ሩቢ ስፖርት
244 subscribers
1.96K photos
2 videos
3 links
Download Telegram
ፓቫ ወደ አርሰናል!

ቲምበርን በጉዳት ለወራት የሚያጣው አርሰናል ቤንጃሚ ፓቫን ፈልጓል።
በርግጥ ቡድኑ ከእርሱ በፊት የላይብዚሹን ሲማኮ የሲቲውን ካንሴዮ እንዲሁም ከኩንዴ እና ኢቫን ፍሬሴንዳ ጋር ስሙ ሲነሳ ቆይቷል።

በባየርን መቆየት የማይፈልገው ፓቫም ከዩናይትድ እና ከኢንተር ጋር ስሙ ሲያያዝ ቆይቶ ነው በአርሰናል ራዳር ውስጥ የተገኘው።
ጋላታሳራይ ሃኪም ዚያሽን አስፈርሟል!

ቡድኑ ተጫዋቹን በውሰት ወደ ቱርክ የወሰደው ሲሆን በቋሚነት የማስፈረም አንቀፅም ተካቶበታል።
ቬራቲ ወደ ሳዑዲ!

ማርኮ ቬራቲ በግል ጥቅማ ጥቅም ጉዳይ ከአል ሂላል ጋር ተስማምቷል።
አሁን የሚጠበቀው የፓሪስ ስምምነት ነው።
ኮኔ ወደ ፓሪስ!

Psg ማኑ ኮኔን መውሰድ ይፈልጋል።
ወጣቱን አማካይ ከሞንቼግላድባህ ለማስኮብለል እንቅስቃሴ ጀምሯል።
ተጫዋቹ ማርኮ ቬራቲን እንዲተካ ይፈለጋል።
ደስት ወደ ፈረንሳይ!

ሰርጊኒዮ ደስት የኒስ ተጫዋች ለመሆን ተቃርቧል።ኒስ ተጫዋቹን በውሰት የሚወስደው ሲሆን የደሞዙን ምን ያህል % እንደሚከፍል ከባርሴሎና ጋር እየተደራደረ ነው።
በኔይማር የሽኝት ፕሮግራም የኪሊያን ኤምባፔ አለመጠራት አነጋጋሪ ሆኗል።
ተጫዋቹ ወደ ሂላል ለመሄድ የመጨረሻው የስንብት ምሽት ላይ የኤምባፔ አለመጠራት በመካከላቸው ያለውን ከፍ ያለ መቃቃር የሚያሳይ ነው ተብሏል።
ሙዋኚ ውድቅ አድርጓል!

ራንደል ኮሎ ሙዋኚ ከቶትንሃም የቀረበለትን የእናስፈርምህ ጥያቄ ውድቅ አድርጓል።
ተጫዋቹ ወደ ፓሪስ ሊያቀና ንግግር ላይ ነው።
ኔይማር ሂላልን አያገለግልም!

ትላንት ምሽት በልዩ ሁኔታ ሳዑዲ አል ሂላል የደረሰው ኔይማር በጉዳት ምክንያት እስከ መስከረም አጋማሽ ቡድኑን አያገለግልም።
ማሊኖቪስኪ ወደ ጣሊያን ተመልሷል!

ሩስለን ማሊኖቪስኪ በውሰት የጄኑዋ ተጫዋች ሆኗል።በማርሴይ የተሳካ ቆይታን ያላደረገው ተጫዋቹ ዳግም ጣሊያን ደርሷል።
ታይለር አዳምስ ወደ በርንማውዝ የሚያደርገው ዝውውር ተጠናቋል!
2ተኛው ተጫዋች ሆኗል!

ጁድ ቤሊንግሃም በመጣበት አመት በተከታታይ 2 ጨዋታዎች ጎል በማስቆጠር 2009 ሮናልዶ የሰራውን ገድል ደግሟል!
በለንደን ሊቆይ ይችላል!

ፍሎሪየን ባሉገን ቆይታው ባይወሰንም በለንደን የመክረም እድሉ ሰፍቷል።
አርሰናል ለዝውውሩ ያቀረበውን ዋጋ ቼልሲ እና ቶትንሃም ለመክፈል ተዘጋጅተዋል።
ልዑል ዊሊያም ይቅርታ ጠይቀዋል!

የእንግሊዝ ልዑል የሆኑት ልዑል ዊሊያም ዛሬ በሚደረገው የሴቶች የአለም ዋንጫ ፍፃሜ ሃገራቸውን እንግሊዝን ሊደግፉ ወደ አውስትራሊያ መሄድ ባለመቻላቸው ነው ይቅርታቸውን እና የመልካም ዕድል ምኞታቸውን ለቡድኑ የላኩት።

የእንግሊዝ እና የስፔን የፍፃሜ ጨዋታ 7 ሰዓት ሲል ይጀምራል።
👍2
ማንቼስተር ዩናይትድ በማርኮ ቬራቲ ዝውውር እጁን አስገብቷል!

አማካዩን ለማስፈረም የሳዑዲው አል ሂላል ቢቀርብም ዩናይትድ አዲሱ ፈላጊ ሆኖ ብቅ ብሏል።የጀርመኑ ባየርንም ፍላጎት አለው።
ወንድማማቾቹ በተመሳሳይ ቀን 2 2 ጎል አስቆጥረዋል።
የቲምበር ቀለበት AFC ትላለች!
የተጫዋቹን ከቡድኑ ጋር በብዙ መዛመድ ይጠቁማል።
ስፔን ሻምፒዮን ሆናለች!

የስፔን ብሔራዊ ቡድን የሴቶች የአለም ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል።ቡድኑ እንግሊዝን 1 ለ 0 ሲረታ ኦልጋ ካርሞና ብቸኛውን ጎል አስቆጥራለች።

ስፔን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ዋንጫውን ስታሳካ።የእንግሊዟ አሰልጣኝ ሳሪና ቬክማን ለ2ኛ ተከታታይ ጊዜ በመድረኩ በፍፃሜው ተረተዋል።
1
የስፔን ቡድን ከጀርመን ብሔራዊ ቡድን በመቀጠል በወንዶቹም በሴቶቹም የአለም ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል!