HAILE GEBRIEL - በማለዳ ንቁ
2.24K subscribers
1.99K photos
96 videos
51 files
3.81K links
❤️ ቅዱሳን አባቶች እንዲህ ይላሉ **ጸጋ ያለምስጋና አያድግም ይላሉ** እግዚአብሔር ሆይ ስለሆነልኝ፣ ክፉውንም ከእኔና ከቤተሰቦቼ ስላራክልኝ 👏 አመሰግንሃለሁ ❤️

👇👇👇
http://www.youtube.com/@haileG2239
Download Telegram
Forwarded from ንዒ ኀቤየ
◈24ቱ ካህናተ ሰማይ 🙏

◈ የሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ መታሰቢያ በዓላቸው ነው ህዳር 24። አንዚህንም እግዚአብሔር ከሠራዊተ ሩፋኤል ሃያ አራት ሊቃናትን መርጦ በመንበረ ስብሐት በመጋረጃዋ ውስጥ ዙሪያዋን ክንፍ ለክንፍ ገጥሞ አስቀምጧቸዋል። ስማቸውንም ካህናተ ሰማይ አላቸው። የእሳት፣ የወርቅ ጽንሐ አስያዛቸው። የብርሀን አክሊል ጳዝዮን ከሚባል የብርሀን ዘውድ ደፋላቸው። የብርሀን ዘንግ ማኅተሙ መስቀል የሆነ አስያዛቸው። የብርሀን ካባ ላንቅ ኅብሩ መብረቅ የመሰለ አለበሳቸው።

እነዚህም በአንድ ላይ በዓጠኑ ጊዜ ከማዕጠንታቸው የሚወጣው ጢስ መልኩ መብረቅ፤ ድምጹ ነጎድጓድ፤ መዓዛው መልካም የሆነ ነው። (መጽሐፈ አክሲማሮስ ዘእሁድ)

◈ "በዙፋኑም ዙሪያ ሃያ አራት ዙፋኖች ነበሩ። በዙፋኖቹም ላይ ነጭ ልብስ ለብሰው በራሳቸውም ላይ የወርቅ እክሊል ደፍተው ሃያ አራት ካህናት ተቀምጠው ነበር።" (ራዕ.4፥4-5)

◈ "ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጽንሐ ይዞ በመሠዊያው አጠገብ ቆመ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሠዊያ ላይ ለቅዱሣን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው፤ የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሣን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ።" (ራዕ 8፥3-5)

24ቱ ካህናተ ሰማይ

1.አካኤል
2.ፋኑኤል
3.ጋኑኤል
4.ታድኤል
5.አፍድኤል
6.ዘራኤል
7.ኤልኤል
8.ተዳኤል
9.ዮአኬል
10.ገርድኤል
11.ልፍድኤል
12.መርዋኤል
13.ኑራኤል
14.ክስልቱኤል
15.ኡራኤል
16.ባቱኤል
17.ሩአኤል
18.ሰላትኤል
19.ጣውርኤል
20.እምኑኤል
21.ፔላልኤል
22.ታልዲኤል
23.ፐሰልዱኤል
24.አሌቲኤል።

ምንጭ:-ተአምኆ ቅዱሳን
ንባቡና ትርጓሜው ገጽ 149
በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ።

◈ ዳግመኛም በዚህ ዕለት ሐዲስ ሐዋርያ አቡነ ተክለሐይማኖት ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር 25ኛ ሆነው የሥላሴን መንበር ያጠኑበት መታሰቢያ በዓላቸው ነው። የጻድቁ አባታችን የአቡነ ተክለሐይማኖት አንዲሁም የካህናተ ሰማይ ረድኤት በረከታቸው በአማላጅነታቸው ከምናምን ከሁላችን ጋር ይሁን።

#ሠዓሊ_ቀሲስ_አማረ_ክብረት

#ውድ_ቤተሰቦቼ_የዩቱብ_ቻናላችንን_ተቀላቁ!

#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
11👍3🥰2
+ ከማያልቀው ጸጋህ +

አንተን መውደድን
ወደ አንተ መቅረብን
አንተን መፍራትን

◈ በቀሪው ዘመናቻን ላለፈው በደላችንና ስንፍናችን መደምሰሻ ምግባር የምንፈጽም አድርገን፤ የሕይወት ጎዳናችንን አቅናልን በቸርነትህ ከአንተ ጋር አንድነታችንን አብዛልን በግብራችን ደስ እናሰኝህ ዘንድ አድርገን።

#ውድ_ቤተሰቦቼ_የዩቱብ_ቻናላችንን_ተቀላቁ!

#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
◈ ኢየሱስ ክርስቶስ ደካማውን የእኛን ሥጋ የለበሰው፣ ራሱን ባዶ አድርጎ በግርግም የተወለደው፣ በስተመጨረሻም እርቃኑን የተሰቀለው ለእኛ ሲል ነው። ይህ ሁሉ ትሕትና እርሱን አንዳች የማይጠቅመው ስለ ሰው መዳን ሲል ግን የከፈለው ትልቅ ዋጋ ነው። የእኛ ትሑት መሆን ከእኛ በቀር ማንን ይጠቅማል? ትዕቢተኛ መሆናችንስ ከእኛ በላይ ማንን ሊጎዳ ይችላል? ጨው ለራስህ ስትል ጣፍጥ እንደሚባለው ክርስቲያን ለራሱ ሲል ትሑት መሆን ይገባዋል።

ትሕትና ለራስ ነው!

#ውድ_ቤተሰቦቼ_የዩቱብ_ቻናላችንን_ተቀላቁ!

#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
13🥰1
◈ እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ፤ ማንም ድምፄን ቢሰማ ደጁንም ቢከፍትልኝ፥ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ጋር ይበላል። (ራዕ 3፥20) 🙏🙏🙏

ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሣት ሥዕላት ሠዐሊ

#ውድ_ቤተሰቦቼ_የዩቱብ_ቻናላችንን_ተቀላቁ!

#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
11
◈ የአይሁዳዊው ጥያቄ "እናንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነው የምትሉት ይሄ ክርስቶስ እውነት የእግዚአብሔር ልጀ ከሆነ፤ ወደ ቢታንያ በመጣ ጊዜ አልዓዛር የተቀበረበትን ቦታ ሳያውቅ ቀርቶ አልዓዘርን የት ቀበራችሁት? ብሎ እንደጠየቀ በወንጌላችሁ ተጽፏል። ለዚህ መልስ ስጡኝ፤ እኔንም ከመጽሐፈ ኦሪቴ ጠቅሳችሁ ጠይቁኝ?" ስል የመከራከሪያ ነጥቡን አቀረበ።

◈ የአባ ጊዮርጊስ ዘገስጫ መልስ፦ "እኔ በወንጌል ሳይሆን በኦሪት እከራከሪሃለው። የምኩራብ መጽሐፍት ሁሉ ለቤተክርስቲያን የታወቁ ናቸውና። ምኩራብ ዘራች፤ ቤተክርስቲያንም አጨደች፤ ምኩራብ ፈተለችው፤ ቤተክርስቲያን ለበሰችው፤ አዳምን በገነት ሳለ "አዳም ሆይ ወደት ነህ" ብሎ የጠየቀው ማነው? አብርሃምንስ ምስትህ ሣራ ወዴት ነች ብሎ የጠየቀ ማነው? እስቲ መልስልኝ። ሰይጣንንስ ከወዴት መጣህ? ብሎ የጠየቀው ማንነው? እግዚአብሔር አብ አይደለምን? በዚህን ጊዜ አይሁዳዊው መልስ አጥቶ ዝም አለ። በረከታቸው ይደርብን።

#ውድ_ቤተሰቦቼ_የዩቱብ_ቻናላችንን_ተቀላቁ!

#Subscribe #Like #Share
👇👇👇👇
www.youtube.com/@haileG2239
www.youtube.com/@pagumentube
15👍1
በእውነት እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን። በአጭር ጊዜ ውሽጥ 4000 ሰብስክራይበር ወይም ቤተሰብ ስላገኘሁ። ይሄ ሁሉ ደግሞ የእናንተም ነውና በርቱ። እግዚአብሔር አምላካችን ሁላችንንም ይርዳን። ምክንያቱም እኔ እንድበረታ እና የተለያዩ ትምህርቶችን እንዳቀርብ ያግዘኛልና። አሁንም ቤተሰብ ያልሆናችሁ እየሆናችሁ። የሆናችሁ ደግሞ ትምህርቶችን ሸር በማድረግ እንማማር አላለሁኝ። አመሰግናለሁ በእውነት። ሁለም እንደምለው "በርቱ፣ ጠንክሩ፣ ጎልምሱ፣ በሃይማኖት ጽኑ" 🙏🙏
15🥰2