Unique Academy
1.79K subscribers
200 photos
6 videos
25 files
214 links
☆ Welcome to Unique Maths!
" LEARN UNIQUELY AND FLUENTLY " Join us for effective learning Process....

☆ Youtube Channal : https://www.youtube.com/@Uniquemathematic

☆ CEO : Yishak Debebe & Henok Debebe
Download Telegram
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ አምቦ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ መደበኛ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ካምፓስ
➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሃጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ

በተጨማሪም ኦንላይን በ estudent.ambou.edu.et ማመልከቻና ሙሉ መረጃ ሞልታችሁ እንድትመዘገቡ ተብሏል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።
1
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ መደበኛ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 18 እና 19/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ ከ8-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

በ2018 ዓ.ም አዲስ ገቢ የሪሚዲያል ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ወደፊት ይገለጻል ተብሏል።
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ መደበኛ አዲስ ገቢ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 21 እና 22/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በቅጣት ምዝገባ የሚከናወነው ጥቅምት 24/ 2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስምንት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

የምዝገባ ቦታ፦
➫ በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የነበራችሁና ያለፋችሁ ምዝገባ ትምህርታችሁን በተከታተላችሁበት ካምፓስ
➫ አዲስ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ምዝገባ በተመደባችሁበት ካምፓስ ማለትም በተፈጥሮ ሳይንስ የስማችሁ ቅደም ተከተል  ከ A ጀምሮ እሰከ Aschalew Wondimu Wosen እንዲሁም በማኅበራዊ ሳይንስ የስማችሁ ቅደም ተከተል  ከ A ጀምሮ እስከ Amanuel Mohammed Murti ድረስ ያላችሁ ምዝገባ የምታከናውኑት ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ ሲሆን፤ የተቀራችሁት በዋናው ካምፓስ ምዝገባችሁን የምታከናውኑ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ መደበኛ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) እና ብሔራዊ መታወቂያ፣
➫ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

በ2018 ዓ.ም በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ ለምትመደቡ ተማሪዎች ወደፊት ጥሪ ይደረጋል ተብሏል።
በ2018 ዓ.ም ወሎ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች እና በ2017 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) ተምራችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች መግቢያ ቀናት ጥቅምት 20 እና 21/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በኮምቦልቻ ግቢ
➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በደሴ ግቢ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ሁለት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።
🆒3👍1
በ2018 ዓ.ም አርሲ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም በአርሲ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ ማለፊያ ውጤት ያመጠችሁ ተማሪዎች የ2018 ዓ.ም ምዝገባ ጥቅምት 19 እና 20/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ

➫ የማኅበራዊ ሳይንስ (አዲስ እና ሪሚዲያል) በቆጂ ካምፓስ
➫ የተፈጥሮ ሳይንስ (አዲስ እና ሪሚዲያል) በግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ እና በዋና ካምፓስ (ዝርዝሩን ከምስሉ ይመልከቱ)

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።
😁5
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተከታታይ (በማታ) የ2018 ዓ.ም የቅድመ-ምረቃ መርሐግብር ምደባ ያገኛችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከጥቅምት 13-15/ 2018 ዓ.ም መሆኑኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

🔔 ማንኛውም ቅሬታ ካለዎት ከዛሬ ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት አድሚሽን ቢሮ ቁጥር 202 እና 203 በመሔድ ማቅረብ ይችላሉ፡፡

portal.aau.edu.et ላይ በመግባት፣ Freshman የሚለውን ይጫኑ፣ My Section የሚለውን ይምረጡ፣ የUGA ቁጥርዎትን ያስገቡና የመታወቂያ ቁጥራችሁን እና የተመደባችሁበትን ኮሌጅ ወይም ትምህርት ቤት ያግኙ፡፡

የምዝገባ ሚስጥር ቁጥር (Password) ከተመደባችሁበት ኮሌጅ ወይም ትምህርት ቤት በሚገኘው የሬጅስትራር ቢሮ ይቀበሉ፡፡

ቅበላ ያገኙ አመልካቾች ዝርዝር እንዲሁም የኦንላይን ምዝገባው ቅደም ተከተል ሂደቱ (Steps for Registration) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ Testing Center-AAU የቴሌግራም ቻናል ላይ ያገኛሉ፡፡

በኦንላይን ያስገባችሁትን የትምህርት ማስረጃዎች እና 4 ጉርድ ፎቶግራፍ በተመደባችሁበት ኮሌጅ ወይም ትምህርት ቤት በአካል ማስገባት ይጠበቅባችኋል፡፡
😁31
በ2018 ዓ.ም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች እና በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተምራችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች እንዲሁም በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም ለመማር ያመለከታችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ቀናት ጥቅምት 20 እና 21/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የመጀመሪያ ዲግሪ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
➫ የብሔራዊ መታወቂያ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

የምዝገባ ቦታ፡-
አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ተማሪዎች
➫ የማኅበራዊ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች ማራኪ ግቢ
➫ የተፈጥሮ ሳይንስ መስክ ተማሪዎች አጼ ቴዎድሮስ ግቢ
የድኅረ-ምረቃ ተማሪዎች
በኮሌጅ / ኢንስቲቲዩት / ትምህርት ቤት ረዳት ሬጅስትራር ጽ/ቤቶች
በ2018 ዓ.ም ወለጋ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች እና በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተምራችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 20 እና 21/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፡-
በዩኒቨርሲቲው ነቀምቴ ካምፓስ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
😁32
የ2018 የትምህርትና ስልጠና ዘመን የቴክኒክና ሙያ ስልጠና የመቁረጫ ነጥብ በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ይፋ ተደርጓል፡፡

(ዝርዝሩ የመቁረጫ ነጥቡን ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ።)
በ2018 ዓ.ም ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት አዲስ ግቢ ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በሠመራ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትላችሁ ማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 19 እስከ 20/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስምንት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
➫ ብሔራዊ የፋይዳ መታወቂያ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣
➫ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

በ2018 ዓ.ም በሠመራ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ ለምትመደቡ ተማሪዎች ወደፊት ጥሪ ይደረጋል ተብሏል።
4😁2
#ብሔራዊ_መታወቂያ

በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞች ብሔራዊ መታወቂያ ማውጣት እንደሚኖርባቸው የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳሰበ።

በተያዘው የትምህርት ዓመት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞች የፈተና ምዝገባ ከመጀመሩ አስቀድመው ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ማውጣት እንዳለባቸው አገልግሎቱ አሳውቋል።

ብሔራዊ መታወቂያ (National ID) የሌለው ተማሪ ለፈተናው መመዝገብም ሆነ በማንኛውም ሁኔታ ለፈተና ለመቀመጥ እንደማይችል አገልግሎቱ ገልጿል።

በመሆኑም ተማሪዎች፣ የተማሪ ቤተሰብ፣ መምህራን እና በየደረጃው ያሉ የትምህርት አመራሮች አስፈላጊውን ግንዛቤ በመፍጠር ዝግጅት እንዲያደርጉ ተጠይቋል።
የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ይዘቶች ይፋ ሆኑ፡፡

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፤ ተማሪዎች፣ የተማሪ ቤተሰቦች፣ መምህራንና የትምህርት አመራር ለፈተና ዝግጅት በሚያደርጉበት ወቅት ፈተና የሚሸፍናቸው የይዘት አካባቢዎች ይፋ አድርጓል።

የ2018 ትምህርት ዘመን 12ኛ ከፍል ፈተና ዝግጅትና አስተዳደር የሚከተሉትን ያካትታል፡፡ 

1. የትምህርት ዓይነቶችን በተመለከተ

ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች ፦
- እንግሊዘኛ፣
- ሒሳብ፣
- እስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣
- ኬሚስትሪ፣
- ፊዝክስና ባዮሎጂ

ለማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች ፦
- እንግሊዘኛ፣
- ሒሳብ፣
- እስኮላስቲክ አፕቲትዩድ፣
- ታሪክ፣
- ጂኦግራፊና ኢኮኖሚክስ ናቸው።

2. ፈተናው ከ9ኛ እስከ 12ኛ ከፍል ደረጃዎችን እና በተማሪው መጽሐፍ ላይ ያሉትን ሁሉንም ምዕራፎች ይሸፍናል፡፡

3. ከ10ኛ – 12ኛ ክፍል ሁሉም የትምህርት ዓይነት ፈተና በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መሠረት እየተዘጋጀ ያለ ሲሆን የ9ኛ ክፍል ደግሞ የሁሉም የትምህርት ዓይነቶች ፈተናዎች ከቀድሞውና ከአዲሱ ሥርዓተ ትምህርቶች የጋራ ይዘቶችን ብቻ አካቶ እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡

4. ፈተናው ማንኛውም ተፈታኝ ተማሪ ከተማረው ሥርዓተ ትምህርትና ከተማሪው መጽሐፍ ላይ ብቻ ተመስርቶ እየተዘጋጀ ይገኛል፡፡

5. የፈተናው አስተዳደር በበይነ መረብና በወረቀት ጎን ለጎን የሚሰጥ ሲሆን አብዛኛው ተፈታኝ በበይነ መረብ እንዲፈተን እየተሠራ ያለ በመሆኑ ተፈታኞች እራሳቸውን በበይነ መረብ ለመፈተን ሊያዘጋጁ ይገባል፡፡

#EAES
4
Unique Academy
Photo
#Digital_ID

በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና የምትወስዱ ተማሪዎች የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያን እንድታወጡ ትምህርት ሚኒስቴር አሳስቧል።

ማንኛውም ተማሪ ፈተና ላይ ለመቀመጥ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ሊኖረው እንደሚገባ መወሰኑ ይታወሳል።

በመሆኑም በ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ የሆናችሁ ተማሪዎች በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ማውጫ ማዕከል በመመዝገብ መታወቂያውን ማውጣት ይኖርባችኋል ተብሏል።