HiTech
1.64K subscribers
250 photos
5 videos
76 files
51 links
HiTech | Learn. Fix. Create. 📱💻🎨
Your Ethiopian tech hub!

We teach: Smartphone Repair
Laptop & Chip-Level Repair
Graphics & Motion Design
Coding & Web Development
Tools, Tips & Tech Reviews

Join the HiTech family — grow your skills & build
Download Telegram
•ፓራሌል/ parallel circuit:-
~ትይዩ ሰርኪዩት ሲሆን ሁሉም አምፖሎች ቀጥታ ሶርስ ስለሚያገኙ አንዱ ቢበላሽ እንኳን ቀሪዎቹ ይሰራሉ።
~በዚህ ጊዜ ደግሞ:
√እያንዳንዱ ቮልቴጅ ከዋናው/ሳፕላይ ቮልቴጅ እኩል ነው።
√የእያንዳንዱ ከረንት ድምር ደግሞ ከዋናው ከረንት እኩል ነው።
√የሪዝስታንስን ድምር ለማግኘት ደግሞ የእያንዳንዱን ሪዝስታንስ ግልባጭ በመደመር ምናገኘው ዉጤት ግልባጭ/resprocal መዉሰድ ነው።

@cellphonetechnology
Series/parallel በአንድ ላይ ልናገኝም እንችላለን።

@cellphonetechnology
Mobile Problem Solution:

መሰረታዊ የኤሌክትሪክ ጥንቃቄዎች/Basic Electrical Safety
💡💡💡መግቢያ/introduction:-
~ቤት ውስጥም ሆነ ስራ ቦታ የኤሌክትሪክ ጥንቃቄ ወሳኝ ነው። መወሰድ ያለባቸው መመሪያዎችም አሉ። እነርሱን ከማየታችን በፊት:
•ኤሌክትሪክ ሾክ/የኤሌክትሪክ ንዝረት ምንድን ነው?
•ኤሌክትሪክ ለምንድን ነው ሰወችን የሚነዝረው/የሰው ልጆች የሪዚስታንስ መጠናቸው ስንት ነው?
.

ኤሌክትሪክ ንዝረት/Electric shock:-
~የኤሌክትሪክ ንዝረት የሚከሰተው አንድ ሰው ከኤሌክትሪክና ኤሌክትሪክ አስተላላፊ ከሆነ ነገር ጋር ቀጥተኛ ወይም ኢ-ቀጥተኛ የሆነ ንክኪ ሲኖረው ነው።
~የኤሌክትሪክ ሃይል/ቻርጅ በሰወች የሰውነት ክፍል ሲፈስ ኤሌክትሪክ ሾክ ይፈጠራል።
•ኤሌክትሪክ ለምንድን ነው ሰወችን የሚነዝረው/የሰው ልጆች የሪዚስታንስ መጠናቸው ስንት ?
~የአንድ ማቴሪያል ኤሌክትሪክ የማስተላለፍ አቅም የሚወሰነው የኤሌክትሪክ ቻርጅ ፍሰት የመቃወም አቅም ነው።
~ከፍተኛ የሪዚስታንስ ዋጋ ካለው ኤሌክትሪክ የማስተላለፍ አቅሙ ዝቅተኛ ነው። ለምሳሌ:- ኤሌክትሪክ በማስተላለፍ ጥሩ የሚባለውና በየቀኑ የምንጠቀምበት መዳብ/Copper ኤሌክትሪክ የማስተላለፍ አቅም 1.72×10^-8 ኦም ሜትር ሲሆን ኤሌክትሪክ የማስተላለፍ አቅሙ ደካማ የሆነው አየር ደግሞ 1.5×10^14 ኦም ሜትር ነው ።
~በዚህ መሰረት የኛ ሰወች ኤሌክትሪክ የማስተላለፍ አቅማችን እናያለን።
~ሰውነታችን የኤሌክትሪክ ፍሰትን የሚቃወም ሪዚስታንስ አለው። ነገር ግን ከ 99% በላይ የሚሆነው ኤሌክትሪክ ሪዚስታንስ የሚገኝው ቆዳችን ላይ ነው። በዚህም መሰረት ቆዳችን ውሃ ወይም እርጥበት ካልነካው ኤሌክትሪክ ሪዚስታንሱ 100,000 ohm ሲሆን ውስጣዊው የሰውነት ክፍላችን ድግሞ 300 ohm ነው። ስለዚህ ዉስጠኛው የሰውነት ክፍላችን ወይም እርጥበት የነካው እጃችን ደግሞ ኤሌክትሪክ የማስተላለፍ አቅሙ ከቆዳችን አንፃር ሲታይ እጅግ ከፍተኛ ነው።
~ ስለዚህ በኤሌክትሪክ አደጋ የምንጠቃው ቆዳችን ከፍተኛ በሆነ ቮልቴጅ(500Vና ከዛ በላይ) ከተሰነጣጠቀ ወይም ቆዳችን በእርጥበት አማካኝነት ኤሌክትሪክ ሪዚስታንሱ ከቀነሰ ነው።
~ ከማንኛውም ኤሌክትሪክ ሀይል መጠን ካለው ሲስተም ራሳችን መጠበቅ አስፈላጊ ሲሆን መውሰድ ያለብንን ጥንቃቄዎች ቀጥለን እናያለን።


@cellphonetechnology
የሞባይል ሚስጥሪዊ አልግሎቶች
1ኛ. ሞባይሉ ዉስጥ ያለዉን ስልክ ቁጥር ለማግኘት፡-*111#
2ኛ. የሞባይል የተሰራበት ዘመንና ባትሪን ለማወቅ፡-*#*#4636#*#*
3ኛ. የሞባይል ሚስጥረ ቁጥር/IMEI/ serial No፡-*#06#
4ኛ. የሞባይሉ ዋና መስገብ ሰርቨስ ለማገኝት፡-*#0*#
5ኛ.የሞባይል ኮሜር መረጃ ለመግኘት፡-*#*#3497
1539#*#*
6ኛ. ሞባይሉ ላይ ሙል ፋይል ለማግኛት፡-*#*#2732
82*255*663282*#*#*
7ኛ. የሞባይሉ ዋይለስ LAN/ ለማየት፡-*#*#232339#*#*
8ኛ. ሞባይልን አገልግሎት ለማስጀመር፡-*#*#197
328640#*#*
9ኛ. የሞባይልን ግልጽ ማብራት ለማየት፡-*#*#0842#*#*
10ኛ. የሞባይልን የእስክር መያዥ ለማየት፡-*#*#2664#*#*
11ኛ.የሞባይልኑ ቫይቭረሽን ለማየት፡-*#*#0842#
*#*
12ኛ.የሞባይሉን ኤፍት ሶፍትወሩን ለማየት፡-*#*#1111#*#*
13ኛ. የሞባይሉን ሶፍትወር እና ሃርድወር መረጃ ለማየት፡-*#125080*
369#
14ኛ. የሞባይሉን ኮንፍግረሽንና ዳያጎሽትክ ለማየት፡-*#9090#
15ኛ. የሞባይሉን ሴታፕና ድሞድ(Dump Modef) ለማያት፡-*#9900#
16ኛ. የሞባይሉን ሜኑ(HSDPA/HSUPA:- *#301279#
17ኛ. የሞባይሎን ዩስፕ(USB) ለማየት፡-*#872564#
18ኛ. የሞባይሎን ጽፈት ለማየት፡- *#7465625#
19ኛ. የሞባይሉን ዳታ መረጃ ወደ መጀመሪያ ምሪት ለመሜልስ፡- *#*#7780#*#*
20ኛ. የሞባይሉን ወደ ፈብርካ ምርት ለመሜልስ፡-*2767*3855#
21ኛ. የሞባይሎን Motorola droids ለማግኘት፡-##776426
We buy any screen damaged phones

ማንኛውንም አይነት የተበላሸ ስልክ እንገዛለን!

እንሠራለን


@cellphonetechnology

+251922888396
👍1
የሞባይል ሚስጥሪዊ አገልግሎቶ!!
1ኛ. ሞባይሉ ዉስጥ ያለዉን ስልክ ቁጥር ለማግኘት፡-*111#
2ኛ. የሞባይል የተሰራበት ዘመንና ባትሪን ለማወቅ፡-*#*#4636#*#*
3ኛ. የሞባይል ሚስጥረ ቁጥር/IMEI/ serial No፡-*#06#
4ኛ. የሞባይሉ ዋና መስገብ ሰርቨስ ለማገኝት፡-*#0*#
5ኛ.የሞባይል ኮሜር መረጃ ለመግኘት፡-*#*#3497
1539#*#*
6ኛ. ሞባይሉ ላይ ሙል ፋይል ለማግኛት፡-*#*#273282*255*663282*#
*#*
7ኛ. የሞባይሉ ዋይለስ LAN/ ለማየት፡-*#*#232339#*#*
8ኛ. ሞባይልን አገልግሎት ለማስጀመር፡-*#*#197
328640#*#*
9ኛ. የሞባይልን ግልጽ ማብራት ለማየት፡-*#*#0842#*#*
10ኛ. የሞባይልን የእስክር መያዥ ለማየት፡-*#*#2664#*#*
11ኛ.የሞባይልኑ ቫይቭረሽን ለማየት፡-*#*#0842#
*#*
12ኛ.የሞባይሉን ኤፍት ሶፍትወሩን ለማየት፡-*#*#1111#*#*
13ኛ. የሞባይሉን ሶፍትወር እና ሃርድወር መረጃ ለማየት፡-*#125080*369#
14ኛ. የሞባይሉን ኮንፍግረሽንና ዳያጎሽትክ ለማየት፡-*#9090#
15ኛ. የሞባይሉን ሴታፕና ድሞድ(Dump Modef) ለማያት፡-*#9900#
16ኛ. የሞባይሉን ሜኑ(HSDPA/HSUPA:- *#301279#
17ኛ. የሞባይሎን ዩስፕ(USB) ለማየት፡-*#872564#
18ኛ. የሞባይሎን ጽፈት ለማየት፡- *#7465625#
19ኛ. የሞባይሉን ዳታ መረጃ ወደ መጀመሪያ ምሪት ለመሜልስ፡-
*#*#7780#*#*
20ኛ. የሞባይሉን ወደ ፈብርካ ምርት ለመሜልስ፡-*2767*3855#
21ኛ. የሞባይሎን Motorola droids ለማግኘት፡-##776426


✍️ ለጓደኛዎ #share ማድረጎን አይርሱ።
👍51
🔘ቴሌግራምን hack እንዳይደረግብዎ ይፈልጋሉ?
🔐መፍትሄውን እነሆ🔐
❖.ቴሌግራም ማለት እንደ ማንኛውም የ messaging application ነው ማለትም እንደ⇝whatsapp, viber, imo, tango.....etc
📌ቴሌግራም እንደ whatsapp, viber,imo...ሁሉ በቀላሉ በ "sms-based verification process" hack ሊደረግ ይችላል
❖. ይህ ዘዴ ሌሎች hack ማድረጊያ hacking Tricks ሳያስፈልገን አፕሊኬሽኖች በመጠቀም
ማለትም የራሳችን ቴሌግራም አፕሊኬሽን ላይ ወይም pc ላይ ቴሌግራም install በማድረግ የምንፈልገውን ቁጥር በማስገባት ኮዱን ካስላክን ብኋላ ኮዱን የምናገኝበት አጋጣሚ ካለ....
❖. በመጀመሪያም ይህ መሆኑን እና አለመሆኑን ለማረጋገጥ አሁን step by step ተከታተሉኝ
❶ Telegram⇢seting⇢privecy and security⇢active session ላይ በመግባት በእናንተ አካውንት የገባ ሰው እንዳለና እንደሌለ ማወቅ ያስችላል።
■Note: እራስዎ በሌላ አፕ ከገቡም ያመጣልዎታል ስለዚህ በደንብ ይመልከቱ።
📌ከዛም Terminate all other sessions ክሊክ በሉት።
☛ ይህ ሚጠቅመው በሌላ ስልክ የእናንተን አካውንት የሚጠቀም ሰው ካለ remove ያደርገዋል።
❷ Security ደግሞ ለማጠናከር
seting⇢privecy and security⇢two step verification⇢set aditional pasword ከዛ የፈለጉትን password ***..ግን የ gmail አካውንት ሊኖራቹ ይገባል።
❖ ይህ ጠንካራ የሚባለው #የቴሌግራም security ነው።
❖ የሚጠቅመው እንደፌስቡክ ሁላ በሌላ ስልክ ስንገባ password ይጠይቀናል (log in) እያልን ነው የምንገባው ማለት ነው።
❖ ሌላ ሰው በsms የተላከውን ኮዳችሁን አግኝቶ እንኳ ቢከፍተው
ወደቴሌግራማችሁ በጭራሽ መግባት አይችልም።
❖ ማንም ሰው ለመግባት በኢሜል የሰጣችሁት ኮድ ማወቅ ስለማይችል በጭራሽ መግባት አይችልም።
⚠️የፃፋችሁትን password እንዳትረሱት።
⚠️ከላይ ያሳየናችሁ ዘዴ ቴሌግራማችሁን በቀላሉ ኮዱን ወስደው በናንተ ቁጥር እንዳይጠቀሙ ነው እንጂ የተለያዩ hacking ዘዴን በመጠቀም ሃክ ከመደረግ አይከለክልም ለምሳሌ ☛Kali linux.
═════════════════
▒▓⇨→መረጃዎች ቶሎ ቶሎ እንዲደርሶት ስልኮቻችሁ ላይ ላሉ
❖ Contact
❖ Group and Channel share አድርጉለን ከምስጋና ጋር።
╚═════📌Share📌════╝
👍3
☑️ ሀከር ምንድን ነዉ ?| Who is a Hacker
ሀከር ማለት አንድ ግለሰብ ወይም ቡድን አንድን ኮምፒዉተር ወይም የኮምፒዉተር ኔትወርክ ሲስተም ለራሱ ትርፍ ወይም ለመዝናናት ሰብሮ የሚገባ ነዉ።
♻️ የሀከር አይነቶች | Types of Hackers
ሀከሮች በሶስት ወሳኝ አይነቶች ይከፈላሉ :-
⚪️White Hat Hackers :-እነዚህ ሀከሮች የሀኪንግ እዉቀታቸዉን ተጠቅመዉ ህገወጥ የመረጃ ብርበራ የማያደርጉ ናቸዉደ ስለዚህ ጥሩ ሀከሮች ነዉ የሚባሉት። እንዲሁም Security expert በመባል ይታወቃሉ።
⚫️ Black Hat Hackers :-የነዚህ አይነት ሀከሮች ብዙ ጊዜ crackers ይባላሉ ። እነዚህ ሀከሮች የሀኪንግ እዉቀታቸዉን ተጠቅመዉ ህገወጥ ተግባራትን ያከናዉናሉ ። ለምሳሌ ልክ እነደ credit card ዘረፋ ፣ ባንኮችን ሀክ ማድረግ ...ወዘተ ክሬዲት ካርድ ዘረፋ ላይ የሚሳተፉ ሀከሮች ናቸው።
🔘 Grey Hat Hackers :-ግሬይ ሀት የምንላቸዉ በwhite hat እና በblack hat መካከል የሚገኙ hybrid ናቸዉ ይህም ማለት አንዳንዴ black hat አንዳነዴ ደሞ white hat ሀከርስ ይወላዉላሉ ማለት ነዉ።
☑️ የሀከሮች ደረጃ | Hacker Hierarchy
❇️ Scriptkiddies :-እነዚህ የሀኪንግ ልምድ የሌላቸዉ ግለሰቦች / ቡድን ግን ሀከር መሆን የሚፈልጉ ናቸዉ። ሀክ ለማድረግ የሚጠቀሙትም ready made tool ወይም የተዘጋጀ ሶፍትዌር ነዉ። በዙ ጊዜም ልምድ ስለሌላቸዉ እራሳቸዉን harm ያደርጋሉ። አንድ ታዋቂ ጥቅስ አለ "Little knowledge is dangerous" ይህም ብዙ ጊዜ የምናየዉ ችግር ነዉ።
❇️ Intermediate hackers :-ከscriptkiddies የበለጠ የሀኪንግ ልምድ እንዲሁም እዉቀት ያላቸዉ ሀከሮች ናቸዉደ ግን የራሳቸዉን exploit ወይም የሀኪንግ ሶፍትዌር መስራት አይችሉም ።ቢሆንም ጥሩ ልምድ ያላቸዉ ሀከሮች ናቸዉ።
❇️ Professional or Elite hackers :-እነዚህ ልምድ ያላቸዉ ሀከሮች የራሳቸዉን exploit ወይም የሀኪንግ ሶፍትዌር መስራት ይችላሉ ።ስለሆነም የትኛዉም አይነት system ሰብረዉ መግባትና ራሳቸዉን የመደበቅ ልምድ አላቸዉ።
🖥 ሀከር ለመሆን ምን ይጠበቅብናል?| What Takes to Become a Hacker?
በአንድ ምሽት master የምናደርገዉ ነገር አይደለም። በጣም ትግስት እና hard work ይፈልጋል። ብዙ ጊዜ ከአዳዲስ ሀከሮች የማየው ችግር በትንሽ ስራ ትልቅ ዉጤት ይጠብቃሉ ። ይሄ ደሞ የማይሆን ነዉ ። ስለዚህ አንድ የሀኪንግ topic ከያዝን ያን topic በደንብ master እስክናደርገዉ አንዲሁም በተግባር እስኪሳካልን ድረስ በደንብ መለማመድ ይጠበቅብናል። ይሄን የምናደርግ ከሆነ እራሳችን ላይ ለዉጡን በፍጥነት ማየት እንችላለን። በተለይምhacker ለመሆን ከ 5 በላይ የ programming languages ማወቅ ያስፈልገናል ። ስለዚህ ከ programming ጀምሩ!!

#የተማሩትን_ማስተማር #ያወቁትን_ማሳወቅ #ብልህነት ነው
#ለሰው መልካሙን እንጅ መጥፎውን አትመኝ🙏
👍4
Blower . . . 8000 birr
ኡቡንቱ(Ubuntu Operating system)

1980ዎቹ ዩኒክስ ኦፕሬትንግ ሲስተም ብዙ ኮንፒተሮች ይጠቀሙ ስለነበር የተለያዩ ሰዎች የኦፕሬትንግ ሲስተምን ኮድ(source code) ባለቤትነት ጥያቄ በማቅረብ የኒክስ ኮዱን ማጋራት አንዲከለከል ወሰኑ፡፡ ይህን ቀድሞ ያየው ተዋቂዉ የኮንፒተር ባለሙያ ሪቻርድ ስታልማን ዩኒክስ ኦፕሬትንግ ሲስተም ተመሳሳይ ግለባጭ ለመስራት ወስነ፡፡

በሪቻርድ ስታልማን እምነት ሶፍትዎር መጋራት(share) ምንም ጉዳት አንደሌለው እና የሶፍትዌር ጥራትንም እደሚጨምር ያምን ነበር፡፡ ሪቻርድ ስታልማን የሰራውን ዩኒክስ ኦፕሬትንግ ሲስተም ለማንም ሰው እዲጠቀመው በነጻ ለቀቀው፡፡

በሪቻርድ ስታልማን እና ኮናኪያል ዩኒክስ ኦፕሬትንግ ሲስተም በማሻሻል አንዲሁም ለአንድ ኦፕሬትንግ ስሰተም ከሃርድዌርጋ ለመግባባት ወሳኝ የሆነው ከርንል በማካተት 2004 ለመጀመሪያ ግዜ ተለቀቀ፡፡ሰሙም ኡቡንቱ ተብሎ ተሰየመ፡፡

ኡቡንቱ ማለት አፍሪካዊ ቃል ስሆን ትርጉሙ “ለሌላው ማስብ” ወይም “ሰብአዊነት” ማለት ነው፡፡ ኡቡንቱ ተወዳጂነት ያተረፈው ወዲያው ነበር ከሌላው ሉኔክስ ኦፕሬቲንግ ስሰተም ቀላል እና ለመልመድ የማያስቸግር በመሆኑ ተወዳጅነትን አትርፍዋል፡፡ኡቡንቱ ከፈተኛ ድጋፍ ከሚደረግላቸው ትልቅ ኦፕሬትንግ ሲስተም ስለሆነ በየስድት ወር ይዘምናል(update)፡፡

ኡቡንቱ ከሌላ ኦፕሬትንግ ሲስተም ምን ይለየዋል፡

👉 የቨይረስ ጥቃት ነጻ መሆኑ
👉 በፍጥነት የተሻለ በመሆኑ
👉 ድራይቨር መጫን አለመጠየቁ ወይም አለማስፈለጉ
👉 የራም አና የሲፒዩ አጠቃቀሙ የተሻለ በመሆኑ
👉 ትልቅ ድጋፍ ስላለው ለሪሰርች
👉 ለሳይንቲፊክ ጥናት ተመራጭ በመሆኑ
👍2
💢 ለላፕቶፕ ኮምፕዩተራችን ልናደርግ የሚገቡ ጥንቃቄዎች⚠️

1⃣. ሁሌም ተጠቅመን ስንጨርስ shutdown ‼️ ማድረግ

⚠️(በ power button ማጥፋት ኮምፒውተሮትን ይጎዳል )

2⃣. የላፕቶፕዎን ቅዝቃዜ ይጠብቁ

⚠️ እግር ላይ, ትራስ ላይ, አልጋ ላይ አስቀምጦ መጠቀም የላፕቶፕ ኮምፒውተሮት 💻 በቶሎ እንዲግል እና ማቀዝቀዣው (fan) እንዳይሰራ ያደርጋል ።

3⃣. በሚጠቀሙበት ጊዜ ባትሪ አይንቀሉ።

4⃣.በማይጠቀሙበት ጊዜ ማንኛውንም accessories ይንቀሉ ምክንያቱም ኮምፕዩተሮትን 🖥 እንዲግል ወይንም አላስፈላጊ ስራ እንዲሰራ ያደርጋሉ።

5⃣. አንቲ ቫይረስ ይጫኑ

⚠️ አፕዴት መደረጉን እርግጠኛ ይሁኑ።

6⃣. ከውሀና ከአቧራ ይጠብቁት።

7⃣. ቢያንስ በአመት 1 ጊዜ service ያስደርጉት ።
@cellphonetechnology
👍1
💢#ሞባይል #ባትሪና #ቻርጀር ስንገዛ ኦርጅናልና ፌክ ኮፒ መሆኑን እንዴት ማወቅ (መለየት) እንደምንችል እነሆ...⬇️⬇️⬇️

✔️ከሌሎች በይበልጥ ሳምሰንግ ስልኮች ተፈላጊነታቸዉ እየጨመረ በመጣ ቁጥር፣ ከኦርጂናሉ ጋር ተመሳስለዉ በቻይና የሚመረቱ #ፌክ ሳምሰንግ ስልኮችም📱 በዛዉ መጠን ይጨምራሉ፡፡

🔆ሳምሰንግ የጉግልን አንድሮይድ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ይጠቃማል፣ የአንድሮይድ ሲስተም ኮድ ደግሞ ማንኛዉም ፍላጎት ያለዉ አካል ኮዱን እንዲጠቀም የሚያስችል
ፍቃድ ስለሚሰጥ፣ አጭበርባሪ ድርጅቶች #ከኦርጂናሉ ስልክ ከፍተኛ ቅናሽ ያለዉን ተመሳሳይ ፌክ ሳምሰንግ ስልክ በማምረት ገበያዉን ያጥለቀልቁታል፡፡

⚠️ኦርጂናሉን ስልክ ከፌኩ በቀላሉ መለየት ያስቸግራል፣ ነገር ግን እነዚህን 👇 መንገዶች በመጠቀም ፌክ ሳምሰንግ
ስልኮችን መለየት ይችላሉ...

የስልኩን ቀፎ አካላዊ ገጽታዎች በመገምገም 👇

💢#ፌክ ሳምሰንግ ስልክ፡

1⃣. የስክሪኑ መስታወት ጥራት የለዉም‼️

2⃣. ስክሪኑ ከቀፎዉ ጠርዝ በጣም ይርቃል‼️

3⃣. ስክሪኑ ድምቀት ይጎድለዋል‼️

4⃣. የሳምሰንግ ሎጎ (ሳምሰንግ የሚለዉ ጽሁፍ) ሲነካ
ይሻክራል፣ በደንብ ከተጫኑት ይለቃል‼️

5⃣. ከኦርጂናል ስልኮች ጋር ሲያስተያዩት፤ የባትሪ መክደኛዉን ሲከፍቱ የሚታዩ ትንንሽ አካሎች እና ባትሪዉ ላይ የሚገኙት መረጃዎች የተለያዩ መሆናቸዉን ይመለከታሉ‼️

የስልኩን ፍጥነት እና የትእዞች አፈጻፀም በመገምገም *

1⃣. በስልኩ ፎቶዎችን ለማንሳት ይሞክሩ፣ በፌክ ሳምሰንግ
ስልኮች የሚያነሱት ፎቶ ጥራት የወረደ ይሆናል 😡

2⃣. በተመሳሳይ ጊዜ በርካታ ጌሞች 🎮 እና አፕሊኬሽኖችን
ለመክፈት ይሞክሩ፣ ፌክ ስልኮች ስታክ(ቀጥ) የማለት ባህሪይ ያሳያሉ፡፡ 😡😡

3⃣. ስልኩን አጥፍተዉ ያብሩት፣ ፌክ ስልኮች ቶሎ አይከፍቱም😡😡😡

የስልኩን የምርት መረጃዎች በመገምገም *

1⃣. ወደ ዋናዉ ማዉጫ ይሂዱ እና አፕስ(Apps) የሚለዉን ቁልፍ ይጫኑ...

2⃣. ከአፕሊኬሽን ማዉጫዉ ላይ፣ #Settings የሚለዉን ይጫኑ...

3⃣. ከ Settings ላይ More የሚለዉን ይጫኑ እና Storage የሚለዉን በመጫን ስልኩ ላይ መጫን ሚችሉትን የዳታ መጠን ይመልከቱ፤ #ከኦርጂናሎቹ ስልኮች በጣም ያነሰ ከሆነ ፌክ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡

4⃣. እንዲሁም About device የሚለዉን ይጫኑ እና
የስልኩን ሞዴል ቁጥር እና baseband, build number
ጉግል ላይ ይፈልጉት፣ የሚያገኙት መልስ ፌክ ወይም #ኦርጅናል መሆኑን ይነግሮታል፡፡

የሳምሰንግ ኮዶችን በመጠቀም *

💢ወደ ስልክ📱 መደወያዉ በመሄድ፣ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ኮዶች ያስገቡ እና Call የሚለዉን ይጫኑ፤ ስልኩ
ያስገቡትን ኮድ አዉቆ መልስ መስጠት ከቻለ ኦርጅናል ✔️
መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡ ካልሆነ ግን 😭 ፌክ ስልክ ነዉ፡፡

1⃣. *#0*# 👉 አጠቃላይ መገምገሚያ

2⃣. *#1234# or *#9999# 👉 ስልኩ የሚጠቀመዉን
ሶፍትዌር እና ሞደም ማወቂያ

3⃣. *#12580*369# 👉 ስለ ስልኩ ሶፍትዌር እና ሀርድዌር ማወቂያ

4⃣. *#06# 👉 የስልኩን ኢንተርናሽናል መለያ ቁጥር
ማወቂያ

5⃣. *#9998*246# 👉 የስልኩን የባትሪ እና ሚሞሪ መረጃዎች ማወቂያ

ሳምሰንግ ኪይስ(Samsung Kies) ሶፍትዌርን በመጠቀም *

💢ከላይ 👆 በተጠቀሱት መንገዶች ፌክ ሳምሰንግ ስልክን መለየት ካልቻሉ ይህን ሶፍትዌር ይጠቀሙት፡፡

1⃣. Samsung Kies ሶፍትዌርን ኮምፒዉተሮት💻 ላይ
ይጫኑት...

2⃣. ለማረጋገጥ የፈለጉትን ስልክ ከኮምፒዉተሮት ጋር ያገኛኙት

3⃣. ሶፍትዌሩ ስልኩን 📱ያነበዉ እና የስልኩን ስም ፣የሚጠቀመዉን ሶፍትዌር እና ሀርድዌር ያሳያል
ሶፍትዌሩ ስልኩን ማንበብ ካልቻለ በድጋሚ ይሞክሩት በድጋሚ ማንበብ ካልቻለ ሰልኩ ፌክ መሆኑን ያረጋግጣሉ፡፡

@cellphonetechnology
2