HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ
2.25K subscribers
1.99K photos
96 videos
51 files
3.81K links
❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️

👇👇👇
http://www.youtube.com/@haileG2239
Download Telegram
የጸሎት አሳብ መበታተን ምልክቶች

1) ጸሎተ ቃልን ከጀመሩ በኋላ የሚናገሩትን ፊደልና ዓረፍተ ነገር አለመስማት (በተለይ በጸሎት መጽሐፍት ንባብ ወቅት)

2) ጸሎቱን እያደረሱ ሳለ ድንገት በምን ርዕስ (ጉዳይ) ላይ አምላክን እያነጋገሩ እንደሆነ መዘንጋት

3) ጸሎተ ጊዜው ላይ ሆነው ያሉበትን ቅጽበት እስኪረሱ ድረስ በጭንቅላት ውስጥ ዝብርቅርቅና ፍቺ በሌላቸው ድምፆችና ምናቦች በመሳብ ሰምጠው መቅረት (መጀመሪያ የሚጀምረው በአንድ ቃል የሌለው ድምፅ አሊያ ቅርጽ አልባ ምናብ ነው፡፡ በመቀጠል በነፋስ እየተቀጣጠለ በፍጥነት እንደሚዛመት ሰደድ እሳት ድምፆቹና ምናቦቹ ተከታታይነት ባለው ወጥ አኳኋን እየበዙ ይሄዳሉ)

4) ተራ ቁጥር 3 ላይ ከተጠቀሰው ጋር ተቀራራቢነት ሲኖረው፤ ከውስጥ የሚፈጠሩት ድምፆችና ስዕሎች ተጨባጭ የሚመስል መልክና ገጽታ ፈጥረው ሕልም እንደምናይ አድርገው ይዘውን ይንሳፈፋሉ (ለምሳሌ የዝሙት ትዕይንቶችን፣ ያለፉ የድርጊት ትውስታዎችን፣ የተረሱ ገጠመኞችንና ንብረቶችን፣ ወደፊት የሚከናወኑ እቅዶችን ማየት)

5) እንዲሁ እንደ ተራ ቁጥር 3 ተመሳሳይ ሲሆን፤ የሚረበሹበት ድምፅ ግን ከውስጥ የሚፈጠር ሳይሆን ከውጪ የጸሎት ቦታ አቅራቢያ በሚደመጥ ንግግር ወይንም ሁካታ የሚመጣ ነው

6) የሚጸለየውን ጸሎት፣ የሚታየውን ስዕለ አድኖና ሌላም በአጠገብ ያለውን ቁስ ሰበብ (መሠረት) ያደረገ ሙግት ከራስ ጋር መግጠም (ምሳሌ የሚጸለየውን ጸሎት ምክንያት ያደረገ፦ "ጸሎቴ ይሰማ ይሁን? ይሄ ትክክለኛ ጸሎት ይሁን? ሌላ የተሻለ ጸሎት ማድረስ አለብኝ ይሆን? ይሄ የጸሎት ቃል ምን ለማለት ፈልጎ ነው? ይሄን የጸሎት መጽሐፍ ማን አዘጋጀው? ፣ ወዘተ..." እያሉ የሕሊና ድምፆችን በራስ ፈቃድ መፍጠርና ለጥያቄዎቹ መልስ ለመስጠት እየዳከሩ እየዳከሩ ድምፆቹን በማብዛትና በማድመቅ በዛው ጭልጥ ማለት)

7) አእምሮ ላይ እፍን በሚያደርግ ድብርታም ስሜት ባለው አዚም ሲንገላጅጁ ቆይቶ ከእንቅልፍ ተቀስቅሰው እንደ ነቁ አይነት መሃል መሃል ላይ መባተት (ይሄ ምልክት ካለ ደጋግሞ ማፋሸክ፣ የዓይን ጨረር መጥበብ፣ የእንባ ነጠብጣቦች መውረድ፣ የራስ ቅል መክበድ፣ የያዙት መጽሐፍ ወይንም የለበሱት ልብስ (ነጠላ) ተንሸራቶ ሲወደቅ አለማወቅና ባሉበት ቦታ ላይ አግድም መተኛት ተጨማሪ ምልክቶች ሆነው ይከሰታሉ)

8) ሰመመንን በተጠጋ ድባብ ውስጥ ሆኖ ከጸሎት አንቀጽ ወደ ጸሎት አንቀጽ እየተሻገሩ መቆየት (ይሄ ምልክት
ካለ እያንዳንዱ ተብሎ የሚታለፈው አንቀጽ ምን እንደነበረ ቢጠየቁ አያውቁም)

9) ጸሎትን እያሰሙ ጥቂት እንደቆዩ የትኩረት አቅም ቀንሶ መንፈሳዊውን ሐሴትና ትርጉም ማጣት

10) ጸሎተ ቆይታውን ቶሎ ፈጽሞ ስለ ቀጣዩ አድራጎት እያምሰለሰሉ መቁነጥነጥ (ሰዓት ደጋግሞ ማየት፣ የጸሎት
መጽሐፉን ቀሪ ገጾች መቁጠር)

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
👍1
"ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።" (1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፥18-19)

◈ የአብራም ጎረቤቶች ከቤተሰባቸው ሲዋረሱት የቆዩት የአኗኗር ሂደት ትክክል እንደሆነ ነው የሚያስቡት፡፡ ለእነርሱ መብላት፣ መጠጣትና የሚያስፈልጋቸውን በወቅቱ ማግኘት፤ የሕይወት ጠቅላላ ትርጉም ሆኗቸዋል፡፡ የዛሬውም የእኛ የአባት ቤት ኑሮም ይኸው ነው፡፡ በሥጋ መደላደልና በቁስ ስኬት ላይ መቆም፤ ቤተሰብ "ልጄ በሚገባ አኩርቶኛል" የሚልበት ሙሉ መለኪያው ነው፡፡ ይሄም መመዘኛ በዓለም ሰፊ አውታር የተለመደ፤ ኑሮን ስለማሸነፍ የሚናገር ሚዛን ስለሆነ፤ እንዲሁ በደፈናው "ትክክል" ተደርጎ ማኅተም ተዘግቶበታል፡፡ ከዘላለም ሕይወት አንጻር፣ "ሰውን ሰው ካሰኘው" መንፈሳዊ ባሕሪያት አንጻር፣ ከመለኮታዊ ፍቃድና እውነት አንጻር፣ ከክፉ መናፍስት ፍላጎትና የጠላትነት ማንነት አንጻር፤ በምንም መንገድ ያልተፈሸ፤ ዝምብሎ ጎበዝ ተማሪ ከመሆን፣ ሐብታም ከመሆን፣ ባለቤት ባለመኪና ከመሆን አንጻር ብቻ የተለካ በክፉ ምሪት የተንጋደደ ውድቀት ነው (በሶሻሊዝም እርሾ የተቦካውን ሊጥ አሁን ድረስ ጋግረን እየበላን እንደሆነ እናጢን)፡፡

◈ የአዳም ልጆች ሁሉ ከእግዚአብሔር ፈቃደ አሳብ እንዲለዩ በማድረግ የገነትን ተንኮል የጀመረው ዲያቢሎስ፤ ዓለም እስከምታልፍበት የመጨረሻዋ ሰኮንድ ድረስ ነፍሳት ወደ አምላካቸው መስመር እንዳይመለሱ "በታላቅ እልህና ፍጥነት" ይሠራል፡፡ ግን የአባት ቤት የልምድ ኑሮ ይህንን የዕድሜ ዘመን ጨካኝ ባላንጣ አያውቀውም፡፡ ሊያውቀው የሚችልበት ስፍራም ላይ አልቆመም፡፡ የዘልማድ ኑሮ ጉዳዩ ሁሉ የሚያጠነጥነው ስለ ሥጋ ብቻ ስለሆነ፤ በሥጋ ውስጥ የሚሰወረውን አጥፊ ኃይል ጨርሶ አያየውም፡፡

◈ እንኪያሳ፥ የክፉው መንፈስ ሠራዊት በረቂቅ ተፈጥሮው ታግዞ በሰው ልጆች ባሕሪይ ውስጥ ዘልቆ በመግባት፤ ክፉ ልምዶችን እያሳደገ፥ መልካም ልምዶችን እያኮሰሰ፤ ሥጋዊ ልማዶች በእጥፍ እንዲጨምሩ ከእውቀት ዛፍ በስተኋላ እየተሸጎረ (የሥጋ ፈቃድ የሚጨምረው አዳዲስ ነገራትን ባወቀን ልክ እንደሆነ ያስተውሏል)፤ የነፍስ ልምዶች በጭራሽ እንዳይኖሩ የእምነት ገጽታዎችን ደብዛቸውን እያጠፋ፤ አብራም በዘመኑ ተለይቶአቸው የወጣቸውን ሰዎች አድርጎን በሐዲስ ኪዳን ጊዜም ላይ ሆነን ብሉይን (ፍዳ ዘመንን) በተጨባጭ እንድንኖር አድርጎናል፡፡ (ኦሪት ዘፍጥረት 12፥1)

እኛስ እንዴት እያሰብን ነው!

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
◈ ጥቂት የማንባል ሰዎች በዚህ በመንፈሳዊው ዓለም ላይ የማንገናዝበው ጉዳይ ቢኖር መቆየትን ነው፡፡ ኃይልን መልበስ በጣም እንፈልጋለን፥ ነገር ግን 'ቆዩ' ያለውን ቃል እንዘለዋለን፡፡ በዚህም ሳቢያ ተንበርክከን የጸለይነው ጸሎት ምላሽ ሳይቆይ እንዲመጣ እንወዳለን፡፡ ዛሬ የጀመርነው ስግደት ዛሬውኑ ኃይል እንዲሰጠን እንቸኩላለን፡፡ አሁን ያለቀስነው እንባ ወዲያኑ እንዲታበስ እንፈልጋለን፡፡

◈ ነገር ግን ሳይቆይ የሚመጣ ነገር ሳይቆይ ሊሄድ እንደሚገባው አናስተውልም፡፡ በመቆየት እውነታ ውስጥ እግዚአብሔር አደራጅቶ በትክክለኛው ሰዓት የሚሰጠን ነገር እኛ ካስፈለገን ሰዓት እንደሚበልጥ አናውቅም፡፡ በመሆኑም፤ ኃይልን እስክንለብስ በኢየሩሳሌም መቆየት አቅቶን፤ በቶሎ የሚተረጎም መፍትሔ ፍለጋ ወጥተን ሄደን፤ "ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው" የሚለውን ቃል ተሻግረን፥ "መሆን ያለበት ሁሉ በኛ ጊዜ ውስጥ ይለፍ" ብለን የእግዚአብሔርን ሥራ ውብነት ከኑሮአችን አርቀን፤ ላንጨርሰው መንገዱን እየጀመርን፥ የወከባ ሰዓትን የጊዜያችን መገለጫ እናደርጋለን፡፡ በመቆየት ጸጋ ውስጥ ቆይተው የቆየች አገራችንን ያቆዩልን አባቶቻችን ይህንን የመቆየት ኃይል በጣም ያውቁታል፡፡

◈ እንኪያስ፥ ቃሉን እየጠበቁ ይቆያሉ፡፡ ጸጋቸውን እያከበሩ ይጠብቃሉ፡፡ የእያንዳንዷ ቀን አካሄዳቸውን ከኢየሩሳሌም ውስጥ ያረጉታል፡፡ አምልኮትን አያቆሙም፡፡ በዚህም ከጊዜ ወደ ጊዜ ኃይላቸው እያደገ እያደገ ይመጣል፡፡ ጽድቃቸው መነበብ ይጀምራል፡፡ ክብሩን ይገልጡታል፡፡ ሞገሱ በገጻቸው ይታያል፡፡ ምክንያቱም ጌታ እንዲህ ያለውን ቃል ኖረውበታል "ኃይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ቆዩ፡፡" እኛስ ውዶች እንዴት እያሰብን ይሆን!

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
2
◈ ቅዱስ ዮሐንስ እስከ መስቀል ድረስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለዉን መከራ በማየቱ ከዚያ ዕለት ጀምሮ 70 ዘመን ሙሉ ፊቱ በኅዘን የተቋጠረ በመሆኑ (ቁጽረ ገጽ) ሆኖ ኖሯል። ቅዱስ ዮሐንስ ብዙ ተጋድሎን አድርጐ ዓለምን ሁሉ ዞሮ ካስተማረ ቦኃላ በመጨረሻም ደቀ መዝሙሩ አብሮኮስን ከወንድሞችም ሌሎች ሁለትን መርጦ መቆፈሪያ ይዘው ይከተሉት ዘንድ አዘዘ፡፡ ጕድጓድም እንዲቆፍሩ አዘዘ ከዚያም ወረዶ ቆመ ልብሱንም አስወገደ የበፍታ ቀሚስ በቀር ሌላ አላረገም ነበር፡፡ እየጸለየ ወደ ከተማም አሰናበታቸው፡፡

◈ በክርስቶስ ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ ለሕዝብ ይነግሩአቸው ዘንድ አዘዘ ሁሉም እንደየ ስራቸው ጌታ እንደሚከፍላቸው ነገራቸው፡፡ ካዛም በኋላ እንዲህ አለ "እኔ ከሁላችሁም ደም ንፁሕ ነኝ" ከእግዚአብሔር ትእዛዝና ሕግ ሳልነግራችሁ የተውኩት ምንም ምን የለምና እናንተም ከእንግዲህ ከቶ ፊቴን አታዩም አላቸው፡፡ እነርሱም እጅና እግሮቹን ስመውት ትተውት ሄዱ ሲመለሱም ልብስና ጫማ እንጂ ምንም አላገኙም እግዚአብሔርንም አመሰገኑት፡፡

◈ ወልደ ነጐድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ዘጠና ዓመትም ኖረ፤ እንደባላሟሎቹ ሐዋርያት በመሰየፍ ሞትን አለቀመሰም፡፡ ‹‹ያ ደቀ መዝሙር አይሞትን እንዲል›› ዮሐ 21 ስለ ድንግልናውና ስለንጽሕናው ይህ ሁሉ ሆነ፡፡ በዚህ በከበረ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን፣ ይቅርም ይበለን በእውነት። አሜን

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
3👍1
◈ ዛሬ ላይ ሰዎች ቅዱሳን መልአክት እንጂ ርኩሳን መልአክት እንዳሉ ፍጹም በዘነጋ አካኋን ያለ ጥንቃቄ ተዘናግተው ይኖራሉ፡፡ የአጥፊ መናፍስት ነገድ ግን በተቻለው አቅም የሰው ልጆችን ሁሉ ሰብስቦ ያጠፋ ዘንድ እያንዳንዷን የሰኮንድ ስባሪ በሥራ ላይ ያውላታል፤ እያዋላትም ነው፡፡ ይሄ እኛ እስከመፈጠሩም የረሳነው ክፉ ባላንጣ፤ እርሱ የዘወትር ሥራው እንደሆንን አስታውሶን፤ ባሕሪያችን ውስጥ ገብቶና ጠባያችንን ተመሳስሎ፤ ውስጣዊ ሰውነታችንን መኖሪያ ቦታው በማድረግ በእያንዳንዱ ቀናችን ውስጥ ውሎአችንን ተጋርቶ በመኖር፤ ብዙ ጥፋት ያጠፋ ዘንድ ከኛ ስንፍና የተነሣ ዕድል ኖሮት ሳለ፤ ቢሆንም ግን እንዳሰበው ያህል ሮጦ ሊያወድም አልቻለም፡፡ ለምን?

◈ ምክንያቱም... ያ ዝም ብለን የምንጠራው ቅዱስ፣ ትኩስ ሻይ ሲደፋብን ስሙን የምናነሣው ቅዱስ፣ ከእውነት ስንናገር ማረጋገጫችን እናደርገው ዘንድ የምንጠራው ቅዱስ፣ ስዕሉን ባየን ጊዜ ሁሉ ፈጥነን የምንስመው ቅዱስ፣ ስለ እርሱ ለመናገር ስንጀምር የዓይን ውኃ የሚያመጣብን ቅዱስ፣ በተጨነቅን ጊዜ ስለተሸነፍንበት ጉዳይ የምናዋየው ቅዱስ፣ በተደሰትንበት ጊዜ ለማመስገን የምንቸኩለው ቅዱስ፤ እርሱ አብዝቶ ይከተለናልና ነው፡፡ ሚካኤል ሚካኤል የምትሉ ሰዎች ሊቀ መልአኩን ፍለጋ ሩቅ አትባዝኑ፡፡ አብሯችሁ አለ፡፡ እመቤቴ እመቤቴ የምትሉ ሰዎች ድንግል ማርያም የሆነ የማይደርስበት ቦታ ላይ ያለች አትምሰላችሁ፡፡ በአጠገባችሁ ናት፡፡ ዑራኤል ዑራኤል የምትሉ ሰዎች ቅዱስ ዑራኤል እናንተ ሕይወት ውስጥ ስንት ጊዜ መጥቶ ከብዙ ከማታዩት የመናፍስት አደጋ እንደጠበቃችሁ አላወቃችሁም፡፡ መድኃኒዓለም መድኃኒዓለም ማለታችሁ ሰንት ቦታ ከስንት ነገር እንደከለላችሁ እንደምን አድርጌ ላሳያችሁ? እኛስ ይሄን መለየት ላይ እንዴት ነን?

እስቲ የእናንተንም ገጠመኝ አጋሩኝ!

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
6👍3
◈ አስተውሉ! መስቀል አሰርንም አላሰርንም ድሃን የሚገፋ ማንነት ካለን፤ በዚያን ዘመን ክርስቶስን ከገፉት አይሁዳውያን መካከል አንዱ ነን፡፡ ይሄ ማነጻጸሪያ አይደለም፡፡ ለስብከት መድመቂያነት ያገለገለ ማያያዣ አይደለም፡፡ ከመጀመሪያው አዳም የተወለድን ሁላችን በእርሱ የሆነው ሁሉ በባሕሪይ እየተተረተረ እስከ ምፅዓት እንደሚቀጥል ሁሉ፤ በዳግማዊው አዳምም ታሪክ የተፈጠሩት ክስተቶች መልክና ትውልድ እየቀየሩ በባሕሪይ መደገማቸውን ይቀጥላሉ፡፡ ባይደገሙማ "እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተም እኔን ምሰሉ" የሚለው ቃል አይቀመጥም ነበር፡፡ በአጭሩ ድሆችን የምንንቅ ሁላችን፥ "ይሄ የዮሴፍ ልጅ አይደል፥ አናውቀውም እንዴ?" ካሉት የንቀት ድምፆች ጋር አንድ ነን (ይህን አንቀጽ የምታነብ ነፍስ "ልብ ይሰጠኝ" ስትል ራሷን አትሸንግል፥ ይልቅስ የተሰጣትን ለባዊነት ተጠቅማ ስለ ንፍገት ደቂቃዎቿ ታልቅስ፥ ትታረምም)፡፡

◈ የእግዚአብሔር ልብ የተባለ ባለገናው እንዲህ ይዘምራል፦ "ለችግረኛና ለምስኪን የሚያስብ ምስጉን ነው፤ እግዚአብሔር በክፉ ቀን ያድነዋል። እግዚአብሔር ይጠብቀዋል፥ ሕያውም ያደርገዋል፥ በምድር ላይም ያስመሰግነዋል፥ በጠላቶቹም እጅ አያሳልፈውም። እግዚአብሔር በደዌው አልጋ ሳለ ይረዳዋል፤ መኝታውን ሁሉ በበሽታው ጊዜ ያነጥፍለታል።" (መዝሙረ ዳዊት 41፥1-3)

◈ ዳዊት አምላክ "እንደ ልቤ" ያለው ታላቅ ሰው ነው፡፡ በእግዚአብሔር ልብ ውስጥ ደግሞ መለኮታዊው አሳብ አለ፡፡ ከላይ በዳዊት የተገለጸው ቃል በእግዚአብሔር ልብ (በአብ) ያለ ነው፡፡ አሳቡን ካወቅን ዘንዳ፥ ፈቃዱን የመፈጸምና ያለመፈጸም መብቱ በእጃችን ሆነ ማለት ነው፡፡ አዎ... መንግሥተ ሰማያት "በመካከላችን" ናት! በረቱን ለማጽዳት ባይቻል እንኳ፤ አለመጠየፍ በራሱ ራሱን የቻለ ክርስቲያናዊ ስብዕና ነው፡፡ ለወደቁት የሚታመም ሰውነት፣ ለተራቡት የሚያዛጋ ሆድ፣ ለተጠሙት የሚደርቅ ጉሮሮ፣ ለተራቆቱት የሚበርደው አካል፣ ለደኸዩት የሚቸገር ቸርነት የሌለው ግለሰብ፤ የቱን ያህል ሃይማኖተኝነት ይኑረው የእግዚአብሔርን ቃልና እውነት የሚገልጥ ልዕልና ላይ አይደርስም፡፡

እግዚአብሔር ሁላችንንም ይባርከን! እንረዳዳ፣ እንተጋገዝ!
https://t.me/haile_gebriel_tube_bot

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
2👍2
◈ ክርስቲያኖች ዓለም ለእነርሱ በጭራሽ ቦታ እንደሌላት ማስተዋል እንዲያቅታቸው፤ አጥፊው ኃይል በአራቱም የምድር ማዕዘናት ምቹ መጠጊያዎችን አበጅቶ "እስቲ አረፍ በሉ" ይላል፡፡ "እሺ" ብለው ማረፊያ ያመቻቹ ክርስቲያኖች ሲኖሩ ታዲያ፤ ጌታ "የሰው ልጅ" ብሎ የጠራው ከእግዚአብሔር ያልተለየ ሥጋ መሆናቸው ቀርቶ የቀበሮ ወይንም የሰማይ ወፎች ሥጋ ሆኑ ማለት ነው፡፡ በእውነትም ይህቺ ዓለም የምትመቸው እንደ እባብ ለሚናደፉ፣ እንደ ጊንጥ ለሚመርዙ፣ እንደ ጅብ ለሆድ ለሚኖሩ፣ እንደ አሳማ በቃኝ ለማያውቁ፣ እንደ ቀበሮ ጣዝማ ለሚልሱ፣ እንደ በቀቀን ወሬ ለሚወዱ፣ እንደ ጃርት ለሚዋጉ፣ እንደ ነብር ደም ለሚመጡ፣ እንደ እስስት ለሚያስመስሉ፣ እንደ ፍየል ለሚቅበዘበዙ፣ እንደ ዝንጀሮ ነጥቀው ለሚሮጡ፣ እንደ ድመት ወገናቸውን ለሚበሉ ሁሉ ነው፡፡ ክርስቶስ እንደለካው የ"ሰው" መጠን ሆነው በተከበረ ውድ ሕልውና የሚመላለሱት በአንጻሩ "በዓለም ሳሉ" ማረፊያ አያገኙም፡፡

◈ ዲያቢሎስ ሰዎች ሰማያዊ መዝገባቸውን ቀደው ከእንስሳት እንደ አንዱ በመሆን በዓለም ምቾት መጠጊያ አግኝተው እንዲኖሩ በማገዝ አያሌ ነፍሳትን በስውር ጥበብ እያጠፋ ይገኛል፡፡ ይሄ ወጥመዱ ላይ ጥቂቶች ነቅተው ክርስቶስን ወደ መከተል "ሰውነት" እርምጃ ሲጀምሩ ደግሞ፤ እያንዳንዷ እንቅስቃሴያቸውን በፈተና ከቦ ትንፋሽ በማሳጣት፤ መንፈሳዊውን ጉዞ እንዲጠሉትና እንዲያማርሩት ያደርጋል፡፡ አማኞች ፈጣሪያቸውን በትክክል ማምለክ ፈልገው የሆነ እንደሆነ ዓለም መቀመጫ እንደምታሳጣቸው አስቀድመው ብርቱ ግንዛቤ ማግኘት አለባቸው፡፡ ምክንያቱም በዓለም ዙፋን ላይ ነግሦ ያለው ገዢ የቅድስናና የበጎ ነገር ሁሉ ተቃዋሚ ነው፡፡ ይህንን መሠረት ከባሕሪይው ሥር ያላኖረ ክርስቲያን፤ ጽድቅንና ድሎትን መሳ ለመሳ አናንብቦ ለመጓዝ ሲጥር፤ ሁለቱ ተቃራኒ ዋልታዎች ማንነቱ ላይ ጦርነት ከፍተው ያሰቃዩታል፡፡ (የምድር መጠጊያን የሚፈልግ መንፈሳዊ ሰው ሆደ ባሻ ነው፡፡ ራሱን በተኮሰው፣ ዓይኑን ባቃጠለው፣ ሆዱን በቆረጠው፣ እግሩን ባዳለጠው፣ ሥራው በደከመው፣ ትምህርት በከበደው፣ ምቾቱ በራቀው ቁጥር ይነጫነጫል! ያማርራል! ለምን በኔ ብቻ ይላል!)

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
👍4