Unique Academy
1.79K subscribers
200 photos
6 videos
25 files
214 links
☆ Welcome to Unique Maths!
" LEARN UNIQUELY AND FLUENTLY " Join us for effective learning Process....

☆ Youtube Channal : https://www.youtube.com/@Uniquemathematic

☆ CEO : Yishak Debebe & Henok Debebe
Download Telegram
Unique Academy
Photo
የRemedial ፕሮግራም ምደባ በቅርቡ ይፋ እንደሚደረግ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
👍73
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም በመደበኛ የዲግሪ ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ
የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች፦ በዋናው ግቢ
የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች፦ በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና ትራስ ጨርቅ፣
➫ የስፖርት ትጥቅ።
4
በ2018 ዓ.ም ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የፍሬሽማን ቅድመ ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ትምህርታችሁን በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ 6 ፓስፖርት መጠን ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና ትራስ ልብስ፣
➫ የስፖርት ትጥቅ።

የትምህርት ማስረጃዎች እና ፎቶግራፍ ስካን አድርጋችሁ በሶፍት ኮፒ ይዛችሁ መሔድ ይኖርባችኋል፡፡
6
💫 በ2018 ዓ. ም ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች ጥሪ አለማድረጉን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ጥሪ እንዳደረገ የሚገልፅ ሐሰተኛ መረጃ በማኅበራዊ ሚዲያ እየተዘዋወረ እንደሚገኝ ለማወቅ መቻሉን ዩኒቨርሲቲው ጠቁሟል።

ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች ምንም አይነት ጥሪ አለማድረጉን ያረጋገጠው ዩኒቨርሲቲው፤ ተማሪዎቹ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገቡበትን ጊዜ በቅርቡ የሚገልፅ መሆኑን ተቋሙ አሳውቋል፡፡
#MaddaWalabuUniversity

በ2018 ዓ.ም መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ አንደኛ ዓመት የመደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ስትከታተሉ ቆይታችሁ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ወስዳችሁ የማለፍያ ነጥብ ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀን ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን አሳውቋል፡፡

በተጠቀሱት ቀናት በዩኒቨርሲቲው ዋና ካምፓስ በመገኘት ምዝገባ እንድታደርጉ የተባለ ሲሆን፤ ትምህርት ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዘዟቸው የሚገቡ፦
➫ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ፣
➫ ከ8-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

በ2018 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ወደፊት ይገለጻል ተብሏል፡፡
ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ለአንደኛ እና ሁለተኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎቹ ጥሪ አድርጓል፡፡

በዚህም በ2017 ዓ.ም በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርት ስትከታተሉ ቆይታችሁ ወደ አንደኛ ዓመት ለመግባት ማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ፣ በትምህርት ሚኒስቴር ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ አንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በደባርቅ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዓመት ተማሪዎች የ2018 ዓ.ም የመመዝገቢያ ቀናት ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በቅጣት ምዝገባ እና ትምህርት የሚጀምረው ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ መጠኑ 3×4 ፎቶግራፍ (4)፣
➫ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፣
➫ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ፣ ብርድ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የአንደኛ ዓመት እና የሪሚዲያል መደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ትምህርት ጥቅምት 19/2018 ዓ.ም እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ 3x4 ፎቶግራፍ (8)፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 11 እና 12/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ጀኔራል ታደሰ ብሩ ካምፓስ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ ከ8-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➫ 3x4 መጠን የሆነ ፎቶግራፍ (4)፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።
1
በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ፍሬሽማን መደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 13 እና 14/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ ከ8-12ኛ ክፍል የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒው፣
➫ የቅርብ ጊዜ ጉርድ ፎቶግራፍ (8)፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።
Fam bzu universitywoch eyeteru nw so make sure that u r checking the above messages ( Scroll Up and check your university)
👍4
በ2018 ዓ.ም ራያ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የሪሚዲያል ትምህርት ወስዳችሁ ያለፋችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ቀናት ጥቅምት 11 እና 12/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ ክፍል ውጤት ሰርቲፊኬት፣
➫ የ12ኛ ክፍል ውጤት ሰርተፊኬት፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣
➫ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

በ2018 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም ራያ ዩኒቨርሲቲ የምትመደቡ ተማሪዎች በሌላ ማስታወቂያ ጥሪ ይደረግላችኋል ተብሏል፡፡
በ2018 ዓ.ም ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የአንደኛ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎች እንዲሁም በ2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው የሪሚዲያል ትምህርት ተከታትላችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 14 እና 15/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የየ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ8ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3X4 የሆነ ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ፡፡

በ2018 ዓ.ም ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ መርሐግብር (Remedial Program) አዲስ ለምትመደቡ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን ወደ ፊት ይገለጻል ተብሏል፡፡
በ2017 ዓ.ም በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ ፕሮግራም ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ እንዲሁም በትምህርት ሚኒስቴር መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የአንደኛ ዓመት ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ጥቅምት 17 እና 18/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ካምፓስ (ቱሉ-አውሊያ)
➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በመካነ ሰላም ካምፓስ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ስምንት 3X4 የሆነ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡

የብሔራዊ መታወቂያ/ፋይዳ (National ID) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) መያዝ እንዳለባችሁ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።
2👍2