ሩቢ ስፖርት
244 subscribers
1.96K photos
2 videos
3 links
Download Telegram
ሩቢ ስፖርት
ሎሚ ሙለታ በ300ዐ መሰናክል ለፍፃሜ አልፋለች!
ሲምቦ አለማየሁ ከምድብ 2 2ተኛ ወጥታ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች!
ሩቢ ስፖርት
ሲምቦ አለማየሁ ከምድብ 2 2ተኛ ወጥታ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች!
ዘርፌ ወንድማገኝ 2ኛ ወጥታ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች!
👍21
በሁለቱም ርቀት የተወዳደሩት 7ቱም አትሌቶች ወደ ፍፃሜ አልፈዋል!
2👍2
የቀድሞ የኢትዮ ኤሌትሪክ እና የቤንቺ ማጂ ተጫዋች ጅላሉ ከማል ለወልቂጤ ከተማ ለ1 አመት ለመጫወት ተስማምቷል!
ዌስትሃም ዝውውሩን እየጨረሰ ነው!

ሞሃመድ ኩዱስም ለመፈረም የተስማማ ሲሆን ዌስትሃም ለአያክስ 45 ሚሊየን ዩሮ ይከፍላል!
ቬይጋ ወደ ሳዑዲ!

ያልተጠበቀው ዝውውር እውን ሊሆን ተቃርቧል።
ወጣቱ ጋብሪ ቬይጋ የአል አህሊ ተጫዋይ ሊሆን ተቃርቧል።
ከናፖሊ ጋር ስሙ ሲያያዝ ቆይቷል።
ጆአኪን ኮሪአ ወደ ፈረንሳይ!

የመስመር አጥቂውን ለመውሰድ ማርሴይ ጥያቄ አቅርቧል።
በ2 ሚሊየን ዩሮ ክፍያ በውሰት እንዲያሳልፍ እና አመቱ ሲያልቅ ቋሚ ለማድረግ ነው የበለድኑ እቅድ።
አልናስር በቋት 4 ተቀምጧል!

የኤስያ ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ ድልድልን ለማውጣት ቡድኖች በ4 ቋት ተሰድረዋል።
በውድድሩ ከ1 ቡድን 5 የውጪ ሃገር ተጫዋቾች + 1 ኤስያ ውስጥ ያለ ተጫዋች ብቻ ነው የተፈቀደው።

ለምሳሌ አልናስር፦ሮናልዶ፣ማኔ፣ፎፋና፣ብሮዞቪች እና ኦታቪዮን ቢጠቀም እንደ ቴሌሽ እና ኮናንን መጠቀም አይችልም ማለት ነው።
1
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥቷል::

በሪሁ የተመረጠው በሰዓቱ ነው:: በስራ አስፈፃሚ የተወሰነ እንጂ አንድ ግለሰብ የወሰነው አይደለም::

"በዚህ መልኩ ሊነገረው አይገባም ነበር:: አትሌት የሆነ ሁሉ ስሜቱን ያውቀዋልና እኔም ተሰምቶኛል" ደራርቱ ቱሉ


ጋዜጠኛ አረጋ ከፈለው
👉 በአፍሪካ ሻምፒዮንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ የመልስ ጨዋታ የክለባችን ተጋጣሚ ኬኤም ኬኤም ልዑካን ቡድን ዛሬ ነሐሴ 18 ቀን 2015 ዓ.ም አዲስ አበባ ሲደርሱ አቀባበል ተደርጓላቸዋል፡፡

ከቡድኑ ገፅ
👍2
ጋቶች ፓኖም የፋሲል ከነማ ተጫዋች ሆኗል!
የ5000ሜትር ወንዶች ማጣሪያ ምሽት 2፡00

- ዮሚፍ ቀጀልቻ
- ሀጐስ ገ/ሕይወት
- በሪሁ አረጋዊ
ጃኦ ፊሊክስ ዳግም ለአትሌቲ መጫወት አያስብም!
በፕሬዝዳንቱ የተሰጠ ማረጋገጫ ነው
1
ከሳዑዲ ብዙ ፍላጎት ነበር ግን ቤኒፊካን እወደዋለሁ ለዛም ወደዚህ መጣሁ!
ጋብርኤል ሄሱስ በልምምድ ላይ!
" ጥላሁን ላይ የደረሰው እኔም ላይ ደርሷል "

በ 19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና 5000ሜ ማጣርያ በማለፍ ፍፃሜውን የተቀላቀለው አትሌት ሀጎስ ገብረ ህይወት በጥላሁን ሀይሌ መቀነስ ላይ ሀሳቡን ሰጥቷል።

በመጀመሪያው ምድብ ማጣርያውን ያከናወነው ሀጎስ "ጥላሁን ላይ የደረሰው ነገር እኔ ላይ ከሁለት አመት በፊት ኦሎምፒክ ላይ ደርሶብኛል አውቀዋለሁ" ብሏል።

አያይዞም "  ስፖርት ሁሌም በፈተና የተመላ ነው " ሲል " ነገር ግን የተመረጥነው በሰዐታችን ነው።" ሲል ከማጣርያው መጠናቀቅ በኋላ ከልዩ ስፖርት ጋር ባደረገው ቆይታ ገልጿል።

ጋዜጠኛ ሀይለእግዚአብሔር አድሀኖም
አትሌት ጥላሁን ሀይሌ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሰ !

በ19ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን በ5000ሜ ይወክል የነበረው ጥላሁን ሀይሌ ዛሬ  ከሰዓት ወደ ኢትዮጵያ መመለሱ ታውቋል።

አትሌቱ ለወራት ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ጋር ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቶ ወደ ሃንጋሪ ቢያመራም  ከቡድኑ መቀነሱ ይታወሳል።

በዚህም ምክንያት አትሌት ጥላሁን ሀይሌ ከአሰልጣኙ ጋር ከተማከረ በኃላ ዛሬ ከሰዓት ወደ #ኢትዮጵያ ማቅናቱ ታውቋል።

አትሌቱ ከዝርዝሩ ወጪ መሆኑን ካረጋገጠ በኋላ በውሳኔው ማዘኑን እና ቅሬታውን በማህበራዊ ሚዲያ ካሰማ በኃላ የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰነዘሩ ቆይተዋል።

ይሄም አትሌቱ ዜግነቱን #ይቀይራል የሚል ቢሆንም አትሌቱ ዜግነቱ መቀየር ሀሳቡም #እንደሌለው እና በቀጣይ ጠንክሮ በመስራት ኢትዮጵያን ወክሎ አቅሙን ማሳየት እንደሚፈልግ ለናሽናል ስፖርት ገልጿል።

ቲክቫህ ስፖርት