Unique Academy
1.79K subscribers
200 photos
6 videos
25 files
214 links
☆ Welcome to Unique Maths!
" LEARN UNIQUELY AND FLUENTLY " Join us for effective learning Process....

☆ Youtube Channal : https://www.youtube.com/@Uniquemathematic

☆ CEO : Yishak Debebe & Henok Debebe
Download Telegram
#BahirDarUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች፣ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም የተከታተላችሁና ወደ Freshman Program ለመግባት የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው ባወጣው የመንግሥት ስኮላርሽፕ (በወጭ መጋራት) የተመዘገባችሁ እና በግላችሁ ከፍላችሁ በመደበኛው መርሐግብር በመጀመሪያ ዲግሪ ለመማር ያመለከታችሁ በሙሉ የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦

➫ ስማችሁ ከ A - Men የሆናችሁ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሰላም ግቢ ፤ ስማችሁ ከ Meq - Z የሆናችሁ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በፔዳ ግቢ

➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ግሻ አባይ (ይባብ) ግቢ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3×4 መጠን ያለው ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

በተለያየ ምክንያት 1ኛ ዓመት 1ኛ ሴሚስተር ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ የሚያበቃ ውጤት ያላችሁና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎች ለመልሶ ቅበላ ጥቅምት 20 እና 21/2018 ዓ.ም ማመልከት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በ2018 ዓ.ም በመደበኛ የቅድመ ምረቃ መርሐግብር መቐለ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ጥቅምት 15 እና 16/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ
➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በዓዲ-ሐቂ ግቢ

ከሰኞ ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም ጀምሮ በማንኛውም የሥራ ሰዓት portal.mu.edu.et ላይ በመግባት ወይም 213.55.94.34 በመጠቀም የማመልከቻ ቅፁን እንድትሞሉ ተብሏል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ11ኛ እና የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3×4 መጠን ያለው ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

በ2017 ዓ.ም በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ከላይ በተገለፀው መሰረት ሪፖርት አድርጉ ተብሏል።
4
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች፣ በ2017 ዓ.ም በሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም የተከታተላችሁና የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ (ሚዛን-አማን ከተማ)
➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቴፒ ካምፓስ (ቴፒ ከተማ)

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3×4 መጠን ያለው ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

በተለያየ ምክንያት 1ኛ ዓመት 1ኛ ሴሚስተር ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ የሚያበቃ ውጤት ያላችሁና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎች ለመልሶ ቅበላ ጥቅምት 20 እና 21/2018 ዓ.ም ማመልከት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።
በ2018 ዓ.ም አክሱም ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች እና በ2017 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን በዩኒቨርሲቲው ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስድስት 3×4 መጠን ያለው ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።
1
Jimma University
👏4🆒2
በ2018 ዓ.ም ጅማ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ መርሐግብር ፍሬሽማን ተማሪዎች እንደዲሁም በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 13 እና 14/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ
➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (ከ Section 1-26) እና በግብርናና እንስሳት ህክምና ኮሌጅ (ከ Section 27-33)

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕትና ውጤት ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት ፓስፖርት መጠን ያለው ፎቶግራፎች፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

ከጥቂት ቀናት በኋላ የአድሚሽን ቁጥርዎን በመጠቀም https://portal.ju.edu.et ላይ ገብታችሁ የተመደባችሁበትን ሴክሽን፣ ዶርም፣ ካፍቴርያ ማወቅ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡
በ2018 ዓ.ም ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የፍሬሽማን ተማሪዎች፣ በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች፣ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የተዘዋወራችሁ እና በ2017 ዓ.ም በተለያዩ ምክንያቶች በ1ኛ ዓመት 1ኛ ሴሚስተር ዊዝድሮዋል ሞልታችዉ የወጣችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 20 እና 21/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን አጠናቃችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች በነበራችሁበት ካምፓስ የምትቀጥሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕትና ውጤት ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ስርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስምንት 3x4 መጠን ያለው ፎቶግራፎች፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

የአዲስ ገቢ (ፍሬሽማን) ተማሪዎች የካምፓስ ምደባ፦
የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች
➫ የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ A-K የሆነ ዋናው ግቢ (ሆሳዕና)
➫ የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ L-Z የሆነ ዱራሜ ካምፓስ (ዱራሜ)
የማኅበራዊ ሳይንስ ሳይንስ ተማሪዎች
➫ የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ A-L የሆነ ዋናው ግቢ (ሆሳዕና)
➫ የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከ M-Z የሆነ ዱራሜ ካምፓስ (ዱራሜ)
በ2017 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ መደበኛ የቅደመ ምረቃ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ12ኛ ክፍል ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስምንት 3x4 መጠን ያለው ፎቶግራፎች፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።
5
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ መደበኛ የቅደመ ምረቃ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በወራቤ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ጥቅምት 20 እና 21/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ ከ8ኛ ክፍል ውጤት ጀምሮ ያሉ የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➫ የብሔራዊ መታወቂያ ካርድ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣
➫ አራት 3x4 መጠን ፎቶግራፎች፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

በ2018 የትምህርት ዘመን አዲስ ወደ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ በሪሚዲያል ፕሮግራም የምትመደቡ ተማሪዎች ወደፊት ጥሪ ይደረግላችኋል ተብሏል።
3
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ ቦረና ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ መደበኛ የቅደመ ምረቃ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በቦረና ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስምንት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ መደበኛ የቅደመ ምረቃ አዲስ ገቢ ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 15 እና 16/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስምንት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።
➫ ብሔራዊ የፋይዳ መታወቂያ (National ID) እና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN)
1
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ አምቦ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ መደበኛ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ካምፓስ
➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሃጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ

በተጨማሪም ኦንላይን በ estudent.ambou.edu.et ማመልከቻና ሙሉ መረጃ ሞልታችሁ እንድትመዘገቡ ተብሏል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።
1
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወደ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ መደበኛ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 18 እና 19/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ ከ8-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

በ2018 ዓ.ም አዲስ ገቢ የሪሚዲያል ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ወደፊት ይገለጻል ተብሏል።
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ መደበኛ አዲስ ገቢ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 21 እና 22/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

በቅጣት ምዝገባ የሚከናወነው ጥቅምት 24/ 2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስምንት 3x4 መጠን የሆኑ ፎቶግራፎች፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

የምዝገባ ቦታ፦
➫ በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች የነበራችሁና ያለፋችሁ ምዝገባ ትምህርታችሁን በተከታተላችሁበት ካምፓስ
➫ አዲስ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ምዝገባ በተመደባችሁበት ካምፓስ ማለትም በተፈጥሮ ሳይንስ የስማችሁ ቅደም ተከተል  ከ A ጀምሮ እሰከ Aschalew Wondimu Wosen እንዲሁም በማኅበራዊ ሳይንስ የስማችሁ ቅደም ተከተል  ከ A ጀምሮ እስከ Amanuel Mohammed Murti ድረስ ያላችሁ ምዝገባ የምታከናውኑት ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ ሲሆን፤ የተቀራችሁት በዋናው ካምፓስ ምዝገባችሁን የምታከናውኑ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡