Halal Fkr
13.6K subscribers
249 photos
168 videos
3 files
720 links
Elegant. Faithful. Halal.


Tiktok: http://tiktok.com/@halal_discuss
Download Telegram
ለወደቀ ሁሉ አንሺ አለው!

በፊቅህ ትምህርት መሀል አንዲት ድንቅ አባባል አለች፦ "لِكُلِّ سَاقِطَةٍ لاقِطَةٌ" (ለኩሊ ሳቂጠቲን ላቂጠህ)። ትርጉሟም፦ "ለማንኛውም ለወደቀ ነገር፣ አንሺ አለው" እንደማለት ነው።
ይህች አጭር ንግግር የህይወትን ትልቅ ምስጢር ትፈታለች። በዱንያ ላይ "ተስፋ የለም" ተብለው የተረሱ፣ እድሜያቸው ያለፈባቸው የሚመስሉ እና ዋጋ ቢስ የሆኑ ነገሮች ሁሉ ጊዜያቸውን ጠብቀው አንሺ ያገኛሉ። መውደቅን ብቻ አትመልከት፤ ከውድቀትህ ጀርባ አላህ ያዘጋጀልህን "አንሺ" ጭምር ተመልከት።

የአንድ  ታሪክ ትዝአለኝ በአንድ ወቅት በአይነቱ ለየት ያለ መከራ የጸናበት አንድ ወጣት ነበር። ችግሩ አይሎበት የሚለብሰውን ልብስ እንኳ እስኪያጣ ድረስ ተቸገረ። "በችግር ላይ ጆሮ ደግፍ" እንዲሉ፣ በአንድ ሌሊት ሌባ ቤቱ ሰርቆ ይገባል። ወጣቱም ሌባ መግባቱን እያወቀ "ምንም በሌለበት ቤት ምን ሊወስድ ነው?" በሚል ስሜት እንደተኛው ዝም ይላል።
ሌባው ቤቱን ቢያምሰው ቢያምሰው ምንም ሊያገኝ አልቻለም። በመጨረሻም እጁ አንዲት ትንሽ የስንዴ ዱቄት ላይ ያርፋል። "ከባዶ እጄን ከመውጣት ይህችን ይዤ ልውጣ" ብሎ ሲነሳ፣ ወጣቱ የመጨረሻ ተስፋው የሆነችው ዱቄት መወሰዷ ስላሳሰበው ከሌባው ጋር ይተናነቃል። ሌባውም ደንግጦ የያዘውን ጥሎ ይፈረጥጣል።
ተአምሩ የሆነው ንጋት ላይ ነው! ንጋቱ ወገግ ሲል ወጣቱ ቤቱን ሲመለከት፣ ያ ፈርጥጦ የሄደው ሌባ በድንጋጤው መሀል ከራሱ ጋር ይዞት የመጣውን በርካታ ንብረትና ሀብት ጥሎለት ጠፍቷል።

The main point Don't give up hope.A little loss can be the opening of many blessings.
Your lifter is "unseen"  you don't know who will lift you up, or from which direction. Your role is not to focus on your "fall" but to believe that Allah is your "raiser".
Be patient.  there is no night that never dawns. The Lord who makes a thief an excuse for a bribe, will inevitably turn your failure into success.

"ለወደቀ ሁሉ አንሺ አለው፤ አንሺህ ማን እንደሆነ ደግሞ የማይታይ የተደበቀ ነውና በሰብር ጠብቅ!"


----------------------------------------
♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

JOIN US: ❯❯ Halal fkr ♡
❤‍🔥2316👍2😘2🔥1
በዘመናችን ደሀ የሆነ  ዲነኛ ጥሩ ስነ ምግባር ያለው ወጣት አንዲትን ሴት ለማግባት ቢጠይቅ እሺ አይባልም

ሀብታም የሆነ ስነ ምግባር የሌለው ዲን የሌለው ወጣት አንዲትን ሴት ለማግባት ቢጠይቅ ግን ችግር የለውም ይባላል .......

ካገባ ብኋላ አላህ ሂዳያ ይሰጠዋል ይባላል..ለምን ታዲያ ደሀውን ሰው አላህ ሀብታም ያረገዋል አትሉም ..?

ሒዳያ ሰጪው ሀብታም አድራጊው ራሱ አይደለም ወይ !

እንዴት ነው ፍርድ የምሰጡት!?

----------------------------------------
♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

JOIN US: ❯❯ Halal fkr ♡
👍4619😁13🤷‍♀8🍓4😭3💔2
"ሀላል ፒካፕ"

በአሁኑ ወቅት "ሀላል ፒካፕ" (Halal Pickup) በሚል መጠሪያ የሚሰሙ ንግግሮች የኢስላማዊ ስነ-ምግባርን የማይመጥኑና የጅንጀናን መልክ ለመቀየር የሚደረጉ የቃላት ጨዋታዎች ናቸው። ቡና በማይሸጥበት ቦታ "ቡና ቤት" እንደሚባለው ሁሉ፣ ማንኛውንም ተግባር "ሀላል" የሚል ታርጋ በመለጠፍ ብቻ ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም።
እንደነዚህ አይነት አሰልቺና ሞዛዛ ቃላትን መጠቀም ሙስሊሙን ማህበረሰብ ከማሳነስ ባለፈ ለትችት የሚዳርግ ተግባር ነው።

ለእውነተኛ ፍቅር የተሻለ መንገድ
በ"ሀላል ፒካፕ" ስም ጊዜያችሁን ከምታባክኑ፣ ስለ ፍቅር እውነተኛ ምንነትና አገላለጽ የምትማሩበትን ጥቁምታ እነሆ፦

የመጽሐፍ ጥቆማ፦ በአድሃም ሸርቃዊ የተጻፈው "عن شيء اسمه حب" (ስለ ፍቅር ስለሚባለው ነገር) የተሰኘው መጽሐፍ።

ጠቀሜታው፦ ይህ መጽሐፍ ፍቅር በኢስላማዊ እይታ እንዴት እንደሚገለጽና ለትዳር የሚሆንን የልብ ትስስር በምን አይነት ስልጣኔ መያዝ እንደሚቻል በዝርዝር ያስተምራል።

ከማላገጥ ይልቅ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ፍቅርን በመገንባት፣ የተባረከ የትዳር ዘመን እንዲኖራችሁ ጥረቱ ከእናንተ ይሁን።
----------------------------------------
♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

JOIN US: ❯❯ Halal fkr ♡
36👍7😍2❤‍🔥1🍓1🤗1🫡1
በአንድ አገዛዝ ስር እየኖርን የሁለት አለም ሰዎች ሆነናል። ሀብታሞች በወይን እየተራጩ የተራበውን ደሃ በተራበ ወንድሙ ላይ እንዲነሳ እያሳመጹ ሊዝናኑ የሚያልሙ በቀለም የተዋቡ የመንፈስ ድሆች ሆነው የሚኖሩባት ጎደሎ ክፋይ ማለት ኢትዮጵያ ናት።

©ቡርሃን አዲስ
♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

JOIN US: ❯❯ Halal fkr ♡
💔54😭5👍42🍓2
"ሕይወት ትግል ብቻ አይደለችም፤ አንዳንዴ ደግሞ እጅ መስጠትም ናት። ለሰው ሳይሆን ለፈጣሪ፣ ለሁኔታዎች ሳይሆን ለውስጣዊ ሰላምህ። ብዙ ጊዜ የምንደክመው ዓለምን ለመለወጥ ስንሮጥ ነው፤ ትልቁ ድል ግን ራስን አግኝቶ መረጋጋት ላይ ነው።"

©"እፎይ"ነቢል አዱኛ
♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

JOIN US: ❯❯ Halal fkr ♡
❤‍🔥39👍117🔥2🍓1
ፍቅርን ለማግኘት ብቸኛው መንገድ መስጠት ነው፡፡ ፍቅር አጨዳ ነው ወዳጄ! የሚያጭድ ደሞ ቀድሞ የዘራ መሆን አለበት፡፡
ከፍቅር ያለህን ድርሻ ከመጠየቅህ በፊት መጀመሪያ ምን ሰጠሁ ብለህ ራስህን ጠይቅ!
እንክብካቤን ቀድመህ ዘርተሀው ከሆነ ታጨደዋለህ፡፡ሌሎች እኛ ለሰራናቸው ነገሮች ምላሽ እንጂ ሌላ አይደሉም፡፡
ሸለቆ ውስጥ ሁነህ ብትጮህ ድምጹ ያንተኑ ንግግር ይመልስብሃል፡፡ፍቅርም እንደዚህ ነው፡፡
መጀመሪያ ዝራውና ከዚያ ታጭዳለህ ሳይዘሩ ማጨድ የለም፡፡

©ሰላም ላንተ ወዳጄ
----------------------------------------
♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

JOIN US: ❯❯ Halal fkr ♡
❤‍🔥168🥰4👍2
ተጠንቀቂ !..

መልክሽ ወደ ትዳር ሊያመጣሽ ይችላል...

ፀባይሽ ግን ወደ አባትሽ ቤት ይመልስሻል!
----------------------------------------
♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

JOIN US: ❯❯ Halal fkr ♡
❤‍🔥31👍23😁13🥰21
Halal Fkr
"ሕይወት ትግል ብቻ አይደለችም፤ አንዳንዴ ደግሞ እጅ መስጠትም ናት። ለሰው ሳይሆን ለፈጣሪ፣ ለሁኔታዎች ሳይሆን ለውስጣዊ ሰላምህ። ብዙ ጊዜ የምንደክመው ዓለምን ለመለወጥ ስንሮጥ ነው፤ ትልቁ ድል ግን ራስን አግኝቶ መረጋጋት ላይ ነው።" ©"እፎይ"ነቢል አዱኛ ♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲             ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ JOIN US: ❯❯ Halal…
"ከቃላት ጀርባ ትልቅ 'እፎይታ' አለ!

በቅርቡ "Halal Fkr" ቤተሰቦች መካከል ለየት ያሉ ጥበብ እንግዶች ይሆራሉ። ነፍስን የሚያክሙ ቃላት፣ ልብን የሚያረሰርሱ ስንኞች... ብቻ ዝግጁ ሆናችሁ ጠብቁን!

----------------------------------------
♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ
30🥰7👍6🔥2😘1
Halal Fkr
እስኪ ባለትዳር የሆናችሁ👍 ያልሆናችሁ💔
እስኪ ዘንድርስ ?

¤ ባለትዳር የሆናችሁ🔥

¤ ያልሆናችሁ💔
💔142🔥28👀4😭1🙉1
Halal Fkr
በየትኛው እድሜ ክልል ውስጥ ናችሁ?
እሺ እድሜያችሁም አልጨመረም¡ በየትው የእድሜ ክልል ገባችሁ!
ከ15 በታች👍 ፤ ከ15 _20🔥
ከ20_25❤️‍🔥 ፤ ከ25_30❤️
ከ30በላይ🍓


----------------------------------------
♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

JOIN US: ❯❯ Halal fkr ♡
❤‍🔥104🔥7622🤣3🍓3👍1
Halal Fkr
እሺ እድሜያችሁም አልጨመረም¡ በየትው የእድሜ ክልል ገባችሁ! ከ15 በታች👍 ፤ ከ15 _20🔥 ከ20_25❤️‍🔥 ፤ ከ25_30❤️ ከ30በላይ🍓 ---------------------------------------- ♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲             ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ JOIN US: ❯❯ Halal fkr ♡
ከ 20―30 አመት እድሜ ክልል ውስጥ ያለነው የህይወትህ በጣም እንግዳው ምዕራፍ!

¤ ጓደኞችህ እያገቡ ነው።...አንዱ ምታቀው አዲስ መኪና ይገዛል...አንዱ ደሞ ሂወትን ለመጀመር እስካሁን እየታገለ ነው።...አንዱ ጥሩ ገቢ እና የተረጋጋ ስራ አለው …አንዱ ደሞ ወላጆቹን ሳያስደስት(ሳይጦር) ከቀን ወደ ቀን እያረጁ ነው።እራስህን ከሌሎች ጋር ማነፃፀርህ የማይቀር ሆኗል...ለሊቶችህ ሙሉ ከአቅም በላይ  በሀሳብ የተሞላ ሁንዋል...ህልሞችህ ውድ እና ማይደረስ እንደሆኑ ይሰማሃል..ጊዜው በጣም እየፈጠነ እንደሆነ ይሰማሃል...በየሄድክበት ፈገግ ትላለህ 😁ግን በዝምታ ውስጥ ብዙ  ጦርነቶችን ትዋጋለህ!...ሁሌም ሲነጋ ዋጋህን ለራስህ ትጠይቃለህ.... አንተ ደካማ አይደለህም!... ብቻህን ከመጠን በላይ ብዙ ነገር እየተሸከምክ ነው🖤

የአብዛኛዎቻችን ወጣቶች ሁኔታ! 🥲

ከአላህ ጋር ሁሉም ነገር ይስተካከል
አብሽር ጀግናው ፤ህልምህን ተከተል!
----------------------------------------
♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

JOIN US: ❯❯ Halal fkr ♡
🔥46💔2316👍9❤‍🔥4😭4🍓1
☬Ʀιмєи∂я 𓅃
"لقد فَعلت المرأةُ كلّ شيٍء كي تَجذِب عينَ الرّجل..
تَعرّي.. مَساحيق.. جَسد مثالي.. شُورت و بَطن مكشوف.. تَجميل و إعادة نَحت.. تودّد و تنازل..
ثُمَّ ماذا؟

ما زالت عينُ الرجل تبحثُ عَن المزيد؛ وتزيغُ يُمنةً و يساراً.. وتلتقطُ مِن هُنا و هناك!

الخِيانات و العلاقات في ازدِياد ..
ولا شيءَ يُشبع الغَرائز ..
فقد زادَ العَرض؛ و رَخُصت السّلعة..
رَخُصت المرأة!

يا سيّدتي ..
لا توجد امرأة تملأ عينَ الرّجل و تَكفيه؛ إلا أن تَكفيه التّقوى!

الخَشية مِن الله؛ هي التي تُغضّ بها الأبصار.. ويشيحُ القلب عن الشّهوات؛ بالخوفِ مِن الله..
و ما سوى ذلك؛ فهو سِعارٌ دفَعت المرأة ثَمنه.. ثمّ فقدت الرّجل الزّوج الرّفيق؛ و بقيَ لها عابر السّبيل!"

- كفاح أبو هنود.

#تنوير_المرأة
ሴት ልጅ ወንድን ልጅ ለማማለል ሁለን ነገር አድርጋለች…
መራቆት ፣ አጭር ልብስ መልበስ ፣ ሜካፕ ፣ እምብርት መክፈት ፣ አርቲፊሻል ሰውነት ፣ ወደ ባእድ ወንዶች መቅረብ ወዘተ ግን ከዚያስ? ?

የወንዶች አይን ተጨማሪ ከመፈለግ አልተወገዱም ፣ ግራ ቀኝ ከመዟዟር አልባዘኑም ፣ cheating ከመጨመር  አልተቋረጠም

ከተቅዋ ውጪ ለወንድን ልጅ አይን የምትበቃ  ሴት በፍፁም አትገኝም ፣ ስለዚህ ንግስቲት ሆይ አሏህ የሚፈራ ወንድ ላይ አተኩሪ!

JOIN US: ❯❯ Halal fkr ♡


📌ለሌሎችም ማጋራት አይዘንጋ
52❤‍🔥12👍10🔥5💔2
ዛሬ ጁመዓ ነው
በጠዋቱ ሻወር ከተወስደ ቡኋላ ቁርስ ወተት በቡና እየጠጣቹህ!

አብሽሩ ላጤዎች¡¡🥲

ሙያ በልብ ነው ያልከው ሰው የት ነህ..

እንደዚህ አድርገሽ መስራት የምትችይ Inbox አውሪኝ ላገባሽ ዝግጁ ነኝ....¡

ለፈገግታ ነዉ ደግሞ እንዳታመሩ!!😭

JOIN US: ❯❯ Halal fkr ♡
🤣288😁4👍1😭1
ጁመዐ ኢማሙ አረፈዱና አንድ እብድ ሚምበር ላይ ወጣ
ሰላምታውን አስቀድሞ ኹጥባውን ጀመረ
"አልሀምዱሊላህ" አለ
አልሀምዱሊላህ ሁለት አድርጎ ፈጠራቹ
ሀብታምና ደህ አድርጎ ለሁለት ከፈላችሁ
እንድትታገሱ ድህነትን እንድታመሰግኑ ሀብትን ሰጣችሁ..
¤
ሀብታሞች አመስጋኝ አልሆናችሁ 
ወይ ደሀዎቹ ሰብር  የላችሁ
ልባችሁ በቂምና ጥላቻ የተሞላችሁ
አላህ ላዕናውን  ያውርድባቹ
¤
ተነሱ ስገዱ ብሎ ኹጥባውን አኽተመ

ጁመዐ ሙባረካ ለማለት ነው🖤
🤣359👍1
የእኔ 'እኔነት' በሰዪደል ውጁድ(ሶላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ዐለም ውስጥ የብናኝ ያህል ግዝፈት ባይኖረውም... የኔ መገኘት ፍጥረተ አለሙን ሞልቶ (ላዩን) በፈሰሰው ልቅናቸው ላይ የሚጨምረው የሚቀንሰው ቅንጣት ባይኖርም...
¤
ሰላሜ..

∞ በእዚያ መከታሁ በነበረው አጎትሁ ህልፈት ምክንያት በእያንዳንዷ ጥቃቅን ቅፅበት ለተሰማሁ ሐዘን..

∞በዚያች የበኩር ፍቅርሁ በደርባባዋ እመቤት በእናታችን ኸዲጃ(ረ.ዓ) መለየት ምክንያት ላሳለፍኩት እያንዳንዱ ስቃይ ...ለእያንዳንዱ የናፍቆት ትዝታ...

¤የመካ ጣዖታውያን ላደረሱብሁ እያንዳድዱ በደል..

¤ጧዒፍ ነዋሪዎቿን በነቂስ አውጥታ ላሳረፈችብሁ እያንዳንዱ ስድብ እና ድንጋይ ...

¤ለእያንዳንዱ ካንቱ ላይ ለተንጠባጠበች የደም ዘለላ..

∞ በኡሁዱ'ለት ለተሸረፈችው ለአንዲቷ ጥርስሁ..

¤ ለእያንዳንዱ አንቱ ፈገግ ላልኩበት..ለተደሰትኩበት ..ካ'ንቱ አይን ለወረደች የእንባ ዘለላ..አንቱ ላሰብኩት..በየቅፅበቱ ለተሰማሁ እያንንዳንዷ ስሜት ..

¤ ደረትሁን ላቀፈው ጡሩር ...ሚስክ ባዘለው እጅሁ ለተጨበጠው ሰይፍሁ ... ከፀልማማሁ ፀጉርሁ ላይ ላረፈው ጥምጣምሁ ...እግርሁ ላይ ለጠለቀው ጫማሁ...

¤ አንቱ ለነካሁት.. ለዳበስኩት.. ለተመለከትኩት..አንቱ ለጨበጥኩት...ለረገጥኩት ሁሉ..

ሩሔ ቤዛ ትሁን !

አላሁመሶሊም ወሰሊም ዓላ ሩሂል
ዉጁድ 🖤
❤‍🔥2011
4 ዓመት ሊሞላው ጥቂት ወራት ለቀሩት ምርጡ እና ሀላል ወዳጁ halal fkr channel ፤ አንድ ነገር በሉልን ብትባሉ ምን ትላላችሁ?"

ምትሉትን ካጣችሁ በ react❤️‍🔥
----------------------------------------
♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

JOIN US: ❯❯ Halal fkr ♡
❤‍🔥5013🤷‍♀3🥰2💔2🍓2😭2🤗2😍1👀1😘1
ለአራተኛ ጊዜ የጁምዓ ሶላት በአክሱም ከተማ አልተሰገደም💔
💔70😭18🤬51
هذه أبياتٌ للشيخ عمر بامخرمة


عليكَ بشُرْبِ البُنِّ في كلِّ ساعةٍ
ففي شُرْبِها يا صاحِ خمسُ فوائدِ

نَشاطٌ وإهضامٌ وإذهابُ بَلْغَمٍ
ونورٌ لأبصارٍ وعَوْنٌ لعابدِ».

ለቡ/ጠ/ማ
በየሰዓቱ ቡና በመጠጣት አደራ ..!

ቡና ጠጪ ጓድ ሆይ አምስት ጥቅም ታገኛለህ..!

ነቃትን፣ የምግብ መፍጨት ፣የአክታ መወገድ፣የአይን ብርሀን መጨመር ፣ለዒባዳ እገዛን ትሰጣለች።!
----------------------------------------
♡ ㅤ     ❍ㅤ       ⎙ㅤ     ⌲            
ˡᶦᵏᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ    ˢᵃᵛᵉ       ˢʰᵃʳᵉ

JOIN US: ❯❯ Halal fkr ♡
🤣2514😁2👍1👀1
...እርግጥ ነው.... እኔም አንተም አንዳንድ እንዳልተከወነ..እንዳልተፈፀመ... እንዳልሆነ..ጭራሽ እንዳልተፈጠረ አድርገን...ልንፍቃቸው..ልንረሳቸው..ወደኋላ ጥለን ልናልፋቸው...የምንፈልጋቸው በህይወት እሽክርክሪት ያካበትናቸው ጥልቅ ሕመሞች እና ትዝታዎች አሉን...አብሽር..ይህ ምኞታችን አላህን በማውሳት እውን ይሆናል...ዳግም ላይመለስ በተፈቃሪያችን እዝነት እንሽራለን...ኢንሻአሏህ ..!
33🍓3
∞ባለቤትሽ በምርጫው የወደደሽ ብቸኛው ሰው ነው∞
¤
አባትሽ የወደደሽ በኃላፊነት ስሜት ነው።
ወንድሞችሽ የወደዱሽ በደም ትስስር ነው።
ልጆችሽ ደግሞ በተፈጥሮ (በደመ-ነፍስ) ይወዱሻል።
¤
ባለቤትሽ ግን ሴቶች በሞሉበት ዓለም ውስጥ ተመልክቶሽ  አንቺን መረጠ በአንቺ ላይ አልተጫነም ካንቺ ጋር የመኖር ግዴታ አልነበረበትም ወይም ሲወለድ ከአንቺ ጋር የሚያስተሳስረው የደም ግንኙነት አልነበረም።
¤
ጉድለቶችሽን፣ የባህሪ መለዋወጥሽንና ስህተቶችሽን እያየ የምፈልጋት ሴት እቺው ናት ብሎ ነው ያገባሽ።

ይህ ዓይነቱ ፍቅር ሆን ተብሎ  በውሳኔ የሚደረግ ነው ።
እርሱ በየቀኑ ሲነቃ ያንኑ ምርጫውን ይቀጥላል የሚሠራው፣ የሚያስተዳድረውና የሚጠብቅሽ ተገዶ ሳይሆን ሕይወቱን ከአንቺ ጋር መገንባት እንደሚገባሽ ስለወሰነ ብቻ  ነው ።

ስለ አንቺ ሲከላከል፣ በሌሊት ወደ አንቺ ሲቀርብ፣
እና በክፉ ወቅቶች (በጭንቅ ቀን) ከአንቺ ጋር ሲቆይ...
ይህ ግዴታ ሳይሆን በየቀኑ የሚታደስ ታማኝነት እና ፍቅር ስላለው  ነው ።

ስለዚህ ይህንን መርጦ እና ወዶ የሰጠሽን ፍቅር እንደ ቀላልና እንደተረጋገጠ ነገር አትቁጠሪው ።


ክብሩን ጠብቂ፣ ተንከባከቢው እርሱም መመረጡን እንዲሰማው አድርጊ ተመራጭነት የሚሰማው ወንድ ይበልጥ ጠንካራ፣ ጽኑ እና ታማኝ ይሆናል ።
¤
መጠራጠርን ያቆማል ሳይጠየቅ ብዙ ይሰጣል ቤቱን በጭንቀት ሳይሆን በኩራት ይጠብቃል በስሜትም ከመራቅ ይልቅ ሁልጊዜም በአቅራቢያሽ ይገኛል ።
ባጭሩ የባልሽ ፍቅር ከደም ትስስር በላይ የላቀ ውሳኔ ነውና ልዩ ቦታ ስጪው።
46❤‍🔥12👍9
ነብዩላህ ሙሳ, The big guy, the strong fit man፣ አንበሳው ከሀገራቸው አምባገነኑ የፊርአውንን መንግስት ሸሽተው ተሰደው ሲጓዙ መድየን ወደምትባል ቀበሌ ደረሱ።

መሄጂያም ማረፊያም ያልነበራቸው ስደተኛውና ሙሳፊሩ ነብዩላህ ሙሳ ዛፏ ስር ቁጭ ብለው

َربِّ إِنِّي لِمَا أَنزَلْتَ إِلَيَّ مِنْ خَيْرٍ فَقِيرٌ" "

¤

ጌታዬ ሆይ እኔ አንተ ወደኔ ላወረድከው በጎ ነገር  ከጃይ ነኝ" ሲሉ ዱአእ አደረጉ።
እቺ ዱአእ ስንት ነገር መለሰች]
¤
ስደተኛው፣ ብቸኛው፣ መሄጃ ያጣው ሙሳ አለይሂሰላምም ዛፏ ስር ቁጭ ብለው ያደረጓትን ዱአእ ፍሬ አገኙ።
ቤት.... ስራ....የገቢ ምንጭ.... ሚስት.... ቤተሰብ!
31❤‍🔥8🥰8