Unique Academy
1.79K subscribers
200 photos
6 videos
25 files
214 links
☆ Welcome to Unique Maths!
" LEARN UNIQUELY AND FLUENTLY " Join us for effective learning Process....

☆ Youtube Channal : https://www.youtube.com/@Uniquemathematic

☆ CEO : Yishak Debebe & Henok Debebe
Download Telegram
የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ይዘቶች ይፋ ሆኑ፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ ተማሪዎች፣ የተማሪ ቤተሰቦች፣ መምህራንና የትምህርት አመራር ለፈተና ዝግጅት በሚያደርጉበት ወቅት ፈተና የሚሸፍናቸው የይዘት አካባቢዎች ይፋ አድርጓል።

የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ከፍል ፈተና ዝግጅትና አስተዳደር የሚከተሉትን ያካትታል፡፡ 

1. የትምህርት ዓይነቶችን በተመለከተ

ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ፦
- እንግሊዘኛ፣
- ሒሳብ፣
- እስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣
- ኬሚስትሪ፣
- ፊዝክስና ባዮሎጂ

ለማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ፦
- እንግሊዘኛ፣
- ሒሳብ፣
- እስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣
- ታሪክ፣
- ጂኦግራፊና ኢኮኖሚክስ ናቸው።

2. ፈተናው ከ9ኛ እስከ 12ኛ ከፍል ደረጃዎችን እና በተማሪው መጽሐፍ ላይ ያሉትን ሁሉንም ምዕራፎች ይሸፍናል፡፡

3. ከ10ኛ – 12ኛ ክፍል ሁሉም የትምህርት ዓይነት ፈተና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት እየተዘጋጀ ያለ ሲሆን የ9ኛ ክፍል ደግሞ የሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ፈተናዎች ከቀድሞውና ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርቶች የጋራ ይዘቶችን ብቻ አካቶ እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡

4. ፈተናው ማንኛውም ተፈታኝ ተማሪ ከተማረው ሥርዓተ ትምህርትና ከተማሪው መጽሐፍ ላይ ብቻ ተመስርቶ እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡

5. የፈተናው አስተዳደር በበይነ መረብና በወረቀት ጎን ለጎን የሚሰጥ ሲሆን አብዛኛው ተፈታኝ በበይነ መረብ እንዲፈተን እየተሠራ ያለ በመሆኑ ተፈታኞች እራሳቸውን በበይነ መረብ ለመፈተን ሊያዘጋጁ ይገባል፡፡

#EAES
4
Unique Academy
Photo
#Digital_ID

በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የምትወስዱ ተማሪዎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን እንድታወጡ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

ማንኛውም ተማሪ ፈተና ላይ ለመቀመጥ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሊኖረው እንደሚገባ መወሰኑ ይታወሳል።

በመሆኑም በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ የሆናችሁ ተማሪዎች በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ማውጫ ማዕከል በመመዝገብ መታወቂያውን ማውጣት ይኖርባችኋል ተብሏል።
ከ20 በላይ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የ2018 ትምህርት ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎቻቸውን ዛሬ እና ነገ ይቀበላሉ፡፡

ዩኒቨርሲቲዎቹ በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር አዲስ የተመደቡ መደበኛ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትለው የማለፊያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን ይቀበላሉ፡፡

ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም አዲስ ገቢ ተማሪዎችን የሚቀበሉ ዩኒቨርሲቲዎች፦

➫ ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
➫ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ
➫ መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ
➫ ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ
➫ ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ
➫ መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ
➫ ዲላ ዩኒቨርሲቲ
➫ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ
➫ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ
➫ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ
➫ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ
➫ ቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ
➫ ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ
➫ አክሱም ዩኒቨርሲቲ
➫ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
➫ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ
➫ ቦረና ዩኒቨርሲቲ
➫ አምቦ ዩኒቨርሲቲ
➫ ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ
➫ መቱ ዩኒቨርሲቲ
➫ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
7
የ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ምደባ ተለቋል፡፡

በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ ብሔራዊ ፈተና ወስዳችሁ ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የ Remedial ፕሮግራም ለመከታተል የሚያስችል ማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የተቋም ምደባችሁን ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ማየት የምትችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

የተመደባችሁበትን ተቋም ለማየት 👇

በድረ-ገፅ፦ https://student.ethernet.edu.et
በቴሌግራም ቦት፦ @moestudentbot
4
#SalaleUniversity

በ2018 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ህዳር 02 እና ዐ3/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ ከ8-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና ትራስ ጨርቅ፣
➫ 3×4 የሆነ አራት ፎቶግራፍ፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ጀኔራል ታደሰ ብሩ ካምፓስ
2👏2
#BoranaUniversity

በ2018 ዓ.ም ቦረና ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ፕሮግራም የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ህዳር 03 እና 04/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ፈተና ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስምንት 3x4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
4
በ2018 ዓ.ም ቀብሪ ደሃር ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ፕሮግራም የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ህዳር 08 እና 09/2018 ዓ.ም እና ምዝገባ ህዳር 08 እና 09/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬቶች ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስምንት 3x4 የሆነ የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
3
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ወደ ፊት የሚገለጽ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

እስከዛ ድረስ ጉርድ ፎቶግራፍ ተነስታችሁ በ https://ssms.wru.edu.et/sp አማካኝነት ወደ ሲስተም ከጥቅምት 30/2018 ዓ.ም እስከ ህዳር 05/2018 ዓ.ም እንድታስገቡ ተብሏል፡፡

የምታስገቡት ጉርድ ፎቶግራፍ ጥራት ባለው ስማርት ስልክ የተነሳችሁት መሆን ይኖርበታል፡፡ ፎቶው ወደ ሲስተሙ ከገባ በኋላ ተቀባይነት እስከሚያገኝ ድረስ Waiting for Approval የሚል ምላሽ ሲስተሙ የሚሰጥ ይሆናል፡፡ ተቀባይነት ካገኘ Approved ፤ ተቀባይነት ካላገኘ Rejected የሚል ምላሽ ሲሰተሙ የሚሰጥ ሲሆን Rejected የተባለው ፎቶግራፍ በሌላ ጥራት ባለው ጉርድ ፎቶግራፍ መቀየር ይኖርብዎታል፡፡

ለበለጠ መረጃ፦
0925139032 / 0712595832 መኪ
0913737976 / 0717737976 ሀሺም
#BahirDarUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ ህዳር 11 እና 12/2018 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች - ግሽ አባይ ግቢ
➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች - ዘንዘልማ ግቢ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 መጠን የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
1
#JigjigaUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባ ከህዳር 05-08/2018 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ ከ8-12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስምንት ፓስፖርት መጠን የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ልብስ፡፡

ህዳር 09/2018 ዓ.ም ለአዲስ ገቢ የሪሚዲያል ተማሪዎች ገለጻ የሚሰጥ ሲሆን፤ የመጀመሪያ ቀን ትምህርት ህዳር 10/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል።
8😁1
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ህዳር 15 እና 16/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 የሆነ የቅርብ ጊዜ ፎቶግራፍ፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣
➫ ዲጂታል መታወቂያ፣
➫ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
1
#RayaUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ራያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ህዳር 22 እና 23/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
#JinkaUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የሚካሔደው ህዳር 10 እና 11/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ ያሉ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው እንዲሁም አንሶላ እና ትራስ ጨርቅ መያዝ ይኖርባችኋል።

ትምህርት ህዳር 15/2018 ዓ.ም ይጀመራል ተብሏል።
👍4
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም እንዲሁም በቅጣት ህዳር 29/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ትምህርት የሚጀምረው ህዳር 29/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ መጠኑ 3×4 የሆነ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣
➫ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
#JinkaUniversity

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ለተመደቡ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲው ከጥቂት ቀናት በፊት ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል።

ይሁን እንጂ የምዝገባው ጥሪ ላልተወሰን ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

በመሆኑም በቀጣይ በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ እስከሚደረግላቹ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል።
1
#DireDawaUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ህዳር 20 እና 21/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3×4 መጠን የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ የብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) FAN No.፣
➫ ከአካባቢው የአየር ሁኔታ ጋር የሚስማማ እንሶላ እና ትራስ ልብስ፡፡

(ተጨማሪ መረጃ ከምስሉ ይመልከቱ።)
4
የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የ3ኛ ዓመት ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት እንዲሰጡ የሚያስገድደው መመሪያ በ2019 የትምህርት ዘመን ተግባራዊ መሆን ይጀምራል።

ለመምህራን የሚቀርበው ጥቅማጥቅምና ደመወዝ በቂ አለመሆን ለመምህራን እጥራት ምክንያት እንደሆነ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ለምክር ቤት አባላት ተናግረዋል። ይህም አዲስ መምህራንን በበቂ ሁኔታ ለማፍራት አስቸጋሪ እንዳረገው ገልፀዋል።

የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ግለሰቦች የአንድ ዓመት የማስተማር ዘዴ (Pedagogy) ኮርስ በመውሰድ ለመምህርነት ብቁ መሆን እንደሚችሉ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል። በዚህም የመምህራንን ቁጥር ለማሳደግ ይቻላል ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለአንድ ዓመት የማስተማር አገልግሎት ሲሰጡ፣ የበለጠ የመምህነነት ሙያ ፍቅር ሊያጎለብቱ እንደሚችሉም ገልፀዋል።

ባለፈው ዓመት ከቅድመ-መዋዕለ ህጻናት እስከ 12ኛ ክፍል በሀገሪቱ አጠቃላይ የመምህራን ቁጥር 625,000 የነበረ ሲሆን፤ በዚህ ዓመት ቁጥሩን ወደ 700,000 ለማሳደግ እየተሠራ መሆኑ ተገልጿል።
#ArbaMinchUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ህዳር 25 እና 26/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ትምህርት ሰኞ ህዳር 29/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡

አዲስ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች https://smis.amu.edu.et/pages/check_campus_placement ሊንክን በመጫንና የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና መለያ ቁጥር በማስገባት የተመደባችሁበትን ካምፓስ ማወቅ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

የምዝገባ ቦታ፦
➫ አባያ እና ጫሞ ካምፓሶች የተመደባችሁ ተማሪዎች አርባ ምንጭ ከተማ በሚገኙት አባያ እና ጫሞ ካምፓሶች
➫ ሳውላ ካምፓስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሳውላ ከተማ በሚገኘው ሳውላ ካምፓስ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 2 ኮፒ፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና 2 ኮፒ፣
➫ አራት ፓስፖርት መጠን የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ እንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡