Halal Fkr
13.6K subscribers
249 photos
168 videos
3 files
720 links
Elegant. Faithful. Halal.


Tiktok: http://tiktok.com/@halal_discuss
Download Telegram

እኛ... ካስለመድከን የፍቅር እንክብካቤ ጥቂቱን ያጣን ጊዜ ደርቀን የምንቀር እንቡጥ አበቦች ነን...! ∞

الله..💜
❤‍🔥3416😍4💔3
በስጋዊ የመሻት ክበብ፣በምኞት ፍርግርግ ታዛ ውስጥ ታጉረው በመባትል የታለፉ መዓልቶችን ለብክነት አልተውክም። በገዛ ክዋኔያቸው ለለመሹ ጉልበቶች እንኳን ተብረክርከው እንዲወድቁ አልፈቀድክም። ነፍስም ወደ ፍቅርህ ጎራ ተቅጣጭታ፣ የጥረት እርምጃዋን ያነሳች ጊዜ መክነፍን ታድላለህ…!

الله..💜
🔥1910❤‍🔥4
ሴቶች መስማት የሚፈልጉት

« ለሚስትህ አይፎን 17 ከገዛህላት ከአንደኛው ሰማይ እሰከ ሰባተኛው ሰማይ ያሉ መላእክት ይወዱሀል »


ሴቶች👏👏👏👏👏👏👏

ሴቶች መስማት የማይፈልጉት

« ልብስሽን ሂጃብሽን አስተካክይ »

ሴቶች 😭አላህ የቀልብን ነው የሚያየው
🤣5211👍7
"አግብተሀል?" አለኝ ጠዋት የወሰድኩት ሰውዬ~

"አይ አላገባሁም"

"ስትበስል አግባ"

"እሺ! መብሰል ማለት ብዙ ነገር ነው አይደል?"
¤
"በመኪና ስትሄድ 'ወራጅ' ትላለህ። በፕሌን ስትሄድ ግን 'ወራጅ' አትልም። እና ትዳር በፕሌን መሄድ ስለሆነ አውቀህ ግባ!
እሱ ነው የሚጥመው! ከነምናምኑ ስትኖረው ነው ትዳር ማለት! ይሄን ያወቅኩት አንብቤ ነው፤ በሗላ ግን ኖርኩት" ~ ብሎ አስረዳኝ። እና ሌላም ሌላም አሳወቀኝ።

ስለመከረኝ ይቅርታም ጠየቀኝ፥ በተቃራኒው ተቆጣሁት።
54🥰2❤‍🔥1😭1
ብዙ ሴት እህቶቻችንን የሚያመሳስላቸው መጥፎ ባህሪ  victim mentality ( የተጠቂነት ስሜት ) ነው።
(ብዙ እና ሁሉም የሚለው መካከል ያለውን ልዩነት የማትረጂ ከሆነ ፅሁፌን ጨርሰሽ እንዳታነቢ ፥ ~
¤
በሆነው ባልሆነው እራሳቸውን ተጠቂ በዙርያቸው ያለውን ሁሉ ደግሞ (ሴቱንም ወንዱንም) አጥቂ የሚያስመስሉ ሴቶች ቁጥር ቀላል አይደለም።በድለው ሲያበቁ ሮጠው የተበዳይን ካርድ ይመዛሉ። አጥፍተው ሳለ ይቅርታ እንዲጠየቁ እንጂ መጠየቅን ፣ጥፋትን ማመን … በዲክሽነሪያቸው ውስጥ የለም ።


ከዚህ ጋር በተያያዘም ባልተያያዘም …
ቅድም አንድ ጓደኛዬ የሆነን ሰው ገጠመኝ ነገረኝ ።ሰውየው ሊያገባ ብሎ የሆነችን ልጅ አየ ። ከዚያም ረሱል ﷺ እንደተናገሩት “ ስታያት የምታስደስትህ “ የተባለችው ዐይነት ስላልነበረች እንዳልተመቸው አሳውቆ መንገዱን ቀጠለ ልጅት ደግሞ “ የተከፈተ አይመለስም “ የሚለው የነጋዴዎች ቀልድ እዚህም የሚሰራ መስሏት ነው መሰለኝ “ ለምን አይቶኝ ተወኝ “ በሚል እየዞረች ስሙን ታጠለሽ ይዛለች ።
¤
ሰዎች እንዴት እንደሚያስቡ ይደንቃል ። አይቶሽ “ ተመችተሽኛል ይሁን “ አልያም “ አልተመቸሽኝም ይቅር “ የሚል ምርጫ ከሌለው ቀድሞውኑ ለምን ያይሻል ። እስከነ ኒቃብሽ አግብቶሽ የሰርጋችሁ ምሽት ላይ blind buy unbox ለምን አያደርግም ?
¤
የመታየትሽ ትርጉሙ ትመቺኛለሽ አልያም አትመቺኝም የሚለውን ለመወሰን አይደለምን ? ሸሪዐው የሰጠውን “ የሚመቸውን የመምረጥ መብት “ ለምን መጋፋት ዳዳሽ ?
¤
በራስ የመተማመን ክፍተትሽን በሰዎች ስም እና ስብዕና ላይ በመዝመት ለመጠገን አትሞክሪ ። ነውር ነው አማኝም አስተዋይም እንደዚህ አያደርግም ። እኛ ምርጫ እንዳለን ሁሉ ሌላውም ሰው ምርጫ እንዳለው ማመን እና መቀበል የበሳሎች መገለጫ ነው ።
¤
ድህነት ጋር ግብግብ ገጥመው ላሉ ሚስኪን ወጣት ወንዶች ምንም ዐይነት ርህራሄ ሳታሳዪ ነው በልበ ሙሉነት “ ሀብታም ካልሆነማ እንደዚ ይሁን እንደዚያ ገደል ይግባ “ ምናምን የምትዪው ። ስለቁመት እና ጠይምነት ( ቁመት ምን እንደሚያደርግላችሁ እንጃ 😀 ) ፣ ስለቦርጭ እና መላጣነት ስታነሺም እኚህ ነገሮች ላሉባቸው ወንዶች ሞራል ሽርፍራፊ ጥንቃቄ አታደርጊም ። ጉዳዩ አንቺ ጋር ሲመጣ ደግሚ ሌላ ታሪክ …
¤
ለማንኛውም አላህ በተከበረው ቃሉ የራሳቸውን መብት እና ጥቅም በማስጠበቅ ላይ እጅግ ብርቱ በተቃራኒው ደግሞ የሰዎች መብትና ሀቅ ላይ መጋኛ የሆኑ double standard  ሰዎችን እንዲህ ሲል አስጠንቅቋል

“ ለሰላቢዎች ወዮላቸው ። [] ለእነዚያ ከሰዎች ባስሰፈሩ ጊዜ የሚያስሞሉ ፡፡ [] ለእነርሱም (ለሰዎቹ) በሰፈሩ ወይም በመዘኑላቸው ጊዜ የሚያጎድሉ (ለኾኑት)፡፡ “
( ሱረቱ አል ሙጠፊፊን 1-3 )
26👍12🥰5😭4
ህይወትና ቀንህ እንዲያምር ከፈለክ stay Positive ይላል ፐረንጅ y'll positive life is really beautiful ቢመሽ ቢነጋ ብታገኝ ብትከስር ህይወት ትቀጥላለች።
ከመኖር ብንጎድል እነገሌ ጎደሉ ተብሎ የሚቆም ሲስተም የለም።ለሰውም ለራስህም ኑር ራስህ ላይም ስራ።

ከቤትህ በሐቅ~ውጣ፤ ቀንህን በፈገግታ ጀምር መነሻ ፈገግታ ከሰዎች አትጠብቅ። መጠበቅ ሲገል ሲያጎድል እያየን ነው።
መልካም ቀን🖤
❤‍🔥21👍135🫡1
ሁሌም በጣም ከሚገርሙኝ የቁርዓን ምዕራፎች መካከል አንደኛው (ሱረቱል አዲያት) ነው። አላህ እዚህ ሱራ ላይ እንዲህ ብሎ በፈረሶች ይምላል...

                                                  وَالْعَادِيَاتِ ضَبْحًا
                          
እያለከለኩ ሯጭ በኾኑት (ፈረሶች) እምላለሁ፡፡

አላህ የማለው ዝም ብለው በቆሙ ፈረሶች አይደለም፤ በከፍተኛ ሩጫ ከመጋለባቸው የተነሳ ደረታቸው ተቃጥሎ ማለክለካቸው በደንብ እስኪሰማ ድረስ በሚተጉ ፈረሶች ነው።
                                            
فَالْمُورِيَاتِ قَدْحً
ሸኮናቸው እያጋጩ እሳትን አውጪዎች በኾኑትም፤

ፍጥነታቸውና ጥንካሬያቸው እጅግ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ፣ ኮቴያቸው ከመሬት እና ከድንጋይ ጋር ሲጋጭ ብልጭታን ወይም እሳትን በሚፈጥሩ ፈረሶች...
                                                 
                                                          فَالْمُغِيرَاتِ صُبْحًا
                                  
በማለዳ ወራሪዎች በኾኑትም፤

​እነዚህ አላህ የማለባቸው ፈረሶች ለጨዋታ አይደለም እንደዛ በፍጥነት የሚሮጡት በጦርነት መካከል ውስጥ ሆነው ነው። ስለዚህ አደጋ ላይ መሆናቸውን ያውቃሉ።

                                                         فَأَثَرْنَ بِهِ نَقْعًا
                                   
  በእርሱ አቧራን በቀሰቀሱትም፤

ከሩጫቸው ብዛት በቦታው ላይ አደገኛን አቧራ ቀስቅሰው ፈረሶቹ የሚተነፍሱት አየር እራሱ ከአቧራ ጋር የተቀላቀለ በሆኑ።

                                                  فَوَسَطْنَ     بِهِ جَمْعًا                      
   በጠላት ክብ መካከል ገብተው በተጋፈጡት እምላለሁ፤

አደገኛ መሆኑን እያወቁ...ሞት መኖሩን እያዩ በጠላት ጦር መሃል ሰንጥቀው በሚገቡ ፈረሶች ይምላል። አላህ በነዚህ ፈረሶች ከማለ ብኋሏ ቀጣዩ አንቀፅ ላይ እንዲህ ይላል...

            إِنّ الْإِنسَانَ لِرَبِّهِ لَكَنُودٌ

                            
ሰው ለጌታው በእርግጥም ብርቱ ከሓዲ ነው፡፡

¤

አላህ ከዚህ አንቀፅ በፊት ስለ ብርቱ ፈረሶችን ምሳሌ አድርጎ ከጠቀሰ ብኋላ፣ ለምንድነው ስለኛ ስለሰው ልጆች ባህሪ መናገር የፈለገው? ምክንያቱም የማለባቸው ፈረሶቹ ይሄንን ሁሉ መስእዋትነት የሚከፍሉት ለሚመግባቸው ለሚንከባከባቸው አሳዳሪያቸው ነው። ለዛ ውለታም ያላቸውን ታማኝነት ያለ ፍርሃት ሞትን እስከመጋፈጥ ድረስ በመሄድ ምስጋናቸውን ያቀርባሉ።
የሰው ልጅ ግን በእርሱ ላይ ያለውን የአላህን ፀጋ ይረሳል።
በአጠቃላይ ይህ ሱራ በሁለት ተቃራኒ የታማኝነት አይነቶች ላይ እንድናሰላስል ያደርገናል። በአንድ በኩል ለጥቂት ምግብና እንክብካቤ ሲል እስትንፋሱ እስኪቆራረጥ ድረስ የሚሮጥ፣ ኮቴው እሳት እስኪያወጣ የሚጋልብና ወደ ጦርነት መሃል ሰንጥቆ በመግባት ለአሳዳሪው ያለውን ታማኝነት በተግባር የሚያሳይ "ፈረስን" እናያለን። ​በሌላ በኩል ደግሞ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን መለኮታዊ ጸጋዎች እየተመገበ፣ ነገር ግን ለፈጣሪው ምስጋና ቢስ ስለሆነው "የሰው ልጅን" እናገኛለን።

በመልካም መንገድ ወደ አላህ የምንመለስ እና ካመሰጋኝ ባሮቹም የምንሆን ያድርገን። አሚን!
25❤‍🔥8
ለቧሎ እንዲህ አለቺዉ :- ታቃለህ አንተኮ መንግስት ነህ

እሱም አመሰግናለሁ የኔ ዉድ ምክንያቱ ግን ምን ይሆን
አላት..?
እሷም ንጉሶች የሆነን ከተማ ሲገቡ ያበላሾታል
አንተም ቤት ገና ከመድረስህ ቤቱን ትገለባብጠዋለህ ታበላሸዋለህ አለቺዉ....

አብቹ ወደ ኮምቦልቻ አልመጣም መሰለኝ እስኪ የኮምቦልቻ ልጆች ሁለት ትላልቅ መስጂድ ጠቁሙኝ?እንድዘይረው!

----------------------------------------
♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

JOIN US: ❯❯ Halal fkr ♡
14🤣10❤‍🔥2😁2
∞ጨረቃ ታይታለች∞
¤
ወርሃ ዙልሒጃ ገብቷል።
የ10ቱ የዙልሒጃ ቀናት ጾም
ነገ (ሰኞ) ግንቦት10 ቀን 2018 ዓ.ል ጀምሮ
1 ብሎ ይጀምራል።
❤‍🔥187
Sooooooo it is ዙልሂጃህ~ ዙል ሂጃ ደግሞ የ ሰይድና ኢብራሂም ናት ሰይድና ኢብራሂም ደግሞ የኔ favorite ነብይ ናቸው፤ እና እነዚህን 8 ቀናት ስንመሳሰጥባቸው ብንቆይ ምን ይላቿል?

ከ ሰይድና ኢብራሂም አለይሂሰላም ጋር በ ፍቅር ጠብ ካደረገኝ ነገር አንዱ የ ህይወት ፍልስፍናዬን የገነባሁበት አንድ ንግግራቸው ነው። ከ ህዝቦቻቸው ጋር በነበራቸው የሆነኛው ውይይት “ እናንተ በ አላህ እያጋራቹ ያልፈራቹ እኔ እናንተ ምታጋሩትን እንዴት እፈራለው? ከ ሁለቱ ቡድኖች ለ ደህንነት ይበልጥ ተገቢው ማንኛው ነው?” ይሏቸዋል። አምን ( ደህንነት)ን በ አላህ ከማመን ጋር የሚያያይዙበት መንገድ ገርሞኝ ዋው ብዬ ቆም ብዬ አያዋን አስተነተንኩ ሙዕሚን እንዴት ይፈራል? አላህን የያዘ ፣አላህ አለኝ ያለ ሰው ምን ይፈራል? ምን ይረብሸዋል? ምን ሰላም ይነሳዋል? አላህ ያለው ለ ደህንነት የተገባ ነው እያሉ እኮ ነው ብዬ ፈገግ አልኩ፤ ገፁ እዚህ ጋር ያልቃል ልክ ወደ ቀጣዩ ገፅ ስሸጋገር የመጀመሪያው አንቀፅ ላይ አላህ (ሱ ወ) “እነዛ ያመኑ ማመናቸውንም በበደል ያልሸፈኑ ለነሱ አምን ( ደህንነት) አላቸው እነሱ የተመሩም ናቸው” ይላል ፤ oh wait ይህ የ ኢማን እና የ ደህንነት ጉዳይ ከማስበው ፣ የገባኝ ከመሰለኝ እና የ ሰይድና ኢብራሂም አገላለፅ ፈገግ ካስባለኝ በላይ deep ነው።

ደህና መሆን አላህ ለነዛ ላመኑ ሰዎች ቃል የገባው ነገር ነው፤ ሙዕሚን በ ችግር ውስጥ ፣ በ ህመም ውስጥ፣ በ ድህነት ውስጥ፣ በ በላዕ ውስጥ ደህና ነው ሙዕሚን በ ሁሉም ነገር ውስጥ ደህና ነው። ደህና መሆን ማለት አለመፈተን አይደለም በፈተና ውስጥ ግን አላህ የሚሰጠው መረጋጋት እና ውስጣዊ ጥንካሬ አለ። አላስተዋላቹም የቅርብ ሰውን አጥተው ወይ በ ጠና ታመው ወይ ትልቅ ገንዘብ ከስረው ኢናሊላህ ብለው ርግት ብለው ህይወታቸውን የሚቀጥሉ ሰዎች? ሰላልተጎዱ ፣ ስላልታመሙ ፣ ስላላዘኑ እኮ አይደለም ግን አላህ “ለሁሙል አምን” ያለውን አምን በ ውስጣቸው ስላኖረው። ለዚህ እኮ ነው ወላ ተጅዐል ሙሲበተና ፊ ዲኒና የምንለው ፈተናችንን አንተን በማጣት ካንተ በመራቅ አታድርግብን የምንለው ለዚህ ነው ከ አላህ ጋር እስካለን ሁሌም አማን ስላለ፣ አላህን ያገኘ ምንም ስለማያጣ ፣ ከ አላህ ጋር በ ፈተና ውስጥ መፅናኛ ስላለ ነው🤎

አላሁመል አምን ያረብ።
30❤‍🔥11
"ሀኪሞች ፍቅርን ከነፍስ በሽታ ውስጥ ቆጥረውት መድሃኒቱንም ገልፀዋል። እኔ ግን ከፍቅር መዳንን አላህን ከለመንኩኝ አላህ አፊያ አያድርገኝ"

ሊሳኑዲን ኢብኑ ኸጢብ


ሁሉም ለለይላው ያለቅሳል ለይላም ለሌላው ታለቅሳለች

ቀኑ ይለፍ እንጂ ጊዜው ይለፍ እንጂ የሁሉ ለይላ ከደጅ ትጠናለች

#አብሽሩ
----------------------------------------
♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

JOIN US: ❯❯ Halal fkr ♡
❤‍🔥2117😍7
∞ሰበር ዜና∞
ቤተል የሚገኙ የአርሰናል
ደጋፊዎች ተቅዋ መስጂድ ገብተን
አዛን ካላልን እያሉ ነው።
በሰላም አሳድረን።

----------------------------------------
♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

JOIN US: ❯❯ Halal fkr ♡
🤣43😁144🙊3😭2
[ከሱብሒ በፊት የምትሰገደዋ ሁለት ረከዓ ሱና ሶላት~ከዚች አለምና በውስጡዋ ከሚገኘው ፀጋ ሁሉ ትበልጣለች]።

ነብዩ ሙሀመድ ሶለላሁ ዓለይሂ ወሰለም።

----------------------------------------

♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ
❤‍🔥4916🥰4👍3
ከአርሰናል ምን እንማራለን🥲
🤣35🥰73
ጓደኛዬ አልደብቅህም መልፋት ሰልችቶኛል፣
ለማሸነፍ መታገል ሰልችቶኛል፣ረጅም ርቀት መሮጥ ሰልችቶኛል፣ ያለማቋረጥ የምወስዳቸው እቅዶችና እርምጃዎች ሰልችተውኛል፣በህይወቴ ነገሮች በምን ያህል ፍጥነት እየተከሰቱ እንደሆነ ማሰብ ሰልችቶኛል፣እጣ ፈንታ ያላቸው ውሳኔዎች፣ ሃላፊነቶች እና ጫናዎች በጠቅላላ ሰልችተውኛል።ሁሉም ነገር ሰልችቶኛል አንተም እንደደከመህ ይገባኛል።
ነገር ግን እቀጥላለሁ የእረፍቴ ቀን ቅርብ ነው፤ የሞቀ አልጋ አልያም ቀዝቃዛ መሬት!

ወዳጄ….. 7 መውደቅ እንዳለብን ስታውቅ …ድልም በሰባተኛው እንደሆነ ሳይጠፋህ።
¤
አራተኛው ላይ ሲደክምህ ይነደኛል!
¤
አምስተኛም ላይ ተው።
¤
ስድስት ወንድምአለም ስድስት ደርሰናል።
በሰባት እንስቃለን።
¤
እስከዛ ግን “ቆሜ አሳይሀለሁ” ነው ለህይወት መልሳችን።
ቆመን እናሳየዋለን..!!! ኢንሸአላህ!!!                          
24❤‍🔥8🔥5
Audio
Relaxing Rain & Quran for Sleep & Relaxation 🌧️

----------------------------------------
♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

JOIN US: ❯❯ Halal fkr ♡
🥰106👍1
ከፋይዳ ጋር አላገናኘህም ብለው 50 ብሬን አገዷት(አገቷት)... ለሷ ብዪ ባንክ ብሄድ ያላግጡብኝ ይሆን?😭
🤣26😁5
[ሁሉም ሰው ~የራሱ የሆነ የህይወት ፍልስፍና አለው።

የኔ የህይወት ፍልስፍና ግን አንቺ ነሽ
¤
<በድቅድቅ ህላዌ ሞት ባጠላው አለም
ውበት እንደማየት ፍልስፍና የለም!!

ሙክክ🎷
🤣17🥰31👍1
ክንዴ!አለችኝ ...ከወዲያኛው የስልኬ ጫፍ የሴት ድምፅ ይሰማኛል.....አይ ተሳስተሻል ብዬ ስልኩን ዘጋሁ ...ብዙ እንዳታወራ :እንዳትቀባጥር በማሰብ።

መልሳ ደወለች አረ ክንድዬ ምነው ጠፉህብኝሳ አለች አሁንም ገና ማንነቴን እንኳን ሳታጣራ


እንመለስ

ለካስ አንዲት ባሏ የጠፉባት ሴት ቁጥር ተሳስታ ወደኔ ደውላ ኑሯል!

©ABX መፅሀፍ የተወሰደ
🤣17😁52