HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ
2.25K subscribers
1.99K photos
96 videos
51 files
3.81K links
❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️

👇👇👇
http://www.youtube.com/@haileG2239
Download Telegram
«ልደቱ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ»
‹‹ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ::›› /ቅዱስ ያሬድ/

ጌታችን ለሰው ልጆች ብሎ፤ የሰው ልጆች ፍቅር አገብሮት ንጽሕትና ቅድስት ከኾነች ከእመቤታችን ያለ ወንድ ዘር በመጋቢት 29 ተጸንሶ ታኅሣሥ 29 በ1 ዓ.ም (ዓለም ከተፈጠረ፥ ዘመን ከተቈጠረ በ5,500 ዓመት) በበረት ተወልደ፡፡ ሰማይና ምድር የማይወስኑትን በረት ቻለው፤ ወሰነውም በሌሊት መንጋቸውን የሚጠብቁ እረኞች ነበሩ፡፡ መልአኩ መጥቶ እንዲህ አላቸው፡- ‹‹እነሆ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና፡፡ ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ›› አላቸው፡፡ (ሉቃ 2፡10-12)

ከመለአኩም ጋራ ሠራዊተ መላእክት መጥተው ‹‹ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ለዕጓለ እመሕያው /ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ/›› አሉ፡፡ ቅዱሳን መላእክትም ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ በወጡ ጊዜ እረኞቹ እርስ በርሳቸው ‹‹እንግዲህ እስከ ቤተ ልሔም ድረስ እንሂድ፣ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ›› ተባባሉና ፈጥነው መጡ፡፡ ማርያምንና ዮሴፍን ሕፃኑንም በግርግም ተኝቶ አገኙ፡፡ አይተውም ስለዚህ ሕፃን የተነገረላቸውን ነገር ገለጡ፤ የሰሙትን ሁሉ እረኞቹ በነገሯቸው ነገር አደነቁ፤ የብርሃን እናቱ እመ አምላክ ግን ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ እያሰበች ትጠብቀው ነበር፡፡ (ሉቃ 2፡13-19)

መላእክትም ሰማይ መንበሩ ምድር የእግሩ መረገጫ የሆኑለት አምላክ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ በጎል ተኝቶ በጨርቅ ተጠቅልሎ አይተውት ደስ ብሏቸው ወደ ሰማይ ቢያርጉ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በዕሪና ከመንበሩ አይተውት ‹‹ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት›› ብለው አመስግነውት በጣዕም ላይ ጣዕም፤ በጸጋ ላይ ጸጋ ተጨምሮላቸው ደስ ብሏቸዋል፡፡ ልደቱን ይሹታልና፤ መላእክትም ብቻ አይደሉም እንስሳትም አራዊትም ደስ ብሏቸዋል፡፡
እንኳን አደረሳችሁ ውድ ቤተሰቦቼ!

#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
👏2
መስገድ እና መጸለይ ስንጀምር በዙሪያችን ባሉ ሰዎች ማዕበል ይነሳብናል || ለሰይጣን ምህረት የማይደረግለት ምህረት ስለማያደርግ ነው #ethiopia 😭😰🙄 https://youtu.be/0PG2PuA5ob8
✍️ ርኩሳን መናፍስትን የማሰር መንገድ ሦስት ምድቦችን የተመረኮዙ ሦስት ቅደም ተከተሎች ሲኖሩት፤ እነርሱም፦

✓ በራስ አካል ላይ ያሉ መናፍስትን ማሰር ÷ "በሥላሴ ስም፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ በድንግል ማርያም ስም፤ ከራስ ጸጉር እስከ እግር ጥፍር ባለ የሰውነት ክፍል ውስጥ የተደበቃችሁ የጥፋት መናፍስት፥ ርኩሳት መናፍስት፥ ሁላችሁም ሠራዊታችሁን ከአካል ክፍሎቼ ላይ በመሰብሰብ በአንድነት ግንባር ላይ ወጥታችሁ ታስራችኋል!"

✓ ከራስ አካል ውጪ በዙሪያ ባሉ ሰዎች ውስጥ ያሉ መናፍስትን ማሰር ÷ "በአብ፣ በወልድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ስም፣ በልዑል እግዚአብሔር ስም፣ በወላዲተ አምላክ ስም፣ ከእኔ አካል ውጪ ዙሪያዬ ባሉ ሰዎች ውስጥ (ቤተሰብ፣ ዘመድ፣ ጓደኛ፣ ጎረቤት፣...) ያላችሁ መናፍስት ባላችሁበት አካል ሳላችሁ ግንባር ላይ ታስራችኋል፡፡ ወደእኔ መምጣት እና በውስጥ ካሉ መናፍስት ጋር መናበብ አትችሉም!"

✓ በሰው አካል ውስጥ የሌሉ መናፍስትን ማሰር ÷ "በቅዱስ ሚካኤል ስም፣ በቅዱስ ገብርኤል ስም፣... ከአካል ሥጋ ውጪ ነፋስን መስላችሁ በዙሪያዬ፣ በአየርና ተክትላችሁኝ ወደ ቤቴ በመምጣት የምታንዣብቡ መናፍስት፤ ባላችሁበት ታስራችኋል፡፡ ወደ እኔ በተጠጋችሁበት ርቀት ልክ እሳተ መለኮት ያቃጥላችሁ!" እያላችሁ ማሰር ትችላላችሁ ለሁሉም እንዲደርስ ይሄን መልእክት ሸር አድርጉ።

✍️ ማሳሰቢያ፦ መናፍስቱን የማሰሩ ሦስቱ ምድቦች ላይ መገንዘብ ያለብን አንድ ነገር አለ፡፡ ይኸውም የመጀመሪያው ቅደም ተከተል ላይ እንደተቀመጠው በራስ አካል ያሉ መናፍስት ግንባር ላይ ውጡና ታሰሩ ሲባሉ እና ቀሪዎቹ ሁለቱ ምድቦች ላይ ያሉት ከኛ ውጪ የሚያደፍጡት መናፍስት ታሰሩ ሲባሉ፤ የመታሰራቸው አፈጻጸም አንድ አይነት አይደለም፡፡ ከኛ አካል ውጪ ያሉትን "ባላችሁበት ታሰሩ" ስንል ትእዛዙ ሙሉ በሙሉ ይፈጸማል፡፡

ማለትም በሥጋ ላይ አድረው ያሉትም ሆነ በአየር ያሉት ወደኛ ሰውነት መጠጋት በፍጹም አይችሉም፡፡ በኛ አካል ውስጥ ግን ያሉት ከባሕሪያችን ጋር ተዳብለው ያሉ ስለሆኑ፤ "ታስራችኋል" ማለታችን "ተወስናችኋል" እንደ ማለት ነው የሚተረጎመው፡፡ በሌላ አገላለጽ መናፍስቱ በኛ ውስጥ መሥራት የሚፈልጉትን ሥራ በሚፈልጉት ልክና መጠን አይከናወንላቸውም፡፡

ከአቅማቸውና ከችሎታቸው ይወሰናሉ፡፡ ወይንም ዐሥር ነገር ይዘው ከነበረ ስምንቱን ይለቁታል ማለት ነው፡፡ ሁለቱ ላይ ግን መዋጋታቸውን ይቀጥላሉ፡፡ እጅግ ክፉ ናቸውና ታስረውም ቢሆን ክፋታቸውን በሚችሉት ሁሉ መግለጣቸውን አያቋርጡም፡፡ ዐሥሩንም ለቀቁ ማለት ታዲያ "መሄድ እንልጋለን" የሚሉበት የሽኝት ነጥብ ላይ ተሸንፈው ደረሱ ማለት ነው፡፡

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
8👍2🥰2
◈ የቀዳሜ ሰማእት የቅዱስ እሥጢፋኖስ ረድኤት በረከት አይለየን። በአማላጅነቱ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይሰውረን።

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
«ማርያም ማለት ሥጦታና ሀብት (ጸጋ ወሀብት) ማለት ነው።»

✍️ መጀመሪያ ከእግዚአብሔር የተሠጠችው ለእናት  አባትዋ ነው። "ልጆች የአግዚአብሔር ሥጦታዎች ናቸው" ተብሎ ተጽፎአልና።

✍️ ሁለተኛ ከእግዚአብሔር የተሠጠችው ደግሞ ለሰው ልጆች ሁሉ ምልክት ሆና ነው። "ጌታ ራሱ ምልክትን ይሠጣችኋል ፣ እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ፣ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል" ተብሎ ተጽፎአልና። (ኢሳ 7:14)

✍️ ሦስተኛ ወላጆችዋ ለእግዚአብሔር ስእለት አድርገው ወደ ቤተ መቅደስ መሥጠታቸው ደግሞ ለእግዚአብሔር የተሠጠች ሥጦታ ያደርጋታል።

✍️ አራተኛ ደግሞ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ራሱን አሳልፎ ከመሥጠቱ በፊት እመቤታችን ራስዋን "እነሆኝ የጌታ ባሪያ" ብላ ለእግዚአብሔር ሥጦታ አሳልፋ መሥጠትዋ ነው።

✍️ አምስተኛው ደግሞ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ  ራሱ እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን በመስቀል ላይ ለወዳጁ ለዮሐንስ "እናትህ እነኋት" ብሎ የሠጠ መሆኑ ነው።  "በጎ ሥጦታና ፍጹም በረከት ከብርሃናት አባት" ከላይ የሚወርዱ ናቸው። ከእነዚህ የፈጣሪ ሥጦታዎች አንድዋ እመቤታችን ናት።

እመቤታችን የሀገራችንን ፍጹም ኀዘንዋን፣ የቤተ ክርስቲያንንም ልቅሶዋን በምልጃዋ ትስማልን።

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
የጸሎት አሳብ መበታተን ምልክቶች

1) ጸሎተ ቃልን ከጀመሩ በኋላ የሚናገሩትን ፊደልና ዓረፍተ ነገር አለመስማት (በተለይ በጸሎት መጽሐፍት ንባብ ወቅት)

2) ጸሎቱን እያደረሱ ሳለ ድንገት በምን ርዕስ (ጉዳይ) ላይ አምላክን እያነጋገሩ እንደሆነ መዘንጋት

3) ጸሎተ ጊዜው ላይ ሆነው ያሉበትን ቅጽበት እስኪረሱ ድረስ በጭንቅላት ውስጥ ዝብርቅርቅና ፍቺ በሌላቸው ድምፆችና ምናቦች በመሳብ ሰምጠው መቅረት (መጀመሪያ የሚጀምረው በአንድ ቃል የሌለው ድምፅ አሊያ ቅርጽ አልባ ምናብ ነው፡፡ በመቀጠል በነፋስ እየተቀጣጠለ በፍጥነት እንደሚዛመት ሰደድ እሳት ድምፆቹና ምናቦቹ ተከታታይነት ባለው ወጥ አኳኋን እየበዙ ይሄዳሉ)

4) ተራ ቁጥር 3 ላይ ከተጠቀሰው ጋር ተቀራራቢነት ሲኖረው፤ ከውስጥ የሚፈጠሩት ድምፆችና ስዕሎች ተጨባጭ የሚመስል መልክና ገጽታ ፈጥረው ሕልም እንደምናይ አድርገው ይዘውን ይንሳፈፋሉ (ለምሳሌ የዝሙት ትዕይንቶችን፣ ያለፉ የድርጊት ትውስታዎችን፣ የተረሱ ገጠመኞችንና ንብረቶችን፣ ወደፊት የሚከናወኑ እቅዶችን ማየት)

5) እንዲሁ እንደ ተራ ቁጥር 3 ተመሳሳይ ሲሆን፤ የሚረበሹበት ድምፅ ግን ከውስጥ የሚፈጠር ሳይሆን ከውጪ የጸሎት ቦታ አቅራቢያ በሚደመጥ ንግግር ወይንም ሁካታ የሚመጣ ነው

6) የሚጸለየውን ጸሎት፣ የሚታየውን ስዕለ አድኖና ሌላም በአጠገብ ያለውን ቁስ ሰበብ (መሠረት) ያደረገ ሙግት ከራስ ጋር መግጠም (ምሳሌ የሚጸለየውን ጸሎት ምክንያት ያደረገ፦ "ጸሎቴ ይሰማ ይሁን? ይሄ ትክክለኛ ጸሎት ይሁን? ሌላ የተሻለ ጸሎት ማድረስ አለብኝ ይሆን? ይሄ የጸሎት ቃል ምን ለማለት ፈልጎ ነው? ይሄን የጸሎት መጽሐፍ ማን አዘጋጀው? ፣ ወዘተ..." እያሉ የሕሊና ድምፆችን በራስ ፈቃድ መፍጠርና ለጥያቄዎቹ መልስ ለመስጠት እየዳከሩ እየዳከሩ ድምፆቹን በማብዛትና በማድመቅ በዛው ጭልጥ ማለት)

7) አእምሮ ላይ እፍን በሚያደርግ ድብርታም ስሜት ባለው አዚም ሲንገላጅጁ ቆይቶ ከእንቅልፍ ተቀስቅሰው እንደ ነቁ አይነት መሃል መሃል ላይ መባተት (ይሄ ምልክት ካለ ደጋግሞ ማፋሸክ፣ የዓይን ጨረር መጥበብ፣ የእንባ ነጠብጣቦች መውረድ፣ የራስ ቅል መክበድ፣ የያዙት መጽሐፍ ወይንም የለበሱት ልብስ (ነጠላ) ተንሸራቶ ሲወደቅ አለማወቅና ባሉበት ቦታ ላይ አግድም መተኛት ተጨማሪ ምልክቶች ሆነው ይከሰታሉ)

8) ሰመመንን በተጠጋ ድባብ ውስጥ ሆኖ ከጸሎት አንቀጽ ወደ ጸሎት አንቀጽ እየተሻገሩ መቆየት (ይሄ ምልክት
ካለ እያንዳንዱ ተብሎ የሚታለፈው አንቀጽ ምን እንደነበረ ቢጠየቁ አያውቁም)

9) ጸሎትን እያሰሙ ጥቂት እንደቆዩ የትኩረት አቅም ቀንሶ መንፈሳዊውን ሐሴትና ትርጉም ማጣት

10) ጸሎተ ቆይታውን ቶሎ ፈጽሞ ስለ ቀጣዩ አድራጎት እያምሰለሰሉ መቁነጥነጥ (ሰዓት ደጋግሞ ማየት፣ የጸሎት
መጽሐፉን ቀሪ ገጾች መቁጠር)

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
👍1
"ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።" (1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፥18-19)

◈ የአብራም ጎረቤቶች ከቤተሰባቸው ሲዋረሱት የቆዩት የአኗኗር ሂደት ትክክል እንደሆነ ነው የሚያስቡት፡፡ ለእነርሱ መብላት፣ መጠጣትና የሚያስፈልጋቸውን በወቅቱ ማግኘት፤ የሕይወት ጠቅላላ ትርጉም ሆኗቸዋል፡፡ የዛሬውም የእኛ የአባት ቤት ኑሮም ይኸው ነው፡፡ በሥጋ መደላደልና በቁስ ስኬት ላይ መቆም፤ ቤተሰብ "ልጄ በሚገባ አኩርቶኛል" የሚልበት ሙሉ መለኪያው ነው፡፡ ይሄም መመዘኛ በዓለም ሰፊ አውታር የተለመደ፤ ኑሮን ስለማሸነፍ የሚናገር ሚዛን ስለሆነ፤ እንዲሁ በደፈናው "ትክክል" ተደርጎ ማኅተም ተዘግቶበታል፡፡ ከዘላለም ሕይወት አንጻር፣ "ሰውን ሰው ካሰኘው" መንፈሳዊ ባሕሪያት አንጻር፣ ከመለኮታዊ ፍቃድና እውነት አንጻር፣ ከክፉ መናፍስት ፍላጎትና የጠላትነት ማንነት አንጻር፤ በምንም መንገድ ያልተፈሸ፤ ዝምብሎ ጎበዝ ተማሪ ከመሆን፣ ሐብታም ከመሆን፣ ባለቤት ባለመኪና ከመሆን አንጻር ብቻ የተለካ በክፉ ምሪት የተንጋደደ ውድቀት ነው (በሶሻሊዝም እርሾ የተቦካውን ሊጥ አሁን ድረስ ጋግረን እየበላን እንደሆነ እናጢን)፡፡

◈ የአዳም ልጆች ሁሉ ከእግዚአብሔር ፈቃደ አሳብ እንዲለዩ በማድረግ የገነትን ተንኮል የጀመረው ዲያቢሎስ፤ ዓለም እስከምታልፍበት የመጨረሻዋ ሰኮንድ ድረስ ነፍሳት ወደ አምላካቸው መስመር እንዳይመለሱ "በታላቅ እልህና ፍጥነት" ይሠራል፡፡ ግን የአባት ቤት የልምድ ኑሮ ይህንን የዕድሜ ዘመን ጨካኝ ባላንጣ አያውቀውም፡፡ ሊያውቀው የሚችልበት ስፍራም ላይ አልቆመም፡፡ የዘልማድ ኑሮ ጉዳዩ ሁሉ የሚያጠነጥነው ስለ ሥጋ ብቻ ስለሆነ፤ በሥጋ ውስጥ የሚሰወረውን አጥፊ ኃይል ጨርሶ አያየውም፡፡

◈ እንኪያሳ፥ የክፉው መንፈስ ሠራዊት በረቂቅ ተፈጥሮው ታግዞ በሰው ልጆች ባሕሪይ ውስጥ ዘልቆ በመግባት፤ ክፉ ልምዶችን እያሳደገ፥ መልካም ልምዶችን እያኮሰሰ፤ ሥጋዊ ልማዶች በእጥፍ እንዲጨምሩ ከእውቀት ዛፍ በስተኋላ እየተሸጎረ (የሥጋ ፈቃድ የሚጨምረው አዳዲስ ነገራትን ባወቀን ልክ እንደሆነ ያስተውሏል)፤ የነፍስ ልምዶች በጭራሽ እንዳይኖሩ የእምነት ገጽታዎችን ደብዛቸውን እያጠፋ፤ አብራም በዘመኑ ተለይቶአቸው የወጣቸውን ሰዎች አድርጎን በሐዲስ ኪዳን ጊዜም ላይ ሆነን ብሉይን (ፍዳ ዘመንን) በተጨባጭ እንድንኖር አድርጎናል፡፡ (ኦሪት ዘፍጥረት 12፥1)

እኛስ እንዴት እያሰብን ነው!

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
◈ ጥቂት የማንባል ሰዎች በዚህ በመንፈሳዊው ዓለም ላይ የማንገናዝበው ጉዳይ ቢኖር መቆየትን ነው፡፡ ኃይልን መልበስ በጣም እንፈልጋለን፥ ነገር ግን 'ቆዩ' ያለውን ቃል እንዘለዋለን፡፡ በዚህም ሳቢያ ተንበርክከን የጸለይነው ጸሎት ምላሽ ሳይቆይ እንዲመጣ እንወዳለን፡፡ ዛሬ የጀመርነው ስግደት ዛሬውኑ ኃይል እንዲሰጠን እንቸኩላለን፡፡ አሁን ያለቀስነው እንባ ወዲያኑ እንዲታበስ እንፈልጋለን፡፡

◈ ነገር ግን ሳይቆይ የሚመጣ ነገር ሳይቆይ ሊሄድ እንደሚገባው አናስተውልም፡፡ በመቆየት እውነታ ውስጥ እግዚአብሔር አደራጅቶ በትክክለኛው ሰዓት የሚሰጠን ነገር እኛ ካስፈለገን ሰዓት እንደሚበልጥ አናውቅም፡፡ በመሆኑም፤ ኃይልን እስክንለብስ በኢየሩሳሌም መቆየት አቅቶን፤ በቶሎ የሚተረጎም መፍትሔ ፍለጋ ወጥተን ሄደን፤ "ነገርን ሁሉ በጊዜው ውብ አድርጎ ሠራው" የሚለውን ቃል ተሻግረን፥ "መሆን ያለበት ሁሉ በኛ ጊዜ ውስጥ ይለፍ" ብለን የእግዚአብሔርን ሥራ ውብነት ከኑሮአችን አርቀን፤ ላንጨርሰው መንገዱን እየጀመርን፥ የወከባ ሰዓትን የጊዜያችን መገለጫ እናደርጋለን፡፡ በመቆየት ጸጋ ውስጥ ቆይተው የቆየች አገራችንን ያቆዩልን አባቶቻችን ይህንን የመቆየት ኃይል በጣም ያውቁታል፡፡

◈ እንኪያስ፥ ቃሉን እየጠበቁ ይቆያሉ፡፡ ጸጋቸውን እያከበሩ ይጠብቃሉ፡፡ የእያንዳንዷ ቀን አካሄዳቸውን ከኢየሩሳሌም ውስጥ ያረጉታል፡፡ አምልኮትን አያቆሙም፡፡ በዚህም ከጊዜ ወደ ጊዜ ኃይላቸው እያደገ እያደገ ይመጣል፡፡ ጽድቃቸው መነበብ ይጀምራል፡፡ ክብሩን ይገልጡታል፡፡ ሞገሱ በገጻቸው ይታያል፡፡ ምክንያቱም ጌታ እንዲህ ያለውን ቃል ኖረውበታል "ኃይልን እስክትለብሱ ድረስ በኢየሩሳሌም ቆዩ፡፡" እኛስ ውዶች እንዴት እያሰብን ይሆን!

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
2
◈ ቅዱስ ዮሐንስ እስከ መስቀል ድረስ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበለዉን መከራ በማየቱ ከዚያ ዕለት ጀምሮ 70 ዘመን ሙሉ ፊቱ በኅዘን የተቋጠረ በመሆኑ (ቁጽረ ገጽ) ሆኖ ኖሯል። ቅዱስ ዮሐንስ ብዙ ተጋድሎን አድርጐ ዓለምን ሁሉ ዞሮ ካስተማረ ቦኃላ በመጨረሻም ደቀ መዝሙሩ አብሮኮስን ከወንድሞችም ሌሎች ሁለትን መርጦ መቆፈሪያ ይዘው ይከተሉት ዘንድ አዘዘ፡፡ ጕድጓድም እንዲቆፍሩ አዘዘ ከዚያም ወረዶ ቆመ ልብሱንም አስወገደ የበፍታ ቀሚስ በቀር ሌላ አላረገም ነበር፡፡ እየጸለየ ወደ ከተማም አሰናበታቸው፡፡

◈ በክርስቶስ ሃይማኖት ይጸኑ ዘንድ ለሕዝብ ይነግሩአቸው ዘንድ አዘዘ ሁሉም እንደየ ስራቸው ጌታ እንደሚከፍላቸው ነገራቸው፡፡ ካዛም በኋላ እንዲህ አለ "እኔ ከሁላችሁም ደም ንፁሕ ነኝ" ከእግዚአብሔር ትእዛዝና ሕግ ሳልነግራችሁ የተውኩት ምንም ምን የለምና እናንተም ከእንግዲህ ከቶ ፊቴን አታዩም አላቸው፡፡ እነርሱም እጅና እግሮቹን ስመውት ትተውት ሄዱ ሲመለሱም ልብስና ጫማ እንጂ ምንም አላገኙም እግዚአብሔርንም አመሰገኑት፡፡

◈ ወልደ ነጐድጓድ ቅዱስ ዮሐንስ ዘጠና ዓመትም ኖረ፤ እንደባላሟሎቹ ሐዋርያት በመሰየፍ ሞትን አለቀመሰም፡፡ ‹‹ያ ደቀ መዝሙር አይሞትን እንዲል›› ዮሐ 21 ስለ ድንግልናውና ስለንጽሕናው ይህ ሁሉ ሆነ፡፡ በዚህ በከበረ ሐዋርያ ጸሎት ይማረን፣ ይቅርም ይበለን በእውነት። አሜን

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
3👍1
◈ ዛሬ ላይ ሰዎች ቅዱሳን መልአክት እንጂ ርኩሳን መልአክት እንዳሉ ፍጹም በዘነጋ አካኋን ያለ ጥንቃቄ ተዘናግተው ይኖራሉ፡፡ የአጥፊ መናፍስት ነገድ ግን በተቻለው አቅም የሰው ልጆችን ሁሉ ሰብስቦ ያጠፋ ዘንድ እያንዳንዷን የሰኮንድ ስባሪ በሥራ ላይ ያውላታል፤ እያዋላትም ነው፡፡ ይሄ እኛ እስከመፈጠሩም የረሳነው ክፉ ባላንጣ፤ እርሱ የዘወትር ሥራው እንደሆንን አስታውሶን፤ ባሕሪያችን ውስጥ ገብቶና ጠባያችንን ተመሳስሎ፤ ውስጣዊ ሰውነታችንን መኖሪያ ቦታው በማድረግ በእያንዳንዱ ቀናችን ውስጥ ውሎአችንን ተጋርቶ በመኖር፤ ብዙ ጥፋት ያጠፋ ዘንድ ከኛ ስንፍና የተነሣ ዕድል ኖሮት ሳለ፤ ቢሆንም ግን እንዳሰበው ያህል ሮጦ ሊያወድም አልቻለም፡፡ ለምን?

◈ ምክንያቱም... ያ ዝም ብለን የምንጠራው ቅዱስ፣ ትኩስ ሻይ ሲደፋብን ስሙን የምናነሣው ቅዱስ፣ ከእውነት ስንናገር ማረጋገጫችን እናደርገው ዘንድ የምንጠራው ቅዱስ፣ ስዕሉን ባየን ጊዜ ሁሉ ፈጥነን የምንስመው ቅዱስ፣ ስለ እርሱ ለመናገር ስንጀምር የዓይን ውኃ የሚያመጣብን ቅዱስ፣ በተጨነቅን ጊዜ ስለተሸነፍንበት ጉዳይ የምናዋየው ቅዱስ፣ በተደሰትንበት ጊዜ ለማመስገን የምንቸኩለው ቅዱስ፤ እርሱ አብዝቶ ይከተለናልና ነው፡፡ ሚካኤል ሚካኤል የምትሉ ሰዎች ሊቀ መልአኩን ፍለጋ ሩቅ አትባዝኑ፡፡ አብሯችሁ አለ፡፡ እመቤቴ እመቤቴ የምትሉ ሰዎች ድንግል ማርያም የሆነ የማይደርስበት ቦታ ላይ ያለች አትምሰላችሁ፡፡ በአጠገባችሁ ናት፡፡ ዑራኤል ዑራኤል የምትሉ ሰዎች ቅዱስ ዑራኤል እናንተ ሕይወት ውስጥ ስንት ጊዜ መጥቶ ከብዙ ከማታዩት የመናፍስት አደጋ እንደጠበቃችሁ አላወቃችሁም፡፡ መድኃኒዓለም መድኃኒዓለም ማለታችሁ ሰንት ቦታ ከስንት ነገር እንደከለላችሁ እንደምን አድርጌ ላሳያችሁ? እኛስ ይሄን መለየት ላይ እንዴት ነን?

እስቲ የእናንተንም ገጠመኝ አጋሩኝ!

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
6👍3