ግጥም ከገጣሚያን
2.59K subscribers
1.09K photos
47 videos
5 files
59 links
👋🏽እንኳን ደህና መጡ በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ አዝናኝና አስተማሪ ግጥም እንዲሁም ፅሁፎች ከገጣሚያን ለእርሶ ተዝናኖት ሲባል ከእራሳችንም እንዲሁም ከየቦታው ተሰባስበው ለእናንተ የሚቀርብበት አውድ ነው!!
🙄ጊዜዎትን ስለሰጡን እናመሰግናለን🙏
ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
ግጥም ለመላክ @Habtemaryam16 ላይ አድረሱን
Download Telegram
።።።ምን አገባኝ ።።።

እኔ ምን አገባኝ
የምትሉት ሀረግ
እሱ ነዉ አገሬን
ያረዳት እንደ በግ
ብዬ ግጥም ልፅፍ
ብድግ አልኩኝና
ምን አገባኝ ብዬ
ቁጭ አልኩ እንደገና

(በእውቀቱ ስዩም)🙏🏾💚💛❤️
━━━━━━━━━━━━━━━
#ሼር 🙏🙏🙏
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
..
@habtamu39
@habtamu39
@habtamu39 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
ዛሬ በሶስቱ መንግስታት ጊዜ ህዝቡ የተናገራቸውን ስነ ቃሎች እንካችሁ ብያለሁ።
በጓድ መንግስቱ ኃይለማርያም ጊዜ
1. መንጌ ኃይለማርያም የብረት ምሰሶ፤
የጠፋውን ሀገር አቀናው መልሶ።
2. ስንደው በሄሊኮፕተር በቆሎው በጀት፤
መንጌ ኃይለማርያም የድሆች አባት።
3. መንጌ ኃይለማርያም አይሙት አይበላሽ፤
ለተራበው ስንዴ ለጠገበው ክላሽ።
በጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ዜናዊ ጊዜ
1. ደርግ ፋሽስት ነው ከወያኔ አይከፋም፤
ስልጣን ቢጥመውም ሀገር አያጠፋም።
ወያኔ እንደ ትል ነው ውስጥ ውስጡን ይበሳል፤
ሰርስሮ ሰርስሮ ወናውን ያስቀራል።
2. ስማችን ወያኔ ስድባችን ቅማላም፤
የደርግን ወታደር ነዳነው እንደ ላም።
3. እነ ውስኪ እራቱ እነ ክትፎ ቁርሱ፤
አሙሲት ሲተኮስ ባህርዳር ደረሱ።
4. ወልቃይት ታረሰ በጥቋቁር በሬ፤
እራያም ታረሰ በጥቋቁር በሬ፤
በቆሎ ብንዘራው በቀለ በርበሬ።
5. ኸረ ምን ታሰበ ምን ተጠረጠረ፤
ራያ ከመሀሉ በሽቦ ታጠረ፤
አላማጣ ወዳ ቆቦ ወድህ ቀረ።
በጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ጊዜ
1. ሙሴ መጣ ብለህ መለከት ስትነፋ፤
የመጣልህ አዳኝ ከፈርዖን ከፋ!
2. ኢህአዴግ ሄደና መጣ ብልፅግና፤
ኑሮም ተወደደ ረከሰ ዝምድና!
3.ባባቴ ቤት ጮማ እንዳልቆረጥኩበት፤
በእናቴ ቤት ጠጁን እንዳልጠጣሁበት፤
ብልፅግና መጥቶ ሹሮም አጣሁበት!
ሙሳ ሙሃባ ወሎ ወረባቦ🙏🏾💚💛❤️Belay Bekele Weya
━━━━━━━━━━━━━━━
#ሼር 🙏🙏🙏
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
..
@habtamu39
@habtamu39🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
አንዳንድ ከርሳም
የሽሚያ አለም ኑሮ በረከት የነሳው፣
እበላለሁ ብሎ ስስት ያሰከረው፣
ትውልድ የበዛበት ዘመነ ጠማማ፣
እጎርሳለሁ ብሎ ከከርሱ ሲስማማ
ይዞት የነበረው የእሱ አይደለምና፣
እውነቱ ሲታወቅ ሀቁ ሲወጣበት፣
ሳይጎርሰው ተቀማ።🙏🏾💚💛❤️
━━━━━━━━━━━━━━━
#ሼር 🙏🙏🙏
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
..
@habtamu39
@habtamu39
@habtamu39 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
💚💛❤️
የሀገር ፍቅራቸው ሞትን አስንቋቸዋል፤ ኢትዮጵያን አብዝተው ወደዷት አክብረውም እስከበሯት። ትውልድ ነኝና እኮራባቸዋለሁኝ፤ ስለክብሬ ሞተዋልና ሰማእት አቡነ ጴጥሮስ እያልኩኝ እጣራለሁኝ 💚💛❤️
“ፋሺስቶች ያገራችንን አርበኞች ሽፍታ ቢሏቸው እውነት እንዳይመስላችሁ፡፡ ሽፍታ ማለት ያለ አገሩ መጥቶ የሰውን አገር የሚወር ይህ በመካከላችሁ መጥቶ የቆመ አረመኔው የኢጣሊያ ፋሺስት ነው ፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ለእርሱ እንዳይገዛ ውጉዝ ነው ፡፡ የኢትዮጵያ መሬት እንዳትቀበለው የተገዘተች ትሁን ፡፡" ይህን ተናግረው በጀግንነት ለሀገራቸው ሲሉ ህይወታቸውን አሳልፈው ሰጡ።>> አቡነ ጴጥሮስ የኢትዮጵያን በጠላት ኃይል መወረር እና የኢትዮጵያውያንን መከራ መቀበል በጽኑ በመቃወም በፋሽስት ኢጣሊያ አማካይነት የጸና መከራ ደርሶባቸዋል ፤ አልፎ ተርፎም ከሀገሬ እና ከሕዝቤ በፊት በማለት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተውሐምሌ ፳፪ ቀን የሰማዕትነትን ጽዋዕ ቀምሰዋል
ሐምሌ 22 1928 ዓ.ም🙏🏾💚💛❤️
━━━━━━━━━━━━━━━
#ሼር 🙏🙏🙏
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
..
@habtamu39
@habtamu39
@habtamu39 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
#ናፈቀኝ
""""""""
ወደሰማዩ ሳይ በደመና ምስል፣
ባይኔ ተከሰተ እርሱን የሚመስል፣
ጉብታውን ስቃኝ ተራራ ዳገቱ፣
ተመሳሰለብኝ ከኮራ ደረቱ፣
ንፋስ የሚገፋው ያየሩ መአዛ፣
እርሱን አስታወሰኝ ናፍቆት እየገዛ፣
እያንዳንዱ ነገር ያሳለፍነው ጌዜ፣
ገደለኝ ትዝታው ሆነብኝ ትካዜ፣
ጩኬ የሰደብኩት ያኔ ሲያበሳጨኝ፣
ትውስ አለኝና ባርባር አለኝ ቆጨኝ፣
መጣብኝ ጫዎታው መጣብኝ ሞገሱ፣
ናፈ'ከኝ ብል እንኳን አይሰማኝም እሱ፣
ናፍቆኛል ጨንቆኛል ግን ባይመለስስ፣
ዝም ልበልና ጎርፍ ዕንባዬን ላፍስስ።
#ናፈቀኝ
✍️ኤዶምገነት ፃፈችው🙏🏾💚💛❤️
━━━━━━━━━━━━━━━
#ሼር 🙏🙏🙏
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
..
@habtamu39
@habtamu39
@habtamu39 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
እውር በምርኩዙ
ነጋዴ በወርቁ ፣
አይደራደርም ብለህ ያስተማርከኝ ፣
መምህሬ የኔታ ዛሬ ገና ገባኝ ።
እውሩም እኔ ነኝ ፣
ምርኩዜም አገሬ ፣
ነጋዴውም እኔ ፣
ወርቋም ናት አገሬ ።
አገር ለማያየው ምርኩዝ አቀብየው ፣
ወርቄን ደበቀና ከምኔው በመዳብ ቀየረው ።
ስለ አቤ ጉበኛ ገና ይቀራል !!
/ Girum Misalie /🙏🏾💚💛❤️
━━━━━━━━━━━━━━━
#ሼር 🙏🙏🙏
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
..
@habtamu39
@habtamu39
@habtamu39 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
ጠብቄሽ ነበረ

ከቀጠርሸኝ ቦታ ፡ ብቻዬን ቁጭ ብዬ
ከትልቋ ዛፍ ስር ፡ ጥላ ተከልዬ
"ና" ካልሽኝ ቦታ ላይ ፡ ሰዐተን አክብሬ
ጠብቄሽ ነበረ ባንቺ ፡ ተቀጥሬ
ፀሀይዋን ሳልሰለች ፡ በፀሀይ መጥቼ
ጉዳይ እያለብኝ ፡ ጉዳዬንም ትቼ
እስክትመጪ ድረስ ፡ ናፍቆቴ እየናረ
ፍቅሬ ለብቻዬ ፡ ጠብቄሽ ነበረ

ታዲያ ምን ያደርጋል
እኔ ስጠብቅሽ ፡ አንቺ አልመጣሽም
ቀጥራኝ ቀረች ብዬ ፡ ለሰው አላማሽም🙏🏾💚💛❤️
━━━━━━━━━━━━━━━
#ሼር 🙏🙏🙏
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
..
@habtamu39
@habtamu39
@habtamu39 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
እና ...
ከከንፈሬ ጣዕም
ከአንገቴ ስር ሽታ
ደስታን ከሚሰጠኝ የላብህ ጠብታ
ያለፈ ፍቅርህን ተው እያልኩህ ነበር !
ለነፍሴ የሰ'ሰትኩት ....
(ላ'ይታይ የሸሸጉኹት )
በአካል ፍትጊያ
በሰውነት ውድቀት ባክኖብኝ እንዳይቀር
እረፈኝ አላልኩም ?
አትዘምርልኝ ፤አትስበከኝ ፍቅርን
አታወሳስብብኝ ፤አትፈትናት ነፍሴን ?
ብቻ!
ብቻ ተው እያልኩህ
አንተም እየተውከኝ
ከአካሌ ስትርቅ ለነፍስህ አቀረብከኝ 😁😋🤗❤️

ፊያሜታ 👌✍️✍️✍️✍️✍️🙏🏾💚💛❤️
━━━━━━━━━━━━━━━
#ሼር 🙏🙏🙏
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
..
@habtamu39
@habtamu39
@habtamu39 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
ሐሰተኛው ከተሰኘው መፅሐፍ የተገኘ
🙏🏾💚💛❤️
━━━━━━━━━━━━━━━
#ሼር 🙏🙏🙏
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
..
@habtamu39
@habtamu39
@habtamu39 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴
💔ማፍቀር መረገም ነው❤️‍🔥

ድሮ ልጅ እያለን ገና ጨቅላ ሆነን
ለእቃቃ ጨዋታ ባልና ሚስት ልኖን!
አብረን ተሰብስበን ፊልም ላይ እንዳየነው
አንደኛው ሲፈቀር አንዱ ነው ሚያፍቅረው

እኛም ይሄን አይተን እኔ ነኝ ማፈቅረው እየተባባልን
ሁለት አፍቃሪ ሆንን ጠልተን መፈቀርን
በማፍቀር መጣላት አብዝተው ተገርመው
አንድ አባት እያዩን ሳቁ ጮክ ብለው😁

አባ እርሶ ይፍረዱን ማነው የሚያፈቅረው
እኔ ወይስ እሷ ብለን ጠየቅናቸው
እሳቸው በመልሱ እንባ ተናንቋቸው
መፈቀርን ፀጋ ማፍቀር መታደል ነው
ሄዋኗ ትፈቀር አፍቅር ደሞ አዳም
ብለው አስተማሩን ፍቅር አያጣላም

ታድያ እነዛ አባት እንዲህ ብለው መክረው
በልጅነት እድሜ ማፍቀርን ተርጉመው😕
ዛሬ ትልቅ ስሆን የእውነት አፍቅሬ
ማፍቀር መታደል ነው እያልኩኝ ተምሬ

ዛሬ ላይ ሄዋኔን አፈቀርኩሽ ብላት
ሴጣን እንደያዘው እንደ እብድ አደረጋት😳
መፈቀር ፀጋ ነው ነበር የተባልኩት
ማፍቀር መታደል ነው ብዬም ነው ያደግኩት



ያ...

አፈቀርኩሽ ስላልኩ ልቤን ካደማችው?💔
ያፈቀራት ልቤን ካቆሳሰለችው?
አባ ተሳስተዋል ያስተምሩ ደግመው
ማፍቀርን ሀጥያት መረገም ነው ብለዉ🙏🏾💚💛❤️
━━━━━━━━━━━━━━━
#ሼር 🙏🙏🙏
ቻናላችንን ይቀላቀሉ
◦◦✧join 👇👇👇👇👇
..
@habtamu39
@habtamu39
@habtamu39 🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴🟢🟡🔴