ኢትዮ ጤና መረጃ - Ethio health info
1.44K subscribers
405 photos
5 videos
62 files
47 links
In this channel updated medical guidelines and information regarding Ethiopian health system will be addressed.
You can use @Mahi122419 for your suggestions and comments. Thank you
Download Telegram
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለዶ/ር ዳምጤ ሽመልስ አወቀ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጠ

ፕሮፌሰር ዳምጤ ሽመልስ አወቀ የሕክምና ዲግሪያቸውን (MD) እና የስፔሻሊቲ ዲግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ የስፔሻሊቲ ዲግሪያቸውን በህፃናት ህክምና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እንዲሁም የሰብ-ስፔሻሊቲ ዲግሪያቸውን እስራኤል ከሚገኘው ከBen Gurion University በPediatric Nephrology አግኝተዋል።

ፕሮፌሰር ዳምጤ ሽመልስ በግላቸውና ከሙያ አጋሮቻቸው ጋር ከ9 በላይ በምርምር የተደገፉ ጥናታዊ ፅሁፎችን በታወቁ ሀገራዊና አለምዓቀፋዊ መፅሄቶች ላይ ለህትመት በማብቃት የፕሮፌሰርነት ማዕረግ ለማግኘት ከሚጠበቅባቸው 35 የህትመት ነጥብ 37.10 አስመዝግበዋል። በተጨማሪም የተለያዩ ኃላፊነቶችን በመውሰድ ለዩኒቨርስቲው አገልግሎት የሰጡ ሲሆን በርካታ የማህበረሰብ አገልግሎቶችና የሙያ ነክ አስተዋጽኦ አበርክተዋል።

በPediatric and Child Health የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው ፕሮፌሰር ዳምጤ ሽመልስ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ፣ በጥቁር አንበሳ ሕክምና ኮሌጅ በሚገኘው የህክምና ትምህርት ቤት ውስጥ በህፃናት ህክምና (Pediatrics) ትምህርት ክፍል ባልደረባ ሆነው በማገልገል ላይ ይገኛሉ።

Source: AAU

@HakimEthio
የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ
___
1. የብቃት ምዘና ፈተናው ነሀሴ 10-14/2013 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን የፈተና ፕሮግራሙም እንደሚከተለው ይሆናል፡-
• ነርሲንግ --------------------- 10/12/2013 ዓ.ም
• ጤና መኮንን --------------- 11/12/2013 ዓ.ም
• ህክምና እና ፋርማሲ ------ 12/12/2013 ዓ.ም
• ሜዲካል ላብራቶሪ ሳይንስ እና አንስቴዥያ --------13/12/
2013 ዓ.ም
• ሚድዋይፈሪ ፣ ዴንታል ሜዲስን እና ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ----------- 14/12/2013 ዓ.ም
2. ከተለያዩ እውቅና ካላቸው የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተመረቃችሁ የጤና ባለሙያዎች በተደጋጋሚ በተገለጸው መሰረት ፈተናውን ከመውሰዳችሁ በፊት የትምህርት ማስረጃዎቻችሁን ህጋዊነትና ትክክለኛነት በከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኤጀንሲ (HERQA) በኩል ማረጋገጥ (Authenticate ማድረግ) የሚጠበቅባችሁ ሲሆን፤ በፈተናው ዕለትም እነዚህን የትምህርት ማስረጃዎች ይዞ መገኘት የሚኖርባችሁ መሆኑን እየገለጽን፤ Authenticate የተደረገ የትምህርት ማስረጃ ይዞ ያልተገኘ ተመዛኝ ለፈተናው መቀመጥ የማይችል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን።
3. በቀን 9/12/2013 ከቀኑ በ 8፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ መከታተል እንዲሁም የመፈተኛ ክፍላችሁን መለየት ይኖርባችኋል፡፡
2. በፈተናው ዕለት በፈተና ጣቢያው ጠዋት 1፡00 ሰዓት ላይ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡
3. በፈተናው ዕለት ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ (የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ ወይም ሌላ በግልጽ የሚታይ ህጋዊ መታወቂያ)፣ የፈተና መስሪያ ግብዓቶች (እርሳስ፣ ላጲስ፣ መቅረጫ) ይዛችሁ መገኘት ይኖርባችኋል፡፡
4. በፈተና ወቅት ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ ፣ ስማርት ሰዓት፣ኤሌክትሮኒክስ መነጽር (የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች፣ምንም አይነት ማጣቀሻዎች እንዲሁም ባዶ ወረቀቶች፣ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡
5. አካል ጉዳተኞች፣ ነፍሰጡር እናቶች እንዲሁም ጨቅላ ህጻናት የያዙ እናቶች ቀድመው ለፈተና ጣቢያ ኃላፊ ማሳወቅ አለባቸው፡፡
6. በፈተናው ወቅት አቴንዳንስ ላይ በአግባቡ መፈረም ይኖርባችኋል፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0118275936 መደወል

#FMOH
@healthinfom
በቅርብ ቀን: በ17 አስገራሚ የልብ ቀዶ ጥገና ታሪኮችና በ236ገፇች የተዋቀረውን መፅሀፌን እንድታነቡልኝ ጋብዣቹሀለሁ።

ቆይ ቆይ አንድ ጊዜ ላስቸግራቹህ የመፆሃፋ የሗላ ሽፋን ላይ ያሰፈርኩትን እስኪ አንድ ጊዜ አንብቧት!

ዶ/ር ፈቀደ አግዋር ፤ የልብ ቀዶ ህክምና ሀኪም

@HakimEthio
#ERMP_Announcement

Registration for the 2021 ERMP will be open for the duration of October 1-21,
2021. Please read the ERMP 2021 Implementation Guideline thoroughly and the instructions before you start filling the application form.

The registration website will be open on October 1.

@http://Www.moh.gov.et
@healthinfom
Call for Undergraduate Medicine Application (2021/2022)
(From IESO to Medicine)
I. Application criteria
1. Bachelor’s degree in Health officer only
2. MSc in Integrated Emergency Surgery and Obstetrics care
3. Cumulative GPA 2.75 for females & applicants from emerging regions and 3.0 for male applicants in BSC degree
4. Currently on clinical service after graduation
5. Age not more than 35 years.
6. Good health (produce medical certificate)
7. Application fee (200 birr), please use Yekatit 12 Hospital Medical College CBE 1000010795218
II. Application documents
1. BSC degree student copy and master degree certificate
2. Medical certificate
3. Evidence of current clinical service( document )
4. Application fee receipt
III. Application date
1. October 4-17 /2021
2. Application only online via college Student information system( SIS portal ) http://www.y12hmc.edu.et
3. You can use application guide attached (https://drive.google.com/.../147QKP6m5.../view... )
4.Entrance exam date will be posted soon
Note : Medical status of Admitted candidates will recheck by the College
@healthinfom
List of 1233 matched candidates.pdf
710.2 KB
የ2014ዓ.ም የብሔራዊ ስፔሻሊቲ ፈተና ውጤት
@healthinfom
አማራ ክልል ጤና ቢሮ ክፍት የስራ መደብ ላይ ተፈላጊውን ችሎታ የሚያሟሉ 631 ሀኪሞችን በ0 አመት የስራ ልምድ ይፈልጋል።
@healthinfom
ሀኪማችንን እናሳክመው
[አማርኛ | English]

ዶ/ር አቤል አለሙ እባላለው። በ2011 ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በህክምና ሙያ ትምህርት የተመረቅሁ ስሆን ለሁለት ዓመት ተኩል በጠቅላላ ሀኪምነት ወገኔን አገልግያለው። በአገልግሎት ጊዜዬ ትዳር መስርቼ የቆንጅዬ ልጅ አባት ሆኜ ደስታዬን እያጣጣምኩ ነበር። አሁን በቀዶ ህክምና ትምህርት ስፔሻላይዜሽን ትምህርት ዕድል አግኝቼ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ እየተማርኩ እገኛለው።

የመጀመሪያ አመት የቀዶ ህክምና ትምህርቴን እየተማርኩ ሳለ ድንገት ደም ከአፌ በተደጋጋሚ ይፈሰ ጀመር። ይህም አሳስቦኝ ስመረመር የደም ካንሰር እንደያዘኝ ውጤቶቼ አስረዱ፣ የደም ካንሰር አይነቱ AML-M3 ሲሆን ይህም የደም ካንሰር ዓይነት ሕክምናው ረዘም ላለ ጊዜ የሚወስድ ነው። ሆኖም ግን ቶሎ ሕክምናውን ከጀመርኩ ሙሉ በሙሉ የመዳን ዕድል አለው።

ሕክምናው ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቅ ስለሆነ እና እኔም በመንግስ ሰራተኛ የሀኪም ደሞዝ የምችለው አይደለም።

እባካችሁ ለአንዲት ልጄ ትንሽዬ እንኳ እኖርላት ዘንድ የቻላችሁትን ትረዱኝ ዘንድ በፈጣሪ ስም እጠይቃለው።

የበኩሎን እገዛ ለማድረግ የሚከተሉትን አካውንት ቁጥሮች ይጠቀሙ፡

ንግድ ባንክ: 1000310318705 አቤል አለሙ
ዳሽን ባንክ: 5121147794021 ዶር አቤል አለሙ
@healthinfom
I am Dr. Abel Alemu. I graduated from Bahir Dar University school of medicine in 2011 E.C. After graduation I started working at a primary hospital. Meanwhile Ivgot married to the love of my life and become a father of a beautiful little girl.

After serving my community for 2 and a half years I joined hawassa university for surgical specialty training. When the final exam of first year residency training was approaching I started to experience bleeding from my gums.

Worried about the symptoms I got tested and the blood work revealed Acute Myeloid Leukaemia M3 (Blood Cancer).

The good news about this type of cancer is, if I start treatment early, it can be cured. However, the treatment will take long duration and it is very expensive which I can't cover as a poorly paid Ethiopian Doctor.

I want to live a little longer for my daughter. Your contribution can save my life. May God bless you all

CBE: 1000310318705 Abel Alemu
Dashen: 5121147794021 Dr Abel Alemu

[Medical records will be provided upon request]
@healthinfom
የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ ሆነ።

በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና በተለያዩ ሀገራዊ ምክንያቶች ወደ 2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ተሸጋግሮ በሁለት ዙር መሰጠቱ ይታወቃል።

የመጀመሪያው ዙር የሲቪክስ ፈተና በሁሉም ትምህርት ቤቶች በሚባል ደረጃ የውጤት መመሳሰልና ግሽበት ታይቶበታል። ስለሆነም የሲቪክስ የፈተና ውጤት ለዩኒቨርስቲ መግቢያ መወዳደሪያነት #እንዳያገለግል ተወስኗል።

በሌሎቹ የትምህርት ዓይነቶች የተገኘው የውጤት ትንተና ሲታይ ምንም ዓይነት ችግር የሌለበት በመሆኑ እንዲመዘገብ ተደርጓል።

ለከፍተኛ ትምህርት ገብተው ለመማር ብቁ የሚሆኑ ሁሉም ተማሪዎች ለመግቢያነት የሚያገለግሉ የትምህርት ዓይነቶችን አጠቃላይ አማካይ ነጥብ 50% እና በላይ ያመጡ ተማሪዎች ይሆናሉ።

ለምሳሌ በሰባት የትምህርት ዓይነት ተፈትነው ከ600 ለሚያዝላቸው ተማሪዎች አማካይ ውጤት 300 እና በላይ ማምጣት ይጠበቅባቸዋል።

ይህ በዲህ እንዳለ በመንግስት ዩኒቨርስቲዎች ገብተው ለሚማሩ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲዎችን የመቀበል አቅም በማገናዘብ ዝርዝር የመግቢያ ነጥብ ወደፊት ይገለፃል።

ተማሪዎች የሚከተሉትን አማራጮች በመጠቀም ውጤታቸውን ማወቅ ይችላሉ።

1) በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዌብሳይት፡- result.neaea.gov.et

2) በትምህርት ሚኒስቴር ዌብሳይት፡- result.ethernet.edu.et

3) በቴሌግራም ቦት (Telegram Bot):- @moestudentbot

4) በ9444 SMS)፡- በመልክት ማስተላለፊያ መጻፊያ ላይ የመለያ ቁጥራቸውን በማስገባት ወደ 9444 በመላክ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ።

(የአገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ)

@healthinfom
BDU call for new residents!
@healthinfom
የተጠባባቂ ጥሪ 👇👇👇
GP Selected.docx
277.1 KB
Addis Ababa City Administration Health Bureau result for GPs.
@healthinfom
Pharmacist Selected.docx
278.5 KB
Addis Ababa City Administration Health Bureau result for pharmacists
@healthinfom
Laboratory Tecnologest Selected.docx
275.2 KB
Addis Ababa City Administration Health Bureau result for Lab techs.
@healthinfom
HEW Selected.docx
276.9 KB
Addis Ababa City Administration Health Bureau result for HEWs
@healthinfom
Drugis Selected.docx
267.6 KB
Addis Ababa City Administration Health Bureau result for druggists.
@healthinfom