HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ
2.24K subscribers
1.99K photos
96 videos
51 files
3.81K links
❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️

👇👇👇
http://www.youtube.com/@haileG2239
Download Telegram
"ሙዝቃ የሰይጣን ማህሌት ነው"

ወንድማችን እንኳን እግዚአብሔር ወደ ቤቱ ጠራህ። የለመንካት እማምላክ ቅድስት ድንግል ማሪያም አሁንም በሕይወት ጎዳናህ ትከተለህ። ቤተሰቦቼ መናፍስት ሰዎችን ምን ያህል እየፈተኑ እንዳለ የወንድማችንን ሕይወት ግልጽ ተሞክሮ ነው። በእውት የምናሳዝነው ይሄን እንኳን እየሰማን የምናሾፍ ሰዎች አንጠፋም። ስለዚህ እግዚአብሔር በእውነት ልቦና ይስጠን። እንበርታ 🙏🙏🙏 ተመስገን ነው በእውነት 🌹
👍189
🙏 በቅርብ ነው ወደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤት የመጣሁት። ዳግም እንዳልጠፋ እና እንዳልባክን ሽምግልናዬን ሳታዩ እንደ ህፃን ልጅ በጸሎታችሁ ታስቡኝ ዘንድ ተንበርክኬ እማጸናችኋለሁ #አርቲስት #ሰለሞን ተካ
***
በይርጋጨፌ ከተማ በተደረገው መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የተገኘው አርቲስት ሰለሞን ተካ በቅርብ ወደ ኦርቶዶክሳዊት መቅደስ ልጅ ሆኖ እንደመጣ ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ ማህበረ ምዕመናንን በጸሎታቸው እንዲያስቡ በአውደምህረቱ ተንበርክከው ተማጽነዋል።

በእውነት እግዚአብሔር ይመስገን!!!

በቤቱ ያጽናዎት። በአረጋዊ ዘመንዎ የመረጦት አምላክ ይመስገን!!
21👍6
🙏 ሰላም ሰላም ውድ ቤተሰቦቼ እንዴት ናችሁ። ጸሎት፣ ስግደት፣ ጾሙ እና ሱባኤ እንዴት ይዟችኋል። እግዚአብሔር አምላካችን ሁላችንንም ይርዳን በርቱ፣ ጠንክሩ። ቤተሰቦቼ የበረከት ሥራችን ቀጥሏል ከፍታችን ታህሳስ 19 የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል እየመጣ ነውና በዚህ ቀን በረከትን እንድናገኝ በበረከት ሥራ ላይ እንሳተፍ እያልኩኝ መልእክተን አቀርባለሁ።

🙏 በአንድ የተቸገረ ሰው ሕይወት ውስጥ ገብቶ ማገዝ ምን ያህል መታደል ነው። የሰዎችን ሀዘን መጋራት ምንኛ መታደል ነው። በሰዎች ፈተና እና መከራ ውስጥ ገብቶ እንደመተጋገዝ ያለ ምን ትልቅ ደስታ አለ ቤተሰቦቼ። ስለዚህ ሁላችንም የአቅማችንን እንተባበር እላለሁ።

🙏 የሚታገዙ ቤተሰቦች አሉና በውስጥ መስመር ሁላችሁም እያናገራችሁኝ የቅዱስ ገብርኤል የበረከት ሥራ ላይ እንሳተፍ እላለሁኝ። 🙏🙏🙏

ለማናገር፦
@haile_gebriel_tube_bot
8👍2
"የትዕቢት መጀመሪያ ሰውን ከእግዚአብሔር ትለየዋለች" (ሲራክ 10፥2)

❖ ሳጥናኤል ከቀደመ ክብሩ ተዋርዶ ዲያብሎስ የኾነው “ይኽ ሕዝብ ፈጣሪውን አጥቶ ተጨንቋል፤ እኔ ፈጠርኳችሁ በማለትም ፈጣሪነትን በእጄ ልያዝ” ብሎ በታበየ ጊዜ ነው፤ ዲያብሎስ ዲያብሎስ የኾነ አስቀድሞ ዲያብሎስ ኾኖ ስለተፈጠረ አይደለም፡፡

❖ በትዕቢት ከመውደቁ በፊት የዐሥሩ ነገደ መላዕክት የአጋዕዝት አለቃ ንዑድ ክቡር መልዐክ ነበርና፤ ከዚኽ ክብሩና ሹመቱ ያዋረደው ትዕቢቱ ነው፤ እሳቱ ወደማይጠፋ ትሉ ወደማያንቀላፋ እሳት የጣለው ትዕቢቱ ነው፤ ወደ ዘለዓለማዊ ሐሳር የጣለው ትዕቢቱ ነው፡፡

❖ ተወዳጆች ሆይ! ትዕቢት የነበረንን መልካም ምግባር ሁሉ የሚየሳምም ደግሞም የሚገድል ክፉ ደዌ ነው፤ ወንጌላዊው እንዲህ ይለናል፦ “በሰው ዘንድ የከበረው በእግዚአብሔር ዘንድ ግን የተዋረደ ነው” እንዲል ውስጣችን በትዕቢት የተሞላ ከኾነ በአፍአ ብንመጸውትም፣ ብንጸልይም ምጽዋታችን ወይም ጸሎታችን በእግዚአብሔር ዘንድ ርኵስ መሥዋዕት ነው፡፡ (ሉቃ 16፥15)

❖ ትዕቢት ካለብን ውስጣችን ንጽሕና የለውም፤ ስለዚኽ ሰው ንጽሕናውን እንዲያጣ የሚያደርገው ዝሙት ወይም ማመንዘር ብቻ አይደለም ማለት ነው፤ ትዕቢት ጭምር እንጂ፤ እንደውም ትዕቢት ከዝሙት ወይም ከማመንዘር በላይ እኛን ያቆሽሻል፤ ለምን? ምንም እንኳን ዝሙት ንስሐ ካልገቡበት ሥርየተ ኀጢአት የሌለው በደል ቢኾንም በዝሙት የቆሸሸ ሰው ንስሐ ለመግባት ቅርብ ነው፤ በትዕቢት የታመመ ሰው ግን እንዲኽ እንደ ዘማዊው ያለ ዓቅምን አያገኝም፤ ስለዚኽ ትዕቢት እጅግ አደገኛ ደዌ ዘነፍስ ነው ማለት ነው፡፡

❖ ከትዕቢተኛ ሰው በላይ ጐስቋላ ሰው የለም፤ የፈለገ ያኽም ብዕል (ሃብት)፣ የዚህን ዓለም ዕውቀት ቢኖረውም ከትዕቢተኛ ሰው የባሰ ጐስቋላ ሰው የለም፤ በንግሥና ወንበር ቢቀመጥ፣ በሰዎች ዘንድ እጅግ “የተከበረ” ቢኾንም ከዚኽ ሰው በላይ ጐስቋላ ሰው የለም ብዬ በእውነት እነግራችኋለኁ፤ እስኪ ንገሩኝ! የዚኽን ከንቱ ደግሞም ኀላፊና ጠፊ ዓለምን ነገር ይዞ ከመታበይ በላይ ምን አላዋቂነት አለ?

❖ ነገ የሚጠወልገውን የመስከረም አደይ አበባን (የዚኽን ዓለም ክብር) ይዞ ከሚታበይ ሰው በላይ ማን ነው ጐስቋላ? ሕልምን ይዞ እውኑን ዓለም ከሚያጣ ከዚኽ ትዕቢተኛ ሰው በላይ ማን ጐስቋላ ሰው አለ ልትሉኝ ትችላላችሁ? አኹን በወርቅ አልጋ ላይ ስለተኛ ከሚታበይ ሰው በላይ ማን ድኻ አለ ልትሉኝ ትችላላችኁ?

በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
8😢1
🌹 በእግዚአብሔር ፊት ከሚቆሙ ከከበሩ ሊቃነ መላእክት አንዱ ቅዱስ ገብርኤል፦ በመልአከ ሞት ከመውደቅ የምትታደግ ገብርኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን። አማላጅነትህን በመታመን ተስፋ እናደርጋለንና በመዓልትም በሌሊትም አንተ ጠብቀን።🙏

(መልክአ ገብርኤል)

እንኳን ለመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
14
❖ መንፈሳዊ ሕይወትን ገና ስትጀምረው ለፍጹምነት ጥቂት የቀረህ ያህል ይሰማሃል፤ አንተ ጋር ያለው ደስታ እና ሰላም ሌሎች ጋር የሌለ ይመስልሃል። በዚህች ሁከት በሞላባት ዓለም አንተ ብቻ ክርስቶስን እንዳገኘኸው ታስባለህ፤ የቀረው ሕዝበ አዳም እንዲሁ በከንቱ ሲርመሰመስ የሚውል ባካና ሆኖ ይታይሃል፤ ታዝንለታለህ፣ አይይይ ይህ ኃጢአተኛ ሕዝብ ምን ይሻለዋል? ትላለህ።

❖ የእውነተኛ መንፈሳዊ እድገት መገለጫ ግን ይህ አይደለም፤ ሰው ወደ እግዚአብሔር እየቀረበ ሲመጣ ከሌላው ሰው ይልቅ የራሱ ጉድለት ይታየዋል፤ መንፈሳዊነት የሚገልጥልህ ሰዎችን ተመልክተህ የምትፈርድበትን ውጫዊ ዓይንህን ሳይሆን ራስህን አይተህ የምትወቅስበት የውስጥ ዓይንህን ነው፤ መንፈሳዊ ሕይወትህ ሲጎመራ "አይ ሰው" ሳይሆን "አይ እኔ!" ያሰኝሃል።

❖ አባ ማቴዎስም እንዲህ ይላል "ሰው የበለጠ ወደ እግዚአብሔር ሲቀርብ ይበልጥ ኃጢአተኛ መሆኑ እየታየው ይመጣል፤ ነቢዩ ኢሳይያስ እግዚአብሔርን ካየ በኋላ ከንፈሮቼ የረከሱብኝና የጠፋሁ ሰው ነኝ እንዳለ"

❖ ከብቃት ደርሰህ መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ ቢታዩህ እንኳን ሁሉ እንዳንተ ስለሚመስልህ እንደ ዮሐንስ ሐጺር "ሚካኤል ይበልጣል ወይስ ገብርኤል?"  እያልህ ከአጠገብህ የቆመውን ትጠይቃለህ እንጂ "አይይ አንተ እንኳን ገና አልበቃህም፤ ብዙ ይቀርሃል" ብለህ ወዳጅህን አታናንቅም ይልቅ "ለእኔ ብቻ ገልጦ ለሌላው እንዲሰውር የሚያደርገው ምንም ቁም ነገር የለኝም" በማለት ከወንድምህ የተሻልህ እንዳልሆንክ በፍጹም ልብህ ታምናለህ።

❖ ለመንፈሳዊ ሕይወት አዲስ ስትሆን ገና ጥቂት ጸልየህ፣ ጥቂት ጾመህ፣ ጥቂት መጽውተህ ሳለ ግን ሩጫህን ወደ መጨረሱ የተቃረብህ ይመስልሃል፤ ጉዞህን በግማሽ እርምጃ ከመጀመርህ ከፍጻሜው ላይ የደረስህ ያህል ይሰማሃል "እኔን ምሰሉ" ማለት ያምርሃል፤ ነገር ግን መንፈሳዊ ሕይወት የቱንም ያህል ብትሮጥበት ሁል ጊዜ እንደ ጀማሪ የሚያደርግ ረጅም ጎዳና ነው፤ ሰማንያ ዓመት በገዳም ሲጋደል የነበረው አባ ሲሶይ ነፍሱ ከሥጋው ልትለይ በቀረበች ጊዜ ብዙ መነኮሳት በአልጋው ዙሪያ ከበውት ሳለ ቅዱሱ "አምላኬ ሆይ፣ እባክህ ለንስሐ የሚሆን ጥቂት ጊዜን ስጠኝ?" እያለ በልቅሶ ሲማጸን ሰሙት። በዚህ የተገረሙት መነኮሳቱ አባ ሲሶይን "አባታችን አንተ እድሜ ልክህን በንስሐ የኖርህ መምህረ ንስሐ ሆነህ ሳለ እንዴት አሁን ጥቂት የንስሐ ጊዜን ትለምናለህ?" ቢሉት፣ ቅዱሱም "ልጆቼ ይህን መንፈሳዊ ጥበብ (ንስሐን) ገና አሁን መጀመሬ ነው" አላቸው።

❖ ጌታ ሆይ መንፈሳዊ ሕይወት እኖር ዘንድ አስጀምረኝ፤ ገና ጀማሪ ሳለሁ ደርሻለሁ ከማለትም ሰውረኝ፤ እንድቆም አትፍቀድልኝ፤ ወደ አንተ ሳበኝ፣ አሳድገኝ።

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
👍53
20231229_184918
<unknown>
🙏 በቅዱስ ገብርኤል ቀን እንዲህ አይነች ምርቃት ይድረሳችሁ በያላችሁበት። በዛሬው ቀን እህታችን ሰብሌ ከቤተሰቧቿ ጋር በመሆን በላከችው የበረከት ሥራ የአንድ እናትን የደስታ ምርቃት ተቀብለናል። እንዲሁ ደግሞ ችግራችሁ ችግራችን በማለት ተጋርተናል እና ይሄው ምርቃቱ ለሁላችሁ ይድረስ ብያለሁ። እህታችን እግዚአብሔር አምላክ ቤታችሁን በበረከት፣ በሰላም ይሙላላችሁ። በእውነት እናታችን እንዴት እንደተደሰተች። ሁላችሁም ቤተሰቦቼ የበረከት ሥራ ላይ እንሳተፍ፣ ያለንን ከሰዎች ጋር እንካፈል። እንበርታ 🙏🙏
16👍2
◈ በንጽሕና ለመኖር እየታገለ የሚወድቅን እግዚአብሔር አያዝንበትም። ድካሙን እና ያልተቋረጠ ጥረቱን አይቶ ድል የሚነሣበትን መንፈሳዊ ጸጋ ይሰጠዋል እንጂ። እንድትኖር በታዘዝከው ልክ ለመኖር ሞክረህ ስላልሆነልህ በራስህ ተስፋ አትቁረጥ። መሆንህን ብቻ ሳይሆን ፈልገህ መሞከርህን እግዚአብሔር ይጽፍልሃል። ሰይጣን አቁስሎህ ስለሻረው ጠባሳህ አትቆጭ። ብዙ ጠባሳ እኮ ለሚዋደቅ ጀግና ወታደር የክብር ምልክቱ ነው። አፈ ወርቅ ዮሐንስ እንደሚለው የማይቆስለው የማይዋጋ ብቻ ነው።

#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
👍5
◈ አቤቱ የሕይወታችን ራስ ክርስቶስ ሆይ ፍጻሜውን ከምናየው ከኃላፊው ሥራ ለየን፤ ወደሚወደድ የሕይወት ፍሬም አድርሰን። ይኸውም የቅድስናህ መልእክተኞችህን አገልጋዮችህ መላእክትን ደስ የሚያሰኛቸው ፊትህን ማየት ነው። ሥራችንም ሆነ አንደበታችን ይህ ብቻ ይሁን። በሰጠኸን ውስን ዘመናችን የፈቃድ ሕጋችንን ፈትነን ገዝተን እንኖር ዘንድ ያለ ኃፍረት ያለመሰወርም ለምሕረትህ በሞገስ ወደ አንተ እንድንቀርብ እርዳን። አሜን በእውነት ያለ ሐሰት።
======//======

#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
10
◈ አገልጋዮች ጀርባቸውን ከእግዚአብሔር ቤት ሲያዞሩ፤ በተተኪው ትውልድ ሕይወት ውስጥ ርኩሳን መናፍስቶችን ያነግሣሉ። ሰዎችም ከመናፍስቶች ጋር ተስማምተውና በአምልኮት ቃል ተግባብተው፤ ከአጋንንቶች ጋር በመዋሃድ ከሰው አጋንንትነት ወደ አጋንንት ሰውነት መሸጋገርን በማምጣት፤ ሰብዓዊነት የሥጋ ቁመናና የልብስ አካል ብቻ ሆኖ፤ ሰው ሥጋና ልብስ የለበሰ አጋንንት እንዲሆን ያግዛሉ። ከዚህም የተነሳ አገልጋዮች ጀርባቸውን ለእግዚአብሔር ሲያዞሩ እውቀታቸው ለሕይወት መድኅን መሆኑ ቀርቶ ለሕይወት ሥቃይ አምጭ ነፍስና ሥጋን ቀጭ በመሆን፤ እርስ በርስ የመጠላለፍ ቅራኔን ያሳድጋሉ። የሞት ጥላ በመሆንም የሰው ልጅን መኖር ይፈታተናል። መጽሐፉም እንዲህ ይላል፦ "ድንጋጤ በድንጋጤ ላይ ይመጣል፤ ወሬም ወሬን ይከተላል፤ ከነብዩም ዘንድ ራዕይን ይሻሉ፤ ከካህኑም ዘንድ ትምህርት፤ ከሽማግሌዎችም ዘንድ ምክር ይጠፋል። ንጉሡም ያለቅሳል፤ አለቃውም ውርደትን ይለብሳል፤ የምድርም ሕዝብ እጅ ትንቀጠቀጣለች።" (ሕዝ.7፡26)

🙏 እግዚአብሔር ሀገራችንን ኢትዮጵያ ሰላም ያድርግልን። ሁላችንንም ይባርከን በእውነት።
======//======

#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
5
◈ ኃያሉ እግዚአብሔር በስሙ የሚቀልዱትን፣ በክብሩ የሚያሾፉትን፣ በቃሉ የሚያሽሟጥጡትን፣ በኃይሉ የሚተብቱትን፣ የጸጋውን ስጦታ የሚያክፋፉትን ሁሉ ሳያውቁት አለን አለን ሲሉ ድንገት ያዋርዳቸዋል። የተፈጠሩበትን ስብዕና፣ የሰጣቸውን ሕልውና ለፈጣሪ ክብርና ለአምልኮት ኃይል ማዋል ሲንቁ፤ ሰውኝነት እየጎደላቸው ከሰው ሰውኝነት ወደ መናፍስታዊ አረማዊነት እየተለወጡ በመሄድ፤ ሥጋ የለበሱ የሲኦል አጋንንት በመሆን ለመልካም ተግባርና ለሥነ-ምግባር የስብዕና መሪሆዎች ሁሉ ስልታዊና ዘመናዊ አደጋ ሆነው፤ ዙሪያ ገባው ሽብር፣ ሁከት፣ ችግር፣ መከራና ሞት አምጭዎች አጋንንት ያደርጋቸዋል። መጽሐፉም እንዲህ ይላል፦ "የጥፋት ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ አንባቢው ያስተውል።" (ማቴ.24፡15)

◈ በታሪክና በእምነት ታማኝ የነበሩ የሥልጣን ወንበሮች በሰው አጋንንቶች ሥልጣን ሲያዙ፤ ትውልድ ተኪው ሕብረተሰብና ተተኪው ትውልድ የሕይወት ብርሃኑ፣ የታሪክና የእምነት ሞገሱ ይጨልማል። ስለዚህ የትውልድ የማስተዋልና አዙሮ የማየት ስብዕና፣ አርቆ የማሰብ ክህሎት፣ የተስፋና የራዕይ በጎ ምልከታን በተለያየ የጥፋት ስልት ከትውልድ ሕሊና ውስጥ በማምከን፤ ለግፍና አለረመኔያዊ ተግባር እንዲሰለፉ በጊዜያዊ ጥቅም ራሱን ለአጥፊዎች ይሸጣል።

"የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል። አሁንም የወንድምህን ደም ከእጅህ ለመቀበል አፍዋን በከፈተች በምድር ላይ አንተ የተረገምህ ነህ።" (ዘፍ.4፡10)

◈ በደም አዙሪት የተለከፉ፣ በደም ጀምረው በደም ያደጉ፣ በደም የከበሩና በደም ሥልጣን የኖሩ ሁሉ፤ አይራሩም! አያዝኑም። ምክንያቱም የራሳቸውም ደም በደም የተበከለ ስለሆነ፤ የደሙ አዙሪት አዙሮ፣ አባሮ፣ አሽቀንጥሮና አዋርዶ ራሳቸውንም ትውልዳቸውንም ይጥላል። እግዚኦ ነው! በእውነት።

ማሳሰቢያ፦ ሀገር እየታመሰች፣ በፈተና ውስጥ በገባችበች ወቅት በየመጠጥ ቤቱ፣ በየግሮሰሪው፣ በየሺሻ ቤቱ፣ በየጭፈራ እና በዳንክራ የተያዛችሁ እባካችሁ አደብ ግዙ። በእውነት እግዚአብሔር ታዲያ እንዴት ይማረን፣ እንዴት ይቅር ይበለን። አያችሁ እግዚአብሔር ዝም ስል እንዲህ ይሆናል። እባካችሁ የሁላችን የጸሎት ኃይል ብዙ ነገሮችን ልቀይር ይችላልና እንበርታ በጸሎት፣ እንበርታ በስግደት። ይማረን በእውነት።

እግዚአብሔር ምህረቱን ይላክልን 🙏🙏
======//======

#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
👍3
◈ የጭንቀት መንፈስ ተጠቂ የሆኑ ሰዎች መገለጫ ባሕሪያቸዉ፦

🙏 ጭንቀት የሚጀምረዉ ከፍርሃት እንደመሆኑም መጠን የሰዉ ልጅ ሲጨንቀዉ ልቡ በፍርሃት ስለሚርድበትና አዕምሮዉ በጣም ስለሚወጣጥርበት ዝምታን እንጂ ማዉራት አይችሉም ስለዚህ የጭንቀት መንፈስ ያለበት ሰዉ አብዝቶ ዝምምም የሚል ይሆናል የዉስጡን ሕመም አዉጥቶ የሚናገርበትን አቅም ያጣል የድካም ስሜት ይጫጫነዋል።

🙏 የሰዉ ልጅ እንደ ልቡ የሚሆንበትን አቅሙን ሲነጠቅ ጨቅጫቃና ተነጫናጭ አማራሪ ስለሚሆን የዚህ መንፈስ ተጠቂ የሆኑ ሰዎችም በትንሽ ነገር የሚናደዱ ቶሎ ሆድ የሚብሳቸዉ የቱንም ያህል መልካም ነገር ቢደረግላቸዉ ደስተኛ የማይሆኑ ሁል ጊዜ እግዚአብሔርን እንዳማረሩት የሚኖሩ ጸባያቸዉ በሰዓት በሰዓት የሚለዋወጥ ፍጥረት ይሆናሉ ምክንያቱም እነዚህ ሰዎች ዉስጣቸዉ ያለዉን አቅምና ኃይል ስለሚያዉቁት ያንን አቅማቸዉን አዉጥተዉ መጠቀም ባለመቻላቸዉና ከሚወዱት ግብ ባለመድረሳቸዉ ብስጩ ይሆናሉና ጸባያቸዉ አስቸጋሪ ይሆናል።

🙏 በጭንቀት ጊዜ አሳብ ስለሚበዛ በዚህም ምክንያት እጅግ በጣም የሰዉነት ክብደት መቀነስ በአንጻሩ ደግሞ በጣም የሰዉነት ክብደት መጨመር፤ በጣም እንቅልፍ ማብዛት በዛዉ ልክ እንቅልፍ የሚባል ነገር ማጣት፤ ጭራሽ የምግብ ፍላጎት መቀነ ምግቡን ሲመለከቱት ማቅለሽለሽ በአንጻሩ በጣም መመገብ። በጭንቀት ወቅት መታወክ ስለሚያጋጥም የሆድ ቁርጠት መከሰትና ወደ መጸዳጃ ቤት መሮጥ፤ ከመጠን ያለፈ የሰዉነት መዝለፈለፍ ድካም የአተነፋፈስ መዛባት ከመጠን ያለፈ የፀጉር መነቃቀል።

◈ ከመጠን ያለፈ የአዕምሮ ዉጥረት ማስተዋል ማጣት ከመጠን ያለፈ የልብ ምት መጨመር (ፍርሃት)፤ የምንም ነገር ፍላጎት ማጣት የሕይወት ትርጉም አልባ መሆን ዙሪያዉ ገድል መስሎ መታየት ለምን እንደሚኖሩ ግራ መጋባት፤ በዉኃ ቀጠነ መጣላት መነጫነጭ ሰዉንም ሆነ ራስንም መጥላት ራስን መጣል መጎሳቆል ግራ ግራዉን ብቻ ማሰብ ወዘተረፈ ናቸዉ። ውድ ቤተሰቦቼ በቀጣይ ደግሞ መፍትሔዎቹን እንመልከት፦

◈ ችግሩን ማወቅ በራሱ ትልቅ መፍትሔ ነዉ፤ ዋናዉ እርሱ ነዉና ለጥቆ ጠበል ሳይታክቱ መጠበል መንፈሱ አዕምሮና ልብን የሚቆጣጠር ስለሆነ ቢቻል የኡራኤልንና የሚካኤልን ጠበል አብዝተዉ ቢጠበሉ መልካም ነዉ፤ ያዉ ቅዱስ ኡራኤል አዕምሮን የሚባርክ መልአክ ስለሆነ በቀላሉ ከዚህ እርጉም መንፈስ እንድትገላገሉ ነዉ ቅዱስ ሚካኤል ደግሞ የልብ ክፍላችን የሚያክም መልአክ ስለሆነ ጠበሉን ብትጠብሉት ከከንቱ ፍርሃት በቀላሉ እንድትገላገሉ ነዉ፤ የሚካኤልና የኡራኤል ጠበል ተጠበሉ ማለቴ፥ ካልተቻላችሁም በአቅራቢያችሁ ወደ ሚገኘዉ ቤተክርስቲያን በመሄድ መጠበል ትችላላችሁ ዋናዉ መጠበላችሁ ስለሆነ የሚፈለግዉ።

◈ የእምባ ጸሎት ማዘዉተር፦ በዚህ ጊዜ እምባ ስለማይቸግር የሰኔ ጎለጎታን እየጸለዩ በእንባ ጸሎት እመቤታችንን ማሳሰብ ሸጋ ነዉ።

◈ አከታትሎ ቅዱስ ቁርባን መዉሰድና መፅሐፍ ቅዱስ ማንበብ ተስፋ ሰጪ ቃላት ለራስ ደጋግሞ መንገርና ጌታ አምላክ ስለእኛ የከፈለዉን ዋጋ ማሰብና ከመከራ በኋላ የተሻለ ነገር እንዳለ ቢወድቁም መነሳት እንዳለ ማሰብ ተገቢ ነዉ ምክንያቱም ይሄ እርጉም መንፈስ ተስፋ አስቆራጭ በሆኑ ሽኩሽታዎች ተስፋ የሚያስቆርጥ ስለሆነ ነዉና ነዉ።

◈ በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ የቅዱሳንን ጠንካራ ጎናቸዉን ብቻ ሳይሆን ደካማ ጎናቸዉን ጌታ ከየት አንስቷቸዉ የት እንዳደረሳቸዉ ጭምር የሚተርክልን እኔና እናንተ እያነበብን እንድንፅናናበትና ራሳችንን እንድናበረታታበት ጌታ አምላካችን እነርሱን እንደረዳ እኛንም እንደሚረዳን እነርሱን ከከፍታ እንዳደረሳቸዉ እኛንም ከምንፈልገዉ ደረጃ እንደሚያደርሰን ተስፋ እንድናደርግበት ነዉ እንጂ ምጽ ብለን ዝም እንድል አይደለም ልብ በል ወዳጄ የመፅሐፍ ቅዱስን ምዕራፉንና ቁጡሩን ሸምድደን እንድንዞር ሳይሆን ሕይወታችን ላይ እዉን ሆኖ እንድናይ ነዉና በርትተህ ፈልግ ታገኘዋለህ ቃሉ እዉነት ነዉና እዉነትም እርሱ ነዉና። ሌላዉ በዚህ ጊዜ አስጨናቂ ከሆኑ ንግግሮች መራቅ አስፈላጊ ነዉ።

◈ ስግደት፦ ይሄ መንፈስ ትኩረታችን ምድራዊ ነገር ሆኖ ተስፋ እንድንቆርጥና በቃ አልችልም ብለን እንድንቀመጥ ዉጊያ የሚከፍትብን መንፈስ ስለሆነ ስግደትን አዘወትሮ መስገድ ያስፈልጋል።

ቤተሰቦቼ በዚህ ችግር ውስጥ ያሉትን ያግዝ ዘንድ ይሄን ትምህርት
#ሸር አድርጉ 🙏
======//======

#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
8👏4👍1