HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ
2.25K subscribers
1.99K photos
96 videos
51 files
3.81K links
❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️

👇👇👇
http://www.youtube.com/@haileG2239
Download Telegram
◈ በተደጋጋሚ ልናገረው የሞክርኩት ጉዳይ ነው፡፡ መንፈሳዊ ሕይወት እምነትና ዕውቀትን አጣምሮ መያዝ በጣም ይፈልጋል፡፡ ከሁለቱ አንዱ በጎደለበት ቦታ ላይ የሥጋና የክፉ መናፍስት ፈቃድ ያይላል፡፡ አምነን ማወቅና ያወቅነውን በእምነት መኖር ሃይማኖትን በመገለጥ እንድንመላለስበት ያደርጋል፡፡ ሳያምኑ ማወቅና ደግሞ ያወቁትን በእምነት ኑሮ አለመተርጎም ቅንጣት አያስጉዝም፡፡ ሃይማኖትን እንደ ድርጅት አሊያ እንደ ፖለቲካ መዋቅር ከመከተል የዘለለ ምንም አይፈይድም፡፡

◈ እንድታነቡና አንብባችሁም ያነበባችሁትን ያህል እንድትተገብሩ መልእክት የሚተላለፈው ስለዚህ ነው፡፡ በማወቅና በማመን ያልተገነባ መንፈሳዊ ስብዕና ፍሬዎችን እያፈራ በሕይወት ውስጥ የሚስተዋል ለውጥ ማምጣት አይችልም፡፡ ሲሆን አዙሪት ውስጥ ዝምብሎ እንደሚሽከረከር ቁስ ሆኖ ከጀመረበት ዞሮ የሚመጣ፤ የቀን እንጂ የሕይወት ለውጥ የሌለው፤ እንዲሁ በከንቱ የሚያልፉ ሰዓታትን የሚመራ ነፍስ አልባ ፍጡር ይሆናል፡፡

◈ እና ምን ይሻላል? አታነቡምን? አታስተውሉም? አትተገብሩም?.. ምን ይሻላል ሌላ መንገድ እኮ የለም፡፡ አምነህ ዕውቀት ትጨምራለህ ባወከው ውስጥም ማመንህን ታሳያለህ፡፡ እንደገና ባመንከው እየተመራህ ሌላ ዕውቀት ትጨምራለህ.. ሌላ መንገድ የለም! አቋራጭ እውነት የለም፡፡ ነገሩስ አልኩ እንጂ ተመርጠው ያሉ፥ የእርሱ ለመሆን ራሳቸውን አሳልፈው የሰጡ፥ ልበ ንጽሕና ከቅንነት ጋር ያላቸው፥ ስለ ለውጥ የሚቃጠል ታላቅ የፍላጎትን መሥዋዕት መባዕ የሚያደርጉ "በጎቹ" ብቻና ብቻ ናቸው ድምፁን የሚሰሙት፡፡

🙏 አስተዉሉ! መስማት የሚፈቅዱት ይሰሙታል፡፡ በአንጻሩ መስማት የማይፈቅዱትም በምንም አይነት ተዓምርና ኃይል አይሰሙም፡፡ ዮሐንስ አባታችን እንዳለው ከእግዚአብሔርና ከስሕተት መንፈስ የሆኑት በዚህ ይለያሉ ብሎናልና፡፡
======//======

#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
👍8
አባቶቻችን አሁንም ይናገራሉ | ጸሎትና ስግደት ከበደኝ ልምትሉ | የትዳር አጋር እንዴት ልምረጥ | የእስላም ዛር መናፍስቶች ፈተና | በማለዳ ንቁ 2024 😭😰 https://youtu.be/T6N4SFcq6Lw
+• ሰውን ወዳጅ አምላክ •+

የሰው ልጅ የሕይወት አቅጣጫ ጠፍቶበት አንዴ ባሕሩን፥ አንዴ ድንጋዩን፥ አንዴ ደመና፥ አንዴ ሰማዩን እያመለከ ለዘመናት ተሰቃይቷል። የበረታበት ፍጥረት ሁሉ አምላኩ እየመሰለው ከመሬት ሲደፋ፥ ፍጥረት የሆኑትን ፈጣሪ እያለ መስዋእት ሲሰዋም እልፍ የጨለማ ዘመናት አልፈዋል። የፈጣሪና የፍጡር መለያ መስመር ጠፍቷቸው በመዳከር ኖረው ብርሃን ሳያዩ ያለፉትን መቼም ዘመን ይቁጠራቸው። እንዲህ ያለውን ብርቱ ጨለማ ግን “እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ፈጠረ” (ዘፍ 1፡1) የሚለው የእውነት ብርሃን ሲፈነጥቅ ተበተነ። ዛሬ ለጆሯችን ብርቅ ስላልሆነ እንደ ቀላል ብናየውም፥ ይህ ስንኝ ብቻውን በዘመኑ ብዙዎችን አስደንግጧል። መስዋእት የተቃጠለለት ሰማይም፥ ብዙ ደም የፈሰሰላት ምድርም አስገኚ እንዳላቸው የተረዳ ሁሉም ወደ ቀልቡ እንዲመለስ ሆኗል።

የሰው ልጅ ማስተዋል ጎድሎት የፈጣሪን ሀለዎት ለመረዳት ብዙ አነከሰ እንጂ፥ ፍጥረታት በራሳቸው አስገኚያቸውን የሚመሰክሩ ናቸው። ታላቁ ንጉሥ ዳዊት በመዝሙሩ “ሰማያት የእግዚአብሔርን ክብር ይናገራሉ፥ የሰማይም ጠፈር የእጁን ሥራ ያወራል።” (መዝ 19፡1) ያለው ይኽንን መሠረታዊ እውነት ስለተገነዘበ ነው። ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ቢሆን ተፈጥሮ እንደ መጽሐፍ የሚነበብ እንደሆነ በትርጓሜው ላይ ያነሳል። ይህንን ለማድረግ ግን ከሕይወት ጥድፊያ አፍታ ወስዶ፥ በጥሞና መንፈስ ሆኖ ተፈጥሮን መመልከት ያስፈልጋል። እኛ ግን በሥነ-ፍጥረት መደነቅ ለፈላስፋ፥ ስለ ተፈጥሮ መቀኘት ለባለቅኔ ብቻ የተተወ ይመስል፤ ሥነ-ፍጥረቱን ሁሉ ልብ ማለቱን ተውነውና፥ በራሳችን እጅ ታላቅ የጥበብ በር ከረቸምን።

በዚህ ዘመን ሁላችንም የተነጠቅነው ነገር ቢኖር ዝምታን ነው። ዘመኑ ጸጥታ ፈልገን ብቻችንን ብንቀመጥ “ምነው ብቻህን?”፥ ከፈጣሪ በውስጣችን መነጋገር ፈልገን አንደበታችንን ያዝ ብናደርግ “ምነው ዝም አልክ?” የምንባልበት ነው። ዝም ማለት ወንጀል እስኪመስል ድረስ ብዙዎች ዝምታን ይፈራሉ። ዝምታ በሕይወታችን ስለማይነግሥ ተፈጥሮን የምናይበት፥ ከራሳችን ጋር የምንሆንበት፥ በጸሎት የጠየቅነውን በዝምታ ምላሽ የምንጠብቅበት ጊዜ የለንም። ይህንን ማድረግ ብንችል ኖሮማ፥ አባቶቻችንን ፍጥረታት “ለአንክሮ ለተዘክሮ ተፈጥረዋል” ያሉትን በተረዳን፥ ከመዝሙረኛው ዳዊት ጋርም “የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ፥ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን፥ ታስበው ዘንድ ሰው ምንድር ነው? ትጎበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድር ነው?” (መዝ 8፡1) ብለን ማመስገን በቻልን ነበር።

በቤተክርስቲያን የቅድሥት ሥላሴ ሥዕለ አድኅኖ ሲሣል እግዚአብሔር ዓለምን ሁሉ በእጁ የያዘ ተደርጎ ይሣላል። ፍጥረትን ሁሉ በመሃል እጁ ይዞ፥ ዓይኖቹ ግን በመልኩ እና በምሳሌው ወደፈጠረው ወደ ሰው ልጅ ናቸው። አምላካችን ቅርጻቸው፥ ግርማቸው፥ ባሕርያቸው ሁሉ ከሚያስገርሙን ፍጥረቶች በላይ ሰውን ማክበሩ ያስገርማል። አብርሃም አምላኩን ሲፈልግ “የፀሐይ አምላክ ተናገረኝ” ቢልም፥ እግዚአብሔር ግን ራሱን “የአብርሃም አምላክ፥ የይስሐቅም አምላክ፥ የያዕቆብም አምላክ ነኝ” (ዘጸ 3፡6) ማለትን እንደመረጠ ስናስብ እናደንቃለን።

ጌታ ሆይ፥ አንተ ሁሉን በመሃል እጅህ ይዘህ ሳለ፥ የእኛ ሕይወት ያሳስብሃል። ከሞቃቷ ፀሐይ ይልቅ ሙቀቷ የሚያቃኝለው ደካማ ፍጥረት፥ ከመሬቱ ይልቅ ወደ መሬት ገብቶ ከአፈር የሚዋሐደው የሰው ልጅ ጉዳይ ትኩረትህ መሆኑን ማሰብ እጅን በአፍ ያስጭናል። በዚህ አድካሚ ዓለም ስንኖር፥ አንተ እንደምትወደን ከማሰብ በላይ የሚያጽናናን የለም። ለክብር ተፈጥረን በመዋረድ፥ ለንጽሕና ተፈጥረን በማደፍ ሕይወታችን እንዳይደመደም በጸጋህ ጠብቀን። ሰውን ወዳጅ እና ይቅር ባይ የሆንክ አምላካችን ሆይ፥ የዓለም ጨው መሆን እንዳቃተን አይተህ፥ ድንጋይ ናቸው ብለህ አትጣለን፥ ታገሰን እንጂ። የዓለም ብርሃን መሆን እንዳልቻልን አይተህ፥ ከዕንቅብ በታች አታስቀምጠን፥ እስክናበራ ጠብቀን እንጂ።
======//======

#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
👍5
31 አረማዊ ደብተራዎች የደገሙት ድጋም ያመጣው ጣጣ || የአዳልሞቴ እና የጠቋር መንፈሶች ከባዱ ፈተና | መታዘዝ ሙላትን ያመጣል | በማለዳ ንቁ 2024 😭😭😰 https://youtu.be/fq0UHM5UNOs
🥰6
"ስንሞት ያመናል እንዴ?"

◈ ሕፃናት መጠየቅ ይወዳሉ። አንዴ መጠየቅ ከጀመሩ በኋላ ደግሞ ከእነርሱ የሚወጣው "ለምን ሆነ?" የሚለው የጥያቄ ዝናብ እንዲህ በቀላሉ ቶሎ የሚያባራ አይደለም። እኛም በእነዚህ ጥያቄዎቻቸው ቶሎ ተሰላችተን ወይም ተበሳጭተን ይሆናል። ይሁን እንጂ ጉዳዩ ግን የሕፃናቱ አዲስ አእምሮ ራሱን የሚያሳድግበትና የነገ ማንነታቸውን የሚቀርጽበት ወሳኝ ሂደት ነው። የነገ ወጣቶችን ማንነት የሚቀርጹት ዛሬ "ለምን?" እያሉ ለሚጠይቁ ሕፃናት የምንመልሳቸው መልሶች ናቸው። ስለዚህ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባናል።

◈ በጠና የታመመ ሕፃን ልጅ ያላት አንዲት እናት ነበረች። ይህች እናት በምትችለው ሁሉ ልጇን አሳክማና ተንከባክባ ለማዳን ብትጥርም፣ ይህ ልፋቷ ግን ሊሳካላት አልቻለም። ልጇን የያዘው በሽታ መድኃኒት ስላልነበረው ወደ ሞት አፋፍ አቅርቦታል። ታዲያ አንድ ቀን ሕፃኑ ልጅ እናቱን እንዲህ ሲል ጠየቃት :- "እናቴ፣ መሞት ምን ይመስላል? ስንሞት ያመናል እንዴ?"

◈ በእናትየው ዓይኖች እንባዎች ሞሉ። ፊቷም በኃዘን ደፈረሰ። የረሳችው ነገር ያለ ይመስል "ቆይ መጣኹ" ብላ ሮጣ ከክፍሉ ወጣች። ብቻዋን ስቅስቅ ብላ አለቀሰች። ልጇ የጠየቃትን ጥያቄ መመለስ እንዳለባት ብታውቅም ለዚህ ለጋ አእምሮ እንዴት አድርጋ መልስ እንደምትሰጥ ግራ ገብቷታል። እንደ ምንም ራሷን አረጋግታና ጥበቡን እንዲሰጣት ወደ ፈጣሪዋ ተማጽና ተመልሳ ወደ ልጇ ክፍል ገባች።

◈ ሕፃኑ መልሱን በጉጉት ይጠብቃል። እናትየውም የውስጧን ኃዘን ለመሰወር ለይምሰል ፈገግ ብላ እንዲህ አለችው "ልጄ፣ ታስታውሳለህ አንድ ጊዜ ጎረቤት ያለ ጓደኛህ ቤት ሄደህ ስትጫወት አምሽተህ ስለደከመህ በዚያው እንቅልፍ ወስዶህ ነበር። ከዚያም በማግስቱ ግን ስትነቃ ራስህ ያገኘኸው በመኖሪያ ቤታችን ውስጥ ስለሆነ 'እንዴት እዚህ መጣኹ?' እያልክ ስትጠይቀኝ ነበር። እኔም አባት ወደዚያ መጥቶ በጥንካራ ክንዶቹ ተሸክሞህ የአንተ ወደ ሆነው ቤትህ እንዳመጣህ ነግሬሃለኹ። አስታወስክ?"

ልጅየው :- "አዎን እናቴ"

◈ እናትየው ቀጠለች :- "የኔ ልጅ፣ ሞትም እንደዚሁ ነው። እኛ መኖሪያችን ባልሆነች በዚህ ዓለም ሆነን እናንቀላፋለን። የሰማይ አባታችን እግዚአብሔር ደግሞ ብርቱ በሆኑ እጆቹ አቅፎ ወደ ሰማይ ይወስደናል። ከዚያም ነግቶ እንደ ገና ስንነቃ ራሳችንን በገዛ አባታችን ቤት ውስጥ እናገኘዋለን" አለችው።

◈ እውነት ነው! ሞት ለክርስቲያኖች ሁሉ የሚኖረው ትርጉም ይህ ነው። ከእግዚአብሔር ተልከን ወደዚህ ዓለም እንደ መጣን ወደ እርሱ መመለሳችን ደግሞ የማይቀር ነው። ሞት ማለት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ "ድንኳን" ብሎ ከገለጸው ከጊዜያዊው መቆያችን ወደ እውነተኛው መኖሪያ አገራችን መሸጋገር ነው።

◈ በ2ኛው ክፍለ ዘመን የነበረው ግሪካዊው ፈላስፋ አርስጣደስ በጊዜው አዲስ ሃይማኖት ስለሆነበት ስለ ክርስትና እና ይህ የክርስትና እምነት በሞት ላይ ስላለው እሳቤ ለአንድ ወዳጁ በጻፈለት ደብዳቤ ላይ እንዲህ የሚል ንግግር አስፍሮ ነበር። "ከክርስቲያኖቹ ውስጥ አንድ ጻድቅ የሆነ ሰው ከዚህ ዓለም በሞት ቢለይ ምእመናኑ ደስ ይሰኛሉ። ለፈጣሪያቸውም ምስጋናን ያቀርባሉ። ያም ሰው ከአንድ ስፍራ ወደ ሌላ ቅርብ ሥፍራ የተሸጋገረ ይመስል ሰውነቱን በመዝሙራትና በምስጋና አጅበው ይሸኙታል" ይላል። ክርስትና እንዲህ ነዋ!

◈ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅም ክርስቲያኖች በሞት ላይ ሊኖራቸው ስለሚገባ እይታ ሲናገር "ከእኛ መካከል አንድ ሰው በሞተ ጊዜ፣ የማያምነው ሬሳ ሲያይ ክርስቲያኑ ግን ያንቀላፋ ሰውነት ይመለከታል። ያላመነው "የሞተው ሰው ሄደ" ይላል። በርግጥ በዚህ እኛም እንስማማለን። ነገር ግን ወደ የት እንደሚሄድም እናውቃለን። የሚሄደው ሐዋርያው ጳውሎስ፣ ጴጥሮስ እንዲሁም ሌሎች የቅዱሳን ማኅበር ወደ አሉበት ነው። በኋላም ተስፋ መቁረጥ ባለበት እንባ ሳይሆን፣ በክብርና በማንጸባረቅ እንደሚነሣ እናስባለን!"

"ለባሪያዎችህ ሞት የለባቸውም ፍልሰት እንጂ"

#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
👍4🥰1😁1
ችግሮቼን አውቃለሁ፣ መፍትሄውንም አውቃለሁ ግን መተግበር አቃተኝ ለምትሉ || በጋብቻ ወቅት ልናደርጋቸው የሚገቡ ጥንቃቄዎች || በእዳ የተያዘ ትውልድ 😭😰🙄 https://youtu.be/iAB--uumpeg
👍7
«ልደቱ ለእግዚእነ ኢየሱስ ክርስቶስ»
‹‹ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ::›› /ቅዱስ ያሬድ/

ጌታችን ለሰው ልጆች ብሎ፤ የሰው ልጆች ፍቅር አገብሮት ንጽሕትና ቅድስት ከኾነች ከእመቤታችን ያለ ወንድ ዘር በመጋቢት 29 ተጸንሶ ታኅሣሥ 29 በ1 ዓ.ም (ዓለም ከተፈጠረ፥ ዘመን ከተቈጠረ በ5,500 ዓመት) በበረት ተወልደ፡፡ ሰማይና ምድር የማይወስኑትን በረት ቻለው፤ ወሰነውም በሌሊት መንጋቸውን የሚጠብቁ እረኞች ነበሩ፡፡ መልአኩ መጥቶ እንዲህ አላቸው፡- ‹‹እነሆ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና፡፡ ይህም ምልክት ይሆንላችኋል፤ ሕፃን ተጠቅልሎ በግርግምም ተኝቶ ታገኛላችሁ›› አላቸው፡፡ (ሉቃ 2፡10-12)

ከመለአኩም ጋራ ሠራዊተ መላእክት መጥተው ‹‹ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ለዕጓለ እመሕያው /ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ይሁን ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ/›› አሉ፡፡ ቅዱሳን መላእክትም ከእነርሱ ተለይተው ወደ ሰማይ በወጡ ጊዜ እረኞቹ እርስ በርሳቸው ‹‹እንግዲህ እስከ ቤተ ልሔም ድረስ እንሂድ፣ እግዚአብሔርም የገለጠልንን ይህን የሆነውን ነገር እንይ›› ተባባሉና ፈጥነው መጡ፡፡ ማርያምንና ዮሴፍን ሕፃኑንም በግርግም ተኝቶ አገኙ፡፡ አይተውም ስለዚህ ሕፃን የተነገረላቸውን ነገር ገለጡ፤ የሰሙትን ሁሉ እረኞቹ በነገሯቸው ነገር አደነቁ፤ የብርሃን እናቱ እመ አምላክ ግን ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ እያሰበች ትጠብቀው ነበር፡፡ (ሉቃ 2፡13-19)

መላእክትም ሰማይ መንበሩ ምድር የእግሩ መረገጫ የሆኑለት አምላክ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ በጎል ተኝቶ በጨርቅ ተጠቅልሎ አይተውት ደስ ብሏቸው ወደ ሰማይ ቢያርጉ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በዕሪና ከመንበሩ አይተውት ‹‹ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት›› ብለው አመስግነውት በጣዕም ላይ ጣዕም፤ በጸጋ ላይ ጸጋ ተጨምሮላቸው ደስ ብሏቸዋል፡፡ ልደቱን ይሹታልና፤ መላእክትም ብቻ አይደሉም እንስሳትም አራዊትም ደስ ብሏቸዋል፡፡
እንኳን አደረሳችሁ ውድ ቤተሰቦቼ!

#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
👏2
መስገድ እና መጸለይ ስንጀምር በዙሪያችን ባሉ ሰዎች ማዕበል ይነሳብናል || ለሰይጣን ምህረት የማይደረግለት ምህረት ስለማያደርግ ነው #ethiopia 😭😰🙄 https://youtu.be/0PG2PuA5ob8
✍️ ርኩሳን መናፍስትን የማሰር መንገድ ሦስት ምድቦችን የተመረኮዙ ሦስት ቅደም ተከተሎች ሲኖሩት፤ እነርሱም፦

✓ በራስ አካል ላይ ያሉ መናፍስትን ማሰር ÷ "በሥላሴ ስም፣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም፣ በድንግል ማርያም ስም፤ ከራስ ጸጉር እስከ እግር ጥፍር ባለ የሰውነት ክፍል ውስጥ የተደበቃችሁ የጥፋት መናፍስት፥ ርኩሳት መናፍስት፥ ሁላችሁም ሠራዊታችሁን ከአካል ክፍሎቼ ላይ በመሰብሰብ በአንድነት ግንባር ላይ ወጥታችሁ ታስራችኋል!"

✓ ከራስ አካል ውጪ በዙሪያ ባሉ ሰዎች ውስጥ ያሉ መናፍስትን ማሰር ÷ "በአብ፣ በወልድ፣ በመንፈስ ቅዱስ ስም፣ በልዑል እግዚአብሔር ስም፣ በወላዲተ አምላክ ስም፣ ከእኔ አካል ውጪ ዙሪያዬ ባሉ ሰዎች ውስጥ (ቤተሰብ፣ ዘመድ፣ ጓደኛ፣ ጎረቤት፣...) ያላችሁ መናፍስት ባላችሁበት አካል ሳላችሁ ግንባር ላይ ታስራችኋል፡፡ ወደእኔ መምጣት እና በውስጥ ካሉ መናፍስት ጋር መናበብ አትችሉም!"

✓ በሰው አካል ውስጥ የሌሉ መናፍስትን ማሰር ÷ "በቅዱስ ሚካኤል ስም፣ በቅዱስ ገብርኤል ስም፣... ከአካል ሥጋ ውጪ ነፋስን መስላችሁ በዙሪያዬ፣ በአየርና ተክትላችሁኝ ወደ ቤቴ በመምጣት የምታንዣብቡ መናፍስት፤ ባላችሁበት ታስራችኋል፡፡ ወደ እኔ በተጠጋችሁበት ርቀት ልክ እሳተ መለኮት ያቃጥላችሁ!" እያላችሁ ማሰር ትችላላችሁ ለሁሉም እንዲደርስ ይሄን መልእክት ሸር አድርጉ።

✍️ ማሳሰቢያ፦ መናፍስቱን የማሰሩ ሦስቱ ምድቦች ላይ መገንዘብ ያለብን አንድ ነገር አለ፡፡ ይኸውም የመጀመሪያው ቅደም ተከተል ላይ እንደተቀመጠው በራስ አካል ያሉ መናፍስት ግንባር ላይ ውጡና ታሰሩ ሲባሉ እና ቀሪዎቹ ሁለቱ ምድቦች ላይ ያሉት ከኛ ውጪ የሚያደፍጡት መናፍስት ታሰሩ ሲባሉ፤ የመታሰራቸው አፈጻጸም አንድ አይነት አይደለም፡፡ ከኛ አካል ውጪ ያሉትን "ባላችሁበት ታሰሩ" ስንል ትእዛዙ ሙሉ በሙሉ ይፈጸማል፡፡

ማለትም በሥጋ ላይ አድረው ያሉትም ሆነ በአየር ያሉት ወደኛ ሰውነት መጠጋት በፍጹም አይችሉም፡፡ በኛ አካል ውስጥ ግን ያሉት ከባሕሪያችን ጋር ተዳብለው ያሉ ስለሆኑ፤ "ታስራችኋል" ማለታችን "ተወስናችኋል" እንደ ማለት ነው የሚተረጎመው፡፡ በሌላ አገላለጽ መናፍስቱ በኛ ውስጥ መሥራት የሚፈልጉትን ሥራ በሚፈልጉት ልክና መጠን አይከናወንላቸውም፡፡

ከአቅማቸውና ከችሎታቸው ይወሰናሉ፡፡ ወይንም ዐሥር ነገር ይዘው ከነበረ ስምንቱን ይለቁታል ማለት ነው፡፡ ሁለቱ ላይ ግን መዋጋታቸውን ይቀጥላሉ፡፡ እጅግ ክፉ ናቸውና ታስረውም ቢሆን ክፋታቸውን በሚችሉት ሁሉ መግለጣቸውን አያቋርጡም፡፡ ዐሥሩንም ለቀቁ ማለት ታዲያ "መሄድ እንልጋለን" የሚሉበት የሽኝት ነጥብ ላይ ተሸንፈው ደረሱ ማለት ነው፡፡

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
8👍2🥰2
◈ የቀዳሜ ሰማእት የቅዱስ እሥጢፋኖስ ረድኤት በረከት አይለየን። በአማላጅነቱ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ይሰውረን።

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
«ማርያም ማለት ሥጦታና ሀብት (ጸጋ ወሀብት) ማለት ነው።»

✍️ መጀመሪያ ከእግዚአብሔር የተሠጠችው ለእናት  አባትዋ ነው። "ልጆች የአግዚአብሔር ሥጦታዎች ናቸው" ተብሎ ተጽፎአልና።

✍️ ሁለተኛ ከእግዚአብሔር የተሠጠችው ደግሞ ለሰው ልጆች ሁሉ ምልክት ሆና ነው። "ጌታ ራሱ ምልክትን ይሠጣችኋል ፣ እነሆ ድንግል ትጸንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ፣ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል" ተብሎ ተጽፎአልና። (ኢሳ 7:14)

✍️ ሦስተኛ ወላጆችዋ ለእግዚአብሔር ስእለት አድርገው ወደ ቤተ መቅደስ መሥጠታቸው ደግሞ ለእግዚአብሔር የተሠጠች ሥጦታ ያደርጋታል።

✍️ አራተኛ ደግሞ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ራሱን አሳልፎ ከመሥጠቱ በፊት እመቤታችን ራስዋን "እነሆኝ የጌታ ባሪያ" ብላ ለእግዚአብሔር ሥጦታ አሳልፋ መሥጠትዋ ነው።

✍️ አምስተኛው ደግሞ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ  ራሱ እናቱን ቅድስት ድንግል ማርያምን በመስቀል ላይ ለወዳጁ ለዮሐንስ "እናትህ እነኋት" ብሎ የሠጠ መሆኑ ነው።  "በጎ ሥጦታና ፍጹም በረከት ከብርሃናት አባት" ከላይ የሚወርዱ ናቸው። ከእነዚህ የፈጣሪ ሥጦታዎች አንድዋ እመቤታችን ናት።

እመቤታችን የሀገራችንን ፍጹም ኀዘንዋን፣ የቤተ ክርስቲያንንም ልቅሶዋን በምልጃዋ ትስማልን።

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
የጸሎት አሳብ መበታተን ምልክቶች

1) ጸሎተ ቃልን ከጀመሩ በኋላ የሚናገሩትን ፊደልና ዓረፍተ ነገር አለመስማት (በተለይ በጸሎት መጽሐፍት ንባብ ወቅት)

2) ጸሎቱን እያደረሱ ሳለ ድንገት በምን ርዕስ (ጉዳይ) ላይ አምላክን እያነጋገሩ እንደሆነ መዘንጋት

3) ጸሎተ ጊዜው ላይ ሆነው ያሉበትን ቅጽበት እስኪረሱ ድረስ በጭንቅላት ውስጥ ዝብርቅርቅና ፍቺ በሌላቸው ድምፆችና ምናቦች በመሳብ ሰምጠው መቅረት (መጀመሪያ የሚጀምረው በአንድ ቃል የሌለው ድምፅ አሊያ ቅርጽ አልባ ምናብ ነው፡፡ በመቀጠል በነፋስ እየተቀጣጠለ በፍጥነት እንደሚዛመት ሰደድ እሳት ድምፆቹና ምናቦቹ ተከታታይነት ባለው ወጥ አኳኋን እየበዙ ይሄዳሉ)

4) ተራ ቁጥር 3 ላይ ከተጠቀሰው ጋር ተቀራራቢነት ሲኖረው፤ ከውስጥ የሚፈጠሩት ድምፆችና ስዕሎች ተጨባጭ የሚመስል መልክና ገጽታ ፈጥረው ሕልም እንደምናይ አድርገው ይዘውን ይንሳፈፋሉ (ለምሳሌ የዝሙት ትዕይንቶችን፣ ያለፉ የድርጊት ትውስታዎችን፣ የተረሱ ገጠመኞችንና ንብረቶችን፣ ወደፊት የሚከናወኑ እቅዶችን ማየት)

5) እንዲሁ እንደ ተራ ቁጥር 3 ተመሳሳይ ሲሆን፤ የሚረበሹበት ድምፅ ግን ከውስጥ የሚፈጠር ሳይሆን ከውጪ የጸሎት ቦታ አቅራቢያ በሚደመጥ ንግግር ወይንም ሁካታ የሚመጣ ነው

6) የሚጸለየውን ጸሎት፣ የሚታየውን ስዕለ አድኖና ሌላም በአጠገብ ያለውን ቁስ ሰበብ (መሠረት) ያደረገ ሙግት ከራስ ጋር መግጠም (ምሳሌ የሚጸለየውን ጸሎት ምክንያት ያደረገ፦ "ጸሎቴ ይሰማ ይሁን? ይሄ ትክክለኛ ጸሎት ይሁን? ሌላ የተሻለ ጸሎት ማድረስ አለብኝ ይሆን? ይሄ የጸሎት ቃል ምን ለማለት ፈልጎ ነው? ይሄን የጸሎት መጽሐፍ ማን አዘጋጀው? ፣ ወዘተ..." እያሉ የሕሊና ድምፆችን በራስ ፈቃድ መፍጠርና ለጥያቄዎቹ መልስ ለመስጠት እየዳከሩ እየዳከሩ ድምፆቹን በማብዛትና በማድመቅ በዛው ጭልጥ ማለት)

7) አእምሮ ላይ እፍን በሚያደርግ ድብርታም ስሜት ባለው አዚም ሲንገላጅጁ ቆይቶ ከእንቅልፍ ተቀስቅሰው እንደ ነቁ አይነት መሃል መሃል ላይ መባተት (ይሄ ምልክት ካለ ደጋግሞ ማፋሸክ፣ የዓይን ጨረር መጥበብ፣ የእንባ ነጠብጣቦች መውረድ፣ የራስ ቅል መክበድ፣ የያዙት መጽሐፍ ወይንም የለበሱት ልብስ (ነጠላ) ተንሸራቶ ሲወደቅ አለማወቅና ባሉበት ቦታ ላይ አግድም መተኛት ተጨማሪ ምልክቶች ሆነው ይከሰታሉ)

8) ሰመመንን በተጠጋ ድባብ ውስጥ ሆኖ ከጸሎት አንቀጽ ወደ ጸሎት አንቀጽ እየተሻገሩ መቆየት (ይሄ ምልክት
ካለ እያንዳንዱ ተብሎ የሚታለፈው አንቀጽ ምን እንደነበረ ቢጠየቁ አያውቁም)

9) ጸሎትን እያሰሙ ጥቂት እንደቆዩ የትኩረት አቅም ቀንሶ መንፈሳዊውን ሐሴትና ትርጉም ማጣት

10) ጸሎተ ቆይታውን ቶሎ ፈጽሞ ስለ ቀጣዩ አድራጎት እያምሰለሰሉ መቁነጥነጥ (ሰዓት ደጋግሞ ማየት፣ የጸሎት
መጽሐፉን ቀሪ ገጾች መቁጠር)

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
👍1
"ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።" (1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1፥18-19)

◈ የአብራም ጎረቤቶች ከቤተሰባቸው ሲዋረሱት የቆዩት የአኗኗር ሂደት ትክክል እንደሆነ ነው የሚያስቡት፡፡ ለእነርሱ መብላት፣ መጠጣትና የሚያስፈልጋቸውን በወቅቱ ማግኘት፤ የሕይወት ጠቅላላ ትርጉም ሆኗቸዋል፡፡ የዛሬውም የእኛ የአባት ቤት ኑሮም ይኸው ነው፡፡ በሥጋ መደላደልና በቁስ ስኬት ላይ መቆም፤ ቤተሰብ "ልጄ በሚገባ አኩርቶኛል" የሚልበት ሙሉ መለኪያው ነው፡፡ ይሄም መመዘኛ በዓለም ሰፊ አውታር የተለመደ፤ ኑሮን ስለማሸነፍ የሚናገር ሚዛን ስለሆነ፤ እንዲሁ በደፈናው "ትክክል" ተደርጎ ማኅተም ተዘግቶበታል፡፡ ከዘላለም ሕይወት አንጻር፣ "ሰውን ሰው ካሰኘው" መንፈሳዊ ባሕሪያት አንጻር፣ ከመለኮታዊ ፍቃድና እውነት አንጻር፣ ከክፉ መናፍስት ፍላጎትና የጠላትነት ማንነት አንጻር፤ በምንም መንገድ ያልተፈሸ፤ ዝምብሎ ጎበዝ ተማሪ ከመሆን፣ ሐብታም ከመሆን፣ ባለቤት ባለመኪና ከመሆን አንጻር ብቻ የተለካ በክፉ ምሪት የተንጋደደ ውድቀት ነው (በሶሻሊዝም እርሾ የተቦካውን ሊጥ አሁን ድረስ ጋግረን እየበላን እንደሆነ እናጢን)፡፡

◈ የአዳም ልጆች ሁሉ ከእግዚአብሔር ፈቃደ አሳብ እንዲለዩ በማድረግ የገነትን ተንኮል የጀመረው ዲያቢሎስ፤ ዓለም እስከምታልፍበት የመጨረሻዋ ሰኮንድ ድረስ ነፍሳት ወደ አምላካቸው መስመር እንዳይመለሱ "በታላቅ እልህና ፍጥነት" ይሠራል፡፡ ግን የአባት ቤት የልምድ ኑሮ ይህንን የዕድሜ ዘመን ጨካኝ ባላንጣ አያውቀውም፡፡ ሊያውቀው የሚችልበት ስፍራም ላይ አልቆመም፡፡ የዘልማድ ኑሮ ጉዳዩ ሁሉ የሚያጠነጥነው ስለ ሥጋ ብቻ ስለሆነ፤ በሥጋ ውስጥ የሚሰወረውን አጥፊ ኃይል ጨርሶ አያየውም፡፡

◈ እንኪያሳ፥ የክፉው መንፈስ ሠራዊት በረቂቅ ተፈጥሮው ታግዞ በሰው ልጆች ባሕሪይ ውስጥ ዘልቆ በመግባት፤ ክፉ ልምዶችን እያሳደገ፥ መልካም ልምዶችን እያኮሰሰ፤ ሥጋዊ ልማዶች በእጥፍ እንዲጨምሩ ከእውቀት ዛፍ በስተኋላ እየተሸጎረ (የሥጋ ፈቃድ የሚጨምረው አዳዲስ ነገራትን ባወቀን ልክ እንደሆነ ያስተውሏል)፤ የነፍስ ልምዶች በጭራሽ እንዳይኖሩ የእምነት ገጽታዎችን ደብዛቸውን እያጠፋ፤ አብራም በዘመኑ ተለይቶአቸው የወጣቸውን ሰዎች አድርጎን በሐዲስ ኪዳን ጊዜም ላይ ሆነን ብሉይን (ፍዳ ዘመንን) በተጨባጭ እንድንኖር አድርጎናል፡፡ (ኦሪት ዘፍጥረት 12፥1)

እኛስ እንዴት እያሰብን ነው!

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube