ሩቢ ስፖርት
244 subscribers
1.96K photos
2 videos
3 links
Download Telegram
ሩቢ ስፖርት
Photo
ኔይማር አል ሂላልን ተቀላቅሏል!
በ2 አመት 300 ሚሊየን ዶላር ያገኛል።
የኔይማር ምስሎች!
ብራይተን!
ኔይማር በሂላል!

ለሁለት አመት 300 ሚሊየን ዩሮ ደሞዝ!
400 ሚሊየን ዩሮ ኮሜርሺያሊ!
ቡድኑ ሲያሸንፍ 80 ሺ ዩሮ!
በIG አካውንቱ ስለ ሊጉ መልካም ገፅታ እና ስለ ሂላል ሲለጥፍ 500 ሺ ዩሮ ያገኛል።

በተጨማሪ የግል ጄት
እሱን የሚንከባከቡ ሰራተኞች(ሾፌር እና ምግብ አብሳይን ጨምሮ)
ቤተሰቦቹ እና ጓደኞቹን ይዞ የሚያርፍበት 1000 ስኩዌር ካሬ ቦታ ከነመኖሪያው ተሰጥቶታል።
ሳላህ ወደ ሳዑዲ!

ሞ ሳላህን ለመውሰድ አል ኢትሃድ እየሰራ ነው።
ኢንተር ማያሚ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ለፍፃሜ ደርሷል!

የሊዮ ሜሲ ምትሃት በአሜሪካ ቀጥሏል።
ለሊት ከፊላደልፊያ ጋር በተደረገ የሊግ ካፕ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ኢንተር ማያሚ 4 ለ 1 አሸንፏል።

ቡድኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዋንጫ ሲደርስ ሊዮ ሜሲ ከ6 ጨዋታ 6ኛ ድሉን አስመዝግቧል።
10 ጎሎች ላይ በቀጥታ ተሳትፏል።
ፊላደልፊያ ከትላንት በፊት በሜዳው 265 ጨዋታዎችን ሲከውን በ1ዱም አጋጣሚ እስከ እረፍት 3 ለ 0 ተመርቶ አያውቅም!

ሜሲ ትላንት ምሽት 2 ሬኮርዶችን ሰብሯል!

1, የመጀመሪያው የማያሚ ተጫዋች በ6 ተከታታይ ጨዋታ ጎል ያገባ
2, በአሜሪካ ታሪክ አዲስ ተጫዋች 6 ተከታታይ ጨዋታ ጎል ሲያስቆጥር ቀዳሚ ሆኗል

ተጫዋቹ ከ32.1 ሜትር ላይ ያስቆጠራት የለሊቷ ጎል በሜሲ ታሪክ ሩቋ ሆና ተመዝግባለች።ከዚህ ቀደም በ2018 ጥር 14 ቀን ሪያል ሶሴዳድ ላይ ከ31.7 ሜትር ያስቆጠራት ኳስ ነበረች ሩቋ።

ሊዮ ለ17ኛ ተከታታይ አመት 20 እና ከዛ በላይ ያስቆጠረበትም አጋጣሚ ሆኗል።
የፍፃሜ ፍልሚያው ለሊዮ 42ኛው ሲሆን ከ41ዱ 29ኙን ድል አድርጓል።
ቪላ አኩኛህን ይፈልጋል!

አስቶን ቪላ ማርኮስ አኩኛህን ለማስፈረም አስቧል።የግራ ተከላካዩ ሉካስ ዲኜ የሚለቅበት ቡድኑ አርጀንቲናዊው ላይ አነጣጥሯል።
ላቪያ የጤና ምርመራውን ያደርጋል!

ሮሚዮ ላቪያ በ58 ሚሊየን ፓወንድ ቼልሲን እንደሚቀላቀል መረጋገጡ ይታወሳል።
በቅርቡ የጤና ምርመራውን ያደርጋል።
ቦኖ ወደ ሳዑዲ!

የኔይማርን ዝውውር ያጠናቀቀው አል ሂላል ያሲን ቦኖን ለማስፈረም ተስማምቷል።
ሂላል ለሴቪያ 19 ሚሊየን ዩሮ አሁን በተጨማሪ 2 ሚሊየን ዩሮ በቀጣይ ይከፍላል።
ዶኩ ወደ እንግሊዝ!

ማንቼስተር ሲቲ ጄሬሚ ዶኩን ለማስፈረም እየሰራ ነው።
ቡድኑ ለወጣቱ የመስመር አጥቂ እስከ 35 ሚሊየን ፓወንድ ሊያወጣ ይችላል።
ኤላ ዋሂ ወደ ሌላኛው ለንደን!

አጥቂው ከቼልሲ ይልቅ ዌስትሃምን እንደመረጠ እየተነገረ ነው።
በቂ የመጫወቻ ቦታን የሚፈልገው ኤላ ዋሂ ዌስትሃምን መርጧል።
የራያ ንቅሳት እና ግጥምጥሞሹ!

ዴቪድ ራያ ማጅራቱ ላይ የቀን ንቅሳት አለበት።ቀኑ ደግሞ በብሬንትፎርድ ለመጀመሪያ ጊዜ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታን የከወነበት ነው።
13-08-201
በወቅቱ ላደገው ቡድን የመክፈቻ ጨዋታው ደግሞ ከራያ የዛሬ ባለቤት ቡድን አርሰናል ጋር የተካሄደ ነው።
አይሜሪክ ላፖርት ወደ ሳዑዲ!

አልናስር ላፖርትን ለማስፈረም ከተጫዋቹ ጋር ንግግር ጀምሯል።
ተከላካዩ በማን ሲቲ ቤት ቋሚ የመሆን እድሉ ጠባብ ነው።
የ2023 የሊጉ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች እጩዎች!
ኦሌክሳንደር ዚኒቼንኮ ወደ ልምምድ ተመልሷል!
የ2015 ኮከቦች ነሐሴ 13 ይታወቃሉ!
ኔይማር አሁንም ውዱ ተጫዋች ነው!

በተለያዩ ዝውውሮች ብዙ ገንዘብ በወጣባቸው ዝርዝር ላይ ኔይማር በድጋሚ ቀዳሚው ተጫዋች ሆኗል።
ኖቲንግሃም ፎረስት ኑኖ ታቫሬዝን ለማስፈረም ተዘጋጅቷል!
ከተጫዋቹ ጋር ድርድሩም ቀጥሏል።