ሩቢ ስፖርት
244 subscribers
1.96K photos
2 videos
3 links
Download Telegram
ማርቲን ኦዴጋርድ አዲስ የ5 አመት ውል ከአርሰናል ጋር ተፈራርሟል!
ዩሊያን ናይግሊስማን የጀርመን ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነዋል!
ኮንትራቱ እስከ 2024ቱ የአውሮፓ ዋንጫ ብቻ ነው!
የአፍሪካ ዋንጫ ቋት!
ማኔ ፌሪሚኒዮ(ሆ) ላይ!

በምሽቱ የአል ናስር እና አል አህሊ ጨዋታ ላይ አል ናስር 3ተኛውን ጎል ሲያስቆጥር ሳዲዮ ማኔ የቀድሞ የቡድን አጋሩ ላይ ወጥቶበታል።
🔥2👍1
ሰላም ክቡራን እንዴት ቆያችሁን!
የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ 6ኛ ሳምንቱ ላይ ተገኝቷል።
በሳምንቱ የመክፈቻ ጨዋታ ማንቼስተር ሲቲ ከ ኖቲንግሃም ፎረስት የሚያደርጉትን ጨዋታ በቀጥታ እናደርሳቹሃለን!

በ100% የአሸናፊነት ጉዞ ላይ የሚገኘው ሲቲ ዛሬስ ያንኑ ያስቀጥል ይሆን?
የፔፕ ቡድን ብዙ ባልተለመደ መልኩ ከዋክብቱ በጉዳት ከሜዳ እየራቁ ነው ተፅዕኖ ይኖረው ይሆን?

በሀገር ውስጥ ቅዱስ ጊዮርጊስን እንዳስሳለን!
የወጣት ቡድኑ በአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ዛሬ 8 ሰዓት ሲጫወት ዋናው ቡድን ነገ በካፍ ቻምፒዮንስ ሊግ ማጣሪያ ከአል አህሊ ይፋለማል ምን እንጠብቅ?በሰፊው እናየዋለን!

ከቀኑ 10 ጀምሮ በብስራት ኤፍ ኤም 101.1 መደመጥ እንጀምራለን ሃሳብዎን ያጋሩን!

ሩቢ ስፖርት
ፊል ፎደን ያስቆጠራት የሲቲ ጎል ከ46 ቅብብል በኋላ የተገኘች ናት!
በሊጉ ከ2006/07 የውድድር ዘመን በኋላ በብዙ ንክኪ የገባ 2ኛው ጎል ነው።
1
ሮድሪ በእግር ኳስ ተጫዋችነት ዘመኑ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀይ ካርድ ተመልክቷል!
የወጣት ቡድን ጨዋታን ጨምሮ ከ470 በላይ ጨዋታዎችን ከውኗል!
በበርሊን ማራቶን ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ትዕግስት አሰፋ
የዓለም የማራቶን ሪከርድን በመስበር አሸነፈች።

የገባችበት ሰዓት 2:11:53
ክብሩም ወደ ቤቱ ተመልሷል!
በቅርቡ የ5000 ሜትር ሪከርድ መመለሱ ይታወሳል።

131 ሰከንድ ነው ያሻሻለችው
👏4
ሩቢ ስፖርት
"ክለቤ እውቅና ያልሰጠኝ ብቸኛው የአለም ዋንጫ አሸናፊ ነኝ። 25ቱ የቡድን አጋሮቼ በቡድናቸው ይሄን አግኝተዋል"። ሊዮ ሜሲ ፓሪስ ምን ያህል እንደገፋው ያመላከተበት ንግግሩ
ሜሲ ክብር ተነፈኩ ለሚለው ሃሳብ ናስር አል ካላይፊ መልስ ሰጥተዋል!

የPSG ፕሬዝደንት ናስር አል ካላይፊ ለሜሲ ሃሳብ ምላሽ ሰጥተዋል።
"ሁሉም እንዳየው በልምምድ ወቅት እንደ ቡድንም ከዛ በግልም ድሉን አብረን አክብረናል።
በተረፈ ፈረንሳይ እና ፈረንሳያውያን ተጫዋቾችንም ስለምናከብር በስታድየም አላከበርንለትም"።
👎2
ጨዋታው ተቋርጧል!

በሆላንድ ኤርዲቪዜ በሜዳው ፋይኖርድን ያስተናገደው አያክስ በመጀመሪያው አጋማሽ 3 ለ 0 መመራቱን ተከትሎ የአያክስ ደጋፊ ያስነሱት ተቀጣጣይ ነገር እና ብጥበጣ ጨዋታው እንዲቋረጥ አድርጎታል።
እንዴት ቆያችሁን ክቡራን!
በስፔን ላሊጋ 6ተኛ ሳምንት ተገናኝተናል።
የማድሪድ ደርቢን ከ 3:30 ጀምሮ እናደርስላቹሃለን።አትሌቲ የሪያልን የ100% አሸናፊነት ይገታ ይሆን?ቤሊንግሃም ዛሬስ ምን አይነት ምሽት ይጠብቀዋል?

በእንግሊዝ የተካሄዱ ጨዋታዎችንም እንዳስሳለን!
ሩቢ በብስራት ኤፍ ኤም 101.1
ዳርዊን ኑኔዥ ባለፉት 5 ጨዋታዎች
4 ጎል አስቆጥሮ 2 አመቻችቷል።
ኒውካስትል ዩናይትድ በብራሞሌን ሼፍልድን 8 ለ 0 ረቷል።
በጨዋታው 8 የተለያዩ ተጫዋቾች ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
ኬረን ትሪፔ 3 ኳሶችን አመቻችቶ አቀብሏል።
ቅዱስ ጊዮርጊስ የመጀመሪያ የአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ የማጣሪያ ጨዋታን ተሸንፏል።
ቅዲስ ጊዮርጊስ  0 - 3 አል አህሊ 
😢3
ሚሽልንታት እና አያክስ ተለያይተዋል!

አያክስ ከFootball ዳይሬክተሩ ስቬን ሚሽልንታት ጋር ተለያይተዋል።
"ነገ ተማሪዎች የአትሌቲኮ ማድሪድን መለያ ለብሰው ወደ ት/ት ቤት ይሄዳሉ"

በማድሪድ ደርቢ የጨዋታው ኮከብ የነበረው አልቫሮ ሞራታ የተናገረው!
ጨዋታውን አትሌቲ 3 ለ 1 ሲያሸንፍ ሞራታ 2ቱን አስቆጥሯል።