هذه أبياتٌ للشيخ عمر بامخرمة
عليكَ بشُرْبِ البُنِّ في كلِّ ساعةٍ
ففي شُرْبِها يا صاحِ خمسُ فوائدِ
نَشاطٌ وإهضامٌ وإذهابُ بَلْغَمٍ
ونورٌ لأبصارٍ وعَوْنٌ لعابدِ».
ለቡ/ጠ/ማ
በየሰዓቱ ቡና በመጠጣት አደራ ..!
ቡና ጠጪ ጓድ ሆይ አምስት ጥቅም ታገኛለህ..!
ነቃትን፣ የምግብ መፍጨት ፣የአክታ መወገድ፣የአይን ብርሀን መጨመር ፣ለዒባዳ እገዛን ትሰጣለች።!
----------------------------------------
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
JOIN US: ❯❯ Halal fkr ♡
🤣25❤14😁2👍1👀1
∞ባለቤትሽ በምርጫው የወደደሽ ብቸኛው ሰው ነው∞
¤
አባትሽ የወደደሽ በኃላፊነት ስሜት ነው።
ወንድሞችሽ የወደዱሽ በደም ትስስር ነው።
ልጆችሽ ደግሞ በተፈጥሮ (በደመ-ነፍስ) ይወዱሻል።
¤
ባለቤትሽ ግን ሴቶች በሞሉበት ዓለም ውስጥ ተመልክቶሽ አንቺን መረጠ በአንቺ ላይ አልተጫነም ካንቺ ጋር የመኖር ግዴታ አልነበረበትም ወይም ሲወለድ ከአንቺ ጋር የሚያስተሳስረው የደም ግንኙነት አልነበረም።
¤
ጉድለቶችሽን፣ የባህሪ መለዋወጥሽንና ስህተቶችሽን እያየ የምፈልጋት ሴት እቺው ናት ብሎ ነው ያገባሽ።
∞
ይህ ዓይነቱ ፍቅር ሆን ተብሎ በውሳኔ የሚደረግ ነው ።
እርሱ በየቀኑ ሲነቃ ያንኑ ምርጫውን ይቀጥላል የሚሠራው፣ የሚያስተዳድረውና የሚጠብቅሽ ተገዶ ሳይሆን ሕይወቱን ከአንቺ ጋር መገንባት እንደሚገባሽ ስለወሰነ ብቻ ነው ።
∞
ስለ አንቺ ሲከላከል፣ በሌሊት ወደ አንቺ ሲቀርብ፣
እና በክፉ ወቅቶች (በጭንቅ ቀን) ከአንቺ ጋር ሲቆይ...
ይህ ግዴታ ሳይሆን በየቀኑ የሚታደስ ታማኝነት እና ፍቅር ስላለው ነው ።
∞
ስለዚህ ይህንን መርጦ እና ወዶ የሰጠሽን ፍቅር እንደ ቀላልና እንደተረጋገጠ ነገር አትቁጠሪው ።
∞
∞
ክብሩን ጠብቂ፣ ተንከባከቢው እርሱም መመረጡን እንዲሰማው አድርጊ ተመራጭነት የሚሰማው ወንድ ይበልጥ ጠንካራ፣ ጽኑ እና ታማኝ ይሆናል ።
¤
መጠራጠርን ያቆማል ሳይጠየቅ ብዙ ይሰጣል ቤቱን በጭንቀት ሳይሆን በኩራት ይጠብቃል በስሜትም ከመራቅ ይልቅ ሁልጊዜም በአቅራቢያሽ ይገኛል ።
ባጭሩ የባልሽ ፍቅር ከደም ትስስር በላይ የላቀ ውሳኔ ነውና ልዩ ቦታ ስጪው።

❤46❤🔥12👍9
ነብዩላህ ሙሳ, The big guy, the strong fit man፣ አንበሳው ከሀገራቸው አምባገነኑ የፊርአውንን መንግስት ሸሽተው ተሰደው ሲጓዙ መድየን ወደምትባል ቀበሌ ደረሱ።
∞
መሄጂያም ማረፊያም ያልነበራቸው ስደተኛውና ሙሳፊሩ ነብዩላህ ሙሳ ዛፏ ስር ቁጭ ብለው
¤
ጌታዬ ሆይ እኔ አንተ ወደኔ ላወረድከው በጎ ነገር ከጃይ ነኝ" ሲሉ ዱአእ አደረጉ።
እቺ ዱአእ ስንት ነገር መለሰች]
¤
ስደተኛው፣ ብቸኛው፣ መሄጃ ያጣው ሙሳ አለይሂሰላምም ዛፏ ስር ቁጭ ብለው ያደረጓትን ዱአእ ፍሬ አገኙ።
ቤት.... ስራ....የገቢ ምንጭ.... ሚስት.... ቤተሰብ!

َربِّ إِنِّي لِمَا أَنزَلْتَ إِلَيَّ مِنْ خَيْرٍ فَقِيرٌ" "
¤
ጌታዬ ሆይ እኔ አንተ ወደኔ ላወረድከው በጎ ነገር ከጃይ ነኝ" ሲሉ ዱአእ አደረጉ።
እቺ ዱአእ ስንት ነገር መለሰች]
¤
ስደተኛው፣ ብቸኛው፣ መሄጃ ያጣው ሙሳ አለይሂሰላምም ዛፏ ስር ቁጭ ብለው ያደረጓትን ዱአእ ፍሬ አገኙ።
ቤት.... ስራ....የገቢ ምንጭ.... ሚስት.... ቤተሰብ!
❤31❤🔥8🥰8
~አንድ ሚስት ብቻ~
¤
"ሁለት ሚስቶች ኖሮት ወደ አንደኛዋ ብቻ ያዘነበለ ሰው በትንሳኤ ቀን አንዱ ጎኑ (ትከሻው) የወደቀ (የዛለ) ሆኖ ይመጣል።
ነብያችን ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም (አቡ ዳውድ የዘገቡት ሲሆን አልባኒ ሶሒሕ ብለውታል)
∞
ሸይኽ አል-አልባኒ (አላህ ይዘንላቸውና) እንዲህ ብለዋል፦
"በዚህ ዘመን ከአንድ በላይ ማግባትን አንመክርም ።
∞
ምክንያቱም ይህ በርካታ ጉዳቶች አሉት ይህን ማለታችን 'ከሴቶች ለእናንተ የተዋበላችሁን አግቡ' የሚለውን የአላህን ቃል መቃወም ሳይሆን፤ ይህ ጋብቻ የሚያስከትለው ጉዳቶች በጣም በርካታና የታወቁ ስለሆኑ ነው በጣም አስገዳጅ ሁኔታ ሲፈጠር ካልሆነ በስተቀር በፍጹም ከአንድ በላይ ሚስት አንመክርም ።"
¤
የሐነፊይ መዝሃብ የሕግ ሊቃውንት (ፈቂሆች) — አላህ ለእኛም ለእነርሱም ይዘንላቸውና — እንዲህ ብለዋል፦
"ሚስቱ በሀዘን እንዳትሰበር (እንዳትከፋ) ብሎ በላይዋ ላይ ሌላ ማግባትን የተወ ሰው አላህ ዘንድ ምንዳ (አጅር) አለው።"
¤
እንዲሁም የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) አሊይ (ረዲየላሁ ዐንሁ) በልጃቸው በፋጢማ (ረዲየላሁ ዐንሃ) ላይ ሌላ ሴት ሊያጩ መሆኑን በሰሙ ጊዜ ተቆጥተው እንዲህ ብለዋል፦
∞
"ፋጢማ የኔ አካል ናት፤ እርሷን የሚያስከፋት ነገር እኔንም ያስከፋኛል።

❤36🥰8👍7❤🔥5🙉1
∞አንድ ፅኑ እምነት አለኝ ... "ሸሪዓ" ሙስሊሙን ሊያሰለጥን.. ሊጠቅም.. አንድ ሙስሊም ዱንያዊ ሐያቱን መስመር ሊያሲዝበት..ነፍሱን ሊገራበት...በ"ሸሪዓ" ከማይተዳደሩ የአደም ዘሮች ልቆ ሊወጣበት ሊፈካበት እንጂ አላህ አልደነገገውም።
¤
"ሸሪዓ" በወቅት መቀያየር ከፍ ዝቅ የማያደርግ..የማይጎዳ.. ወደ ኋላ የማያስቀር..የሰው ልጅ ለፈጠራቸው ርዕዮተ አለማዊ መተዳደሪያዎች ተገዥ የማይሆን (እነሱን ልቆ በመገኘት) ..
የመሰልጠን ምንጭ..የስልጣኔዎች መመዘኛ የሆነ... የአላህ መለኮታዊ እና የማይሻር ህግ ነው ።
¤
በሸሪዓ ላይ ሌላኛው ፅኑ እምነቴ ....የሰው ልጅ አረዳድ እና ግንዛቤ ይሳሳታል እንጂ በፍፁም መለኮታዊ ህጉ አይሳሳትም። አንድ ሙስሊም "ሸሪዓ" ብሎ የያዘው መተዳደሪያ ህግ ወደኋላ ካኮሰሰው ...ለሌሎች ሰዋዊ ህጎች ባርያ እንዲሆን ካመቻቸው...ተገልጋይነቱ ቀርቶ የሌሎች መገልገያ ካደረገው "ሸሪዓ" ብሎ የያዘውን መተዳደሪያ ህግ መለስ ብሎ ሊያጤነው ይገባል። ምክንያቱም የሱ "ሸሪዓ" ሚናውን እየተወጣ አይደለምና።
∞
መለኮታዊ ህጉ (ሸሪዓ) ሚናው አንተ ላይ ካልሰራ ከአረዳድህ እንጂ ከህጉ ጉድለት ወይህም ስህተት እንደሌለበት መገንዘብ ይገባሃል። የራስህ አረዳድ ከሌለህና በሆኑ ግለሰቦች አረዳድ የምትጓዝም ከሆነ መለስ ብለህ ያንን ማጤንም ይገባሃል።
---------_-----_-----____---

❤24👍8
«...ልቡ እንዲከፈትለት...ወንጀሉ እንዲማርለት... ችግሩ እንዲነሳለት ...ጭንቁ እንዲወገድለት... የፈለገ ሰው በሰይዳችን ላይ አብዝቶ ሶለዋት ያውርድ..»
ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ )
አላሁመሶሊ ዐላ ሰዪዲና ሙሐመድ...ወዓላ ዓሊ ሰዪዲና ሙሐመድ።
ኢብኑል ቀይም (ረሂመሁላህ )
አላሁመሶሊ ዐላ ሰዪዲና ሙሐመድ...ወዓላ ዓሊ ሰዪዲና ሙሐመድ።
❤46❤🔥11
∞
እኛ... ካስለመድከን የፍቅር እንክብካቤ ጥቂቱን ያጣን ጊዜ ደርቀን የምንቀር እንቡጥ አበቦች ነን...! ∞
الله..💜

❤🔥34❤16😍4💔3
በስጋዊ የመሻት ክበብ፣በምኞት ፍርግርግ ታዛ ውስጥ ታጉረው በመባትል የታለፉ መዓልቶችን ለብክነት አልተውክም። በገዛ ክዋኔያቸው ለለመሹ ጉልበቶች እንኳን ተብረክርከው እንዲወድቁ አልፈቀድክም። ነፍስም ወደ ፍቅርህ ጎራ ተቅጣጭታ፣ የጥረት እርምጃዋን ያነሳች ጊዜ መክነፍን ታድላለህ…!
الله..💜
الله..💜
🔥19❤10❤🔥4
ሴቶች መስማት የሚፈልጉት
« ለሚስትህ አይፎን 17 ከገዛህላት ከአንደኛው ሰማይ እሰከ ሰባተኛው ሰማይ ያሉ መላእክት ይወዱሀል »
ሴቶች👏👏👏👏👏👏👏
ሴቶች መስማት የማይፈልጉት
« ልብስሽን ሂጃብሽን አስተካክይ »
ሴቶች 😭አላህ የቀልብን ነው የሚያየው

🤣52❤11👍7
"አግብተሀል?" አለኝ ጠዋት የወሰድኩት ሰውዬ~
"አይ አላገባሁም"
"ስትበስል አግባ"
"እሺ! መብሰል ማለት ብዙ ነገር ነው አይደል?"
¤
"በመኪና ስትሄድ 'ወራጅ' ትላለህ። በፕሌን ስትሄድ ግን 'ወራጅ' አትልም። እና ትዳር በፕሌን መሄድ ስለሆነ አውቀህ ግባ!
እሱ ነው የሚጥመው! ከነምናምኑ ስትኖረው ነው ትዳር ማለት! ይሄን ያወቅኩት አንብቤ ነው፤ በሗላ ግን ኖርኩት" ~ ብሎ አስረዳኝ። እና ሌላም ሌላም አሳወቀኝ።
ስለመከረኝ ይቅርታም ጠየቀኝ፥ በተቃራኒው ተቆጣሁት።

❤54🥰2❤🔥1😭1
ብዙ ሴት እህቶቻችንን የሚያመሳስላቸው መጥፎ ባህሪ victim mentality ( የተጠቂነት ስሜት ) ነው።
(ብዙ እና ሁሉም የሚለው መካከል ያለውን ልዩነት የማትረጂ ከሆነ ፅሁፌን ጨርሰሽ እንዳታነቢ ፥ ~
¤
በሆነው ባልሆነው እራሳቸውን ተጠቂ በዙርያቸው ያለውን ሁሉ ደግሞ (ሴቱንም ወንዱንም) አጥቂ የሚያስመስሉ ሴቶች ቁጥር ቀላል አይደለም።በድለው ሲያበቁ ሮጠው የተበዳይን ካርድ ይመዛሉ። አጥፍተው ሳለ ይቅርታ እንዲጠየቁ እንጂ መጠየቅን ፣ጥፋትን ማመን … በዲክሽነሪያቸው ውስጥ የለም ።
∞
∞
ከዚህ ጋር በተያያዘም ባልተያያዘም …
ቅድም አንድ ጓደኛዬ የሆነን ሰው ገጠመኝ ነገረኝ ።ሰውየው ሊያገባ ብሎ የሆነችን ልጅ አየ ። ከዚያም ረሱል ﷺ እንደተናገሩት “ ስታያት የምታስደስትህ “ የተባለችው ዐይነት ስላልነበረች እንዳልተመቸው አሳውቆ መንገዱን ቀጠለ ልጅት ደግሞ “ የተከፈተ አይመለስም “ የሚለው የነጋዴዎች ቀልድ እዚህም የሚሰራ መስሏት ነው መሰለኝ “ ለምን አይቶኝ ተወኝ “ በሚል እየዞረች ስሙን ታጠለሽ ይዛለች ።
¤
ሰዎች እንዴት እንደሚያስቡ ይደንቃል ። አይቶሽ “ ተመችተሽኛል ይሁን “ አልያም “ አልተመቸሽኝም ይቅር “ የሚል ምርጫ ከሌለው ቀድሞውኑ ለምን ያይሻል ። እስከነ ኒቃብሽ አግብቶሽ የሰርጋችሁ ምሽት ላይ blind buy unbox ለምን አያደርግም ?
¤
የመታየትሽ ትርጉሙ ትመቺኛለሽ አልያም አትመቺኝም የሚለውን ለመወሰን አይደለምን ? ሸሪዐው የሰጠውን “ የሚመቸውን የመምረጥ መብት “ ለምን መጋፋት ዳዳሽ ?
¤
በራስ የመተማመን ክፍተትሽን በሰዎች ስም እና ስብዕና ላይ በመዝመት ለመጠገን አትሞክሪ ። ነውር ነው አማኝም አስተዋይም እንደዚህ አያደርግም ። እኛ ምርጫ እንዳለን ሁሉ ሌላውም ሰው ምርጫ እንዳለው ማመን እና መቀበል የበሳሎች መገለጫ ነው ።
¤
ድህነት ጋር ግብግብ ገጥመው ላሉ ሚስኪን ወጣት ወንዶች ምንም ዐይነት ርህራሄ ሳታሳዪ ነው በልበ ሙሉነት “ ሀብታም ካልሆነማ እንደዚ ይሁን እንደዚያ ገደል ይግባ “ ምናምን የምትዪው ። ስለቁመት እና ጠይምነት ( ቁመት ምን እንደሚያደርግላችሁ እንጃ 😀 ) ፣ ስለቦርጭ እና መላጣነት ስታነሺም እኚህ ነገሮች ላሉባቸው ወንዶች ሞራል ሽርፍራፊ ጥንቃቄ አታደርጊም ። ጉዳዩ አንቺ ጋር ሲመጣ ደግሚ ሌላ ታሪክ …
¤
ለማንኛውም አላህ በተከበረው ቃሉ የራሳቸውን መብት እና ጥቅም በማስጠበቅ ላይ እጅግ ብርቱ በተቃራኒው ደግሞ የሰዎች መብትና ሀቅ ላይ መጋኛ የሆኑ double standard ሰዎችን እንዲህ ሲል አስጠንቅቋል
“ ለሰላቢዎች ወዮላቸው ። [] ለእነዚያ ከሰዎች ባስሰፈሩ ጊዜ የሚያስሞሉ ፡፡ [ ] ለእነርሱም (ለሰዎቹ) በሰፈሩ ወይም በመዘኑላቸው ጊዜ የሚያጎድሉ (ለኾኑት)፡፡ “
( ሱረቱ አል ሙጠፊፊን 1-3 )

“ ለሰላቢዎች ወዮላቸው ። [
( ሱረቱ አል ሙጠፊፊን 1-3 )
❤26👍12🥰5😭4
ህይወትና ቀንህ እንዲያምር ከፈለክ stay Positive ይላል ፐረንጅ y'll positive life is really beautiful ቢመሽ ቢነጋ ብታገኝ ብትከስር ህይወት ትቀጥላለች።
ከመኖር ብንጎድል እነገሌ ጎደሉ ተብሎ የሚቆም ሲስተም የለም።ለሰውም ለራስህም ኑር ራስህ ላይም ስራ።
∞
ከቤትህ በሐቅ~ውጣ፤ ቀንህን በፈገግታ ጀምር መነሻ ፈገግታ ከሰዎች አትጠብቅ። መጠበቅ ሲገል ሲያጎድል እያየን ነው።
መልካም ቀን🖤

❤🔥21👍13❤5🫡1
ሁሌም በጣም ከሚገርሙኝ የቁርዓን ምዕራፎች መካከል አንደኛው (ሱረቱል አዲያት) ነው። አላህ እዚህ ሱራ ላይ እንዲህ ብሎ በፈረሶች ይምላል...
وَالْعَادِيَاتِ ضَبْحًا
እያለከለኩ ሯጭ በኾኑት (ፈረሶች) እምላለሁ፡፡
∞
አላህ የማለው ዝም ብለው በቆሙ ፈረሶች አይደለም፤ በከፍተኛ ሩጫ ከመጋለባቸው የተነሳ ደረታቸው ተቃጥሎ ማለክለካቸው በደንብ እስኪሰማ ድረስ በሚተጉ ፈረሶች ነው።
فَالْمُورِيَاتِ قَدْحً
ሸኮናቸው እያጋጩ እሳትን አውጪዎች በኾኑትም፤
ፍጥነታቸውና ጥንካሬያቸው እጅግ ከፍተኛ ከመሆኑ የተነሳ፣ ኮቴያቸው ከመሬት እና ከድንጋይ ጋር ሲጋጭ ብልጭታን ወይም እሳትን በሚፈጥሩ ፈረሶች...
فَالْمُغِيرَاتِ صُبْحًا
በማለዳ ወራሪዎች በኾኑትም፤
እነዚህ አላህ የማለባቸው ፈረሶች ለጨዋታ አይደለም እንደዛ በፍጥነት የሚሮጡት በጦርነት መካከል ውስጥ ሆነው ነው። ስለዚህ አደጋ ላይ መሆናቸውን ያውቃሉ።
فَأَثَرْنَ بِهِ نَقْعًا
በእርሱ አቧራን በቀሰቀሱትም፤
ከሩጫቸው ብዛት በቦታው ላይ አደገኛን አቧራ ቀስቅሰው ፈረሶቹ የሚተነፍሱት አየር እራሱ ከአቧራ ጋር የተቀላቀለ በሆኑ።
فَوَسَطْنَ بِهِ جَمْعًا
በጠላት ክብ መካከል ገብተው በተጋፈጡት እምላለሁ፤
አደገኛ መሆኑን እያወቁ...ሞት መኖሩን እያዩ በጠላት ጦር መሃል ሰንጥቀው በሚገቡ ፈረሶች ይምላል። አላህ በነዚህ ፈረሶች ከማለ ብኋሏ ቀጣዩ አንቀፅ ላይ እንዲህ ይላል...
إِنّ الْإِنسَانَ لِرَبِّهِ لَكَنُودٌ
¤
አላህ ከዚህ አንቀፅ በፊት ስለ ብርቱ ፈረሶችን ምሳሌ አድርጎ ከጠቀሰ ብኋላ፣ ለምንድነው ስለኛ ስለሰው ልጆች ባህሪ መናገር የፈለገው? ምክንያቱም የማለባቸው ፈረሶቹ ይሄንን ሁሉ መስእዋትነት የሚከፍሉት ለሚመግባቸው ለሚንከባከባቸው አሳዳሪያቸው ነው። ለዛ ውለታም ያላቸውን ታማኝነት ያለ ፍርሃት ሞትን እስከመጋፈጥ ድረስ በመሄድ ምስጋናቸውን ያቀርባሉ።
የሰው ልጅ ግን በእርሱ ላይ ያለውን የአላህን ፀጋ ይረሳል።
በአጠቃላይ ይህ ሱራ በሁለት ተቃራኒ የታማኝነት አይነቶች ላይ እንድናሰላስል ያደርገናል። በአንድ በኩል ለጥቂት ምግብና እንክብካቤ ሲል እስትንፋሱ እስኪቆራረጥ ድረስ የሚሮጥ፣ ኮቴው እሳት እስኪያወጣ የሚጋልብና ወደ ጦርነት መሃል ሰንጥቆ በመግባት ለአሳዳሪው ያለውን ታማኝነት በተግባር የሚያሳይ "ፈረስን" እናያለን። በሌላ በኩል ደግሞ ስፍር ቁጥር የሌላቸውን መለኮታዊ ጸጋዎች እየተመገበ፣ ነገር ግን ለፈጣሪው ምስጋና ቢስ ስለሆነው "የሰው ልጅን" እናገኛለን።
∞
በመልካም መንገድ ወደ አላህ የምንመለስ እና ካመሰጋኝ ባሮቹም የምንሆን ያድርገን። አሚን!

ሰው ለጌታው በእርግጥም ብርቱ ከሓዲ ነው፡፡

❤25❤🔥8
ለቧሎ እንዲህ አለቺዉ :- ታቃለህ አንተኮ መንግስት ነህ
እሱም አመሰግናለሁ የኔ ዉድ ምክንያቱ ግን ምን ይሆን
አላት..?
እሷም ንጉሶች የሆነን ከተማ ሲገቡ ያበላሾታል
አንተም ቤት ገና ከመድረስህ ቤቱን ትገለባብጠዋለህ ታበላሸዋለህ አለቺዉ....
አብቹ ወደ ኮምቦልቻ አልመጣም መሰለኝ እስኪ የኮምቦልቻ ልጆች ሁለት ትላልቅ መስጂድ ጠቁሙኝ?እንድዘይረው!
----------------------------------------
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
JOIN US: ❯❯ Halal fkr ♡
እሱም አመሰግናለሁ የኔ ዉድ ምክንያቱ ግን ምን ይሆን
አላት..?
እሷም ንጉሶች የሆነን ከተማ ሲገቡ ያበላሾታል
አንተም ቤት ገና ከመድረስህ ቤቱን ትገለባብጠዋለህ ታበላሸዋለህ አለቺዉ....
አብቹ ወደ ኮምቦልቻ አልመጣም መሰለኝ እስኪ የኮምቦልቻ ልጆች ሁለት ትላልቅ መስጂድ ጠቁሙኝ?እንድዘይረው!
----------------------------------------
♡ ㅤ ❍ㅤ ⎙ㅤ ⌲
ˡᶦᵏᵉ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
JOIN US: ❯❯ Halal fkr ♡
❤14🤣10❤🔥2😁2
Sooooooo it is ዙልሂጃህ~ ዙል ሂጃ ደግሞ የ ሰይድና ኢብራሂም ናት ሰይድና ኢብራሂም ደግሞ የኔ favorite ነብይ ናቸው፤ እና እነዚህን 8 ቀናት ስንመሳሰጥባቸው ብንቆይ ምን ይላቿል?
∞
ከ ሰይድና ኢብራሂም አለይሂሰላም ጋር በ ፍቅር ጠብ ካደረገኝ ነገር አንዱ የ ህይወት ፍልስፍናዬን የገነባሁበት አንድ ንግግራቸው ነው። ከ ህዝቦቻቸው ጋር በነበራቸው የሆነኛው ውይይት “ እናንተ በ አላህ እያጋራቹ ያልፈራቹ እኔ እናንተ ምታጋሩትን እንዴት እፈራለው? ከ ሁለቱ ቡድኖች ለ ደህንነት ይበልጥ ተገቢው ማንኛው ነው?” ይሏቸዋል። አምን ( ደህንነት)ን በ አላህ ከማመን ጋር የሚያያይዙበት መንገድ ገርሞኝ ዋው ብዬ ቆም ብዬ አያዋን አስተነተንኩ ሙዕሚን እንዴት ይፈራል? አላህን የያዘ ፣አላህ አለኝ ያለ ሰው ምን ይፈራል? ምን ይረብሸዋል? ምን ሰላም ይነሳዋል? አላህ ያለው ለ ደህንነት የተገባ ነው እያሉ እኮ ነው ብዬ ፈገግ አልኩ፤ ገፁ እዚህ ጋር ያልቃል ልክ ወደ ቀጣዩ ገፅ ስሸጋገር የመጀመሪያው አንቀፅ ላይ አላህ (ሱ ወ) “እነዛ ያመኑ ማመናቸውንም በበደል ያልሸፈኑ ለነሱ አምን ( ደህንነት) አላቸው እነሱ የተመሩም ናቸው” ይላል ፤ oh wait ይህ የ ኢማን እና የ ደህንነት ጉዳይ ከማስበው ፣ የገባኝ ከመሰለኝ እና የ ሰይድና ኢብራሂም አገላለፅ ፈገግ ካስባለኝ በላይ deep ነው።
∞
ደህና መሆን አላህ ለነዛ ላመኑ ሰዎች ቃል የገባው ነገር ነው፤ ሙዕሚን በ ችግር ውስጥ ፣ በ ህመም ውስጥ፣ በ ድህነት ውስጥ፣ በ በላዕ ውስጥ ደህና ነው ሙዕሚን በ ሁሉም ነገር ውስጥ ደህና ነው። ደህና መሆን ማለት አለመፈተን አይደለም በፈተና ውስጥ ግን አላህ የሚሰጠው መረጋጋት እና ውስጣዊ ጥንካሬ አለ። አላስተዋላቹም የቅርብ ሰውን አጥተው ወይ በ ጠና ታመው ወይ ትልቅ ገንዘብ ከስረው ኢናሊላህ ብለው ርግት ብለው ህይወታቸውን የሚቀጥሉ ሰዎች? ሰላልተጎዱ ፣ ስላልታመሙ ፣ ስላላዘኑ እኮ አይደለም ግን አላህ “ለሁሙል አምን” ያለውን አምን በ ውስጣቸው ስላኖረው። ለዚህ እኮ ነው ወላ ተጅዐል ሙሲበተና ፊ ዲኒና የምንለው ፈተናችንን አንተን በማጣት ካንተ በመራቅ አታድርግብን የምንለው ለዚህ ነው ከ አላህ ጋር እስካለን ሁሌም አማን ስላለ፣ አላህን ያገኘ ምንም ስለማያጣ ፣ ከ አላህ ጋር በ ፈተና ውስጥ መፅናኛ ስላለ ነው🤎
አላሁመል አምን ያረብ።

❤30❤🔥11
"ሀኪሞች ፍቅርን ከነፍስ በሽታ ውስጥ ቆጥረውት መድሃኒቱንም ገልፀዋል። እኔ ግን ከፍቅር መዳንን አላህን ከለመንኩኝ አላህ አፊያ አያድርገኝ"
ሊሳኑዲን ኢብኑ ኸጢብ
ሁሉም ለለይላው ያለቅሳል ለይላም ለሌላው ታለቅሳለች
ቀኑ ይለፍ እንጂ ጊዜው ይለፍ እንጂ የሁሉ ለይላ ከደጅ ትጠናለች
#አብሽሩ

❤🔥21❤17😍7