መንፈስቅዱስ 😭
9.75K subscribers
201 photos
376 videos
9 files
755 links
Follow us on :-tiktok.com/@halwot5
https://www.instagram.com/@halwot5
https://www.youtube.com/@HALWOT5
“ሁሉም በመንፈስ ቅዱስ ተሞሉ፤ መንፈስም እንዲናገሩ በሰጣቸው መጠን በሌሎች ቋንቋዎች ይናገሩ ጀመር።”
— ሐዋርያት 2፥4 (አዲሱ መ.ት)
🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥🔥
Download Telegram
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2ኛ ተሰሎንቄ 3:3

ጌታ ግን ታማኝ ነው እርሱም ያበረታችሇል ከክፉውም ይጠብቃችሇል
እ/ር ለተናገረው ቃል ሁሌም ታማኝ ነው ነገር ግን ሁኔታዎቻችን ይህን ላይነግሩን ይችላሉ ዛሬ ማለዳ ግን የጌታን ታማኝነት እናውጅበታለን!!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
እስቲ ዛሬ ምሽት ጌታ ያደረገልንን እያስታወስን ሰበብ እየፈለግን እየፈላለግን ጌታን እናመስግነው እናክብረው ይህን ጊዜ የጠላት ሃሳብ ይበተናል በጠላት መንደር ዋይታ ይሆናል እናም ያልተደረገልንን ትተን የተደረገልንን ነገር እየቆጠርን እናመስግነው ጌታን አንድ ነገር ልንገራችሁ እ/ርን ብናመሰግነውም ባናመሰግነውም የሚጨመርለትም የሚጎልበትም ክብር የለም ስናመሰግን ግን እ/ር ለኛው ፀጋን ያበዛልናል ድል ይሆንልናል ስለዚህ እንዲህ እንላለን-ተመስገን!!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ✝️📯•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•🍁☪️
<<ትምህርተ ሥላሴ እና የቤተክርስቲያን ታሪክ>>
ክፍል አንድ(፩)

በመጀመሪያ ይህን ክፍል ለማጥናት ምሥጢረ ስላሴ ምን ማለት ነው!?

🚩የትምህርተ ሥላሴ ቀዳማይ አመንጪ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። አንዳንድ ሥላሴን ስሩን ሳይዙት ዕውቀን ጨርሰናል በማለት ሲናገሩ አስተውያለሁ በዕውነቱ ያሳዝናል ለዚህም ነው በተለይ በአባቶች መምህራን የምሥጢረ ሥላሴ በስፋቱና በትልቅነቱ ሲነገርም እንዲህ ይባላል ፦

<<ምሥጢረ ሥላሴን ጠልቆ ለማወቅ መሞከር ባሕረ ውቅያኖስን በዕንቁላል እየቀዱ ለመጨረስ እየጨለፉም ለመጨለጥ እንደ ማሰብ ነው ይላሉ>>...እውነት ነው፤ ለሰው ከተሰጡ ስራዎች ምሥጥረ ሥላሴን ከመመርመር የሰፋና እና የከበደ የለም።

➝ ሆኖም ስለ ሥላሴ በትክክል ማሰብ ለክርስቲያናዊ ኑሮ ዋንኛ ነገር መሆኑን አንባቢ ልብ ይበል።...አይሁድ፣ ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች አንድን አምላክ ሲያመልኩ፥ የሥላሴን ትምህርት በአንድ አምላክ ከሚያምኑ ሌሎች ሁሉ ክርስቲያኖች ይለዩዋቸዋል።..ስለዚህ ክርስቲያን ለራሱ ብቻ ሳይሆን የራሱን እምነት ለሌሎች ለመግለጥም የሥላሴን ትምህርት ማወቅ ይገባዋል።..

➝ሥላሴ የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን
አይገኝም።...በግእዝ ቋንቋ ቃሉ <<ሦስትነት>> ማለት ነውና በትምህርተ መለኮት ጥቅም ላይ ሲውል..በአንዱ እግዚአብሔር ሦስት አካላት እንዳሉ ያሳስባል።

🚩በ2ኛው መቶ ዓመት የአንጾኪያ ጳጳስ የነበረው ቴዎፍሎስ በግሪክ ቋንቋ <<ትሪአስ>> እና ጠርጡሊያን በላቲን ቋንቋ <<ትርንታስ>> በእንግሊዘኛው ደግሞ TRINITY የሚለው ሲሆን፣ ቃሉ "Tri" ወይም "ሦስት" እና "Unity" ወይም "ኅብረት/አንድነት" ከሚሉት ሁለት የላቲን ቃላቶች የመጣና አንድ ቃል ሆኖ በተገናኝ የሚነበብ ("tri" + "unity" ) ነው።(፩)

🚩ሥላሴ የሚለው ቃልና ትምህርቱ <<እንደ መነጥር ሆነው በመፅሐፍ ቅዱስ ያለውን ትምህርት ጉልሕ ሆኖ እንዲታየን ያደርጋሉ እንጂ በእግዚአብሔር ቃል ላይ አዲስን ትምህርት አይጨምሩም።>>...ትምህርተ ሥላሴ ለክርስቲያን ረቂቅ ፍልስፍናም አይደለም። ወደፊት እግዚአብሔር ቢፈቅድ ሥላሴን በደንብ እንመረምራለን....ወደ ዋናው ርዕሴ ወደ ሚያንደረድር ሀሳብ ልመለስ....

🚩ትምህርተ ሥላሴ እንደ አርዮስ ያሉ የመናፍቃን ጥቃት በቤተክርስቲያን ላይ ሲያደርሱ የመጠበቁ ሂደት ውስጥ ትልቅ ድርሻ ከነበራቸው አትናቴዎስ(Athanasius) አንዱ ቢሆንም ርእሰ ጉዳዩን በዳበረ መልኩ የተነተኑት ቀጰዶቃውያን አበው ናቸው።....በመጀመሪያ ከዛ በፊት <<ቀጰዶቃውያን>> አበው እነማን ናቸው የሚለውን በጥቂቱ እንመልከት...

ቀጰዶቃውያን አበው(Cappadocian Fathers) የሚባሉት ውስጥ፦
1, የቂሳርያው ትልቁ አባት ባልዮስ( Basil The Great)
2, ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ(Gregory of Nazianzus)
3,ጎርጎሪዮስ ዘኑሲስ (Gregory Nyssa) ናቸው።.ከላይ እንዳልኳቹህ እንደ እግረ መንገድ ዳሰሳ አደረግን እንጂ.ወደፊት በስፋት እንመለከተዋለን..

🚩ትምህርተ ሥላሴ በቤተክርስቲያን ታሪክ ቅድመ ጉባኤ ኒቂያ አበው ግንዛቤአቸው ምን ነበር!?

ከላይ እነዳየነው ሥላሴ የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን ባይገኝም ትምህርተ ሥላሴ የነገረ መለኮት ዐብይ ርዕስ መሆኑን አይተናል።...የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ምን ያህል ትምህርተ ሥላሴን እንደተረዱት ባናውቅም ግን፥ << እግዚአብሔር ሦስት አካላት እንዳሉ አምነው የመለኮትን አንድነትንና የአካል ሦስትነትን ለትምህርታቸው መሠረት አደረጓቸው>>.....

🚩 የትምሕርተ ሥላሴ ቀዳሚ አመንጪ መጽሐፍ ቅዱስ ቢሆንም፣ በሐዋሪያት እግር ስር የተማሩ ቀደምት የሆኑ የቤተክርስቲያን አበው ምን አሉ የሚለውን ጉዳይ መቃኘት፣ የተዛባ የታሪክ መረጃ ያላቸው ሰዎችን ለማቅናት ጠቃሚነት ስላለው ይህ ጽሑፍ ዳሰሳዊ ጥናት ስለሆነ የሁሉንም አበው እማኝነትና ትምህርት በክፍል አንድ በስፋት ማቅረብ ስለማይቻል በተወሰነው እንመለከታለን....

1) ጶሊቃርጶስ (Polycarp) :- በ70ዓ.ም ተወልዶ በ155 ዓ.ም ወይም በ160 ዓ.ም የሞተ፣ የሐዋሪያው ዮሐንስ ደቀ መዝሙር የነበረ እንዲሁም የሰምርኔስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት የነበረ ሰው ነው።..ይህ ሰው ትምህርተ ሥላሴን በተመለከተ እንዲህ ብሏል፦

<<ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ሆይ...ዘላለማዊና ሰማያዊ በሆነ ሊቀ ካህናት በምትወደውና ባከበርኸው ልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለአንተና ለእርሱም እንዲሁም ለመንፈስ ቅዱስ አሁንም ሆነ ለዘላለም ክብር ይሁን>>(፪)

2) ዮስጦስ ሰማዕት (Justin Martyr) ፦ የቤተክርስቲያን አቃቤ እምነት የነበረና የሰማዕትነትን ክብር የተቀናጀው ይህ አባት አባት በ100 ዓ.ም ተወልዶ በ165 ዓ.ም እንደ ሞተ ይገመታል። ይህ አባት ትምህርተ ሥላሴን በተመለከተ እንዲህ ብሏል፦

<<የዓለማት ጌታ በሆነው በእግዚአብሔር በስመ አብ፣ በመድሐኒታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ በውሃ መታጠብን ያገኛሉ>>(፫)

3)አግናጢዮስ ዘአንጾኪያ (Ignatius of Antioch) ፦ የአንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት የነበረና በ98 ዓ.ም ወይም በ117 ዓ.ም እንደሞተ የሚገመት ክርስትናን ከመናፍቃን በመከላከሉ ዙሪያ ብዙ የጻፈ ዐቃቤ ክርስትና ነው። እንዲህም አለ፦

<<በእምነትና በፍቅር፤ በወልድ፣ በአብና በመንፈስ ቅዱስ፤ በመጀመሪያው እና በመጨረሻው፤ ከሚያስደንቅ ጳጳስችሁ ጋር እናም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ካሉ ዲያቆናት ጋር በሚገባ በጠበቀ መንፈሳዊ አክሊል የምታደርጉትን ሁሉ በስጋና በመንፈስ እንዲከናወን በጌታችንና በሐዋርያት ትምህረት እድትጸኑ አጥኑ። ክርስቶስ ኢየሱስ ለአብ በስጋው እንደተገዛለት እናም ሐዋርያት ለክርስቶስ፣ ለአብና ለመንፈስ ቅዱስ እደሚታዘዙ እናንተም ለጳጳሳችሁ እና እርስ በእርሳችሁ ተገዙ(ታዘዙ) በዚያን ጊዜ በስጋችሁም በመንፈሳችሁም አንድነት ይኖራችኋል።>>(፬)

4) ጠርጡሊያኖስ ወይም ተርቱሊያኖስ (Tertullian 160-215) ፦ አፍሪካዊ ዕቃቤ ክርስትና እንዲሁም የነገረ መለኮት ሊቅ ነው። ክርስትናን ከመናፍቃንና ከሌሎች ሐያስያን ለመከላከል ብዙ ጽፎአል፦

<<አብና ወልድ ሁለት ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ደግሞ ሦስት መሆናቸውን እንገልጻለን። የቁጥሩንም ቅድመ ተከተል ከድነት አንጻር ነው....ይህም አንድነትና ሦስትነትን መሠረት አድርጎ ሦስቱንም ማዕከል ያደረገ ነው፤ እነርሱም አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ። [አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ] ሦስት ናቸው....ነገር ግን በባሕርይ ሳይሆን በገጽ፣ በኀይል ሳይሆን ነገር ግን በዐይነት። በባሕርይና (Substance) በኀይል አንድ ናቸው፤ ምክንያቱም አንድ አምላክ ብቻ ስላለና ይህም ባሕርይ፣ ገጽና ዐይነት በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ዙሪያ ያለ በመሆኑ>>(፭)

5) አርጌንስ (Origen 185-254) ፦ የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን የነገረ መለኮት ምሁር ነው። አርጌንስ ክርስትናን በተመለከተ ብዙ የጻፈ ነው፦

<<የእግዚአብሔር ቃል ወይም የእግዚአብሔር ጥበብ ጅማሬ አለው የሚል ማንኛውም ሰው፣ ቢያንስ እግዚአብሔርን መናቁ እንደሆነ ልብ ሊለው ይገባል...ምክንያቱም እግዚአብሔር ባለፉት ዓመታት ሆነ ዘመናት ከዚህ ውጪ ሊገመት በሚችልበት ጊዜ ሁሉ፣ እግዚአብሔር የጥበብ ባለቤት ነውና ይህ እውነት ለእግዚአብሔር አብ እንደሆነው ሁሉ ለወልድም ነው>>(፮)
Forwarded from ✝️📯•እውነት እውነቱንᴼᵀᶜ•🍁☪️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
መንፈስ ቅዱስ ዓለምን እና ሕያዋን ፍጥረታትን ሁሉ ሲፈጥር ተካቷል (ዘፍ 1፡2፤ ኢዮብ 33፡4፤ መዝሙር 104፡30)።

መንፈስ ቅዱስ የቅዱሳት መጻሕፍት ጸሐፊዎች የእግዚአብሔርን ቃልና ተግባር እንዲመዘግቡ አነሳስቷቸዋል (2ኛ ጴጥ 1፡21፤ 2 ጢሞቴዎስ 3፡16)።

መንፈስ ቅዱስ ለአገልግሎቱ፣ ለሞቱ እና ትንሳኤው ኢየሱስ ክርስቶስን ኃይል ሰጥቶ ቀባው (ኢሳ 61፡1፣ ሉቃስ 4፡18፣ ሐዋ. 10፡38፣ ሮሜ 1፡4)።

መንፈስ ቅዱስ ስለ ኃጢአት፣ ጽድቅ እና ፍርድ ዓለምን ይወቅሳል፣ እናም ሰዎችን ወደ ንስሐ እና በኢየሱስ ክርስቶስ እምነት ይስባል (ዮሐንስ 16፡8-11፤ የሐዋርያት ሥራ 2፡37-38)።

መንፈስ ቅዱስ አማኞችን በተለወጡ ጊዜ ያድሳል፣ ያጠምቃል፣ ያድራል፣ ያጠምቃል፣ ይሞላል እና ስጦታ ይሰጣል (ኤፌሶን 5:18፣ 1 ቆሮንቶስ 12:4-11)

መንፈስ ቅዱስ ያስተምራል፣ ይመራል፣ ያጽናናል፣ ይመክራል፣ ይማልዳል፣ ይከራከራል፣ እና አማኞች ከእግዚአብሔር ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ሲያድጉ ይመሰክራል (ዮሐ. 14:26፤ ዮሐንስ 16:13፤ ዮሐንስ 14:16፤ ሮሜ 8:26-27) (ዮሐንስ 15:26)

መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ሕይወት ውስጥ የእግዚአብሔርን ባሕርይ የሚያንጸባርቅ ፍሬ ያፈራል (ገላ 5፡22-23)።

መንፈስ ቅዱስ አማኞችን ለአገልግሎት፣ ለአገልግሎት፣ ለመመስከር እና ለተልእኮ ኃይል ይሰጣል (ሐዋ. 1፡8፤ ሮሜ 15፡19፤ 1 ቆሮንቶስ 2፡4-5)።

               ⚜️@HALWOT5⚜️
             
⚜️ @HALWOT5  ⚜️
       
🎯     ♡         ❍ㅤ      ⎙ㅤ  ⌲ 
       ʲᵒᶦⁿ    ˡᶦᵏᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃ
የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በድምቀት ልናከብር ጥቂት ቀናት ብቻ ቀርቶናል🤩

🔥ግን የቴሌግራም ቻናሎች ከ አሁኑ በዓሉን ድምቅ ማረጉን ተያይዘውታል🤩🤩
ያው ቻናሎቹን የተቀላቀላቹ ታውቁታላቹ😍

ያልተቀላቀላቹ ካላቹ "እሺ" በሉኝ እና ተቀላቀሉ በዓልን አብረን ፏ ብልጭ እንበል🥳🤩
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM