Unique Academy
1.79K subscribers
200 photos
6 videos
25 files
214 links
☆ Welcome to Unique Maths!
" LEARN UNIQUELY AND FLUENTLY " Join us for effective learning Process....

☆ Youtube Channal : https://www.youtube.com/@Uniquemathematic

☆ CEO : Yishak Debebe & Henok Debebe
Download Telegram
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 11 እና 12/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ጀኔራል ታደሰ ብሩ ካምፓስ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ ከ8-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➫ 3x4 መጠን የሆነ ፎቶግራፍ (4)፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።
1
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ፍሬሽማን መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 13 እና 14/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ ከ8-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➫ የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶግራፍ (8)፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።
Fam bzu universitywoch eyeteru nw so make sure that u r checking the above messages ( Scroll Up and check your university)
👍4
በ2018 ዓ.ም ራያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የሪሚዲያል ትምህርት ወስዳችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 11 እና 12/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ ክፍል ውጤት ሰርቲፊኬት፣
➫ የ12ኛ ክፍል ውጤት ሰርተፊኬት፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
➫ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

በ2018 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም ራያ ዩኒቨርሲቲ የምትመደቡ ተማሪዎች በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ ይደረግላችኋል ተብሏል፡፡
በ2018 ዓ.ም ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 14 እና 15/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የየ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ8ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3X4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ፡፡

በ2018 ዓ.ም ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ መርሐግብር (Remedial Program) አዲስ ለምትመደቡ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ወደ ፊት ይገለጻል ተብሏል፡፡
በ2017 ዓ.ም በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም በትምህርት ሚኒስቴር መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ካምፓስ (ቱሉ-አውሊያ)
➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በመካነ ሰላም ካምፓስ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስምንት 3X4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡

የብሔራዊ መታወቂያ/ፋይዳ (National ID) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) መያዝ እንዳለባችሁ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።
2👍2
በ2018 ዓ.ም አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ጥቅምት 12 እና 13/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ ከ8-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ውጤት ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3X4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።
በ2018 ዓ.ም ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ጥቅምት 14 እና 15/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ውጤት ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስድስት 3X4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።
👍4😁1
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ፍሬሽማን ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በሪሚዲያል ፕሮግራም ዲላ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስምንት 3×4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።
😁2
በ2018 ዓ.ም በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታችሁን በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ እንድትከታተሉ በትምህርት ሚኒስቴር የተመደባችሁ ተማሪዎች፣ ዩኒቨርሲቲው በ2017 ዓ.ም የማለፊያ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ባወጣው ልዩ የስኮላርሺፕ ፕሮግራም ተመዝግባችሁ የተመለመላችሁና ስማችሁ በዩኒቨርሲቲው ዌብሳይት እና የፌስቡክ ገፅ ላይ የተገለፀ እንዲሁም በ2015 ዓ.ም እና በ2016 ዓ.ም የማለፊያ ነጥብ አምጥታችሁ በኦንላይን ተመዝግባችሁ የተመለመላችሁና ስማችሁ በዩኒቨርሲቲው ዌብሳይት እና የፌስቡክ ገፅ ላይ የተገለፀ ተማሪዎች በሙሉ ሪፖርት ማድረጊያ ቀናት ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ ክፍል ውጤት ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ሦስት ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

ሁሉንም የትምህርት መረጃዎች Scan በማድረግ በአንድ PDF ሶፍት ኮፒ እንዲሁም ስካን ተደርጎ በሶፍት ኮፒ የተዘጋጀ ጉርድ ፎቶግራፍ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ወልድያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ ተማሪዎች፣ በ2017 ዓ.ም በወልድያ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ መርሐግብር የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም አንደኛ ዓመት 1ኛ ሴሚስተር በተለያዩ ምክንያቶች መልሶ ቅበላ በመሙላት ያቋረጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3X4 መጠን ያለው ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች መማር ማስተማር ጥቅምት 24/2018 ዓ.ም የሚጀምር መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች በቅርቡ በሂሳብ ትምህርት ላይ የውጤት ማስተካከያ ስለተደረገ በድጋሜ በትምህርት ሚኒሰቴር ውጤት ማሳዎቂያ ፔጅ ላይ ውጤታችሁን ቼክ እንድታደርጉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3X4 መጠን ያለው ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

በ2018 ዓ.ም ለሪሚዲያል ትምህርት አዲስ የምትመደቡ ተማሪዎች ትምህርት ሚኒስቴር ምደባችሁን ይፋ እንዳደረገ ጥሪ በሌላ ማስታዎቂያ ይደረግላችኋል ተብሏል፡፡
4