ሩቢ ስፖርት
244 subscribers
1.96K photos
2 videos
3 links
Download Telegram
ከሳዑዲ ብጠየቅ አልቀበለውም!

በተንታኝነት የሚሰራው ጂሚ ካራገር የሳዑዲ ሊግ ሊጋቸውን እንድሰራ አሁን ከሚከፈለኝ 4 እጥፍ ቢያቀርቡልኝም አልቀበለውም(ውድቅ አደርገዋለሁ)።
ይግባኙ ውድቅ ሆኗል!

ሮማ ለአሰልጣኝ ጆዜ ሞሪኒሆ ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ ተደርጓል።
አሰልጣኙ በሮማ የመጀመሪያ 4 ጨዋታዎች ላይ በአሠልጣኝ ቦታ ላይ ሆነው ቡድኑን አይመሩም።

ጆዜ ባለፈው የውድድር ዘመን በዩሮፓ ሊግ ፍፃሜ ዳኛውን መናገራቸው ነው ለቅጣት የዳረጋቸው።
2ተኛ ሽንፈት!

ሴካፋ ከ18 አመት በታች የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በታንዛኒያ 2 ለ 0 ተሸንፏል።
በመድረኩ ከ2 ጨዋታ 2ተኛ ሽንፈት ሆኗል።
የማያሚ ከፍተኛ አስቆጣሪ!

ሜሲ የኢንተር ማያሚ የምንጊዜውም ከፍተኛ አስቆጣሪ ለመሆን 27 ጎሎች ብቻ ይቀሩታል።
የሜሲ ቤተሰብ!
አጠገባቸው የተገኙት ስሜታቸው!
ቤንዜማ እና ካንቴ ዛሬ በአል ኢትሃድ መለያ የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ሶው ወደ ስፔን!

የፍራንክፉርቱ አማካይ ጅብሪል ሶው ወደ ሴቪያ ለማቅናት በድርድር ላይ ነው።
የ26 አመቱ ተጫዋች ከጀርመኑ ክለብ ካምፕ መውጣቱም ተነግሯል።
የጣሊያኑ ላትሲዮም የተጫዋቹ ፈላጊ ነው።
ብራዚላዊው ከፓሪስ ሊለቅ ይችላል!

የPSG አምበል ማርኪኒዮስ ሳይጠበቅ ከፓሪስ ሊወጣ እንደሚችል እየተነገረ ነው።
የ29ኝ አመቱ ተከላካይ የቡድኑ አመራሮች እየሄዱበት ባለው መንገድ ደስተኛ እንዳልሆነ ነው የተነሳው።
ደጋፊዎች አልተቀበሉትም!

ሉካ ሄርናንዴዝ ወደ PSG ማምራቱን ተከትሎ በአቀባበሉ ወቅት ላይ ተቃውሞ ገጥሞታል።
የፓሪስ ፅንፈኛ ደጋፊዎች ባልመጣህብን ብለውታል!

ምክንያታቸው ደው ተጫዋቹ የማርሴይ ሰው መሆኑ ነው።
ማርሴ ከፓሪስ የፈረንሳይ ትልቁ ደርቢ ነው(ለክላሲክ)::
ካልቪን ስቴንጅስ ወደ ሃገሩ ተመልሷል!

ሆላንዳዊው የ24 አመት ተጫዋች ካልተሳካ የኒስ ጉዞ በኋላ ነው ወደ ፋይኖርድ ያቀናው።
ኒስ ተጫዋቹን ከ2 አመት በፊት ከኤዜ አልካማር ቢያስፈርመውም የታሰበውን ያክል መጓዝ አልቻለም።
የኤርዲቪዜው ሻምፒዮን ለስቴንጅስ 8 ሚሊየን ዩሮ አሁን እና እየታየ የሚጨመር 2 ሚሊየን ዩሮ ይከፍላል።
ሎቭሮ ማየር ወደ ጀርመን!

የስታደሬኔው አማካይ ሎቭሮ ማየር ወደ ቮልስቡርግ ለማቅናት ተስማምቷል።
ቮልስቡርግ ለተጫዋቹ 20 ሚሊየን ዩሮ ቢያቀርብም የብሩኖ ጄኔሲዮ ቡድን በትንሹ 25 ሚሊየን ዩሮ ይፈልጋል።
ኤላ ዋሂ ቼልሲን ያስባል!

አጥቂው የቼልሲ ዝውውሩ በቶሎ እንዲጠናቀቅ ይፈልጋል።
ባሳለፍነው የውድድር ዘመን 19 የሊግ ጎል ያስቆጠረው ዋሂ ከሞንፔይሌ ለቆ ለንደን መክተምን ጓግቷል።
ቡድኑ ቼልሲ ያቀረበውን 27 ሚሊየን ዩሮ ውድቅ ማድረጉ ይታወሳል።
አል ሂላል ኦስሜሄንን ፈልጓል!

የሳዑዲው ቡድን አልሂላል ቪክቶር ኦስሜሄንን ለማስፈረም አስቧል።
ኪሊያን ኤምባፔን ማግኘት ያልቻለው ቡድኑ ናይጄሪያዊውን አጥቂ ለማስፈረም እየሰራ ነው።
ዳንሶ ወደ ጣሊያን!

ናፖሊ ኬቨን ዳንሶን ለማስፈረም ጥያቄ አቅርቧል።
ቡድኑ የ24 አመቱን ተከላካይ የግሉ ለማድረግ 30 ሚሊየን ዩሮ ለሎንስ ለመክፈል ተዘጋጅቷል።
ናፖሊ የመሃል ተከላካዩን የኪም ሚን ጄ ምትክ ለማድረግ ነው ዳንሶን ያለመው።
👍1
የኦስሜሄን ምክር ለቺኩዌዜ ሚላን መግባት ዋነኛው ምክንያት እንደሆነ ተጫዋቹ ተናግሯል።
ጋርናቾ በኢንስታግራም ገፁ ያጋራው ምስል!