CODE TECH™ (channel)
227 subscribers
42 photos
1 video
8 files
21 links
“Any fool can write code that a computer can understand. Good programmers write code that humans can understand.” – Martin Fowler

Channel ➻ @h_programming
Group ➻ @h_programmers_group
Bot ➻ @h_gramBot
Download Telegram
ሰላም ዉድ የ CodeTech ቤተሰቦች 🤞

ሰሞኑን በተፈጠረዉ የ internet መቋረጥ ምክንያት ረዘም ላለ ጊዜ ትምርትችን ሳንሰጥ ቆይተናል : : ይሄንንም ታሳቢ በማድረግ ከላይ በዛ ያሉ ትምርቶችን ለቀናል : : እናንተም በትኩረት እንደምታነቧቸዉ እና ያልገባችሁን እንደምትጠይቁ ተስፋ እናደርጋለን : :

መልካም ንባብ !!!
ከኛ ጋር ናችሁ ? እንቀጥል ?

(ከሆናችሁ የ like ምልክቷን ጠቅ 😉)
እንዴት አርገን አንዴ የተፈጠረ dictionary ዉስጥ key-value pair እንጨምራለን ?

x = {}

ለምሳሌ ከላይ የምታዩት dictionary ዉስጥ ይህን 👉 "name":"sara"👈 key-value pair መጨመር ብፈልግ..

x["name"] = "sara"

አረጋለሁ ማለት ነዉ : :

በዚ መሰረት "name":"key" የሚባል key-value pair ወደ dictionary'ዉ አስገባን ማለት ነዉ : : መግባቱን ለማረጋገጥ #print አርገን ማየት እንችላለን : -

print(x)

ዉጤት : -
{"name":"sara"}

🌐 ባጠቃላይ key-value pair ለመጨመር መጀመሪያ የ dictionary 'ዉን ስም እንፅፋለን (ልክ እኔ x'ን እንደፃፍኩት) ከዛም square bracket ( [ ) እንከፍታለን ከዛም #key እንፅፋለን በመቀጠልም square bracket( ] ) እንዘጋለን በመቀጠል assignment operator ( = ) እናስገባና #value እንፅፋለን : :


@h_programming
CODE TECH™ (channel)
እንዴት አርገን አንዴ የተፈጠረ dictionary ዉስጥ key-value pair እንጨምራለን ? x = {} ለምሳሌ ከላይ የምታዩት dictionary ዉስጥ ይህን 👉 "name":"sara"👈 key-value pair መጨመር ብፈልግ.. x["name"] = "sara" አረጋለሁ ማለት ነዉ : : በዚ መሰረት "name":"key" የሚባል key-value pair ወደ dictionary'ዉ አስገባን ማለት ነዉ…
የቀጠለ...

የ list'ን ወይም የ tuple'ን element 'ኦች access ለማረግ index እንጠቀም ነበር ይህ ግን በ dictionary አይሰራም : : በ dictionary #key 'ን እንደ index ተጠቅመን #value 'ን access እናረጋለን እንጂ index አንጠቀምም!

💡በነገራችን ላይ: በ አንድ dictionary ዉስጥ ሁለት ተመሳሳይ #key ዎች ሊኖሩን አይችልም : :

🔆 አንድ dictionary ላይ የሚገኙ #key 'ዎች የያዙትን #value በሌላ value መቀየር..

x = {"name" : "Johnson", "age" : 17}

ለምሳሌ ከላይ ያለዉ dictionary ላይ "age" የምትባለዉ #key የያዘቺዉን #value ማለትም 17 'ን ለምሳሌ በ 18 መቀየር ብፈልግ እንደዚ👇 አረጋለሁ

x["age"] = 18

በዚመሰረት ቀየርኩት ማለት ነዉ

🌐 ከላይ እንዳረኩት መጀመሪያ የ dictionary ዉን ስም እንፅፋለን ከዛም square bracket ( [ ] ) #key እንፅፋለን ከዛም assignment operator ( = ) ካረግን በኋላ #value እንፅፋለን : :


🏡 የቤት ስራ 😊
Dictionary #mutable የ data አይነት ነዉ ? ወይስ #immutable የ data አይነት ?

ከላይ የተማርነዉ ይሄን ጥያቄ የሚመልስ ይመስለኛል 😉



@h_programming
CODE TECH™ (channel)
የቀጠለ... የ list'ን ወይም የ tuple'ን element 'ኦች access ለማረግ index እንጠቀም ነበር ይህ ግን በ dictionary አይሰራም : : በ dictionary #key 'ን እንደ index ተጠቅመን #value 'ን access እናረጋለን እንጂ index አንጠቀምም! 💡በነገራችን ላይ: በ አንድ dictionary ዉስጥ ሁለት ተመሳሳይ #key ዎች ሊኖሩን አይችልም : : 🔆 አንድ…
...የቀጠለ

ለቤት ስራዉ መልስ በመስጠት ልጀምር..

ባለፈዉ አንዴ የተፈጠረ dictionary ዉስጥ የሚገኝን #value እንዴት #key 'ን በመጠቀም መቀየር እንደሚቻል አይተናል : : አንዴ ከተፈጠረ በኋላ መሻሻል የሚችል ከሆነ ደሞ dictionary #mutable data type ነዉ ማለት ነዉ : : (ለዛ ነበር መልሱ ከላይ አለ ያልኳቹ)

ዛሬ የምናየዉ እንዴት አርገን dictionary ዉስጥ የሚገኝን #vlaue ነጥለን ማዉጣት እንደምንችል ነዉ : :

ባለፈዉ እንዳረግነዉ ይሄንንም ለማረግ #key እንጠቀማለን : :

x = {"name":"Sophia", "ID":2}

ለምሳሌ ከላይ 🙄 ያለዉ dictionary ዉስጥ 2'ን ነጥለን ማዉጣት እና #print ማረግ ብንፈልግ ይሄን እናረግለን 👇

print(x["ID"])

ዉጤት:-
2

የ dictionary 'ዉን ስም ከዛ square bracket ( [ ] ) ዉስጥ #key እንፅፋለን. በዚህም መሰረት #key 'ዉ ላይ የሚገኘዉን #value ነጥለን እናወጣለን ማለት ነዉ : :

ነገር ግን dictionary ዉስጥ የማይገኝ #key ብንፅፍስ 🤔

ለምሳሌ :-

x = {"name":"Sophia", "ID":2}

print(x["age"])

ዉጤት:-
error

"age" የሚባል #key dictionary ዉስጥ ባለመኖሩ error ይፈጠረል ማለት ነዉ : :


ይቀጥላል...




📣 @h_programming
🔆 ከ dictionary ላይ key-value pair መደለት

ይህን ለማረግ del key word 'ን እና #key 'ን እንጠቀማለን : :

del key word በ python አንዴ declare የተደረገ variable 'ን(literal የተወከለበትን variable), ከ mutable data type 'ኦች ላይ element 'ኦችን ለመደለት እንዲሁም define የተደረገ function 'ን ለመደለት የምንጠቀምበት key word ነዉ : :

📝 Note: key word ማለት የምንፅፈዉ code ላይ የተለየ ትርጉም ያላቸዉ ቃላቶች ናቸዉ : :
ለምሳሌ:- assert, and, as, break, class, continue, del, def, for,...,etc. እያንዳንዱ key word የየራሱ የተለየ ትርጉም እና ተግባር አለዉ : : እነዚህ ቃላት በ python የተያዙ ወይም reserved word ስለሆኑ እንደ identifier 'ም ሆነ እንደ literal መጠቀም አንችልም : :

እየተነጋገርን ያለነዉ ስለ dictionary እንደመሆኑ እስኪ እንዴት አርገን del 'ን በመጠቀም ከ dictionary ላይ key-value pair መደለት እንደምንችልት እንይ 👇

ለምሳሌ: -

user_data= {"name":"Sara", "age":19, "ID":2}

ለምሳሌ ከላይ ካለዉ dictionary ዉስጥ "age":2 የሚለዉን key-value pair ለመደለት #key 'ዉን ማለትም "age" 'ን በመጠቀም እንደሚከተለዉ እናረጋለን : -

del user_data["age"]

👆በዚ መሰረት ("age":19)'ን ከ dictionary ዉስጥ አሶጣን ማለት ነዉ : መዉጣቱን ለማረጋገጥ print አርገን ማየት እንችላለን

print(user_data)

ዉጤቱ : -

{"name":"Sara", "ID":2}

✅ በርግጥም መቷል 🙄

ለ list 'ም ተመሳይ መንገድ እንጠቀማለን... ነገር ግን #key ሳይሆን index በመጠቀም ∇

ለምሳሌ ከታች list ዉስጥ ካሉት element 'ኦች 1'ን መደለት ብንፈልግ

x = [1, 2, 3, 4]

del x[0]

...እናረጋለን : : 0'ን የፃፍኩት ያዉ እንደምታቁት 1 index 0 ላይ ስለምትገኝ ነዉ : :

#እስኪ_እናረጋግጥ

print(x)

ዉጤቱ : -
[2, 3, 4]

✅ በርግጥም ተደልቷል ማለት ነዉ !




⚜ እንቀጥላለን ⚜

@h_programming
⚜ Dictionary | ማጠቃለያ
------------------------------------------

dictionary አንዱ የ python data type ሱሆን በ ዉስጡ key-value pair 'ኦችን ለማስቀመጥ ይጠቅማል : :

list ላይ እና tuple ላይ index 'ን በመጠቀም element 'እችን access እንደምናረገዉ ሁሉ dictionary ላይ ደሞ #key 'ን በመጠቀም #value 'ን access ማረግ እንችላለን : : ለምሳሌ key 'ን በመጠቀም :-

👉 key-value pair ወደ dictionary ማስገባት (https://t.me/h_programming/422)

👉 key 'ላይ የሚገኘዉን value በሌላ value መቀየር (https://t.me/h_programming/423)

👉 value 'ን ነጥለን ማዉጣት (https://t.me/h_programming/425)

👉 key-value pair መደለት (https://t.me/h_programming/429)

... እንደምንችል አይተናል : :

🔺 Dictionary mutable data type እንደሆነም አይተናል (https://t.me/h_programming/425)


ባጠቃላይ ስለ #dictionary ያየነዉ ይሄን ይመስላል : :



@h_programming
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ㅤㅤSet
--------------------

#set አንዱ የ python data type ሲሆን በዉስጡ የተለያዩ ሌሎች data type 'ኦችን ለማስቀመጥ ይጠቅማል : :

✔️ set በ curly brackets( {} ) የተከበበ ነዉ : :

ምሳሌ : -
{1, 2, 3}

✔️ በ አንድ set ዉስጥ ሁለት ተመሳሳይ element 'ኦች ሊኖሩ አይችሉም : :

ምሳሌ
x = {1, 2, 2}
print(x)

output :-
{1, 2}

✔️ #set mutable data type ነዉ : :

✔️ በ #set ዉስጥ የሚገኙ element 'ኦች immutable data type መሆን አለባቸዉ : :

ምሳሌ :-

{[1,2] , [3,4]} #wrong❌

❔ ምክንያቱም list mutable data type ስለሆነ የ set element መሆን አይችልም : :

{{"name":"sara"}, {"id":2}} #wrong❌

❔ ምክንያቱም dictionary mutable data type በመሆኑ የ set element መሆን አይችልም

{{1,2} , {3,4}} #wrong❌

❔ ምክንያቱም set mutable data type በመሆኒ የ #set element መሆን አይችልም : :

{1, 1.0, "1", (1, 2)} #correct ✅

❔int, float, string, tuple, እና ሌሎችም የ python immutable data type 'ኦች የ #set element መሆን ይችላሉ : :


@h_programming
🌐 ማጠቃለያ | python data type

እስካሁን ዋና ዋና እና ብዙ ጊዜ የምንጠቀምባቸዉ የ python data type 'ኦች ስናል ቆይተናል : :

አንዴ declare ከተደረጉ (ከተፈጠሩ በኋላ) መሻሻል ይችላሉ ወይስ አይችሉም የሚለዉን መሰረት በማረግ በ ሁለት ከፍለን ለማየት ሞክረናል : -

1⃣ mutable: ከተፈጠሩ በኋላ መስተካከል (modify) መሆን የሚችሉ የ python data type ናቸዉ : :

ምሳሌ : - List, Dictionary, Set

2⃣ immutable: እነዚ ደሞ አንዴ ከተፈጠሩ በኋላ መሻሻል የማይችሉ የ python data type 'ኦች ናቸዉ : :

ምሳሌ:- String, Integer, Float, Tuple



⚜ ስለ data type ለ ጊዜዉ በዚ እናበቃለን ወደፊት ግን አንዳንድ ተጨማሪ ነገሮችን የምናይ ይሆናል : :


@h_programming
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🐍 ስለ python data type እስካሁን የተማርነዉን ለማጠናከር ይሄንን video እንድትመለከቱ እመክራለሁ!

https://youtu.be/3z16g2oOxaQ

❤️ በዛዉም Subscribe እና like በማረግ ሌሎች የ python እና ከ technology ጋር የተገናኙ ትምህርቶችን ማግኘት ትችላላቹ !


@h_programming
CODE TECH™ (channel) pinned «🐍 ስለ python data type እስካሁን የተማርነዉን ለማጠናከር ይሄንን video እንድትመለከቱ እመክራለሁ! https://youtu.be/3z16g2oOxaQ ❤️ በዛዉም Subscribe እና like በማረግ ሌሎች የ python እና ከ technology ጋር የተገናኙ ትምህርቶችን ማግኘት ትችላላቹ ! @h_programming»
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Which error(s) occur during execution of this code?

try: print(1 / 0) except: raise ValueError
Anonymous Quiz
52%
ZeroDivisionError
19%
ValueError
19%
ZeroDivisionError, ValueError
10%
None
Which number is not printed by this code?

try: print(1) print(20 / 0) print(2) except ZeroDivisionError: print(3) finally: print (4)
Anonymous Quiz
7%
1
24%
2
7%
3
9%
4
11%
1, 2
11%
2, 3
4%
3, 4
27%
None
CODE TECH™ (channel)
Quiz በምንጠይቅበት ጊዜ
ጥሩ!
ለ #Quiz_4 ተዘጋጁ በቅርቡ ትፈተናላቹ : : 😊

ፈተናዉ የሚወጣዉ ከ #Quiz_3 እስካሁን በተማርናቸዉ ነገሮች ዙሪያ ይሆናል !

በነገራችን ላይ የራሳችሁን ጥያቄ አዉጥታችሁ መላክ ትችላላችሁ : : እኛም ጥያቄዎቻችሁን ሰብሰብ አርገን #quiz_4 ላይ አካተን የምናመጣቸዉ ይሆናል : :

ጥያቄዎችን ለመላክ @h_grambot ን ተጠቀሙ!



@h_programming
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM