ሩቢ ስፖርት
243 subscribers
1.96K photos
2 videos
3 links
Download Telegram
100 የተለያዩ ቡድኖች ላይ አስቆጥሯል!

ሊዮ ሜሲ ትላንት ለኢንተር ማያሚ አትላንታ ዩናይትድ ላይ ያስቆጠረው ጎል በክለብ ጨዋታዎች 100 ኛ ክለቡ ላይ ያስቆጠረው ኳስ ነው።
"ለቦታዬ እፋለማለሁ"
ዳዮ ኦፓሜካኖ

ቶማስ ቱከል በባየርን ማቲያስ ዴሊት እና ኪም ሚን ጄን ቀዳሚ የተከላካይ አጣማሪ ሊያደርጉ እንደሚችሉ ይገመታል።
በዚህም ቦታውን የመነጠቅ ስጋት ያለበት ፈረንሳያዊው ተከላካይ ለቦታዬ እፋለማለሁ ብሏል።
"እስከ እለተ ሞቴ የቀዮቹ ነኝ"

ከ12 አመታት የአንፊልድ ቆይታ በኋላ ወደ ሳዑዲ ያመራው ጆርዳን ሄንደርሰን "ያለፉትን 12 አመታት በቃል መግለፅ ከባድ ነው ቻው ብሎ መሰናበትም እንደዛው፣እስከ ዕለተ ሞቴ እኔ የሊቨርፑል ነኝ"ሲል ስንብቱን ገልጧል።
ቬራቲ ወደ አል ሂላል!

የሳዑዲው ቡድን እንቅስቃሴ ከቀን ወደ ቀን እያስፈራ መጥቷል።
ትንሿን አውሮፓ በአል ሂላል እየገነቡም ይመስላል።
አሁን ደግሞ ጣሊያናዊውን ማርኮ ቬራቲ ከPSG ለማስኮብለል ድርድር ላይ ናቸው።
ሁለቱ ቡድኖችም በዝውውሩ እንደተስማሙ ነው እየተነገረ ያለው።
ማርኮ ቬራቲ በቀጣዩቹ ቀናት የ3 አመት ኮንትራቱን እንደሚቀበል ይጠበቃል።
ዛሬ በፌዴሬሽን የፀደቁ ዝውውሮች!
ማልኮም በ60 ሚሊየን ዩሮ የአልሂላል ተጫዋች ሆኗል!
109,318 ሠው የተመለከተው ጨዋታ!

2014 በዚሁ ወቅት ማን ዩናይትድ ከ ሪያል ማድሪድ በሚችገን ሲጫወቱ በስታድየሙ 109,318 ሠው ታድሟል።
ከ9ኝ አመት በኋላ ዛሬ ለሊት ሁለቱ ቡድኖች ዳግም በአሜሪካ ይጫወታሉ።
ኤምባፔ ውድቅ አድርጎታል!

ኪሊያን ኤምባፔ የአለማችን ውዱን ዝውውር እንደማይቀበለው ተናግሯል።
የሳዑዲው አልሂላል ተጫዋቹን ለማነጋገር ተወካዮችን ቢልክበትም ጥያቄውን እንደማይቀበል አሳውቋል።
👍1
ከማድሪድ ጋር ይጫወታሉ!

ቫራን እና ካዝሚሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ከማድሪድ ተቃራኒ ሆነው ዛሬ ለሊት ይጫወታሉ።
👏1
ሃላንድ!
👍1
የወዳጅነቱ በማድሪድ 2 ለ 0 አሸናፊነት ተጠናቋል!

የማድሪድ አዲስ ፈራሚዎች ቤሊንግሃም እና ሆሴሉ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
በዩናይትድ በኩል ኦናና የመጀመሪያውን ጨዋታ አድርጓል።
ኮቤ ማይኖ በጉዳት ከሜዳ ወጥቷል።
ተጨማሪ ምስሎች!