HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ
2.25K subscribers
1.99K photos
96 videos
51 files
3.81K links
❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️

👇👇👇
http://www.youtube.com/@haileG2239
Download Telegram
◈ አስተውሉ! ጸሎት የማድረስ ፍላጎታችን ደካማና የሰለቸ ከሆነ፤ መናፍሰቱ እዚህች ጠባይ ውሰጥ በመግባት ከመንፈስ ቅዱሰ የሚሰነዘረው ጥቃት እንዳያቃጥላቸው መከ'ለል ይችላሉ፡፡ ምን ማለት ነው፤ መንፈስ ቅዱስ እኛንም መናፍስቱንም በአንድነት ደርቦ አያጠቃምና፥ ተጻራሪዎቹን ከእኛ ውስጥ ሳሉ ለብቻቸው እንዲያገኛቸው እኛን ከፊት አድርገው ከተከለሉበት የባሕሪይ መጋረጃ መውጣት አለባቸው፡፡ እኛ ጸሎት ማድረግ የማንፈልግ ስንሆን መናፍስቱም ጸሎትን አይፈልጉምና በዚህ ባሕሪይ ስንታይ አንድ ሆነናል፡፡ ይህም ሲሆን መንፈስ ቅዱስ ክፉዎቹን እየለየ እንዳያቃጥላቸው ራሳችን ጠበቃ ሆንንበት ተብሎ ሊታሰብ ይችላል፡፡ እኛ ጸሎት የማድረስ እውነተኛ ልባዊ ፍላጎት ካለን ግን፤ ከውስጥ ያለው የጠላት ባሕሪይ መንፈሳዊነትን የማይፈልግ ነውና፤ ይሄ የመፈለግና ያለመፈለግ ባሕሪያት ጥል ከአካላችን ላይ ተቃራኒ ስበቶችን ይፈጥራል፡፡ በዚህ ጊዜመናፍስቱን ብናስር፣ እንዲጸልዩ ብናስገድድ፣ ቅዱሳንን ብንጠራ መስተቃርኑን የበለጠ የሰፋ ያደርገዋልና የጠላት መደበቂያ በሚከተለው በትግሉ ሂደት እየፈረሰ እየፈረሰ ይመጣል፡፡ በአጭር አማርኛ መንፈሱ መገለጥ ይጀምራል፡፡ (አንቀጹ ተደጋግሞ ይነበብ!)

#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
3👍2
◈ እንደ ቸርነትህ ◈

እንደ ቸርነትህ አቤቱ ማረን(፪)
እንደምህረትህም ይቅርታን ስጠን(፪)
ከኃጢአቴም አንጻኝ ከክፉ በደሌ(፪)

ለዚያች ክፉ ኃጢአት እንዳልሆናት ሎሌ(፪)
እኔስ አበሳዬ በደሌን ሳውቀው(፪)
ከቶ የሚያድነኝ ቸርነትህ ነው(፪)

አንተን ብቻ በደልኩ ክፉም አደረግሁ(፪)
አሁን ይቅር በለኝ ከፊትህ ወደቅሁ (፪)
ከፊትህ ወድቄ ስለምን አንተን(፪)

መውደቄን ተመልከት አምላከ ብርሃን(፪)
አሁን ትባርክ ዘንድ ጉባኤያችንን ጸሎታችንን
ጌታ ሆይ ላክልን መንፈስ ቅዱስን

ጰራቅሊጦስን
አሁን ትጠብቅ ዘንድ ሀገራችንን ኢትዮጵያን
ጌታ ሆይ ላክልን ቅዱስ ሚካኤልን ቅዱስ ገብርኤልን።

ሊቀመዘምራን ኪነጥበብ
======//======

#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
🙏11😢2
"የምንለወጠው ምን ስናደርግ ነው?"

❖ በታመምህ ጊዜ ድካም ይሰማሃል፤ ብርታት ያንስሃል፤ ፊትህም ይገረጣል፤ የዕለት ተዕለት ሥራዎችህን በአግባቡ ማከናወን ይሳንሃል፤ በዚህ ጊዜም ሕመምህ ምን ያህል እንደ በረታ ሰዎች ያስተውላሉ፤ መታከም እንደሚገባህም ይነግሩሃል፤ ስለዚህ ወደ ሐኪም ትኼዳለህ ወደ ሐኪም የምትኼደው ግን ሐኪሙ ምን እንዲያደርግልህ ነው? አሁን ለሚሰሙህ ስሜቶች የሚሽሩ መድኃኒቶችን እንዲሰጥህ ነው፡፡

❖ ኾኖም ይሰሙህ የነበሩ ስሜቶች ቢሻሉህም ሰውነትህ አሁንም እንደ ደከመ፣ ፊትህ እንደ ገረጣ ከቀረ፣ የዕለት ተዕለት ሥራዎችህንም በአግባቡ ማከናወን ከተሳነህ በተሰጠህ ሕክምና ደስተኛ ትኾናለህን? አትኾንም። “እውነታው ምንድን ነው?” ስንል ወደ ሐኪሙ የኼድከው የበሽታህን ምንጭ ለመታከም ሳይኾን የበሽታህን ምልክቶች ለማስታገሥ ስለኾነ ነው፤ በሌላ መልኩ ደግሞ የበሽታህ መንሥኤ እስካልታከመ ድረስ የበሽታህ ምልክቶች ለጊዜው ቢታገሡም ቅሉ ፈጽመው ሊወገዱ እንደ ማይችሉ ሐኪሙ በደንብ ያውቃል፡፡

❖ በክርስቶስ ክርስቲያን፣ በወልድ ውሉድ፣ በመንፈስ ቅዱስም መንፈሳውያን የተባልን እኛም እግዚአብሔር መንፈሳዊ በሽታችንን እንዲያስወግድልን እንሻለን፤ እንደ እውነታው ግን ብዙዎቻችን ወደ እግዚአብሔር ቀርበን እንዲያስወግድልን የምንሻው ምልክቶቹን ነው፡፡

🔘 ለምሳሌ

❖ ችግርን፣ ኀዘንን፣ ቀቢጸ ተስፋንና የመሳሰሉትን እንዲያርቅልን እንፈልጋለን።

❖ እግዚአብሔር ደግሞ ከዚህ በተቃራኒ የእነዚህ ምክንያት የኾነውንና ሥር የሰደደውን፣ ዋና ምክንያትም የኾነውን መንፈሳዊ በሽታችንን ሳይሽር እነዚህን ምልክቶች ሊያርቅልን አይፈልግም፤ ችግር የሚኾነውም ይህን ጊዜ ነው ምልክቶቹን እንዲያርቅልን ስንደክም ወደ ውሳጤያችን ገብቶ የችግሩን ምንጭ ሊያርቅልን የሚችለውን የእግዚአብሔርን ጸጋ (ኃይልን) አጥብቀን እንቃወማለንና፤ በውሳጤያችን የተሸሸገውን በሽታ ማስወገድ አንፈልግም፤ አመለካከታችን እንዲለወጥ አንፈቅድም፡፡

❖ እውነተኛ ለውጥ የሚመጣውና አማን በአማን የምንታከመው ግን የልባችንን ውሳጤ ለእግዚአብሔር ስንከፍትለትና እርሱም በዚያ በመረቀዘው ቁስላችን ላይ ጽኑ መድኃኒት ሲያስርልን ነው፤ እንዲለወጡ የምንፈልጋቸው ምልክቶች በእርግጥም የሚለወጡት ይህ በልባችን ውስጥ የተደበቀው መንፈሳዊ በሽታችን ሲጠፋ ነው፡፡

"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል" (ምሳ 1፥33)


በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

======//======

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
12👍1
"ሙዝቃ የሰይጣን ማህሌት ነው"

ወንድማችን እንኳን እግዚአብሔር ወደ ቤቱ ጠራህ። የለመንካት እማምላክ ቅድስት ድንግል ማሪያም አሁንም በሕይወት ጎዳናህ ትከተለህ። ቤተሰቦቼ መናፍስት ሰዎችን ምን ያህል እየፈተኑ እንዳለ የወንድማችንን ሕይወት ግልጽ ተሞክሮ ነው። በእውት የምናሳዝነው ይሄን እንኳን እየሰማን የምናሾፍ ሰዎች አንጠፋም። ስለዚህ እግዚአብሔር በእውነት ልቦና ይስጠን። እንበርታ 🙏🙏🙏 ተመስገን ነው በእውነት 🌹
👍189
🙏 በቅርብ ነው ወደ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤት የመጣሁት። ዳግም እንዳልጠፋ እና እንዳልባክን ሽምግልናዬን ሳታዩ እንደ ህፃን ልጅ በጸሎታችሁ ታስቡኝ ዘንድ ተንበርክኬ እማጸናችኋለሁ #አርቲስት #ሰለሞን ተካ
***
በይርጋጨፌ ከተማ በተደረገው መንፈሳዊ ጉባኤ ላይ የተገኘው አርቲስት ሰለሞን ተካ በቅርብ ወደ ኦርቶዶክሳዊት መቅደስ ልጅ ሆኖ እንደመጣ ይፋ ያደረገ ሲሆን፤ ማህበረ ምዕመናንን በጸሎታቸው እንዲያስቡ በአውደምህረቱ ተንበርክከው ተማጽነዋል።

በእውነት እግዚአብሔር ይመስገን!!!

በቤቱ ያጽናዎት። በአረጋዊ ዘመንዎ የመረጦት አምላክ ይመስገን!!
21👍6
🙏 ሰላም ሰላም ውድ ቤተሰቦቼ እንዴት ናችሁ። ጸሎት፣ ስግደት፣ ጾሙ እና ሱባኤ እንዴት ይዟችኋል። እግዚአብሔር አምላካችን ሁላችንንም ይርዳን በርቱ፣ ጠንክሩ። ቤተሰቦቼ የበረከት ሥራችን ቀጥሏል ከፍታችን ታህሳስ 19 የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል እየመጣ ነውና በዚህ ቀን በረከትን እንድናገኝ በበረከት ሥራ ላይ እንሳተፍ እያልኩኝ መልእክተን አቀርባለሁ።

🙏 በአንድ የተቸገረ ሰው ሕይወት ውስጥ ገብቶ ማገዝ ምን ያህል መታደል ነው። የሰዎችን ሀዘን መጋራት ምንኛ መታደል ነው። በሰዎች ፈተና እና መከራ ውስጥ ገብቶ እንደመተጋገዝ ያለ ምን ትልቅ ደስታ አለ ቤተሰቦቼ። ስለዚህ ሁላችንም የአቅማችንን እንተባበር እላለሁ።

🙏 የሚታገዙ ቤተሰቦች አሉና በውስጥ መስመር ሁላችሁም እያናገራችሁኝ የቅዱስ ገብርኤል የበረከት ሥራ ላይ እንሳተፍ እላለሁኝ። 🙏🙏🙏

ለማናገር፦
@haile_gebriel_tube_bot
8👍2
"የትዕቢት መጀመሪያ ሰውን ከእግዚአብሔር ትለየዋለች" (ሲራክ 10፥2)

❖ ሳጥናኤል ከቀደመ ክብሩ ተዋርዶ ዲያብሎስ የኾነው “ይኽ ሕዝብ ፈጣሪውን አጥቶ ተጨንቋል፤ እኔ ፈጠርኳችሁ በማለትም ፈጣሪነትን በእጄ ልያዝ” ብሎ በታበየ ጊዜ ነው፤ ዲያብሎስ ዲያብሎስ የኾነ አስቀድሞ ዲያብሎስ ኾኖ ስለተፈጠረ አይደለም፡፡

❖ በትዕቢት ከመውደቁ በፊት የዐሥሩ ነገደ መላዕክት የአጋዕዝት አለቃ ንዑድ ክቡር መልዐክ ነበርና፤ ከዚኽ ክብሩና ሹመቱ ያዋረደው ትዕቢቱ ነው፤ እሳቱ ወደማይጠፋ ትሉ ወደማያንቀላፋ እሳት የጣለው ትዕቢቱ ነው፤ ወደ ዘለዓለማዊ ሐሳር የጣለው ትዕቢቱ ነው፡፡

❖ ተወዳጆች ሆይ! ትዕቢት የነበረንን መልካም ምግባር ሁሉ የሚየሳምም ደግሞም የሚገድል ክፉ ደዌ ነው፤ ወንጌላዊው እንዲህ ይለናል፦ “በሰው ዘንድ የከበረው በእግዚአብሔር ዘንድ ግን የተዋረደ ነው” እንዲል ውስጣችን በትዕቢት የተሞላ ከኾነ በአፍአ ብንመጸውትም፣ ብንጸልይም ምጽዋታችን ወይም ጸሎታችን በእግዚአብሔር ዘንድ ርኵስ መሥዋዕት ነው፡፡ (ሉቃ 16፥15)

❖ ትዕቢት ካለብን ውስጣችን ንጽሕና የለውም፤ ስለዚኽ ሰው ንጽሕናውን እንዲያጣ የሚያደርገው ዝሙት ወይም ማመንዘር ብቻ አይደለም ማለት ነው፤ ትዕቢት ጭምር እንጂ፤ እንደውም ትዕቢት ከዝሙት ወይም ከማመንዘር በላይ እኛን ያቆሽሻል፤ ለምን? ምንም እንኳን ዝሙት ንስሐ ካልገቡበት ሥርየተ ኀጢአት የሌለው በደል ቢኾንም በዝሙት የቆሸሸ ሰው ንስሐ ለመግባት ቅርብ ነው፤ በትዕቢት የታመመ ሰው ግን እንዲኽ እንደ ዘማዊው ያለ ዓቅምን አያገኝም፤ ስለዚኽ ትዕቢት እጅግ አደገኛ ደዌ ዘነፍስ ነው ማለት ነው፡፡

❖ ከትዕቢተኛ ሰው በላይ ጐስቋላ ሰው የለም፤ የፈለገ ያኽም ብዕል (ሃብት)፣ የዚህን ዓለም ዕውቀት ቢኖረውም ከትዕቢተኛ ሰው የባሰ ጐስቋላ ሰው የለም፤ በንግሥና ወንበር ቢቀመጥ፣ በሰዎች ዘንድ እጅግ “የተከበረ” ቢኾንም ከዚኽ ሰው በላይ ጐስቋላ ሰው የለም ብዬ በእውነት እነግራችኋለኁ፤ እስኪ ንገሩኝ! የዚኽን ከንቱ ደግሞም ኀላፊና ጠፊ ዓለምን ነገር ይዞ ከመታበይ በላይ ምን አላዋቂነት አለ?

❖ ነገ የሚጠወልገውን የመስከረም አደይ አበባን (የዚኽን ዓለም ክብር) ይዞ ከሚታበይ ሰው በላይ ማን ነው ጐስቋላ? ሕልምን ይዞ እውኑን ዓለም ከሚያጣ ከዚኽ ትዕቢተኛ ሰው በላይ ማን ጐስቋላ ሰው አለ ልትሉኝ ትችላላችሁ? አኹን በወርቅ አልጋ ላይ ስለተኛ ከሚታበይ ሰው በላይ ማን ድኻ አለ ልትሉኝ ትችላላችኁ?

በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
8😢1
🌹 በእግዚአብሔር ፊት ከሚቆሙ ከከበሩ ሊቃነ መላእክት አንዱ ቅዱስ ገብርኤል፦ በመልአከ ሞት ከመውደቅ የምትታደግ ገብርኤል ሆይ ሰላም ላንተ ይሁን። አማላጅነትህን በመታመን ተስፋ እናደርጋለንና በመዓልትም በሌሊትም አንተ ጠብቀን።🙏

(መልክአ ገብርኤል)

እንኳን ለመልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
14
❖ መንፈሳዊ ሕይወትን ገና ስትጀምረው ለፍጹምነት ጥቂት የቀረህ ያህል ይሰማሃል፤ አንተ ጋር ያለው ደስታ እና ሰላም ሌሎች ጋር የሌለ ይመስልሃል። በዚህች ሁከት በሞላባት ዓለም አንተ ብቻ ክርስቶስን እንዳገኘኸው ታስባለህ፤ የቀረው ሕዝበ አዳም እንዲሁ በከንቱ ሲርመሰመስ የሚውል ባካና ሆኖ ይታይሃል፤ ታዝንለታለህ፣ አይይይ ይህ ኃጢአተኛ ሕዝብ ምን ይሻለዋል? ትላለህ።

❖ የእውነተኛ መንፈሳዊ እድገት መገለጫ ግን ይህ አይደለም፤ ሰው ወደ እግዚአብሔር እየቀረበ ሲመጣ ከሌላው ሰው ይልቅ የራሱ ጉድለት ይታየዋል፤ መንፈሳዊነት የሚገልጥልህ ሰዎችን ተመልክተህ የምትፈርድበትን ውጫዊ ዓይንህን ሳይሆን ራስህን አይተህ የምትወቅስበት የውስጥ ዓይንህን ነው፤ መንፈሳዊ ሕይወትህ ሲጎመራ "አይ ሰው" ሳይሆን "አይ እኔ!" ያሰኝሃል።

❖ አባ ማቴዎስም እንዲህ ይላል "ሰው የበለጠ ወደ እግዚአብሔር ሲቀርብ ይበልጥ ኃጢአተኛ መሆኑ እየታየው ይመጣል፤ ነቢዩ ኢሳይያስ እግዚአብሔርን ካየ በኋላ ከንፈሮቼ የረከሱብኝና የጠፋሁ ሰው ነኝ እንዳለ"

❖ ከብቃት ደርሰህ መላእክት ሲወጡና ሲወርዱ ቢታዩህ እንኳን ሁሉ እንዳንተ ስለሚመስልህ እንደ ዮሐንስ ሐጺር "ሚካኤል ይበልጣል ወይስ ገብርኤል?"  እያልህ ከአጠገብህ የቆመውን ትጠይቃለህ እንጂ "አይይ አንተ እንኳን ገና አልበቃህም፤ ብዙ ይቀርሃል" ብለህ ወዳጅህን አታናንቅም ይልቅ "ለእኔ ብቻ ገልጦ ለሌላው እንዲሰውር የሚያደርገው ምንም ቁም ነገር የለኝም" በማለት ከወንድምህ የተሻልህ እንዳልሆንክ በፍጹም ልብህ ታምናለህ።

❖ ለመንፈሳዊ ሕይወት አዲስ ስትሆን ገና ጥቂት ጸልየህ፣ ጥቂት ጾመህ፣ ጥቂት መጽውተህ ሳለ ግን ሩጫህን ወደ መጨረሱ የተቃረብህ ይመስልሃል፤ ጉዞህን በግማሽ እርምጃ ከመጀመርህ ከፍጻሜው ላይ የደረስህ ያህል ይሰማሃል "እኔን ምሰሉ" ማለት ያምርሃል፤ ነገር ግን መንፈሳዊ ሕይወት የቱንም ያህል ብትሮጥበት ሁል ጊዜ እንደ ጀማሪ የሚያደርግ ረጅም ጎዳና ነው፤ ሰማንያ ዓመት በገዳም ሲጋደል የነበረው አባ ሲሶይ ነፍሱ ከሥጋው ልትለይ በቀረበች ጊዜ ብዙ መነኮሳት በአልጋው ዙሪያ ከበውት ሳለ ቅዱሱ "አምላኬ ሆይ፣ እባክህ ለንስሐ የሚሆን ጥቂት ጊዜን ስጠኝ?" እያለ በልቅሶ ሲማጸን ሰሙት። በዚህ የተገረሙት መነኮሳቱ አባ ሲሶይን "አባታችን አንተ እድሜ ልክህን በንስሐ የኖርህ መምህረ ንስሐ ሆነህ ሳለ እንዴት አሁን ጥቂት የንስሐ ጊዜን ትለምናለህ?" ቢሉት፣ ቅዱሱም "ልጆቼ ይህን መንፈሳዊ ጥበብ (ንስሐን) ገና አሁን መጀመሬ ነው" አላቸው።

❖ ጌታ ሆይ መንፈሳዊ ሕይወት እኖር ዘንድ አስጀምረኝ፤ ገና ጀማሪ ሳለሁ ደርሻለሁ ከማለትም ሰውረኝ፤ እንድቆም አትፍቀድልኝ፤ ወደ አንተ ሳበኝ፣ አሳድገኝ።

#Subscribe #Like #Share
   👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
👍53
20231229_184918
<unknown>
🙏 በቅዱስ ገብርኤል ቀን እንዲህ አይነች ምርቃት ይድረሳችሁ በያላችሁበት። በዛሬው ቀን እህታችን ሰብሌ ከቤተሰቧቿ ጋር በመሆን በላከችው የበረከት ሥራ የአንድ እናትን የደስታ ምርቃት ተቀብለናል። እንዲሁ ደግሞ ችግራችሁ ችግራችን በማለት ተጋርተናል እና ይሄው ምርቃቱ ለሁላችሁ ይድረስ ብያለሁ። እህታችን እግዚአብሔር አምላክ ቤታችሁን በበረከት፣ በሰላም ይሙላላችሁ። በእውነት እናታችን እንዴት እንደተደሰተች። ሁላችሁም ቤተሰቦቼ የበረከት ሥራ ላይ እንሳተፍ፣ ያለንን ከሰዎች ጋር እንካፈል። እንበርታ 🙏🙏
16👍2