ሐሰን ዳውድ
1.13K subscribers
106 photos
20 videos
48 files
236 links
ኢስላማዊ እውቀት የሚተላለፍበት ቻናል
1,አቂዳ
2, ፊቂህ
3, ሀዲስ
4, ሉጋህ( ነህው;ሶርፍ,በላጋ,በያን,አደብ,አሩድ)
5, ሙስጠላህ
6,ኡሱል
ሌሎችም አጫጭር መረጃዎች ያገኙበታል።
Download Telegram
.


قال الإمام الذهبــﮯ رحمــه الله
فالمؤمــن إذا امتحن صبــر و اتعظ و استغفر
و لم يتشاغل بذم من انتقــم منه


سير اعلام النبلاء【 ٨١/٨
1.12 ኒካህ ለማሰር መሟላት ያለባቸው አራት መስፈርቶች
1, ማንነታቸው መታወቅ

ሁለቱም ኒካህ የሚያስሩት አካላት ማንነታቸው ተለይቶ መታወቅ አለበት። አንድ አባት ለአንድ ሰው ከልጆቼ መሀከል አንዷን ድሬልሀለው ቢለው ይህ ኒካህ ልክ አይሆንም ምክንያቱም የትኛዋን ልጁን እንደሆነ በግልጽ አላስቀመጠምና ነው። ግን ሰውየው ያለው አንድ ልጅ ከሆነና ልጄን ድሬልሀለው ቢል ትክክል ይሆናል ወይም ደግሞ ልጁ አጠገቡ ኖራ ወደሷ እያመላከተ ይህችን ልጄን ድሬልሀለው ቢል ይሆናል።
ቁርአን ላይ ያሉ ስለ ኒካህ ማሰር የሚናገሩ አንቀጾችም የግለሰቡ ማንነት በግልጽ ሚጠቁሙ ናቸው። ለምሳሌ ያክል

{{ فَلَمَّا قَضٰى زَيْدٌ مِّنْهَا وَطَرًا زَوَّجْنٰكَهَا }}
{{ ዘይድም ከእርሷ ጉዳይን በፈጸመ ጊዜ እርሷን አጋባን }}
2,ፍቃደኝነታቸው

ወንድም ይሁን ሴት ያለ ፍላጎታቸው ማንም አስገድዶ ሊድራቸው አይችልም። ለዚህ ማስረጃው መልእክተኛው ﷺ እንዲህ ማለታቸው ነው
{{ لا تنكح البكر حتى تستأذن، ولا تنكح الأيم حتى تستأمر }}
{{ልጃገረድ የሆነች ሴት እስኪያስፈቅዷት አግብታ የፈታች ደግሞ እስኪያማክሯት ድረስ አትዳርም}}

በመሆኑም ያለ እሷ ፍቃደኝነት በጠለፋም ይሁን በቤተሰብ አስገዳጅነት የሚፈጸም ኒካህ ትከከለኛ አይሆንም መስፈርት ስላላሟላ።
3, ወልይ
ለሴት ልጅ⁹² ኒካህ የሚያስርላት ወልዩዋ ነው ራሷ ለራሷ ኒካህ ማሰር አትችልም ማስረጃውም ከቁርአን

{ وَلَا تَنكِحُوا الْمُشْرِكٰتِ حَتّٰى يُؤْمِنَّ ۚ }

{{ለአጋሪዎቹም እስከሚያምኑ ድረስ አትዳሩላቸው፡፡}}

በዚህ አንቀጽ ላይ አትዳሯቸው ማለቱ ሴት ልጅ ራሷን እንደማትድርና የሚድራት ወልዩዋ መሆኑን ይጠቁመናል።

በሀዲስ ደግሞ የአላህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል
{{ لا نكاح إلا بولي }}
{{ በወልይ እንጂ ኒካህ የለም}}

ይህ አብዛኛዎች ኡለሞች ያሉበት አቋም ነው ማንኛውም ሴት ያለወልይ ልትዳር አትችልም ልጃገረድም ትሁን አግብታ
የምታቅም ብትሆን ያለ ወልይ ኒካህ የለም።

ወልይ መሆን የሚችለው ሰው እነዚህን መስፈርቶች ሊያሟላ ይገባል
▪️ ብሉግ

(አቅመ አዳም) የደረሰና አእምሮ ጤነኛ የሆነ መሆን አለበት
▪️ ወንድ መሆን አለበት። እናት ልጇን ወልይ ሆና መዳር አትችልም

▪️የኒካህን ጥቅምና የሚበጃትን መለየት የሚችል መሆን አለበት ሞኛሞኝ ሆኖ ለጠየቀው ሁላ የሷን ጥቅም ሳያገናዝብ የሚድር ከሆን ወልይ ሊሆናት አይችልም

▪️ በእምነት ተመሳሳይ መሆናቸው ግዴታ ነው። ሙስሊም ሴት አባቷ ክርስቲያን ከሆነ እሱ ለሷ ወልይ ሆኖ ሊድራት አይችልም። ካፊር ሙስሊም ላይ በምንም ሁኔታ የበላይ ሊሆን አይገባም። አላህ እንዲህ ይላል

{ وَلَن يَجْعَلَ اللَّهُ لِلْكٰفِرِينَ عَلَى الْمُؤْمِنِينَ سَبِيلًا }
{{አላህም ለከሓዲዎች በምእምናን ላይ መንገድን በፍጹም አያደርግም፡፡}}

4. በግልጽ መሆኑ ወይ ደግሞ ምስክር መኖሩ
ኒካው በድብቅ መሆን የለበትም ሰዎች ሊያውቁት ይገባል። መልእክተኛው እንዲህ ብለዋል
{أعلنوا النكاح}
{{ኒካህን ግልጽ አድርጉ}}

ምስክር መኖር እንዳለበትም የሚጠቁሙ ሀዲሶች ቢኖሩም ነገር ግን ደካማ መሆናቸውን ኡለሞች ተናግረዋል።ነገር ግን ከኺላፍ ለመውጣት ምስክር ባለበት መሆኑ ተገቢ ነው እንላለን። ኒካሁ ሰው አውቆት በግልጽ መሆኑ ግን ግዴታ ነው በዚህ ላይ ከላይ ያሳለፍነው ግልጽ ሀዲስ ስለመጣበት።በድብቅ የታሰረ ኒካህ ትክክል አይሆንም። ምስክር ያለበት ሆኖ በግልጽ የተፈጸመ ኒካህ ሁለቱንም ያሟላ ሰለመሆን ከኺላፍም የጸዳው ነውና የተሻለው
https://t.me/Hassendawd
ሸይኹ ሹዩኺና አል ዐላማህ አዝ ዛሂድ ሀጂ ሙሓመድ ራፊእ رحمه الله አዲስ አበባ በሚኖሩበት ወቅት ዳሰስ ባለች ቀበሌ ቤት ነበር ሚኖሩት ብሎ አንድ እሳቸዉን በሀያት እያሉ የሚዘይራቸዉ ወንድም ሲነግረኝ አዘንኩ ።
ዑለሞችን በሂወት እያሉ ለምን አንኻድማቸዉም !!!
አንተ ሶስተኛ አራተኛ ቤት ከምትሰራ ከ አንድ በላይ ዲንን የሚያስተምሩ ሸይኾች እንዲኖሩበት ቤት አታመቻችም !!!
አንተ ቤትህን ለቅንጦት ምታሳድስበት ለአንድ ሸይኽ የአመት ወይም ከዛ በላይ የቤት ክራይ ይዘጋ ይሆናል ።
ማስታወሻ፦

ነገ ሰኞ የወርሃ ሸዋል 13ኛ ቀን ነው። ከዚያም 14ኛውና 15ኛው ተከታታይ የአያመ-ል-ቢዽ ቀናቶች ናቸው።  የሸዋልን ፆም የምትፆሙ ሁለቱንም ነይታችሁ ብትፆሙ በሁለቱም ትመነዳላችሁ። ነገ ደግሞ ሰኞ ስለሆነ ሸዋላችሁንም፣ አያመ-ል-ቢዻችሁንም፣ ሰኟችሁንም (በአንድ ቀን 3 ምንዳ) ታፍሳላችሁ። ኒያችሁን አሳምሩ ብቻ!
إذا استغنى الناس بالدنيا؛ فاستغن أنت بالله، وإذا فرِحوا بالدنيا؛ فافرح أنت بالله، وإذا أنِسوا بأحبابهم؛ فاجعل أنسك بالله، وإذا تعرّفوا إلى ملوكهم وكبرائهم، وتقرَبوا إليهم لينالوا بهم العزّة والرِّفعة؛ فتعرَّف أنت إلى الله، وتودد إليه، تَنل بذلك غايةَ العزّة والرّفعة.

ابن القيم | الفوائد.
ኢማሙ አሕመድ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ አሉ፦

ዙህድ "ቸልተኝነት" 3ት አይነት ነው።

1ኛ,ሀራምን መተው ሲሆን፡ይሄ የተራው ሰው "ቸልተኝነት"ነው።
2ኛ,ሐላል ከሆኑ ነገራቶች ትርፋትርፎችን መተው ነው።ይሄ ደግሞ "ልዩ የሚባሉ ሰዎች ቸልተኝነት" ነው።
3ኛ,ከአላህ(ዒባዳ) ቢዚ የሚያደርጉ ነገራቶችን መተው ሲሆን፡ይሄ የ"ዓዋቂዎች ቸልተኝነት" ነው።

📚መዳሪጁ አስ'ሳሊኪን 2/181
Forwarded from ፈዋኢድ (عبد الرزاق بن محمد)
1. አልሃፊዝ ኢብኑ ሀጀር رحمه الله "ሙእጀም አጠበራኔ "ን ከዙሁር እስከ ዐስር ሙሉውን አንብበዋል ።
2. ኢራቃዊ የፊቅህ ሊቅ አብዱላህ ቢን ሙሀመድ " ሙግኔ " የተሰኘውን ኪታብ ከ20 ግዜ በላይ አንብበውታል።
3. አል ኢማም ኸጢብ አል በግዳዲ በ3 ቀን ውስጥ ሰሂህ አል ቡኻሪ መሉውን በሸይኻቸው ኢስማኤል አል ሂሪይ ቀርተዋል ።
2ቱን ቀን ከመግሪብ እስከ ፈጅር ያነበብ ሲሆን 3 ኛዉን ቀን ከ ረፋዱ ሰዐት እስከ መግሪብ ከዛም ቀጥለውም ከመግሪብ እስከ ፈጅር ቀርተዋል ።
በሌላ ጊዜም በታላቋ ሙስኒዳህ ከሪማ አል መሩዚያህ رحمها الله ላይ በ5 ቀን ውስጥ ቀርተውት ጨርሰዋል ።

أخي لا تكن شاب البدن أشيب الهمة
قم وانهض إلى بناء مجدك
قال الإمام الذهبي:
ﺃَﺣْﻤَﺪُ ﺑﻦُ ﺇِﺳْﺤَﺎﻕَ ﺃَﺑُﻮ ﺇِﺳْﺤَﺎﻕَ *
اﻹِﻣَﺎﻡُ، اﻟﺰَّاﻫِﺪُ، اﻟﻌَﺎﺑِﺪُ، اﻟﻤُﺠَﺎﻫِﺪُ، ﻓﺎﺭﺱ اﻹﺳﻼﻡ، ﺃَﺑُﻮ ﺇِﺳْﺤَﺎﻕَ: ﻣِﻦْ ﺃَﻫْﻞِ ﺳُﺮْﻣَﺎﺭَﻯ، ﻣِﻦْ ﻗُﺮَﻯ ﺑُﺨَﺎﺭَﻯ.
ﺳَﻤِﻊَ: ﻣَﻦْ ﻳَﻌْﻠَﻰ ﺑﻦِ ﻋُﺒَﻴْﺪٍ، ﻭَﻋُﺜْﻤَﺎﻥَ ﺑﻦِ ﻋُﻤَﺮَ ﺑﻦِ ﻓﺎﺭﺱ، ﻭَﺃَﺑِﻲ ﻋَﺎﺻِﻢٍ، ﻭَﻃَﺒَﻘَﺘِﻬِﻢ.
ﺣَﺪَّﺙَ ﻋَﻨْﻪُ: اﺑْﻨُﻪُ، ﻭَﺃَﺑُﻮ ﻋَﺒْﺪِ اﻟﻠﻪِ اﻟﺒُﺨَﺎﺭِﻱُّ ﻓِﻲ (ﺻَﺤِﻴْﺤِﻪِ) ، ﻭَﺇِﺩْﺭِﻳْﺲُ ﺑﻦُ ﻋَﺒْﺪَﻙَ، ﻭَﺁﺧَﺮُﻭْﻥَ.
ﻭَﻛَﺎﻥَ ﺃَﺣَﺪَ اﻟﺜِّﻘَﺎﺕِ، ﻭَﺑِﺸَﺠَﺎﻋَﺘِﻪِ ﻳُﻀْﺮَﺏُ اﻟﻤَﺜَﻞُ.
1.13 አባት ሴትን ልጅ ያለፍቃዷ ስለመዳር
አብዛኛዎች ኡለሞች ሴት ልጅን አባቷ ፍቃዷን ሳይጠይቅ መዳር ይችላል የሚል አቋም አላቸው በዚህ ላይ ኢጅማእ እንዳለበትም የጠቀሱ አሉ።
ሆኖም ነጥቡ ኺላፍ አለበት ኢብን ሺብሪማ አባቷም ቢሆን ማስገደድ አይችልም የሚል አቋም ነበረው ከማስረጃ አንጻር ሚዛን ሚደፋውም አቋም ይህ ነው።

ማስረጃው መልእክተኛው ﷺእንዲህ ማለታቸው ነው

{{لا تنكح البكر حتى تستأذن ,ولا تنكح الأیم حتى تستأمر }}
{{ልጃገረድ የሆነች ሴት እስኪያስፈቅዷት አግብታ የፈታች ደግሞ እስኪያማክሯት ድረስ አትዳርም}}

ይህ ሀዲስ ጥቅል ነው አባት ከሆን እሷን መዳር ይችላል የሚል ነገር አልመጣም። አባቷ እሷን ማስገደድ ከቻለ ለምን
ያስፈቅዳት ተባለ? እሷ ባትፈቅድም መዳርን ከቻል በማስፈቀዱ ምን ጥቅም አለው ?
እዚህ ጋር የሚነሳ ጥያቄ አለ እሱም አቡ በከር ሲዲቅ አኢሻን ለአላህ መልእክተኛ በስድስት አመቷ ድሮላቸው በ ዘጠኝ አመቷ አብረው ሆነው የለ ወይ? ይህ ታዲያ አባት ልጁን ያለ ፍቃዷ ለመዳር ማስረጃ አይሆንም?

መልስ ፦ አዎ ታሪኩ እውነት ነው ግን ማስረጃ አይሆንም ምክንያቱም አኢሻን አቡበከር ሲድራት ተጠይቃ እንቢ አልፈልግም ብላ አባቷ አስገድዷት እንደዳራት በምን አወቅክ? ምንም እንደዛ ሚል ነገር አታገኝም እንደውም አኢሻ አባቷ ቢያስፈቅዳት ፍቃደኛ ትሆን እንደነበረ ሚጠቁን ማስረጃ ነው ያለው። ይህን የቁርአን አንቀጽ እስኪ ተመልከት

{ يٰٓأَيُّهَا النَّبِىُّ قُل لِّأَزْوٰجِكَ إِن كُنتُنَّ تُرِدْنَ الْحَيٰوةَ الدُّنْيَا وَزِينَتَهَا فَتَعَالَيْنَ أُمَتِّعْكُنَّ وَأُسَرِّحْكُنَّ سَرَاحًا جَمِيلًا (28) وَإِن كُنتُنَّ تُرِدْنَ اللَّهَ وَرَسُولَهُۥ وَالدَّارَ الْءَاخِرَةَ فَإِنَّ اللَّهَ أَعَدَّ لِلْمُحْسِنٰتِ مِنكُنَّ أَجْرًا عَظِيمًا (29) }
{{አንተ ነቢይ ሆይ! ለሚስቶችህ (እንዲህ) በላቸው «ቅርቢቱን ሕይወትና ጌጧን የምትፈልጉ እንደ ሆናችሁ ኑ፤ አጣቅማችኋለሁና፡፡ መልካምንም ማሰማራት (በመፍታት) አሰማራችኋለሁና፡፡አላህንና መልክተኛውን የመጨረሻይቱን አገርም የምትፈልጉ ብትሆኑም፤ እነሆ አላህ ከእናንተ ለመልካም ሠሪዎቹ ትልቅን ምንዳ አዘጋጅቷል፡፡}}

የአላህ መልእክተኛ ﷺ ይህ የቁርዓን አንቀጽ ሲወርድ መጀመሪያ በአኢሻ ነበር የጀመሩት እሷ ጋር ሄደው እንዲህ
አሏት “አባትሽን እሲኪ በዚ ጉዳይ(ፍቺ ይሻልሻል ወይስ ከኔ መቆየት በሚለው ጉዳይ ማለት ነው) አማክሪው” አሏት
እሷም “የአላህ መልእክተኛ ሆይ በዚህ ነው እንዴ አባቴን ማማክረው?! እኔ አላህንና አኼራን ነው ምፈልገው”
አለቻቸው።

📖 ስለዚህ ሴት ልጅን ማንም ቢሆን አስገድዶ ሊድራት አይችልም አባቷም ቢሆን ሊያስገድዳት አይችልም።እሱን
ካላገባሽ ከማህበረሰቡ ትገለያለሽ ከቤት ትባረሪያለሽ እያሉ በማስፈራራት እንድታገባው ማስገደድም እዚሁ ውስጥ
ይገባል።
https://t.me/Hassendawd
Audio
1.14 የሴት ልጅ ወልዮች እነማን ናቸው
ሴት ልጅን ወልይ ሆነው ሊድሯት የሚችሉት በቅደም ተከተል ስንመለከት
1.ኛ አባቷ እሱ ከሌለ የአባቷ አባት እያለ .......ወደላይ ይቀጥላል እነዚ ከሌሉ ወደ ሁለተኛው እንሄዳለን

2.ኛ ልጇ እሱ ከሌለ የወንድ ልጇ ልጅ እያለ .....ወደታች ይቀጥላል ከሌሉ ወደ ሶስተኛው እንሄዳለን

3.ኛ በአባትም በእናትም የሚገጥም ወንድሟ እሱ ከሌለ በአባት ብቻ ሚገጥም ወንድሟ

4.ኛ የወንድሟ ልጅ (አባትም በእናትም የሚገጥም ወንድሟ ልጅ) እሱ ከሌለ በአባት ብቻ ሚገጥም ወንድሟ ልጅ

5.ኛ የአባቷ ወንድም (አጎቷ)

6.ኛ የአጎቷ ልጅ (የአባቷ የወንድም ልጅ

መታወቅ ያለባቸው ነጥቦች

▪️ ቅርብ የሆነው ወልይ እያለ ያለ ምንም ምክንያት የሩቁ ካሰረ ኒካው አይሆንም። ለምሳሌ አባት እያለ እሱ ሳይጠየቅ ወንድም ሊያስር አይችልም። ወንድም እያለም እሱ ተዘሎ አጎት አያስርም።ሌላውም እንዲሁ ቅደም ተከተሉን ጠብቆ ነው መሄድ ያለበት።

▪️ ነገር ግን ቅርብ የሆነው ወልይ በህይወት ቢኖርም ከሀገር ጠፍቶ አሁን ላይ ሊገኝ ካልተቻለና እሱን ማግኘት ካዳገተ ቀጣዩ ወልይ ያስራል

▪️በእናት በኩል ያለ ቤተሰብ ወልይ ሆኖ ኒካህ አያስርም
▪️ የእንጀራ አባትም ያሳደጋት እሱ ቢሆንም እክኋል ወልይ ሊሆናት አይችልም።
*ወልይ ሆኗት ራሱ ሚያገባት*
የአጎት ልጅ ያጎቱን ልጅ ራሱ ወልዩዋ ሆኖ ለራሱ ሊድራት ይችላል።
https://t.me/Hassendawd
Audio
1.15 ቤተሰቦቿ በሙሉ ክርስቲያን የሆኑባት ሴት ማን ይድራታል?
ክርስቲያን አባት ሙስሊም ልጁን ወልይ ሆኖ መዳር ዕንደማይችል ከላይ አሳልፈናል።በመሆኑም ቤተሰቦቿ በሙሉ ክርስቲያን የሆኑባት ሴት የሷ ወልይ የሚሆነው ሙስሊም መሪው ወይም ደግሞ የሸሪአ ፍ/ት ቃዲ ነው ያለችው ካፊር ሀገር ሆኖ ሙስሊም መሪም ቃዲም ከሌለ በአካባቢ ያለ የሙስሊሞች መርከዝ ወይም ተቋም ጋር ሄዳ የዛ እስላማዊ ተቋም ሙዲር ወልይ ሆኖ ሊድራት ይችላል። ምንም አይነት ሙስሊሞችን ሊወክል የሚችል ተቋም በሌለበት አካባቢ ብትሆንና ሊያገባት ከፈለገው ሰው ውጪ ከጎኗ ማንም ከሌለ ከሱ ጋር ደግሞ ኒካህ ካላሰርን ዝሙት ላይ እንወድቃለን ብለው ከፈሩ ደሩራ ነውና ምንም አማራጭ ስለሌለ ራሷን ትድርለታለች።በዚህ አማራጭ በጠፋበት ግዜ ራሱ ሚያገባት ወልይ ይሆናታል ያሉም አሉ።
https://t.me/Hassendawd
1.16 በዝሙት የተወለደች ሴት ልጅ ማን ወልይ ይሆናታል?
ሚዛን በሚደፋው የኡለሞች አቋም መሰረት በዝሙት የተወለደች ልጅ የምትጠራው በእናቷ እንጂ በአባቷ አደለም። በዚህ ላይ ደግሞ የመጣ ሀዲስ አለ።በመሆኑም አባቷ ለሷ ወልይ አይሆናትም ቢሞትም አትወርሰውም ብትሞትም አይወረሳትም።እናት ደግሞ ወልይ ሆና ኒካህ ማሰር አትችልም የናት ቤተሰቦችም እንዲሁ ወልይ መሆን አይችሉም። ስለዚህ ይህች ሴት ወልይ የላትም።ወልይ የሌላት ደግሞ ወልዩዋ የሙስሊም ባለስልጣን ነው።

መልእክተኛው ﷺ እንዲህ ብለዋል {ባለስልጣን ወልይ ነው ወልይ ለሌለው}

በመሆኑም በአካባቢዋ ሸሪአ ፍ/ቤት ካለ የዛ ፍርድ ቤት ቃዲ ወልይ ሆኖ ያስርላታል።ያ ከሌለ በአካባቢዋ ያለ ሙስሊሞችን የሚወክል ተቋም ካለ የዛ ተቋም ሙዲር (ተጠሪ) ወልይ ሆኖ ይድራታል።ያም ከሌለ የመስጂድ ኢማም ወልይ ይሆናታል።
https://t.me/Hassendawd
1.17 መወከልስ ይቻላል?
ወልይ የሆነ ሰው ኒካህ ለማሰር ቦታው ላይ መገኘት ካልቻለ በቦታው ሌላ የፈለገውን ሰው መተካት ይችላል።የተተካው ሰው ልክ እንደወልይ ሆኖ ኒካውን ያስራል። ሙስሊም ያልሆነን ሰው መወከልን በተመለከተ ኡለሞች መሀከል ጭቅጭቅ ያለበት ሲሆን ሻፍእዮችና ሀናቢላዎች አይቻልም ይላሉ።ማሊኪዮችና ሀነፍዮች ግን ይቻላል ይላሉ።አይቻልም ያሉ ኡለሞች ለራሱ ወልይ መሆን ስለማይችል መወከልም አይችልም ይላሉ።የተሻለው ከኺላፉ ለመውጣት ካፊርን አለመወከን ነው።
https://t.me/Hassendawd
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አሰላሙ ዐለይኩም ወራህቱሏሂ ወበረካቱሁ የተከበራቹ ሙስሊም ወንድሞችና እህቶች ከላይ ባለው ቪዲዮ ላይ የምትመለከቱት ቦታ በሰሜን ወሎ ዞን የሚገኘው የወልዲያ ዪኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች መስጂድ ሲሆን ከምትመለከቱት የውዱዕ ማድረጊያ በታች ያለው መሬት መንገድ በመሆኑ ለመስጂዱ የሚቀረው ቦታ በቂ አይደለም።በተጨማሪም መስጂዱም እንደምትመለከቱት በአግባቡ የተሰራ ባለመሆኑ ተጨማሪ የመስጂድ ቦታ ለመግዛትና መስጂዱንም በአግባቡ ለመገንባት የተማሪው አቅም ስላልቻለ የእናንተን እገዛ እንሻለን ።በመሆኑም አቅማቹ በቻለው ሁሉ እንድታገዙንና ለሌሎችም ሼር በማድረግ እንድትተባበሩን በአሏህ ስም እንጠይቃለን።

የጀመዐው የባንክ አካውንት

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:1000520261943 woldia universities Muslim student union

http://t.me/wdumuslimstu
1.18 ያለ ወልይ የታሰረ ኒካህ (የሹብሀ ኒካህ)
ኒካህ ለማሰር ወልይ መስፈርት መሆኑን ከላይ አሳልፈናል።በመሆኑም ያለ ወልይ ኒካህ ማሰር አይቻልም።ነገር ግን ያለ ወልይ ማሰር የሚቻል መስሎት ካለ ወልይ ኒካህ አስረው ሚኖሩ ከሆነ ይህ ኒካ የሹብሀ ኒካ ይባላል።በመሆኑም ያለ ወልይ ማሰር እንደማይቻል ካወቁ ሰአት ጀምሮ ኒካሁን ማደስ ይጠበቅባቸዋል።ነገር ግን እስካሁን ያሳለፉት እንደ ዝሙት አይቆጠርም ልጅ ወልደውም ከሆነ በራሳቸው ነው ሚጠራው።ኒካሁን ለማደስ ፈትቼሻለሁ ማለት አይጠበቅበትም።
https://t.me/Hassendawd
አዕምሮ ሶስት ምድብ አለው!

የላይኛው ምድብ ባለቤቶች አዲስ ሀሳብ የሚያፈልቁና እንዴት ወደ ተግባር መቀየር እንዳለባቸው የሚወያዩ ናቸው:: ከመካከል የሚገኘው ምድብ ባለቤቶች ደግሞ ከተሰሩት የሆኑትን ያክል እንዴት በራሳቸው መስራት እንደሚችሉ የሚያሰናስሉና መንገድ የሚፈልጉ ናቸው:: በምድብ ሶስት የሚገኙት የታችኛው ክፍል ባለቤቶች ደግሞ ስራቸውን ከላይ ባሉ ሁለት ምድብ ባለቤቶች ላይ ማውራትን ያደርጋሉ:: ከረቂብና ዓቲድ ውክልና ወስደው የሚንቀሳቀሱ በሚያስመስል ልክ ስራ ፈትተው የሚሰሩትን ይከታተላሉ:: ከዚያም ነገረ ስራቸው ባጠቃላይ ፉላን ወፉላን ብቻ ይሆናል::

ምድብ አንድን ለመሆን ትጋ:: አቅም ከጎደለህ እስኪሞላ በምድብ ሁለት እርጋ:: ፈፅሞ ግን ያለውክልና የረቂብና የዓቲድን ስራ የሰራህ መስሎህ በምድብ ሶስት ውስጥ በውክልና የሸይጧንን ስራ እንዳትሰራ::
ጂን;- ማለት ስውር ወይም ድብቅ ማለት ነው፡፡ጂን የተባሉበት ምክንያት ለእኛ ስለ ማይታዩን እና ከኛ የተደበቁ ስለሆኑ ነው፡፡ በእነሱ ማመን ከኢልመል ገይብ የሚመደብ ሲሆን በእነሱ ማመን ግዳታ ነው፡፡ የእነሱን መኖር ማስተባበል ኩፍር(ክህደት) ነው፡፡ጂኖች ልክ እንደ ሰዎች አማኞች፣ መልካም እና ጥሩ የአላህ ባርያዎች የሆኑ አሉ ፤እንዲሁም ካሃዲዎች እና መጥፎዎችም አሉ፡፡ ጂኖች የተፈጠሩት ከእሳትነው፡፡
وَالْجَانَّ خَلَقْنَاهُ مِن قَبْلُ مِن نَّارِ السَّمُومِ
‹‹ጃንንም(ከሰው) በፊት ከእሳት ነበልባል ፈጠርነው፡፡›አል ሂጅር 27
• በቅድምያ እነዚህን ማጤን ይኖርብናል!!
وَمَا هُم بِضَارِّينَ بِهِ مِنْ أَحَدٍ إِلَّا بِإِذْنِ اللَّهِ
‹‹እነርሱም በአላህ ፈቃድ ካልኾነ በርሱ አንድንም ጎጂዎች አይደሉም፡፡ ›› አል-በቀራህ 102
إِنَّ كَيْدَ الشَّيْطَانِ كَانَ ضَعِيفًا
‹‹የሰይጣን ተንኮል ደካማ ነውና፡፡›› አን-ኒሳእ 76
إِنَّمَا ذَٰلِكُمُ الشَّيْطَانُ يُخَوِّفُ أَوْلِيَاءَهُ فَلَا تَخَافُوهُمْ وَخَافُونِ إِن كُنتُم مُّؤْمِنِينَ
‹‹እንዲህ የሚላችሁ ሰይጣን ብቻ ነው፡፡ ወዳጆቹን ያስፈራራችኋል፡፡ አትፍሩዋቸውም፡፡ ምእምናንም እንደኾናችሁ ፍሩኝ፡፡ ›› አል-ኢምራን 175
وَإِن يَمْسَسْكَ اللَّهُ بِضُرٍّ فَلَا كَاشِفَ لَهُ إِلَّا هُوَ ۖ وَإِن يَمْسَسْكَ بِخَيْرٍ فَهُوَ عَلَىٰ كُلِّ شَيْءٍ قَدِيرٌ
‹‹አላህም በጉዳት ቢነካህ ለእርሱ (ለጉዳቱ) ከእርሱ በቀር ሌላ አስወጋጅ የለም፡፡ በበጎም ነገር ቢነካህ እርሱ በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡ ›› አል አንዓም 17
إِنَّ عِبَادِي لَيْسَ لَكَ عَلَيْهِمْ سُلْطَانٌ ۚ وَكَفَىٰ بِرَبِّكَ وَكِيلًا
«ባሮቼ በእነሱ ላይ ፈጽሞ ላንተ ስልጣን የለህም፡፡ መጠጊያም በጌታህ በቃ፡፡»አል ኢስራእ 65
إِنَّ عِبَادِي لَيْسَ لَكَ عَلَيْهِمْ سُلْطَانٌ إِلَّا مَنِ اتَّبَعَكَ مِنَ الْغَاوِينَ
«እነሆ ባሮቼ በእነሱ ላይ ላንተ ስልጣን የለህም፡፡ ከጠማሞቹ የተከተለህ ሰው ብቻ ሲቀር፡፡»አል ሂጅር 42
አላህ ﷻ በቁርአን እንደነገረን ሰይጣን በመልካም ባሮች ላይ ምንም ስልጣን አና አቅም እንደለለው እና በአላህ ፍቃድ እንጂ መጉዳት እንደማይችሉ ማመን እና መገንዘብ ይኖርብናል፡፡
• ጂኖዎች የሚያደርሱት ጉዳት
ጂኖች በሰዎች ላይ የተለያዩ ጉዳቶች ማድረስ ይችላሉ ይህ ስንል ግን በአላህ ፍቃድ እንጂ ምንም አይነት ጉዳት ሊያደርሱ አይችሉም፡፡
• ከትክክለኛው መንገድ ማጥመም ፡-
የሰው ልጆችን ትክክለኛውን መንገድ(ኢስላምን) እንዳይዙ፣አላህን በብቸኝነት እንዳያመልኩ በተለያዩ አቅጣጫ በመምጣት ያሳስታሉ ይህም ዋነኛ ስራቸው ነው፡፡ሸይጧን እንዲህ ሲል ነበር የፎከረው
قَالَ رَبِّ بِمَا أَغْوَيْتَنِي لَأُزَيِّنَنَّ لَهُمْ فِي الْأَرْضِ وَلَأُغْوِيَنَّهُمْ أَجْمَعِينَ إِلَّا عِبَادَكَ مِنْهُمُ الْمُخْلَصِينَ
‹‹ኢብሊስ) አለ «ጌታዬ ሆይ! እኔን በማጥመምህ ይኹንብኝ ለነርሱ በምድር ላይ (ኀጢአትን) እሸልምላቸዋለሁ፡፡ ሁሉንም አጠማቸዋለሁም፡፡ከነርሱ ፍጹሞቹ ባሮችህ ብቻ ሲቀሩ፡፡» አል-ሂጂር 39-40
قَالَ فَبِمَا أَغْوَيْتَنِي لَأَقْعُدَنَّ لَهُمْ صِرَاطَكَ الْمُسْتَقِيمَ ثُمَّ لَآتِيَنَّهُم مِّن بَيْنِ أَيْدِيهِمْ وَمِنْ خَلْفِهِمْ وَعَنْ أَيْمَانِهِمْ وَعَن شَمَائِلِهِمْ ۖ وَلَا تَجِدُ أَكْثَرَهُمْ شَاكِرِينَ
‹‹ስለአጠመምከኝም ለእነርሱ በቀጥተኛው መንገድ ላይ በእርግጥ እቀመጥባቸዋለሁ» አለ፡፡«ከዚያም ከስተፊቶቻቸው ከኋላቸውም ከቀኞቻቸውም ከግራዎቻቸውም በእርግጥ እመጣባቸዋለሁ፡፡ አብዛኞቻቸውንም አመስጋኞች ኾነው አታገኛቸውም» (አለ)፡፡ ›› አል-አዕራፍ 15-17
• አካላዊ ወይም ስነ ልቦናዊ ጉዳት ማድረስ፡-ጂኖች በሰዎች ላይ አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ ፡፡ ለምሳሌ
-ሀይለኛ ፍርሀት መልቀቅ፡፡
-ብዥታ እና ማስመሰል፡፡
-ስዎችን ማጣላት እና ማለያየት በተለይ ባል እና ሚስት፡፡
-ጭንቀት፡፡
-ማሳበድ፡፡
-የሚጥል በሽታ፡፡
-የሰውነት ክፍሎችን ሸባ ማድረግ ለምሳሌ እጅ እና እግር፡፡
-መካንነት እና ግዜውን ያልጠበቀ ደም መፍሰስ፡- ከወር አበባ እና ከወሊድ ዉጭ ደም መፍሰስ፡፡
• በንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ፡-ቤት ማቃጠል፣ድንጋይ እና ሌሎች ነገሮችን ወደ ሰዎች ቤት በመወርወር ሰዎችን ማወክ ወዘተ…፡፡
• ጂኖች ለምን ሰዎችን ያጠቃሉ
• ጂኖች ሰዎችን በተለያዩ ምክንያቶች ሊያጠቁ ይችላሉ፡-
- ሰዎች በቢድዓ እና ሺርክ ሲዘፈቁ ፡- ሰዎች በሽርክ እና በቢድዓ ምክንያት በጂን ሊጠቁ ይችላሉ ለምሳሌ ከአላህ ውጭ ለሆነ አካል ማረድ ለጂን፣ለቀብር እና ለመሳሰሉት፤ በተጨማሪም ለጂኖች ሲሰግዱ እና ዛር ቆሌ እያሉ የተለያዩ ሽርክ እና ሀራም የሆኑ ነገሮችን ሲፈፅሙ ጂኖች በሰዎቹ ላይ አቅም ይኖራቸዋል በመጨረሻም ሊያጠቋቸው ይችላሉ፡፡
- ከሰው ጋር ፍቅር ስይዛቸው፡- ጂኖች ከሰው ጋር ፍቅር ልይዛቸው ይችላል ለምሳሌ ወንድ ጂን ከሰው ሴት እና ሴት ጂን ከሰው ወንድ ጋር ፍቅር ሊይዛቸው ይችላል፤ በዚህ ግዜ ካፈቀሩት ሰው አካል በመግባት ሰውየውን ሊያጠቁት ይችላሉ፡፡
-ያለ ምክንያት ሰዎችን ሊያጠቁ ይችላሉ፡፡
- በቀል፡- ሰዎች በጂኒዎች ጉዳት ሲያደርሱ ጂኒዎች ሊበቀሉ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ ቢስሚላህ ሳይል ሙቅ ዉሃ ማፍሰስ፣ጉድጓድ ላይ መሽናት፣ቢስሚላህ ሳይል ከፍታ ካለው ቦታ ላይ መዝለል እና በነዚህ ቦታዎች ላይ ጂኒዎች ቢኖሩ በሰውየው ላይ ጉዳት ሊያደርሱ ይችላሉ፡፡
-ሀራም ላይ መዘፈቅ፡-ለምሳሌ ሀራም የሆነ የፍቅር ግኑኝነት መመስረት፣ አጅነቢ ከሆኑ ተቃራኒ ፆታዎች ጋር አላስፈላጊ መግባባቶች እና ግኑኝነቶች፡፡
• በጂን የተያዘ ሰው የሚያሳየው ምልክት
• በንቃት ግዜ የሚያሳየው ምልክት፡-
-ቁርአን ሲቀሩ ወይም ሲሰሙ መተኛት፣ የድብርት እና የህመም ስሜት የሚሰማን ከሆነ
ወይም መጨነቅ እና ቁርአንን መጥላት፡፡
-ዒባዳ ስያደርጉ መሳነፍ እና የድብርት ስሜት የሚሰማን ከሆነ፡፡
-የባህሪ ለውጥ ማሳየት መነጫነጭ፣በጣም መቆጣት እና መናደድ፡፡
-ያለ ምክንያት መፍራት፣ማልቀስ፣መጨነቅ፡፡
-ሸባ መሆን(ሜዲካል ምክንያት ሳይኖር) እጅ፣ እግር ወይም ሌሎች የሰውነት ክፍል፡፡
-ለሴት ደም መፍሰስ ከወር አበባ ውጭ
-ቋሚ የሆነ የራስ ምታት(ሜዲካል ምክንያት ሳይኖር)
https://t.me/Hassendawd
-መፀዳጃ ቤት ለረጂም ስኣታት ቁጭ ማለት
-ብቸኝነት መውደድ
-ያለ ምክንያት ሰውን መጥላት ወዘተ…
-በእንቅልፍ ግዜ የሚያሳየው ምልክት
-በተደጋጋሚ የሚያስፈራ ህልም ማየት እና መቀባዠር፡- የሚያሥፈሩ ነገሮችን ማየት ለምሳሌ እባብ፣ትላልቅ አስፈሪ ነገሮችን ማየት፣ከከፍተኛ ቦታ መውደቅ፣ በህልሙ/ሟ በተደጋጋሚ የሚያስፈራት/ው ሰው ማየት(ጂኖች ሰዎችን ስያፈቅሩ የሚከሰት ነው) ማለትም በህልም በተደጋጋሚ ግኑኝነት ማድረግ ፡፡
 እነዚህ ምክንያቶች ያሉት ሰው ሁሉ በጂን ተይዟል ማለት አይደለም በሌሎች ምክንያቶች ሊከሰቱ ይችላሉ፡፡