ወደ ሌላ ክፍል ወስደው ለሰአታት ያሰቃዩኛል....እባክህ ጌታ ሆይ ልውጣ እባክህ...."
ጉድጓዱ ውስጥ ካለችው ሴት ጋር አብሬ አለቀስኩ። ጌታ ልቤን የናንተንም ከመራርነት ይጠብቀው።" ጌታ ሆይ ጥላቻ በልቤ እንዳይገባ ጠብቀኝ.." አልኩት። እርሱም "..እንሂድ " ብሎኝ አልፈን ሄድን።

ይቀጥ
ላል


በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ከሲዖል ማምለጫ ብቻ ሳይሆን ለዘልአለም በእግዚአብሔር ፍቅር መኖሪያ ብቸኛ መንገድ ነው።
የጤንነት በመንፈሳዊ እይታ በሚል ርዕስ በቅርቡ ይጠብቁን
2ኛ ጢሞቴዎስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እንግዲህ፥ ልጄ ሆይ፥ አንተ በክርስቶስ ኢየሱስ ባለው ጸጋ በርታ።
² ብዙ ሰዎች የመሰከሩለትን ከእኔም የሰማኸውን ሌሎችን ደግሞ ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ።
³ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ በጎ ወታደር ሆነህ፥ አብረኸኝ መከራ ተቀበል።
⁴ የሚዘምተው ሁሉ ለጦር ያስከተተውን ደስ ያሰኝ ዘንድ ትዳር በሚገኝበት ንግድ ራሱን አያጠላልፍም።
⁵ ደግሞም በጨዋታ የሚታገል ማንም ቢሆን፥ እንደሚገባ አድርጎ ባይታገል፥ የድሉን አክሊል አያገኝም።
⁶ የሚደክመው ገበሬ ፍሬውን ከሚበሉት መጀመሪያ እንዲሆን ይገባዋል።
⁷ የምለውን ተመልከት፤ ጌታም በነገር ሁሉ ማስተዋልን ይስጥህ።
⁸ በወንጌል እንደምሰብከው፥ ከሙታን የተነሣውን፥ ከዳዊት ዘርም የሆነውን ኢየሱስ ክርስቶስን አስብ፤
⁹ ይህንም በመስበክ እንደ ክፉ አድራጊ እስክታሰር ድረስ መከራ እቀበላለሁ፥ የእግዚአብሔር ቃል ግን አይታሰርም።
¹⁰ ስለዚህ እነርሱ ደግሞ በክርስቶስ ኢየሱስ ያለውን መዳን ከዘላለም ክብር ጋር እንዲያገኙ ስለ ተመረጡት በነገር ሁሉ እጸናለሁ።
¹¹ ቃሉ የታመነ ነው እንዲህ የሚለው፦ ከእርሱ ጋር ከሞትን፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ በሕይወት እንኖራለን፤
¹² ብንጸና፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ እንነግሣለን፤ ብንክደው፥ እርሱ ደግሞ ይክደናል፤
¹³ ባናምነው፥ እርሱ የታመነ ሆኖ ይኖራል፤ ራሱን ሊክድ አይችልምና።
¹⁴ ይህን አሳስባቸው፥ በቃልም እንዳይጣሉ በእግዚአብሔር ፊት ምከራቸው፥ ይህ ምንም የማይረባ የሚሰሙትንም የሚያፈርስ ነውና።
¹⁵ የእውነትን ቃል በቅንነት የሚናገር የማያሳፍርም ሠራተኛ ሆነህ፥ የተፈተነውን ራስህን ለእግዚአብሔር ልታቀርብ ትጋ።
ራእይ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ቶሎ ይሆን ዘንድ የሚገባውን ነገር ለባሪያዎቹ ያሳይ ዘንድ እግዚአብሔር ለኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠው በእርሱም የተገለጠው ይህ ነው፥ ኢየሱስም በመልአኩ ልኮ ለባሪያው ለዮሐንስ አመለከተ፥
² እርሱም ለእግዚአብሔር ቃልና ለኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ላየውም ሁሉ መሰከረ።
³ ዘመኑ ቀርቦአልና የሚያነበው፥ የትንቢቱን ቃል የሚሰሙትና በውስጡ የተጻፈውን የሚጠብቁት ብፁዓን ናቸው።
⁴-⁵ ዮሐንስ በእስያ ላሉት ለሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት፤ ካለውና ከነበረው ከሚመጣውም፥ በዙፋኑም ፊት ካሉት ከሰባቱ መናፍስት፥ ከታመነውም ምስክር ከሙታንም በኵር የምድርም ነገሥታት ገዥ ከሆነ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን። ለወደደን ከኃጢአታችንም በደሙ ላጠበን፥
⁶ መንግሥትም ለአምላኩና ለአባቱም ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኃይል ይሁን፤ አሜን።
⁷ እነሆ፥ ከደመና ጋር ይመጣል፤ ዓይንም ሁሉ የወጉትም ያዩታል፥ የምድርም ወገኖች ሁሉ ስለ እርሱ ዋይ ዋይ ይላሉ። አዎን፥ አሜን።
⁸ ያለውና የነበረው የሚመጣውም ሁሉንም የሚገዛ ጌታ አምላክ፦ አልፋና ዖሜጋ እኔ ነኝ ይላል።
⁹ እኔ ወንድማችሁ የሆንሁ ከእናንተም ጋር አብሬ መከራውንና መንግሥቱን የኢየሱስ ክርስቶስንም ትዕግሥት የምካፈል ዮሐንስ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ኢየሱስ ምስክር ፍጥሞ በምትባል ደሴት ነበርሁ።
¹⁰ በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፥ በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ፥
¹¹ እንዲሁም፦ የምታየውን በመጽሐፍ ጽፈህ ወደ ኤፌሶንና ወደ ሰምርኔስ ወደ ጴርጋሞንም ወደ ትያጥሮንም ወደ ሰርዴስም ወደ ፊልድልፍያም ወደ ሎዶቅያም በእስያ ወዳሉት ወደ ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ላክ አለኝ።
¹² የሚናገረኝንም ድምፅ ለማየት ዘወር አልሁ፤ ዘወርም ብዬ ሰባት የወርቅ መቅረዞች አየሁ፥
¹³ በመቅረዞቹም መካከል የሰው ልጅ የሚመስለውን አየሁ፥ እርሱም እስከ እግሩ ድረስ ልብስ የለበሰው ደረቱንም በወርቅ መታጠቂያ የታጠቀ ነበር።
¹⁴ ራሱና የራሱ ጠጕርም እንደ ነጭ የበግ ጠጕር እንደ በረዶም ነጭ ነበሩ፥ ዓይኖቹም እንደ እሳት ነበልባል ነበሩ፤
¹⁵ እግሮቹም በእቶን የነጠረ የጋለ ናስ ይመስሉ ነበር፥ ድምፁም እንደ ብዙ ውኃዎች ድምፅ ነበረ።
¹⁶ በቀኝ እጁም ሰባት ከዋክብት ነበሩት፥ ከአፉም በሁለት ወገን የተሳለ ስለታም ሰይፍ ወጣ፤ ፊቱም በኃይል እንደሚበራ እንደ ፀሐይ ነበረ።
¹⁷ ባየሁትም ጊዜ እንደ ሞተ ሰው ሆኜ ከእግሩ በታች ወደቅሁ። ቀኝ እጁንም ጫነብኝ እንዲህም አለኝ፦ አትፍራ፤ ፊተኛውና መጨረሻው ሕያውም እኔ ነኝ፥
¹⁸ ሞቼም ነበርሁ እነሆም፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ሕያው ነኝ፥ የሞትና የሲኦልም መክፈቻ አለኝ።
¹⁹ እንግዲህ ያየኸውን አሁንም ያለውን ከዚህም በኋላ ይሆን ዘንድ ያለውን ጻፍ።
²⁰ በቀኝ እጄ ያየሃቸው የሰባቱ ከዋክብትና የሰባቱ የወርቅ መቅረዞች ምሥጢር ይህ ነው፤ ሰባቱ ከዋክብት የሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት መላእክት ናቸው፥ ሰባቱም መቅረዞች ሰባቱ አብያተ ክርስቲያናት ናቸው።
Revelation 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ This is what God gave to Jesus Christ to show His servants what must happen quickly, and this is what was revealed in Him, and Jesus sent His angel to His servant John.
² And he testified to the word of God and to the witness of Jesus Christ to all who saw him.
³ For the time is near, blessed are those who read, hear the words of the prophecy and keep what is written in it.
⁴-⁵ John to the seven churches in Asia; May grace and peace be with you from Jesus Christ, who is and who was, and who is to come, and who is before the throne, and who is the seven spirits, who is the faithful witness, who is the firstborn of the dead, and who is the ruler of the kings of the earth. To him who loved us and washed us from our sins in his blood.
⁶ To him who made us to be priests to his God and Father, to him be glory and power forever and ever; Amen.
⁷ Behold, he comes with clouds; And every eye shall see him, and all the nations of the earth shall wail for him. Yes, Amen.
⁸ The Lord God who rules all that is and was and is to come says: I am the Alpha and the Omega.
⁹ I, John, who is your brother and who shares with you the sufferings and the kingdom and the patience of Jesus Christ, was on the island called Phetmos for the word of God and the testimony of Jesus.
¹⁰ I was in the spirit on the Lord's day, and afterwards I heard a great sound like the sound of a trumpet;
¹¹ Also: Write down what you see in a book and send it to Ephesus, Smyrna, Pergamon, Thyatron, Sardis, Philadelphia, Laodicea, and the seven churches in Asia.
¹² I turned to see the voice that spoke to me; And I turned and saw seven golden candlesticks;
¹³ And I saw in the midst of the lampstands one who looked like a son of man, and he was clothed with a garment down to his feet, and his chest was girded with a golden girdle.
¹⁴ His head and his own hair were like white wool and white as snow, and his eyes were like a flame of fire;
¹⁵ His feet were like hot brass refined in a furnace, and his voice was like the voice of many waters.
¹⁶ In his right hand he had seven stars, and out of his mouth came a sharp sword drawn on two sides; His face was like the sun, shining with power.
¹⁷ When I saw him, I fell at his feet like a dead man. He put his right hand on me and said to me: Do not be afraid; I am the living, the first and the last.
¹⁸ I was dead, and behold, I am alive forever and ever, and I have the keys of death and hell.
¹⁹ Then write down what you have seen and what will happen hereafter.
²⁰ This is the secret of the seven stars and the seven golden lampstands that you saw in my right hand; The seven stars are the angels of the seven churches, and the seven candlesticks are the seven churches.