ሩቢ ስፖርት
244 subscribers
1.96K photos
2 videos
3 links
Download Telegram
ወደ አሜሪካ የተጓዘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ሃገር ቤት እየተመለሰ ነው!
የሊጉ የምንጊዜውም ውዱ ምርጥ 11!
ዶክመንተሪ ተሰርቶ ሊመጣ ነው!

የማንቼስተር ሲቲ የሶስትዮሽ ዋንጫን የሚያስዳስስ ዶክመንተሪ ፊልም ተሰርቶ ለእይታ ሊበቃ ነው።
ዶክመንተሪው የመልበሻ ክፍል ገመናዎችን፣የፔፕ ጓርዲዮላን የመልበሻ ክፍል ንግግሮች፣ከድል እና ከሽንፈት በኋላ የተጫዋቾቹ ሁኔታ እና በርካታ ኢንተርቪዎችን ይዟል!
1
አንድሬስ ክርስቲያንሰን ወደ ቼልሲ የተዘዋወረበት ውል ምርመራ ተጀምሮበታል!
ቼልሲ ያለ አግባብ የፈፀመው ገንዘብ አለ ተብሏል።
አል ሂላል ፊሊክስን ይፈልጋል!

የሳዑዲው ቡድን ፖርቱጋላዊውን በውሰት ማስፈረም ይፈልጋል።
ተጫዋቹ ወደ ባርሳ ማቅናት ምርጫው ቢሆንም አትሌቲ በቋሚነት መሸጥ አይፈልግም።
ጆ ሮዶን ወደ ሊድስ!

ተከላካዩ በውሰት ለመቆየት ነው ወደ ሊድስ ለማቅናት የተቃረበው።
Estadi Olímpic Lluís Companys

ባርሴሎና በውድድር ዘመኑ የሚጠቀምበት ስታድየም።
ሲቲ ፓኩዌታን ይፈልጋል!

ሲቲ የአማካይ ክፍሉን ለማደስ ብራዚላዊውን ለማስፈረም በትኩረት እየሰራ ነው።
ተመልሷል!

ሜሰን ግሪንዉድ ሙሉ ለሙሉ ወደ ልምምድ ተመልሷል።
ከቡድኑ ጋር በቅርቡ ይቀላቀላል።
በውሰት ይሰጥ ወይ ይቆይ የሚለው ውሳኔ ብቻ ይጠበቃል።
"ሉካኩ ክዶናል(አታሎናል) ይሄ ደግሞ እኛን በጣም አበሳጭቶናል።
ዳግም በእኛ መለያ የማየት እቅዱ የለንም።
ይሻላል ያለውን መንገድ መርጧል"።

የባሉገን ዝውውር የተወሳሰበባቸው የኢንተር ባለስልጣናት(ሃቪዬር ዛኒቲ) ስለሉካኩ ተጠይቀው የሠጡት ምላሽ ነው።
ዩናይትድ ተከላካይ ይፈልጋል!

ቡድኑ ለጂያን ክሌይር ቶዲቦ የመጀመሪያ ጥያቄውን ሊያቀርብ ነው።
ኒስ ለተጫዋቹ ከ30 ሚሊየን ፓወንድ በላይ ይፈልጋል።
ሩቢ ስፖርት
ካይል ዎከር በሲቲ ለመቆየት ወስኗል!
ካይል ዎከር በማን ሲቲ ተጨማሪ 1 አመት የሚያቆየውን ውል ለመፈረም ዝግጁ ሆኗል።
ሲቲ እንደ ዎከር ሁሉ የበርናርዶ ሲልቫ ቆይታን ለማረጋገጥ እየሰራ ነው።
ሳይጫወት ሊለቅ ነው!

ኢልካይ ጎንዶዋን የባርሳ ህልሙ ሊጨናገፍ ይመስላል።
እስካሁን ስሙ በባርሴሎና ያልተመዘገበው ተጫዋች እስከ እሁድ የማይመዘገብ ከሆነ መልቀቁ አይቀሬ ነው።
ኔይማር ከፓሪስ እየወጣ ይመስላል!

ብራዚላዊው በፓሪስ መቆየት አለመፈለጉን ከተናገረ በኋላ በትላንትናው የቡድኑ ልምምድ ላይ አልተገኘም።
በጭን(ታፋ) ጉዳት አልተገኘም ቢባልም ልቡ ከዛ ለመራቁ ማረጋገጫ ሆኗል።

ከእርሱ ዝውውር ጋር የባርሳው አሰልጣኝ ቻቪ ሄርናንዴዝ ስለ ሌላ ቡድን ተጫዋች ስም አላነሳም ዝውውሩ ኦገስት 31 ይዘጋል እስከዛ የሚሆነውን ማየት ነው ብለዋል።
ሮጀር ኢባኔዝ ወደ ሳዑዲ!

አል አህሊ ተከላካዩን ለማስፈረም ከሮማ ጋር ተስማምቷል።
28.5 ሚሊየን ዩሮ እና 3 ሚሊየን ዩሮ በሚጨመር ሂሳብ ነው ብራዚላዊው ወደ ሳዑዲ የሚያመራው።

ተከላካዩ ከአል አህሊ የሚለቅ እና የሚሸጥ ከሆነ ሮማ የሽያጩን 20% ለማግኘት ተደራድረዋል።
ደሚራል ከአታላንታ ይለቃል!

ቱርካዊው ከአታላንታ መልቀቅ ተቀዳሚ ምርጫው ሲሆን ኢባኔዝን የሚያጣው ሮማ ቀዳሚ ፈላጊው ነው።
የእንግሊዞቹ ዌስትሃም እና ኖቲንግሃም ፍረስት የደሚራል ፈላጊዎች ናቸው።
ጋሪ ኦኔል ወደ ዎልቭስ!

አሰልጣኙ ዩሊያን ሌፕቴጉዌን ተክተው የዎልቭስ አሰልጣኝ ሊሆኑ ነው።
ስኮት ፓርከር ከበርንማውዝ ሲሰናበት በጊዜያዊነት በርንማውዝን ይዘው የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ከዎልቭስ ጋር ማድረጋቸው ይታወሳል።
ራስሙስ ሆይለንድ የመጀመሪያው ጨዋታ ያልፈዋል!

አጥቂው ከጀርባ ህመም ጋር በሊጉ መክፈቻ ጨዋታ ላይ አይኖርም።