CODE TECH™ (channel)
227 subscribers
42 photos
1 video
8 files
21 links
“Any fool can write code that a computer can understand. Good programmers write code that humans can understand.” – Martin Fowler

Channel ➻ @h_programming
Group ➻ @h_programmers_group
Bot ➻ @h_gramBot
Download Telegram
Variables & Literals

#Variable ማለት identifier ማለት ነዉ : : #Literal ማለት ደሞ አንድ variable ላይ የሚወከለዉ ነገር ማለት ነዉ : :

x = 2

⚜ ለምሳሌ ከላይ ባለዉ ምሳሌ ላይ 'x' variable ስትሆን '2' ደሞ literal ነች : :

🔺 በ python ሁልጊዜም ቢሆን variable በግራ በኩል የሚቀመጥ ሲሆን literal ደሞ በቀኝ በኩል መቀመጥ አለበት : : 👇

x = 3 ✅
3
= x ❌

🔺 አንዴ አንድን literal በሆነ variable ከወከልን በኋላ variable 'ኡን በመጠቀም የተለያዩ ነገሮችን ማረግ እንችላለን : :

⚜ ምሳሌ : -

x = 1

ከላይ ባለዉ ምሳሌ ላይ እንደምታዩት '1' ቁጥር በ 'x' ተወክላለች : : ስለዚህ '1' ቁጥርን print ማረግ ብንፈልግ x 'ን ተጠቅመን print ማረግ እንችላለን : : ልክ እንደዚ 👇

print(x)

✨ ሌሎችንም ነገሮች የ literal 'ኡ የተወከለበትን variable በመጠቀም ማከናወን ይቻላል : :

⚜ለምሳሌ : -

y = x + 1

እንደምታዉቁት 'x' የወከለችዉ '1' ቁጥርን ነዉ : : ስለዚህ x + 1 የሚመጣዉ '2' ነዉ : : ስለዚህ 'y' ማለት '2' ነዉ ማለት ነዉ : :

🌐 ባጠቃላይ variable በየትኛዉም ቦታ የ literal 'ኡን ቦታ በመተካት ማገልገል ይችላል : :

🔅 ሁሉንም የ python data type ( የ ዳታ አይነቶች ) እንደ literal መጠቀም ማለትም በፈለግነዉ variable መወከል እንችላለን : :

ከነዚህ የ python data types መካከል 3 'ቱን (string, integer, እና float) 'ን አይተናል : : በቀጣይ ከነሱ በተጨማሪ ያሉ የ python የ data አይነቶችን ለማየት እንሞክራለን : :

#ሰናይ_ቀን




@h_programming
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Data types in python

በ python variable ላይ ልንወክላቸዉ የሚችሉ ወይም literal መሆን የሚችሉ የ data አይነቶች የሚከተሉት ናቸዉ : :

ከዚ በፊት 3 'ቱን(string, integer እና float) 'ን ስላየን 4 ብዬ እጀምራለሁ : :

4⃣ List

List ማለት የተለያዩ የ data አይነቶችን በዉስጡ የያዘ የ data type ስብስብ ነዉ : :

✔️ List ዉስጥ ያሉ እያንዳንዱ data type 'ኦች በ comma (,) የተለዩ ናቸዉ : :

✔️ እንዲሁም list በ square bracket ( [ ] ) የተዘጋ ነዉ : :

⚜ ምሳሌ : -

[1, "codeTech", 1.0]

🔺 ለምሳሌ ከላይ የምትመለከቱት list የሚባለዉን data type ነዉ : : እንደምትመለከቱት በዉስጡ 3 ነገርችን ይዟል እነሱም integer(1), string("codeTech"), እና float(1.0) : : እነዚህም element 'ኦች በ comma( , ) ተለይተዋል : :

🔘 Empty list: empty list ማለት በ ዉስጡ ምንም የሌለዉ ሊስት ማለት ነዉ : : ልክ እንደዚ 👇

[]

🔘 list 'ኦችን ወደ አንድ list መቀየር

በ python 3 ሁለት ወይም ከዛ በላይ የሆኑ list 'ኦችን ወደ አንድ list ለመቀየር የ መደመር ምልክትን ( + ) እንጠቀማለን : :

⚜ ምሳሌ : -

["code"]
["tech"]

🔺 ለምሳሌ ከላይ የምታዩአቸዉን ሁለት list 'ኦች ወደ አንድ list ለመቀየር : -

["code"] + ["tech"]

...እናረጋለን, ዉጤቱም እንደዚ 👇 ይሆናል

["code", "tech"]

🔘 አንድን list የተደጋገመ ለማረግ

ይህን ለማረግ የ ማባዛት ምልክት ( * ) 'ን እንጠቀማለን : :

["code", "tech"]

🔺ለምሳሌ ከላይ ያለዉ list ሁለቴ እንዲደጋገም ብፈልግ በ 2 አባዛዋለሁ : : ልክ እንደዚ 👇

["code", "tech"] * 2

በዉጤቱም ይህን 👇 አገኛለሁ...

["code", "tech", "code", "tech"]

🌐 ባጠቃላይ እንዲደጋገም በፈለግነዉ ቁጥር ልክ እያባዛን የተደጋገመ list መስራት እንችላለን : :

ስለ list ይቀጥላል....


@h_programming
CODE TECH™ (channel)
Data types in python በ python variable ላይ ልንወክላቸዉ የሚችሉ ወይም literal መሆን የሚችሉ የ data አይነቶች የሚከተሉት ናቸዉ : : ከዚ በፊት 3 'ቱን(string, integer እና float) 'ን ስላየን 4 ብዬ እጀምራለሁ : : 4⃣ List List ማለት የተለያዩ የ data አይነቶችን በዉስጡ የያዘ የ data type ስብስብ ነዉ : : ✔️ List ዉስጥ ያሉ…
....የቀጠለ

☑️ አንድ list ዉስጥ የሚገኙ element 'ኦች የየራሳቸዉ መለያ ቁጥር አላቸዉ : : ይህንንም መለያ ቁጥር "index" እንለዋለን : :

☑️ የመጀመሪያዉ list ዉስጥ የሚገኝ element index 'ኡ '0' ሲሆን 2 'ተኛዉ ላይ የሚገኘዉ element ደሞ index 'ኡ '1' ነዉ : : 3, 4 ... እያለ ይቀጥላል : :

"ጠጅ በብርሌ : ነገር በምሳሌ" እንዲሉ አበዉ እስኪ በምሳሌ ለማየት እንሞክር ...

⚜ ምሳሌ : -

[0, 1, 2, "codeTech"]

🔺 ለምሳሌ ከላይ በምታዩት list ዉስጥ index 0 ላይ የሚገኘዉ element 0 ነዉ : index 1 ላይ የሚገኘዉ ደሞ 1 ነዉ : index 2 ላይ የሚገኘዉ ደሞ 2 ነዉ : የመጨረሻዉና index 3 ላይ የሚገኘዉ ደሞ "codeTech" ነዉ : :

☑️ index 'ን በመጠቀም የተለያዩ ነገሮችን ማረግ እንችላለን ለምሳሌ: -

✔️ አንዴ የፈጠርነዉን list አባላቶቹን መቀየር
✔️ ከ አንድ list ዉስጥ element 'ኦችን ቆርጦ ለማዉጣት : :

...e.t.c

ለዛሬ ከላይ የጠቀስናቸዉን ለማየት እንሞክር : :

1⃣ አንዴ የተፈጠረን list አባላቶች መቀየር

በምሳሌ እንየዉ...👇

x = [1, 3, 3, 4, 5]

🔺 ከላይ የምታዩት list 'x' በሚባል variable ተወክሏል : : ለምሳሌ በ list 'ኡ ዉስጥ index 1 ላይ የሚገኘዉን element ማለትም 3 'ትን በ 2 መቀየር ብንፈልግ እንዚ 👇 እናረጋለን

x[1] = 2

እንደምታዩት መጀመሪያ list 'ኡ የተወከለበትን variable እንፅፋለን( እኔ የሰራሁት list የተወከለዉ በ 'x' ስለሆነ x ብዬ ፅፌአለሁ)

:> በመቀጠል square bracket እንከፈታለን ( [ )

:> ከዛ በመቀጠል መቀየር የፈለግነዉን የ list element የሚገኝበትን index እንፅፋለን (እኔ መቀየር የፈለኩት element index 1 ላይ የሚገኘዉን ማለትም 3'ን ስለሆነ 1 ብዬ ፅፌአለሁ )

:> በመቀጠል የከፈትነዉን square bracket እንዘጋዋለን ( ] )

በዚ መሰረት index 1 ላይ ያለዉን element ቀየርኩት : : የተቀየረዉም list ይሄን ይመስላል 👇

[1, 2, 3, 4, 5]

2⃣ ከ አንድ list ዉስጥ element 'ኦችን ቆርጦ ለማዉጣት...

ይህንንም በ ምሳሌ እንየዉ 👇

x = [1, 2, 3, 4, 5]

ለምሳሌ ከዚህ list ዉስጥ ከ 2 እስከ 5 ( 5'ን ሳያካትት) ቆርጠን ለማዉጣት ብንፈልግ እንደዚ እናረጋለን 👇

x[1: 4]

:> እንደምታዩት መጀመሪያ list 'ኡ የተወከለበትን variable እንፅፋለን( እኔ የሰራሁት list የተወከለዉ በ 'x' ስለሆነ x ብዬ ፅፌአለሁ)

:> በመቀጠል square bracket እንከፈታለን ( [ )

:> ከየት ጀምሮ ነዉ መቁረጥ የምንፈልገዉ ? index 'ኡን እንፅፋለን: : (እኔ መቁረጥ የፈለኩት ከ 2 ጀምሮ ስለሆነ 2 የምትገኝበትን index ማለትም 1'ን ፅፌአለሁ)

:> በመቀጠል ሁለት ነጥብ እናረጋለን( : )

:> እስከየት ነዉ መቁረጥ የፈለግነዉ ? index እንፅፋለን (እኔ መቁረጥ የፈለኩት እስከ 5 ስለሆነ 5 የምትገኝበትን index ማለትም 4'ን ፅፌአለሁ)

:> በመቀጠል የከፈትነዉን square bracket እንዘጋለን ( ] )


ጥያቄ ካላቹ ግሩፕ ላይ ጠይቁን!


@h_programming

(I typed this fast in my 5.5 inch mobile, if any mistakes I am sorry)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እስካሁን በተማርነዉ መሰረት ጥያቄ ልጠይቃቹ

❓ከትች የለዉን list ከ 1 እስከ 4 (4'ን ጨምሮ) ቆርጣቹ አዉጡ!

[1, 2, 3, 4, 5, 6]

❓ከትች የምታዩት list የ ሆነ ቦታ ቅደም ተከተሉን አልጠበቀም : : አስተካክሉት!

["A", "B", "B", "D", "E"]

መልሳችሁን በ 👉 @h_grambot
የመጀመሪያዉ...

x = [1, 2, 3, 4, 5, 6]
print(x[0:4])


ወይም ባጭሩ : -

print([1, 2, 3, 4, 5, 6][0:4])

ሁለተኛዉ : -
list 'ኡ ቅደም ተከተሉን እንዳይጠብቅ የሆነዉ "B" በመደገሙ ነዉ ስለዚህም ለማስተካከል "B" 'ን በ "C" እንቀይራለን : :

x = ["A", "B", "B", "D", "E"]
x[2] = "C"


በዚ መሰረት ተስተካክሏል ለማረጋገጥ #print አርገን ማየት እንችላለን...

print(x)
ዛሬ ስ list አንዳንድ ተጨማሪ ነገሮችን እናያለን ከዛ በፊት ግን ስለጠፋሁ በጣም ይቅርታ መጠየቅ እፈልጋለሁ 🙏 : : ማንም left ያረገ ባለመኖሩም ደስ ብሎኛል : : እኛ እንድንበረታታ እና ቶሎ ቶሎ ትምርት እንድንለቅ በየጊዜዉ የምንሰጣቸዉ ጥያቄውች ስሩ መልሳቸዉንም ላኩ : ግሩፑ ላይም ያልገባችሁን ጥያቄ በመጠየቅ ተሳተፋ ! የምንሰጣቸዉን example run ስታረጉ error ካጋጠማችሁ ምን አልባትም type ሳረግ ተሳስቼ ይሆናልና ግሩፕ ላይ ወይም @h_grambot ላይ ጠይቁ ማስተካከያ ታገኛላችሁ !

#ለምትከታተሉን_እና_member_በመጨመር_ለምታግዙን_እናነሰግናለን 🙏
CODE TECH™ (channel)
....የቀጠለ ☑️ አንድ list ዉስጥ የሚገኙ element 'ኦች የየራሳቸዉ መለያ ቁጥር አላቸዉ : : ይህንንም መለያ ቁጥር "index" እንለዋለን : : ☑️ የመጀመሪያዉ list ዉስጥ የሚገኝ element index 'ኡ '0' ሲሆን 2 'ተኛዉ ላይ የሚገኘዉ element ደሞ index 'ኡ '1' ነዉ : : 3, 4 ... እያለ ይቀጥላል : : "ጠጅ በብርሌ : ነገር በምሳሌ" እንዲሉ አበዉ እስኪ…
...የቀጠለ

3⃣ በተወሰነ መጠን እየዘለሉ ቆርጦ ማዉጣት

[x: y: z]

ባለፈዉ ለማየት እንደሞከርነዉ x የምንጀምርበት ቦታ index ነዉ : y ደሞ የምንጨርስበት ቦታ indez ነዉ : z ደሞ ዛሬ የምናዉ ነዉ እሱም በ ምን ያህል እየጨመረ ይሂድ የሚለዉን የምንፅፍበት ቦታ ነዉ : :

በምሳሌ እንየዉ...

x = [1, 2, 3, 4, 5, 6]

ለምሳሌ ከላይ በ x ከተወከለዉ list ዉስጥ 1'ን, 3'ን, እና 5'ን ቆርጠን ብንፈልግ እንደዚ እናረጋለን 👇

x[0: 5: 2]

:> 0 ያረግንበት ምክንያት መቁረጥ የምንፈልገዉ ከ index 0 ጀምሮ በመሆኑ ነዉ : :

:> መቁረጥ የምንፈልገዉ እስከ 6 (6'ን ሳይጨምር) ነዉ : 6 ደሞ የምትገኘዉ index 5 ላይ ነዉ ስለዚ 5 አልን ማለት ነዉ : :

:> 2 ያልበት ምክንያት በ ሁለት በሁለት እየጨመረ እንዲሄድ ስለፈለግን ነዉ : በ ሁለት እየጨመረ ማለት አንድ አንድ እየዘለለ እንዲሄድ ያደርግልናል : :

በዚህም መሰረት እንደዚህ 👇አይነት እናገኛለን : :

[1, 3, 5]

4⃣ Negative indexing

እስካሁን ያየነዉ የ indexing አይነት positive indexing ይባላል : እሱም ከ ግራ ወደ ቀኝ ለ እያንዳንዱ element የምንሰጠዉ ቁጥር ነዉ : :

negative indexing ማለት ደሞ ከ ቀኝ ወደ ግራ ለእያንዳንዱ element የሚሰጥ ቁጥር ነዉ : :

[1, 2, 3, 4]

በ negative indexing
4 የምትገኘዉ index👉 -1 ላይ ነዉ
3 የምትገኘዉ index👉 -2 ላይ ነዉ
2 የምትገኘዉ index👉 -3 ላይ ነዉ
1 የምትገኘዉ index👉 -4 ላይ ነዉ

positive indexing 'ን ለመተካት ቆርጦ, ለማዉጣት እንደተጠቀምንበት ሁሉ negative index 'ንም ተጠቅመን ተመሳሳይ ነገር ማረግ እንችላለን : :

x = [1, 2, 2, 4, 5]

ለምሳሌ

:> negative indexing ተጠቅማችሁ ከላይ ያለዉ list -ዉስጥ የምትገኘዉን 2 ቁጥር በ 3 ተኩ ቢባል : -

x[-3] = 3

-3 ያልንበት ምክንያት በ negative indexing 2 የምትገኘዉ index -3 ላይ በመሆኑ እንደሆነ አስተዉሉ !

:> negative indexing ተጠቅማችሁ ከላይ ያለዉን list ከ 1 እስከ 4(4'ን ሳይጨምር) ቆርጣችሁ አዉጡ ቢባል : -

x[-5 : -2]

-5 ያልነዉ 1 በ negative indexing -5 ላይ ስለምትገኝ ሲሆን -2 ያልነዉ ደሞ 4 በ negative indexing የምትገኘዉ -2 ላይ በመሆኑ ነዉ : :



ያልገባችሁን group ላይ ጠይቁ !


@h_programming
@h_programmers_group
CODE TECH™ (channel)
...የቀጠለ 3⃣ በተወሰነ መጠን እየዘለሉ ቆርጦ ማዉጣት [x: y: z] ባለፈዉ ለማየት እንደሞከርነዉ x የምንጀምርበት ቦታ index ነዉ : y ደሞ የምንጨርስበት ቦታ indez ነዉ : z ደሞ ዛሬ የምናዉ ነዉ እሱም በ ምን ያህል እየጨመረ ይሂድ የሚለዉን የምንፅፍበት ቦታ ነዉ : : በምሳሌ እንየዉ... x = [1, 2, 3, 4, 5, 6] ለምሳሌ ከላይ በ x ከተወከለዉ list ዉስጥ 1'ን…
....የቀጠለ

3⃣ ከ ቀኝ ወደ ግራ መቁረጥ

እስካሁን ያየነው እንዴት አርገን ከ ግራ ወደ ቀኝ እንደምንቆርጥ ነዉ አሁን ደሞ ከ ቀኝ ወደ ግራ እንዴት አርገን የ list 'ኡን element 'ኦች ማዉጣት እንደምንችል እናያለን : :

በምሳሌ እንየዉ ...
x = [1, 2, 3, 4, 5]

ለምሳሌ ከላይ የሚታየዉን list ከ 4 እስከ 1(አንድን ሳይጨምር) ቆርጣችሁ አዉጡ ቢባል እንደዚ እናረጋለን 👇

x[3 : 0 : -1]

:> መቁረጥ የፈለኩት ከ 4 ጀምሮ ስለሆነ እና 4 ደሞ index 3 ላይ ስለምትገኝ 3 'ን ፃፍኩኝ : :

:> መቁረጥ የፈለኩት እስከ 1 ስለሆነ እና 1 ደሞ index 0 ላይ ስለምትገኝ 0 'ን ፃፍኩኝ : :

:> ከ ቀኝ ወደግራ መቁረጥ ስለፈለኩ ደሞ -1 'ን ፃፍኩ : :

ባለፈዉ እንዳየነዉ 3'ተኛ ላይ የሚፃፈዉ ቁጥር በምንቆርጥበት ጊዜ በምን ያህል መጠን እየዘለልን እንሂድ የሚለዉን የምንወስንበት ቁጥር ነዉ : : 1 ብናስገባ ለምሳሌ በ አንድ አንድ እየጨመረ ስለሚሄድ ምንም ሳይዘል ይቆርጥልናል : : 2 ብናስገባ ሁለት ሁለት ሁለት እየጨመረ ስለሚሄድ አንድ አንድ እየዘለለ ይቆርጥልናል : : .....negative ካረግነዉ ደሞ የምንቆርጥበትን አቅጣጫ ይቀይርልናል ማለትም ከ ቀኝ ወደ ግራ ያረግልናል : :

ስለዚህ አሁን ለምን -1 እንደፃፍኩ የገባችሁ ይመስለኛል : በዚ መሰረት የቆረጥነዉን list #print አናርገዉ ...

print(x[3 : 0 : -1])

ዉጤቱ : -
[4, 3, 2]

እስካሁን የሰራነዉ በ positive indexing ነዉ ይሁንና በ negative indexing መስራትም ይቻላል : : 👇

print(x[-2 : -5 : -1])

:> -2 የፃፍኩት 4 በ negative indexing -2 ላይ ስለምትገኝ ነዉ

:> -5 የፃፍኩት 1 በ negative indexing -5 ላይ ስከምትገኝ ነዉ

:> መጨረሻ ላይ -1 ያልኩት (ቅድም ተናገርኩ አልደግመዉም 😊)
ተጨማሪ

x = [1, 2, 3, 4]
print(x[::])

ከላይ የምታዩት code ዉጤቱ ምን ይመስላችኋል ❓

እስከዛሬ ስለመቁረጥ ስናይ መጀነሪያ ላይ የምንፅፈዉ መቁረጥ የምንጀምርበትን የ list አባል index ነበር : ከላይ ባለዉ code ላይ ግን ምንም አልተፃፈም ይህማለት ከመጀመሪያ ጀምሮ ቁረጥ እንደማለት ነዉ : :

እስከዛሬ ስናይ ሁለተኛዉ ላይ የምንፅፍ የበበረዉ መቁረጥ የምናበቃበትን index ነበር : :
ከላይ ባለዉ code ላይ ግን ምንም አልፃፍንም ይህ ማለት እስከመጨረሻዉ ቁረጥ ማለት ነዉ : :

3 'ተኛ ላይም የምንፅፈዉ ቁጥር ደሞ በምንቆርጥበት ጊዜ በምን ያህል መጠን እየጨመርን እንሂድ የሚለዉን እና የምንቆርጥበትን አቅጣጫ የምንወስንበትን ቁጥር የምንፅፍበት ቦታ ነዉ : : በሱ ቦታ ምንም አልፃፍንም ማለት 1 ብለን እንደፃፈን ይቆጠራል : :

በዚህም መሰረት ከላይ የተፃፈዉ code ዉጤት👇

[1, 2, 3, 4]

ምሳሌ : -

x = [5, 4, 3, 2, 1]
print(x[ : : -1])

👆ዉጤቱን ፃፋ👇

መፍትሄ : -
መጀመሪያ ላይ ምንም አልተፃፈም ስለዚ መቁረጥ የምንጀምረዉ ከ መጀመሪያዉ ነዉ (ማለትም ከ 5)

ሁለተኛዉ ላይም ምንም አልተፃፈም ስለዚ የምንቆርጠዉ እስከ 1(1'ን ጨምሮ) ነዉ

ሦስተኛ ላይ የተፃፈዉ -1 ነዉ ይህም ማለት የምንቆርጠዉ ከ ቀኝ ወደ ግራ ነዉ ማለት ነዉ

በዚመልኩ ከሰራን የሚመጣዉ ዉጤት 👇

[1, 2, 3, 4, 5]
ምሳሌዎች

1⃣
y = [1, 2, 3, 4, 5, 6, 7, 8, 9, 10]
print(y[ : : 2])

ዉጤቱ 👇
[1, 3, 5, 7, 9]

2⃣
x = [1, 2, 3, 4]
print(x[2])

👆ዉጤቱ👇
3

3⃣
x = ['a', 'b', 1, 2]
print(x[2: 100])

👆ዉጤቱ👇
[1, 2]

x = ["code", "tech"]
print(x[2:5])

👆ዉጤቱ👇
[]

4⃣

x = [1, 2, 3, 4, 5, 6]
print(x[ : :-2])

👆ዉጤቱ👇
[6, 4, 2]



በምናስተምረዉ ላይ ምንኛዉም ጥያቄ ካላችሁ በ👇
@h_programmers_group

ወይም

@h_grambot

...ላይ መጠየቅ ትችላላችሁ : :



✍ @h_programming
🌐 ማጠቅለያ

🔘 list ከ python mutable data type 'ኦች አንዱ ሲሆን በውስጡ ሌሎች data type 'እችን በ coma( ,) እየለያየን ማስቀመጥ እንችላለን : : እንዲሁም list በ square bracket( [ ] ) የተከበበ ነዉ : :

🔘 list ዉስጥ የሚገኙ element 'ኦችን access ለማረግ index እንጠቀማለን : : indexማለት list ውስጥ ለሚገኙ element 'ኦች የምንሰጣቸዉ መለያ ቁጥር ነዉ : : ሁለት አይነት የ indexing አይነቶች እንዳሉ አይተናል እነሱም : -

☑️ positive indexing: በ positive indexing ሁልጊዜም መጀመሪያ ላይ የሚገኘዉ element index'ኡ 0 ነዉ : : ከዛም ቀጣዩ 1 ነዉ : እንደዚ እያለ እስከመጨረሻዉ ይቀጥላል : :

☑️ negative indexing
በ negative indexing የምንጀምረዉ ከመጨረሻዉ ነዉ : : መጨረሻ ላይ ለሚገኘዉ element -1 እንሰጥና -2, -3 እያልን እስከ መጀመሪያው እንቀጥላለን : :

🔘 index 'ን በመጠቀም የ list 'ኡን element በ ሌላ element መቀየር እእእ... ሌላ ደሞ ወደ ቀኝ ወይም ወደ ግራ መቁረጥ እና እየዘለሉ መቁረጥ ይቻላል : :

ስለ list በትንሹ ይሄን ይመስላል : : ወደፊት ተጨማሪ ነገሮችን እናያለን !

በቀጣይ #tuple ስለሚባል የ ፓይተን data type እናያለን : : ከዛ በፊት ግን ስለ list እንደገባችሁ የ 👍 ምልክቷን በመንካት አሳዩን : : ካልገባችሁ ደሞ የ 👎..

👨‍💻 CodeTech

@h_programming
1) string
2) integer
3) float
4) list

5⃣ Tuple

#tuple 'ም አንዱ የ python data type ሲሆን. ሌሎች data type 'ኦችን በዉስጡ ሊይዝ የሚችል ነዉ : : #tuple በ ቅንፍ ምልክት የተከበበ ነዉ : :

(1, 2, 3)

🔺 ለምሳሌ ከላይ የምታዩት #tuple የሚባለዉን የ python data type ነዉ : :

በብዛት #tuple ከ #list ጋር ተመሳሳይነት አለዉ : :

🔆 የሚመሳሰሉበት : -

☑️ list ዉስጥ የሚገኙ አባላትኦች index የሚቢል መለያ ቁጥር እንዳላቸዉ ሁሉ #tuple ዉስጥ የሚገኙ አባላትችም በተነሳሳይ መልኩ የየራሳቸዉ index አላቸዉ : :

ለምሳሌ : -

x = (1, 2, 3, 4)

👆👇

1 index 0 ላይ ትገኛለች
2 >> 1 >> >>
3 >> 2 >> >>
4 >> 3 >> >>

ወይም በ negative index

4 index -1 ላይ ትገኛለች
3 >> -2 >> >>
2 >> -3 >> >>
1 >> -4 >> >>

☑️ ልክ list ላይ ስናረግ እንደነበረዉ positive index ወይም negative index በመጠቀም ከ አንድ tuple ላይ አባላቶችን ቆርጠን ማዉጣት እንችላለን : :

🔆 የሚያለያያቸዉ : -

▶️ የ python data type 'ኦች በ ሁለት ይከፈላሉ. mutable እና immutable ተብለዉ : :

▶️ immutable data types :> የምንላቸዉ አንዴ ከፈጠርናቸዉ በኋላ ማሻሻል የማንችላቸዉ ናቸዉ እነሱም: > string, integer, float, tuple, set...

▶️ mutable data type :> የምንላቸዉ ደሞ አንዴ ከፈጠርናቸዉ በኋላ ማሻሻል የምንችላቸዉ የ data አይነቶች ናቸዉ : : እነሱም :> list, dictionary...

▶️ ታዲያ list እና tuple የሚለያዩበት መሰረታዉ ነገር list mutable የ data አይነት ሲሆን tuple ደሞ immutable የ data አይነት ነዉ : :

በምሳሌ እንየዉ...

x = (1, 1, 3)

ለምሳሌ ከዚበፊት list ላይ ስናረግ እንደነበረዉ ከላይ የምታዪት tuple ዉስጥ የምትገኘዉን 1 ቁጥር በ 2 ቁጥር ለመቀየር ብንሞክር አይቻልም ምክንያቱም tuple ከላይ እንዳልነዉ immutable data type ነዉ : : አንዴ ከተፈጠረ በኋላ ማሻሻል አይቻልም •

• ይህ ትልቁ የ list እና የ tuple ልዩነት ነዉ •
1) string
2) integer
3) float
4) list
5) tuple

6⃣ dictionary

{"key-1": "value-1", "key-2 : "value-2",....,"key-n" : "value-n"}

#dictionary ከላይ የምታዪት አይነት ቅርፅ ያለዉ የ python data type ነዉ : :

ከላይ እንደምታዩት የ key-value ጥንዶች ስብስብ ነዉ : : አንድ key-value ጥንድ ለመስራት key'ዉን እንፅፋለን በመቀጠል #colon ( : ) ወይም ሁለት ነጥብ እናረጋለን ከዛም ቀደም ብለን በፃፍነዉ key የሚወከለዉን value እንፅፋለን : : እንደዚ እያረግን ብዙ key-value ጥንዶች በ dictionary ዉስጥ ማስቀመጥ እንችላለን ሆኖም ጥንዶቹ በ #comma ( , ) የተለያዩ መሆን አለባቸዉ : : እንዲሁም dictionary በ curly bracket ( { } ) የተከበበ ነዉ : :

❇️ ምሳሌ:>
x = {"name" : "Jhon", "ID" : 2}
👆👇
"name" እና "ID" --> #key ናቸዉ : :
"Jhon" እና 2 --> #value ናቸዉ : :

🔘 #value ማንኛዉም የ python data type መሆን ይችላል : :

🔘 #key ግን ሁልጊዜም immutable data type መሆን አለበት : : እንደምታስታዉሱት immutable data type የምንላቸዉ : - integer, float, እና string ናቸዉ : :

❇️ ምሳሌ :>

v = {[1] : 1, [2] : 2, [3]: 3} ---> ❌

👆👇

#value ማንኛውም ነገር ሊሆን ይችላል : : ነገር ግን #key immutable data type መሆን አለበት : : በሌላ አማረኛ mutable data type 'ኦችን ለምሳሌ list'ን እንደ #key መጠቀም አይችልም : : ከላይ ባለዉ list ግን list'ን እንደ #key ተጠቅሟል ስለዚህም #Error ይፈጠርበታል ማለት ነዉ : :

❇️ ምሳሌ :>
x = {"channel" : "codeTech", "group" : "programmers group", "bot" : "Hgrambot"}

ለምሳሌ ከላይ የምታዩት dictionary ነዉ : : በዉስጡ 3 key-value ጥንዶችን ይዟል : : "channel", "group", እና "bot" key 'ዎች ሲሆኑ "codeTech", "programmers group", እና Hgrambot" ደሞ value 'ዎች ናቸዉ : : እያንዳንዱ key የተጣመረዉን value የሚገልፅ ነዉ : :


x = {}

ከላይ የምታዩትም dictionary ነዉ ግን በዉስጡ ምንም key-value pair የለዉም : : እንደዚ አይነቱን dictionary ባዶ dictionary ወይም #empty dictionary እንለዋለን : :
ሰላም ዉድ የ CodeTech ቤተሰቦች 🤞

ሰሞኑን በተፈጠረዉ የ internet መቋረጥ ምክንያት ረዘም ላለ ጊዜ ትምርትችን ሳንሰጥ ቆይተናል : : ይሄንንም ታሳቢ በማድረግ ከላይ በዛ ያሉ ትምርቶችን ለቀናል : : እናንተም በትኩረት እንደምታነቧቸዉ እና ያልገባችሁን እንደምትጠይቁ ተስፋ እናደርጋለን : :

መልካም ንባብ !!!
ከኛ ጋር ናችሁ ? እንቀጥል ?

(ከሆናችሁ የ like ምልክቷን ጠቅ 😉)
እንዴት አርገን አንዴ የተፈጠረ dictionary ዉስጥ key-value pair እንጨምራለን ?

x = {}

ለምሳሌ ከላይ የምታዩት dictionary ዉስጥ ይህን 👉 "name":"sara"👈 key-value pair መጨመር ብፈልግ..

x["name"] = "sara"

አረጋለሁ ማለት ነዉ : :

በዚ መሰረት "name":"key" የሚባል key-value pair ወደ dictionary'ዉ አስገባን ማለት ነዉ : : መግባቱን ለማረጋገጥ #print አርገን ማየት እንችላለን : -

print(x)

ዉጤት : -
{"name":"sara"}

🌐 ባጠቃላይ key-value pair ለመጨመር መጀመሪያ የ dictionary 'ዉን ስም እንፅፋለን (ልክ እኔ x'ን እንደፃፍኩት) ከዛም square bracket ( [ ) እንከፍታለን ከዛም #key እንፅፋለን በመቀጠልም square bracket( ] ) እንዘጋለን በመቀጠል assignment operator ( = ) እናስገባና #value እንፅፋለን : :


@h_programming
CODE TECH™ (channel)
እንዴት አርገን አንዴ የተፈጠረ dictionary ዉስጥ key-value pair እንጨምራለን ? x = {} ለምሳሌ ከላይ የምታዩት dictionary ዉስጥ ይህን 👉 "name":"sara"👈 key-value pair መጨመር ብፈልግ.. x["name"] = "sara" አረጋለሁ ማለት ነዉ : : በዚ መሰረት "name":"key" የሚባል key-value pair ወደ dictionary'ዉ አስገባን ማለት ነዉ…
የቀጠለ...

የ list'ን ወይም የ tuple'ን element 'ኦች access ለማረግ index እንጠቀም ነበር ይህ ግን በ dictionary አይሰራም : : በ dictionary #key 'ን እንደ index ተጠቅመን #value 'ን access እናረጋለን እንጂ index አንጠቀምም!

💡በነገራችን ላይ: በ አንድ dictionary ዉስጥ ሁለት ተመሳሳይ #key ዎች ሊኖሩን አይችልም : :

🔆 አንድ dictionary ላይ የሚገኙ #key 'ዎች የያዙትን #value በሌላ value መቀየር..

x = {"name" : "Johnson", "age" : 17}

ለምሳሌ ከላይ ያለዉ dictionary ላይ "age" የምትባለዉ #key የያዘቺዉን #value ማለትም 17 'ን ለምሳሌ በ 18 መቀየር ብፈልግ እንደዚ👇 አረጋለሁ

x["age"] = 18

በዚመሰረት ቀየርኩት ማለት ነዉ

🌐 ከላይ እንዳረኩት መጀመሪያ የ dictionary ዉን ስም እንፅፋለን ከዛም square bracket ( [ ] ) #key እንፅፋለን ከዛም assignment operator ( = ) ካረግን በኋላ #value እንፅፋለን : :


🏡 የቤት ስራ 😊
Dictionary #mutable የ data አይነት ነዉ ? ወይስ #immutable የ data አይነት ?

ከላይ የተማርነዉ ይሄን ጥያቄ የሚመልስ ይመስለኛል 😉



@h_programming