HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ
2.25K subscribers
1.99K photos
96 videos
51 files
3.81K links
❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️

👇👇👇
http://www.youtube.com/@haileG2239
Download Telegram
"በዐረብና በተርሴስ ወርቅ እንዳጌጠች ታቦት በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ያጌጥሽ ማርያም ቀንሞስ ቀናንሞስ የሚባሉ ሽቱዎች ኢያቄምና ሐና ለጳጦስ ምሳሌ የኾንሽ አንቺን ከአስገኙሽ ዘንድ በሦስት ዓመት በቤተ መቅደስ የመኖር ተአምርን አሳየሽ።"

(አባ ጽጌ ድንግል )

ቅድስትሆይ ከልጅሽ ዘንድ ምህረትን ይቅርታን ለምኝልን🙏🏾

#ውድ_ቤተሰቦቼ_የዩቱብ_ቻናላችንን_ተቀላቁ!

#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
🥰114👍2
#_ወደ_አገልግሎት_ተመልሻለሁ!

#_እሑድ_ታህሳስ_7_አገልግሎት_ይጀመራል!

አያት አምስት ሰንሻይን አፓርታማ መጥምቁ ዮሐንስ እና እመቤታችን ቤተ ክርስቲያን!

በቀሲስ ሄኖክ ወልደ-ማርያም

ሼር በማድረግ ለወዳጆ አዳርሱ!

የወለላይቱ እመቤት ልጆች አያት አምስት ሰንሻይን አፖርታማ ጋር በሚገኘው በመጥምቁ ዮሐንስ እና በእመቤታችን ቤተ ክርስቲያን እሑድ ጠዋት ታህሳስ 7 ቀን ከቅዳሴ መልስ የተለመደውን የጥምቀት አገልግሎት በቋሚነት እሰጣለሁ፡፡ ስለዚህ መጥታችሁ አገልግሎቱን እንድታገኙ ቅድስት ቤተ ክርስቲያኗ ጥሪዋን ታስተላልፋለች፡፡

የተለመደው የጸበል ጥምቀት፣ የንስሐ እና የቄደር ጥምቀት፣ የቅብዓ ቅዱስ እና የዝክር አገልግሎት ይቀጥላል፡፡ እሑድ ጠዋት ታህሳስ 7 እመቤታችን በዘርፋፋ ቀሚሷ አቅፋ ደግፋ፣ መጥምቁ ዮሐንስ በጸሎቱ እቅፍ ድግፍ አድርገውን በሰላም በደጃቸው ያገናኙን፡፡

#_የትራንስፖስት_መምጫው

#_ከመገናኛ አያት መጥተው ከአያት በቦሌ አራብሳ ታክሲ ተሳፍረው አያት አምስት ሰንሻይን አፓርታማ ጋር ወርደው በባጃጅ ቤተ ክርስቲያኑ ደጅ ይወርዳሉ

#_ከቦሌ አያት መጥተው ከዛ የቦሌ አራብሳ ታክሲ ተሳፍረው ሰንሻይን አፓርታማ ጋር ወርደው በባጃጅ ቤተ ክርስቲያኑ ደጅ ይወርዳሉ

#_ከቃሊቲ፣ ከቱሉ ዲምቱ፣ ከኮዬ ፈጬ የምትመጡ አያት ወርዳችሁ ከአያት የቦሌ አራብሳ ታክሲ ተሳፍራችሁ አያት አምስት ሰንሻይን አፓርታማ ዳር ወርዳችሁ በባጃጅ ቤተ ክርስቲያኑ ደጅ ትወርዳላችሁ

#_ከለገ_ጣፎ አያት መጥታችሁ፣ ከአያት የቦሌ አራብሳ ታክሲ ተሳፍራችሁ አያት አምስት ሰንሻይን አፓርታማ ጋር ወርዳችሁ በባጃጅ ቤተ ክርስቲያኑ ደጅ ትወርዳላችሁ

#_በግል_መኪና የምትመጡ ከየትኛውም አቅጣጫ አያት አምስት ሰንሻይን አፓርታማ ደርሳችሁ በመግቢያው ታጥፋችሁ ቀጥታ ቤተ ክርስቲያኑ ደጅ ትደርሳላችሁ

"በጸሎት እየነቃችሁ ለእርሱ ትጉ" ቆላስ 4፥2

#ውድ_ቤተሰቦቼ_የዩቱብ_ቻናላችንን_ተቀላቁ!

#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
◈ "ሰው ለጸሎት ሲቆም ሰይጣን ይቀመጣል ሰው ጸሎት ሲያቁዋርጥ ሰይጣን ሥራ ይጀምራል" (ዜና አበው)

◈ "ጌታ ሆይ ታላቅ ሲሆን ታናሽ የሆነ፤ ንቁ ሲሆን የተኛ፤ ንጹሕ ሲሆን የተጠመቀ፤ ሕያው ሲሆን የሞተ፤ ንጉሥ ሲሆን ራሱን ያዋረደ እንዳንተ ያለ ማን አለ?" (ቅዱስ ኤፍሬም)

◈ "አትናቴዎስ ሆይ ዓለም ሁሉ ጠልቶሃል" ሲሉት እንዲህ አለ "እኔ አስቀድሜ ዓለምን ስለጠላሁት ነው ብሏል" በረከታቸው ይደርብን!

#ውድ_ቤተሰቦቼ_የዩቱብ_ቻናላችንን_ተቀላቁ!

#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
👍133🔥1
◈ አስተውሉ! የጸሎት ትኩረት የጥንካሬ ጉልበት አግኝቶ ሳይደክም እንድንተጋ ለአምላክ ካለ ፍቅር የሚጀምር ፈቃድ እና ስለ ጽድቅ ሕይወት የመዋደቅ ቁርጥ ውሳኔ ከኛ ይጠበቃል፡፡ የሚያሳዝነው ደግሞ አብዛኞቻችን እነዚህ የሉንምና መንፈሱ እፉዬ ገለባን የመሸከም ያህል ንቆ ይጫወትብናል፡፡
 
◈ የጸሎት አሳብ ከተመስጦአችን እያፈነገጠ እንዳይበታተን የምናስርበት መንፈሳዊ ገመድ፤ አስቀድመን ጸሎት ለማድረግ የምንፈልግበት የመነቃቃት ጉልበት ላይ ይመረኮዛል፡፡ ጸሎት እንደ ውኃ ጠምቶን እንደ ምግብ ርቦን ከሆነ ልንጸልይ የፈለግነው፤ የጸሎት አሳባችንም የመበተን ዕድሉ ጠባብ ነው፡፡ ምክንያቱም ሰው ፈልጎ የሚያደርገውን ነገር ሲያደርግ፤ ትኩረቱን በሚያደርገው ነገር ላይ ለመሰብሰብ አይቸገርም፡፡

◈ አንድ እናት ልጆቿን ጠዋት ቁርስ የማብላት ኃላፊነት እንደሚሰማት ሁሉ፤ ጸሎትም ላይ ይሄ ይሰማት፡፡ አንድ አባት ቤተሰቡን የማስተዳደር ኃላፊነት በትከሻው እንዳለ እንደሚያስብ ሁሉ ጸሎትንም እንዲሁ ያክብረው፡፡ አንድ ተማሪ ትምህርቱን የማጥናት ኃላፊነት ቢያንስ ለፈተና ግድ ሆኖ እንደሚታየው ሁሉ ጸሎትንም እንዲህ ይየው፡፡ ምንም ውስብስብ ነገር የለውም፤ ለሥጋ የምናስበውን ያህል ለነፍስም እናስብለት፡፡

◈ እነዚህን ጠላቶች በመዋጋቱ ረገድ የመጀመሪያው ቀዳሚ መፍትሔ፤ ወደ ጸሎት ቤት እንደገባን በቀጥታ መደበኛውን ጸሎት ከማድረስ አስቀድሞ መናፍስቱን በሰማያዊ ስሞች ማሰር ያስፈልጋል፡፡
#በርቱ 🙏

#ውድ_ቤተሰቦቼ_የዩቱብ_ቻናላችንን_ተቀላቁ!

#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
👍4
🌹 የሰማዕቷ የቅድስት አርሰሜ ረድኤት በረከት በሁላችን ላይ ጸንቶ ይኑር። ቃልኪዳንዋ አይለየን 🌹 ታህሳስ 6 ቅዳሴ ቤቷ ይከብራል። 🙏🙏 እንኳን አደረሳችሁ 🌹
28
"ኃይል የሌለውን ምንኛ ረዳኸው!
ብርታት የሌለውን ክንድ ምንኛ አዳንኸው!" ኢዮ 26፥2
🥰4😢2
ጥያቄ 1: ከጌታችን መድኃኂታችን ኢየሱስ ከርስቶስ ልደት አስቀድሞ የሚመጡ ሦስቱ እሑዶች ስያሜያቸው ምንድን ነው? ሁላችሁም ተሳተፉ።
Anonymous Quiz
13%
ሀ፡ ስብከት፣ ኒቆዲሞስ፣ ደብረ-ዘይት
62%
ለ፡ ስብከት፣ ብርሃን፣ ኖላዊ
20%
ሐ፡ ቅድስት፣ ዘወረደ፣ መፃጉዕ
4%
መ፡ ምኩራብ፣ ገብርሔር፣ ብርሃን
👍2
ጥያቄ 2፡ የሰው ልጅ ከአራቱ ባሕርያተ ሥጋ መፈጠሩ ግልጽ ሲሆን ዕድሜውም እንዲሁ በዐራት ደረጃዎች የተከፈለ ነው። በዚህም መሠረት ከሃያ እስከ ዐርባ ዓመት ያለው ጌዜ የትኛውን ባሕርይ ያመለክታል? የራሳችሁን አሳብም መጻፍ ይቻላል።
Anonymous Quiz
71%
ሀ፡ የእሳት
9%
ለ፡ የውሃ
11%
ሐ፡ የነፋስ
9%
መ፡ የመሬት
👍1
ጥያቄ 3፡ በገጠሩ ሀገራችን ኢትዮጵያ እናቶች ልጆች ሲታመሙ ወይም ጭንቀት ሲይዛቸው መድሐኒት ነው በማለት ለቡዳ፣ ለዓይነጥላ በማለት አንገት፣ ክንድ፣ ጭን ላይ ኪታብ ወይም እጄ-ሰብ ያስራሉ? በጬሌ ይዳብሳሉ። የግል ምልከታችሁን ጻፉ?
Anonymous Poll
62%
ሀ፡ እውነት (ችግሩ ለመናፍስት በማለዳው እንሰጣለን)
14%
ለ፡ ሐሰት (እንዲህ የሚባል ነገር የለም)
33%
ሐ፡ በትክክል እኔም ገጥሞኛል፣ ተዳብሻለሁ፣ አስሪያለሁ።
5%
መ፡ የግል አሳባችሁን ጻፉ
1
ጥያቄ 5: ስለ ስንበተ-ክርስቲያንና ስለ ዕለተ ምጽአት የሚናገረው የቅዳሴ ክፍል?
Anonymous Quiz
31%
ሀ፡ ቅዳሴ ጎርጎርዮስ
22%
ለ፡ ቅዳሴ ማርያም
28%
ሐ፡ ቅዳሴ አትናቴዎስ
19%
መ፡ ቅዳሴ ባስልዮስ
👍1
ጥያቄ 6፡ የልጅ በሕሪይን የሚያላብስ የሚያስለቅስ፣ ጣፋጭ ነገር ከረሜላ ወይም ስኳር አብዝተን እንድንጠቀም የሚያደርግ፣ የተቆራረጡ ልብሶች ወይም እርቃን እንድንሆን የሚያደርግ የቤተሰብ ዛር መንፈስ የቱ ነው። ትልቅ ሆነን እንደ ልጅ የሚያደርግ መንፈስ? እድሜያችን ገፍቶ እንኳን ቀለም መቀባት፣ ልፕስቲክ፣ ሰው ሰራሽ ጸጉር መቀጠል? እንዲህ የሚያደርጉ መንፈሶች በብዛት የትኛው ነው?
Anonymous Quiz
4%
ሀ፡ ሼህ አምበሶ
11%
ለ፡ አውልያ የከራማ መንፈሶች
77%
ሐ፡ ሙጬ ወይም ሙጫዮ
4%
መ፡ ጨንገር አባ ላፋ
3%
ሠ፡ የግል አሳባችሁን ጻፉ