HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ
2.25K subscribers
1.99K photos
96 videos
51 files
3.81K links
❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️

👇👇👇
http://www.youtube.com/@haileG2239
Download Telegram
◈ ጥቂት የማንባል ሰዎች በዚህ በመንፈሳዊው ዓለም ላይ የማንገናዝበው ጉዳይ ቢኖር መቆየትን ነው፡፡ ኃይልን መልበስ በጣም እንፈልጋለን፥ ነገር ግን 'ቆዩ' ያለውን ቃል እንዘለዋለን፡፡ በዚህም ሳቢያ ተንበርክከን የጸለይነው ጸሎት ምላሽ ሳይቆይ እንዲመጣ እንወዳለን፡፡ ዛሬ የጀመርነው ስግደት ዛሬውኑ ኃይል እንዲሰጠን እንቸኩላለን፡፡ አሁን ያለቀስነው እንባ ወዲያኑ እንዲታበስ እንፈልጋለን፡፡

◈ ነገር ግን ሳይቆይ የሚመጣ ነገር ሳይቆይ ሊሄድ እንደሚገባው አናስተውልም፡፡ በመቆየት እውነታ ውስጥ እግዚአብሔር አደራጅቶ በትክክለኛው ሰዓት የሚሰጠን ነገር እኛ ካስፈለገን ሰዓት እንደሚበልጥ አናውቅም፡፡ በመሆኑም፤ ኃይልን እስክንለብስ በኢየሩሳሌም መቆየት አቅቶን፤ በቶሎ የሚተረጎም መፍትሔ ፍለጋ ወጥተን ሄደን፤ "ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው" የሚለውን ቃል ተሻግረን፥ "መሆን ያለበት ሁሉ በኛ ጊዜ ውስጥ ይለፍ" ብለን የእግዚአብሔርን ሥራ ውብነት ከኑሮአችን አርቀን፤ ላንጨርሰው መንገዱን እየጀመርን፥ የወከባ ሰዓትን የጊዜያችን መገለጫ እናደርጋለን፡፡ በመቆየት ጸጋ ውስጥ ቆይተው የቆየች አገራችንን ያቆዩልን አባቶቻችን ይህንን የመቆየት ኃይል በጣም ያውቁታል፡፡

◈ እንኪያስ፥ ቃሉን እየጠበቁ ይቆያሉ፡፡ ጸጋቸውን እያከበሩ ይጠብቃሉ፡፡ የእያንዳንዷ ቀን አካሄዳቸውን ከኢየሩሳሌም ውስጥ ያረጉታል፡፡ አምልኮትን አያቆሙም፡፡ በዚህም ከጊዜ ወደ ጊዜ ኃይላቸው እያደገ እያደገ ይመጣል፡፡ ጽድቃቸው መነበብ ይጀምራል፡፡ ክብሩን ይገልጡታል፡፡ ሞገሱ በገጻቸው ይታያል፡፡ ምክንያቱም ጌታ እንዲህ ያለውን ቃል ኖረውበታል "ኃይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ቆዩ፡፡" እኛስ ውዶች እንዴት እያሰብን ይሆን!

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
2
◈ ቅዱስ ዮሐንስ እስከ መስቀል ድረስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለዉን መከራ በማየቱ ከዚያ ዕለት ጀምሮ 70 ዘመን ሙሉ ፊቱ በኅዘን የተቋጠረ በመሆኑ (ቁጽረ ገጽ) ሆኖ ኖሯል። ቅዱስ ዮሐንስ ብዙ ተጋድሎን አድርጐ ዓለምን ሁሉ ዞሮ ካስተማረ ቦኃላ በመጨረሻም ደቀ መዝሙሩ አብሮኮስን ከወንድሞችም ሌሎች ሁለትን መርጦ መቆፈሪያ ይዘው ይከተሉት ዘንድ አዘዘ፡፡ ጕድጓድም እንዲቆፍሩ አዘዘ ከዚያም ወረዶ ቆመ ልብሱንም አስወገደ የበፍታ ቀሚስ በቀር ሌላ አላረገም ነበር፡፡ እየጸለየ ወደ ከተማም አሰናበታቸው፡፡

◈ በክርስቶስ ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ ለሕዝብ ይነግሩአቸው ዘንድ አዘዘ ሁሉም እንደየ ስራቸው ጌታ እንደሚከፍላቸው ነገራቸው፡፡ ካዛም በኋላ እንዲህ አለ "እኔ ከሁላችሁም ደም ንፁሕ ነኝ" ከእግዚአብሔር ትእዛዝና ሕግ ሳልነግራችሁ የተውኩት ምንም ምን የለምና እናንተም ከእንግዲህ ከቶ ፊቴን አታዩም አላቸው፡፡ እነርሱም እጅና እግሮቹን ስመውት ትተውት ሄዱ ሲመለሱም ልብስና ጫማ እንጂ ምንም አላገኙም እግዚአብሔርንም አመሰገኑት፡፡

◈ ወልደ ነጐድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ዘጠና ዓመትም ኖረ፤ እንደባላሟሎቹ ሐዋርያት በመሰየፍ ሞትን አለቀመሰም፡፡ ‹‹ያ ደቀ መዝሙር አይሞትን እንዲል›› ዮሐ 21 ስለ ድንግልናውና ስለንጽሕናው ይህ ሁሉ ሆነ፡፡ በዚህ በከበረ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን፣ ይቅርም ይበለን በእውነት። አሜን

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
3👍1
◈ ዛሬ ላይ ሰዎች ቅዱሳን መልአክት እንጂ ርኩሳን መልአክት እንዳሉ ፍጹም በዘነጋ አካኋን ያለ ጥንቃቄ ተዘናግተው ይኖራሉ፡፡ የአጥፊ መናፍስት ነገድ ግን በተቻለው አቅም የሰው ልጆችን ሁሉ ሰብስቦ ያጠፋ ዘንድ እያንዳንዷን የሰኮንድ ስባሪ በሥራ ላይ ያውላታል፤ እያዋላትም ነው፡፡ ይሄ እኛ እስከመፈጠሩም የረሳነው ክፉ ባላንጣ፤ እርሱ የዘወትር ሥራው እንደሆንን አስታውሶን፤ ባሕሪያችን ውስጥ ገብቶና ጠባያችንን ተመሳስሎ፤ ውስጣዊ ሰውነታችንን መኖሪያ ቦታው በማድረግ በእያንዳንዱ ቀናችን ውስጥ ውሎአችንን ተጋርቶ በመኖር፤ ብዙ ጥፋት ያጠፋ ዘንድ ከኛ ስንፍና የተነሣ ዕድል ኖሮት ሳለ፤ ቢሆንም ግን እንዳሰበው ያህል ሮጦ ሊያወድም አልቻለም፡፡ ለምን?

◈ ምክንያቱም... ያ ዝም ብለን የምንጠራው ቅዱስ፣ ትኩስ ሻይ ሲደፋብን ስሙን የምናነሣው ቅዱስ፣ ከእውነት ስንናገር ማረጋገጫችን እናደርገው ዘንድ የምንጠራው ቅዱስ፣ ስዕሉን ባየን ጊዜ ሁሉ ፈጥነን የምንስመው ቅዱስ፣ ስለ እርሱ ለመናገር ስንጀምር የዓይን ውኃ የሚያመጣብን ቅዱስ፣ በተጨነቅን ጊዜ ስለተሸነፍንበት ጉዳይ የምናዋየው ቅዱስ፣ በተደሰትንበት ጊዜ ለማመስገን የምንቸኩለው ቅዱስ፤ እርሱ አብዝቶ ይከተለናልና ነው፡፡ ሚካኤል ሚካኤል የምትሉ ሰዎች ሊቀ መልአኩን ፍለጋ ሩቅ አትባዝኑ፡፡ አብሯችሁ አለ፡፡ እመቤቴ እመቤቴ የምትሉ ሰዎች ድንግል ማርያም የሆነ የማይደርስበት ቦታ ላይ ያለች አትምሰላችሁ፡፡ በአጠገባችሁ ናት፡፡ ዑራኤል ዑራኤል የምትሉ ሰዎች ቅዱስ ዑራኤል እናንተ ሕይወት ውስጥ ስንት ጊዜ መጥቶ ከብዙ ከማታዩት የመናፍስት አደጋ እንደጠበቃችሁ አላወቃችሁም፡፡ መድኃኒዓለም መድኃኒዓለም ማለታችሁ ሰንት ቦታ ከስንት ነገር እንደከለላችሁ እንደምን አድርጌ ላሳያችሁ? እኛስ ይሄን መለየት ላይ እንዴት ነን?

እስቲ የእናንተንም ገጠመኝ አጋሩኝ!

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
6👍3
◈ አስተውሉ! መስቀል አሰርንም አላሰርንም ድሃን የሚገፋ ማንነት ካለን፤ በዚያን ዘመን ክርስቶስን ከገፉት አይሁዳውያን መካከል አንዱ ነን፡፡ ይሄ ማነጻጸሪያ አይደለም፡፡ ለስብከት መድመቂያነት ያገለገለ ማያያዣ አይደለም፡፡ ከመጀመሪያው አዳም የተወለድን ሁላችን በእርሱ የሆነው ሁሉ በባሕሪይ እየተተረተረ እስከ ምፅዓት እንደሚቀጥል ሁሉ፤ በዳግማዊው አዳምም ታሪክ የተፈጠሩት ክስተቶች መልክና ትውልድ እየቀየሩ በባሕሪይ መደገማቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ባይደገሙማ "እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተም እኔን ምሰሉ" የሚለው ቃል አይቀመጥም ነበር፡፡ በአጭሩ ድሆችን የምንንቅ ሁላችን፥ "ይሄ የዮሴፍ ልጅ አይደል፥ አናውቀውም እንዴ?" ካሉት የንቀት ድምፆች ጋር አንድ ነን (ይህን አንቀጽ የምታነብ ነፍስ "ልብ ይሰጠኝ" ስትል ራሷን አትሸንግል፥ ይልቅስ የተሰጣትን ለባዊነት ተጠቅማ ስለ ንፍገት ደቂቃዎቿ ታልቅስ፥ ትታረምም)፡፡

◈ የእግዚአብሔር ልብ የተባለ ባለገናው እንዲህ ይዘምራል፦ "ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል። እግዚአብሔር ይጠብቀዋል፥ ሕያውም ያደርገዋል፥ በምድር ላይም ያስመሰግነዋል፥ በጠላቶቹም እጅ አያሳልፈውም። እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል፤ መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል።" (መዝሙረ ዳዊት 41፥1-3)

◈ ዳዊት አምላክ "እንደ ልቤ" ያለው ታላቅ ሰው ነው፡፡ በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ ደግሞ መለኮታዊው አሳብ አለ፡፡ ከላይ በዳዊት የተገለጸው ቃል በእግዚአብሔር ልብ (በአብ) ያለ ነው፡፡ አሳቡን ካወቅን ዘንዳ፥ ፈቃዱን የመፈጸምና ያለመፈጸም መብቱ በእጃችን ሆነ ማለት ነው፡፡ አዎ... መንግሥተ ሰማያት "በመካከላችን" ናት! በረቱን ለማጽዳት ባይቻል እንኳ፤ አለመጠየፍ በራሱ ራሱን የቻለ ክርስቲያናዊ ስብዕና ነው፡፡ ለወደቁት የሚታመም ሰውነት፣ ለተራቡት የሚያዛጋ ሆድ፣ ለተጠሙት የሚደርቅ ጉሮሮ፣ ለተራቆቱት የሚበርደው አካል፣ ለደኸዩት የሚቸገር ቸርነት የሌለው ግለሰብ፤ የቱን ያህል ሃይማኖተኝነት ይኑረው የእግዚአብሔርን ቃልና እውነት የሚገልጥ ልዕልና ላይ አይደርስም፡፡

እግዚአብሔር ሁላችንንም ይባርከን! እንረዳዳ፣ እንተጋገዝ!
https://t.me/haile_gebriel_tube_bot

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
2👍2
◈ ክርስቲያኖች ዓለም ለእነርሱ በጭራሽ ቦታ እንደሌላት ማስተዋል እንዲያቅታቸው፤ አጥፊው ኃይል በአራቱም የምድር ማዕዘናት ምቹ መጠጊያዎችን አበጅቶ "እስቲ አረፍ በሉ" ይላል፡፡ "እሺ" ብለው ማረፊያ ያመቻቹ ክርስቲያኖች ሲኖሩ ታዲያ፤ ጌታ "የሰው ልጅ" ብሎ የጠራው ከእግዚአብሔር ያልተለየ ሥጋ መሆናቸው ቀርቶ የቀበሮ ወይንም የሰማይ ወፎች ሥጋ ሆኑ ማለት ነው፡፡ በእውነትም ይህቺ ዓለም የምትመቸው እንደ እባብ ለሚናደፉ፣ እንደ ጊንጥ ለሚመርዙ፣ እንደ ጅብ ለሆድ ለሚኖሩ፣ እንደ አሳማ በቃኝ ለማያውቁ፣ እንደ ቀበሮ ጣዝማ ለሚልሱ፣ እንደ በቀቀን ወሬ ለሚወዱ፣ እንደ ጃርት ለሚዋጉ፣ እንደ ነብር ደም ለሚመጡ፣ እንደ እስስት ለሚያስመስሉ፣ እንደ ፍየል ለሚቅበዘበዙ፣ እንደ ዝንጀሮ ነጥቀው ለሚሮጡ፣ እንደ ድመት ወገናቸውን ለሚበሉ ሁሉ ነው፡፡ ክርስቶስ እንደለካው የ"ሰው" መጠን ሆነው በተከበረ ውድ ሕልውና የሚመላለሱት በአንጻሩ "በዓለም ሳሉ" ማረፊያ አያገኙም፡፡

◈ ዲያቢሎስ ሰዎች ሰማያዊ መዝገባቸውን ቀደው ከእንስሳት እንደ አንዱ በመሆን በዓለም ምቾት መጠጊያ አግኝተው እንዲኖሩ በማገዝ አያሌ ነፍሳትን በስውር ጥበብ እያጠፋ ይገኛል፡፡ ይሄ ወጥመዱ ላይ ጥቂቶች ነቅተው ክርስቶስን ወደ መከተል "ሰውነት" እርምጃ ሲጀምሩ ደግሞ፤ እያንዳንዷ እንቅስቃሴያቸውን በፈተና ከቦ ትንፋሽ በማሳጣት፤ መንፈሳዊውን ጉዞ እንዲጠሉትና እንዲያማርሩት ያደርጋል፡፡ አማኞች ፈጣሪያቸውን በትክክል ማምለክ ፈልገው የሆነ እንደሆነ ዓለም መቀመጫ እንደምታሳጣቸው አስቀድመው ብርቱ ግንዛቤ ማግኘት አለባቸው፡፡ ምክንያቱም በዓለም ዙፋን ላይ ነግሦ ያለው ገዢ የቅድስናና የበጎ ነገር ሁሉ ተቃዋሚ ነው፡፡ ይህንን መሠረት ከባሕሪይው ሥር ያላኖረ ክርስቲያን፤ ጽድቅንና ድሎትን መሳ ለመሳ አናንብቦ ለመጓዝ ሲጥር፤ ሁለቱ ተቃራኒ ዋልታዎች ማንነቱ ላይ ጦርነት ከፍተው ያሰቃዩታል፡፡ (የምድር መጠጊያን የሚፈልግ መንፈሳዊ ሰው ሆደ ባሻ ነው፡፡ ራሱን በተኮሰው፣ ዓይኑን ባቃጠለው፣ ሆዱን በቆረጠው፣ እግሩን ባዳለጠው፣ ሥራው በደከመው፣ ትምህርት በከበደው፣ ምቾቱ በራቀው ቁጥር ይነጫነጫል! ያማርራል! ለምን በኔ ብቻ ይላል!)

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
👍4
+ አልቆም ያለ ደም+

"በኋላውም ቀርባ የልብሱን ጫፍ ዳሰሰች፥ የደምዋም ፈሳሽ በዚያን ጊዜ ቆመ" (ሉቃ. 8:44)

◈ ከአሥራ ሁለት ዓመትም ጀምሮ ደም የሚፈሳት ሴት ነበረች፥ ትዳርዋንም ሁሉ ለባለመድኃኒቶች ከስራ ማንም ሊፈውሳት አልተቻለውም። ደምዋ ፈስሶ አያልቅም ወይ? ዓሥራ ሁለት ዓመት ሙሉ? እንዴት ያለ ሕመም ነው?! ሰው በክፉ ሽታዋ እስኪርቃት ድረስ የማይቆም ደም::

◈ ባለ መድኃኒቶች ሊያቆሙት ያልቻሉትን የደም ጎርፍ የናዝሬቱ ባለ መድኃኒት በቀሚሱ ብቻ አቆመው:: በልብሱ ጫፍ ብቻ:: ሳያያት ሳይነካት እጁን ሳይጭንባት በልብሱ ጫፍ ብቻ የደምዋን ዝናብ እንዲያባራ አደረገው:: የሕመምዋን ማዕበል ገሠጸው::

◈ በልብሱ ጫፍ ብቻ የሚፈውስ ሐኪም እንዴት ያለ ነው? ቀጠሮ ሳይሠጥህ ሳያናግርህ ቀና ብሎ ሳያይህ ስትነካው ብቻ የምትድንበት ከሆነ እርሱ መድኃኒት የሚያዝ ሐኪም ሳይሆን ራሱ መድኃኒት ነው:: የልብሱን ጫፍ የነካ ከዳነ ሥጋውን የበሉ ደሙን የጠጡማ ምንኛ ይድኑ ይሆን?

◈ ሊፈውሳት አስቦ አልነበረም የዐሥራ ሁለት ዓመት ሴት ልጅ ከሞት ሊያስነሣ መንገድ ሲሔድ ግን እግረ መንገዱን የዓሥራ ሁለት ዓመት የቁም ሙትዋን ፈወሳት:: መድኃኔዓለም እንዲህ ነው:: ወደ በሽተኛው ሳይሔድ በቃሉ ብቻ ተናግሮ ይፈውሳል፤ በሽተኛው ቤት ገብቶ በአልጋው ላይ ይፈውሳል:: ሊፈውስ ሲሔድም ይፈውሳል:: እናም የሴቲቱ አልቆም ያለ ደም በልብሱ ጫፍ ብቻ ቀጥ አለ::

◈ ጌታዬ ሆይ የእኔንስ ደም የምታቆመው መቼ ነው? ምን ደም ፈስሶህ ያውቃል ካልከኝ ኃጢአት የሚባል ደም ሲፈሰኝ አይታይህም? አንተስ በቃልህ "ኃጢአታችሁ እንደ ደም ብትቀላ እንደ ባዘቶ ትጠራለች" ብለህ የለ? እንደ ደም የቀላው የእኔ ኃጢአት ነው:: ይኸው ሲፈስ ከሴቲቱ በላይ ቆየ::

◈ ላቆመው ብል አልቆም አለኝ:: ያላሰርኩበት ጨርቅ፣ ያልሞከርኩት ቅባት፣ ያልሔድኩበት ባለ መድኃኒት የለም:: ገንዘቤን ከሰርኩ እንጂ ኃጢአቴ ግን መቆም አልቻለም:: እንዲያውም መጠኑ እየጨመረ ነው:: ባሕር ሆኖ ሊያስጥመኝ የደረሰ የኃጢአት ደም ከብቦኛል::

◈ ለእኔ የሚሆን የቀሚስ ጫፍ ታጣ ይሆን? እኔ እንደ ሴቲቱ ታላቅ እምነት የለኝም ቀሚስህ ግን አሁንም ኃይል አለው:: ልትፈውሰኝ ና አልልህም ስታልፍ ግን ልዳስስህና ልዳን:: ጉዞህን ሳላሰናክል ሰው ሳይሰማ በልብስህ ጫፍ ብቻ ደሜን አቁምልኝ:: የእኔን ደሜን መግታት ላንተ ምንህ ነው? ደምህንስ አፍስሰህልኝ የለ?

◈ እባክህን ደሜ ሳይቆም ሌላ ዓመት አልሻገር:: እኔ ኃጢአቴን "ያለፈው ዘመን ይበቃል" ማለት ቢያቅተኝም አንተ ግን ይበቃሃል በልልኝ:: በእምነት ማጣት የታጠፈውን እጄን ወደ ልብስህ ጫፍ ዘርጋልኝ:: እኔ ማቆም ያልቻልኩትን የበደል ደም ጸጥ አድርገህ "አንድ ሰው ዳስሶኛል ኃይል ከእኔ ወጥቶአል" በል:: እነ ጴጥሮስም ይደነቁ እኔም በሰላም ልሒድ::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube