Unique Academy
1.79K subscribers
200 photos
6 videos
25 files
214 links
☆ Welcome to Unique Maths!
" LEARN UNIQUELY AND FLUENTLY " Join us for effective learning Process....

☆ Youtube Channal : https://www.youtube.com/@Uniquemathematic

☆ CEO : Yishak Debebe & Henok Debebe
Download Telegram
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ወደ ፊት የሚገለጽ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

እስከዛ ድረስ ጉርድ ፎቶግራፍ ተነስታችሁ በ https://ssms.wru.edu.et/sp አማካኝነት ወደ ሲስተም ከጥቅምት 30/2018 ዓ.ም እስከ ህዳር 05/2018 ዓ.ም እንድታስገቡ ተብሏል፡፡

የምታስገቡት ጉርድ ፎቶግራፍ ጥራት ባለው ስማርት ስልክ የተነሳችሁት መሆን ይኖርበታል፡፡ ፎቶው ወደ ሲስተሙ ከገባ በኋላ ተቀባይነት እስከሚያገኝ ድረስ Waiting for Approval የሚል ምላሽ ሲስተሙ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ተቀባይነት ካገኘ Approved ፤ ተቀባይነት ካላገኘ Rejected የሚል ምላሽ ሲሰተሙ የሚሰጥ ሲሆን Rejected የተባለው ፎቶግራፍ በሌላ ጥራት ባለው ጉርድ ፎቶግራፍ መቀየር ይኖርብዎታል፡፡

ለበለጠ መረጃ፦
0925139032 / 0712595832 መኪ
0913737976 / 0717737976 ሀሺም
#BahirDarUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ ህዳር 11 እና 12/2018 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች - ግሽ አባይ ግቢ
➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች - ዘንዘልማ ግቢ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 መጠን የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
1
#JigjigaUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ ከህዳር 05-08/2018 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ ከ8-12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስምንት ፓስፖርት መጠን የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ልብስ፡፡

ህዳር 09/2018 ዓ.ም ለአዲስ ገቢ የሪሚዲያል ተማሪዎች ገለጻ የሚሰጥ ሲሆን፤ የመጀመሪያ ቀን ትምህርት ህዳር 10/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።
8😁1
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ህዳር 15 እና 16/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 የሆነ የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፍ፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣
➫ ዲጂታል መታወቂያ፣
➫ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
1
#RayaUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ራያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 22 እና 23/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
#JinkaUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ህዳር 10 እና 11/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ያሉ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው እንዲሁም አንሶላ እና ትራስ ጨርቅ መያዝ ይኖርባችኋል።

ትምህርት ህዳር 15/2018 ዓ.ም ይጀመራል ተብሏል።
👍4
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም እንዲሁም በቅጣት ህዳር 29/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ትምህርት የሚጀምረው ህዳር 29/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ መጠኑ 3×4 የሆነ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣
➫ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
#JinkaUniversity

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ለተመደቡ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው ከጥቂት ቀናት በፊት ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ የምዝገባው ጥሪ ላልተወሰን ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በመሆኑም በቀጣይ በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ እስከሚደረግላቹ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል።
1
#DireDawaUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ህዳር 20 እና 21/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3×4 መጠን የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ የብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) FAN No.፣
➫ ከአካባቢው የአየር ሁኔታ ጋር የሚስማማ እንሶላ እና ትራስ ልብስ፡፡

(ተጨማሪ መረጃ ከምስሉ ይመልከቱ።)
4
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ በ2019 የትምህርት ዘመን ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

ለመምህራን የሚቀርበው ጥቅማጥቅምና ደመወዝ በቂ አለመሆን ለመምህራን እጥራት ምክንያት እንደሆነ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለምክር ቤት አባላት ተናግረዋል። ይህም አዲስ መምህራንን በበቂ ሁኔታ ለማፍራት አስቸጋሪ እንዳረገው ገልፀዋል።

የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ግለሰቦች የአንድ ዓመት የማስተማር ዘዴ (Pedagogy) ኮርስ በመውሰድ ለመምህርነት ብቁ መሆን እንደሚችሉ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በዚህም የመምህራንን ቁጥር ለማሳደግ ይቻላል ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ሲሰጡ፣ የበለጠ የመምህነነት ሙያ ፍቅር ሊያጎለብቱ እንደሚችሉም ገልፀዋል።

ባለፈው ዓመት ከቅድመ-መዋዕለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል በሀገሪቱ አጠቃላይ የመምህራን ቁጥር 625,000 የነበረ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ቁጥሩን ወደ 700,000 ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።
#ArbaMinchUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ትምህርት ሰኞ ህዳር 29/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡

አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች https://smis.amu.edu.et/pages/check_campus_placement ሊንክን በመጫንና የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መለያ ቁጥር በማስገባት የተመደባችሁበትን ካምፓስ ማወቅ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

የምዝገባ ቦታ፦
➫ አባያ እና ጫሞ ካምፓሶች የተመደባችሁ ተማሪዎች አርባ ምንጭ ከተማ በሚገኙት አባያ እና ጫሞ ካምፓሶች
➫ ሳውላ ካምፓስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሳውላ ከተማ በሚገኘው ሳውላ ካምፓስ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 2 ኮፒ፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና 2 ኮፒ፣
➫ አራት ፓስፖርት መጠን የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ እንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
#MattuUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር መቱ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ታህሳስ 01 እና 02/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ትምህርት ታህሳስ 03/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦ በበዴሌ እና በመቱ ካምፓሶች

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት መጠኑ 3×4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)
➫ ብሔራዊ መታወቂያ (Fayda)
➫ ብርድ ልብስ፣ እንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
#MekdelaAmbaUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
➫ የተፈጥሮ ሳይንስ የሪሚዲያል ተማሪዎች በዋናው ካምፓስ (ጊምባ)
➫ የማኅበራዊ ሳይንስ የሪሚዲያል ተማሪዎች በመካነ-ሰላም ካምፓስ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስምንት መጠኑ 3×4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣
➫ ብሔራዊ መታወቂያ (Fayda)፣
➫ የሌሊት አልባሳት እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
4
#AmboUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር አምቦ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 29 እና 30/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ካምፓስ
➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሃጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት መጠኑ 3×4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
#BuleHoraUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ ህዳር 29 እና 30/2018 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ትምህርት ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም ይጀመራል ተብሏል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 2 ኮፒ፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና 2 ኮፒ፣
➫ ስምንት 3x4 መጠን የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ የብሔራዊ መታወቂያ ፋይዳ (National ID) ፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
#WolloUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በኮምቦልቻ ግቢ
➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በደሴ ግቢ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 2 ኮፒ፣
➫ አራት መጠኑ 3×4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ፡፡
#AssosaUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ታህሳስ 02 እና 03/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ትምህርት ታህሳስ 04/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 2 ኮፒ፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና 2 ኮፒ፣
➫ ስምንት መጠኑ 3×4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ ብሔራዊ መታወቂያ ፋይዳ (National ID)፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስምንት መጠኑ 3×4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣
➫ ብሔራዊ መታወቂያ (Fayda)፣
➫ የሌሊት አልባሳት እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
1
#WoldiaUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ታህሳስ 06 እና 07/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ትምህርት የሚጀምረው ታህሳስ 08/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ መጠኑ 3×4 የሆነ የቅርብ ጊዜ አራት ፎቶግራፍ፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣
➫ ብሔራዊ መታወቂያ (Fayda)፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
#SamaraUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ መጠኑ 3×4 የሆነ ስምንት ፎቶግራፍ፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣
➫ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡