CODE TECH™ (channel)
227 subscribers
42 photos
1 video
8 files
21 links
“Any fool can write code that a computer can understand. Good programmers write code that humans can understand.” – Martin Fowler

Channel ➻ @h_programming
Group ➻ @h_programmers_group
Bot ➻ @h_gramBot
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#winners

1) iboy (@iBoyd)
2) <(') ᴘʀ0xʏ ᴘɪʀ4ᴛᴇ<(')™💀⚓ (@Piratemendax777)
3) Mr~
4) <>: (@s8cr8t)
5) M.AMANUEL (@invisibliticalGhost)
6) @Mu1Se
World of Tech

በዚ ቻናል ላይ ስለ : -

💢 HTML
💢Javascript
💢 Python
💢 Hacking

ቀለል ባለና ግልፅ በሆነ መንገድ መማር ትችላላቹ : :

እባካቹ ተቀላቀሉ..

👇👇
https://t.me/reprograms
CODE TECH™ (channel) pinned «#winners 1) iboy (@iBoyd) 2) <(') ᴘʀ0xʏ ᴘɪʀ4ᴛᴇ<(')™💀⚓ (@Piratemendax777) 3) Mr~ 4) <>: (@s8cr8t) 5) M.AMANUEL (@invisibliticalGhost) 6) @Mu1Se»
🔔 የቻናላችንን link ለ ወዳጆቻችሁ share አርጉ : :
ቻናሉን አብረን እናሳድገው...

👇👇
╭─••─═•📱••••••••═─•📱•─╮
➙ @h_programming
➙ @h_programming
╰─••─═•📱••••••••═─•📱•─╯
✨ እስኪ logo እንቀይር..

ከታች ካለዉ logo የወደዳቹትን ምረጡ : :

በብዙ ሰዎች የተመረጠዉ የ channel 'አችን logo ይሆናል : :
A
B
C
Vote here 👇
Final Results
29%
A
33%
B
38%
C
እሺ ሰዎች ምርጫዉ ተጠናቋል : :

😋 በብዙ ሰዎች የተመረጠዉ logo.
🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊🎊

Logo C

ስለመረጣቹ እናመሰግናለን 🙏
ሰላም ዉድ የCodeTech ቤተሰቦች ዛሬ ባለፈዉ የሰጠኋችሁን challenge እንሰራለን : :

Challenge - 1

#ከታች እንደምታዩት input function 'ን በመጠቀም ከ ተጠቃሚዉ radius እንዲያስገባ እናረጋለን : : assignment operator ( = ) 'ን በመጠቀም ተጠቃሚዉ የሚያስገባዉን ቁጥር 'radius' በሚባል identifier ወይም variable የ እንወክላለን : : 👇

radius = input("Enter radius: ")

# የተቀበልነዉን radius #eval function 'ን በመጠቀም ወደ ቁጥር እንቀይራለን : : ከዛም radius በሚባል identifier እንወክለዋለን : : 👇

radius = eval(radius)

#ከ ተጠቃሚ የተቀበልነዉን radius በመጠቀም area እናሰላለን : : መልሱንም 'area' በሚባል identifier እንወክለዋለን : : 👇

area = 3.14 * radius * radius

#ከ ተጠቃሚ የተቀበልነዉን radius በመጠቀም circumference እናሰላለን : : መልሱንም circumference በሚባል identifier እንወክለዋለን : : 👇

circumference = 2 * 3.14 * radius

#በመቀጠልም #print function 'ን ተጠቅመን : አስልተን ያገኘነዉን area console 'ላይ print እናረጋለን : : 👇

print("Area of the circle is " + str(area))

#በተመሳሳይ የመጣልንን circumference #print function 'ን በመጠቀም console ላይ እንዲታይ እናረጋለን : : 👇

print("Circumference of the circle is " + str(circumference))

#Done

radius = input("Enter radius: ")

radius = eval(radius)

area = 3.14 * radius * radius

print("Area of the circle is " + str(area))

circumference = 2 * 3.14 * radius

print("Circumference of the circle is " + str(circumference)
)


በቀጣይ challenge - 2 እንዴት እንደሚሰራ እናያለን : :



@h_programming




#challenge_1
Algorithm

ባለፈዉ እንዳየነዉ Python 'ን ተጠቅመን የተለያዩ problem 'ኦችን solve ማረግ እንችላለን : : ሁልጊዜም ቢሆን አንድን problem ለመስራት መጀመሪያ ማረግ ያለብን #algorithm መንደፍ / መፃፍ ነዉ : : Algorithm መንደፍ ማለት የተሰጠንን problem እንዴት አርገን መስራት እንደምንችል በቅደም ተከተል ማስቀመጥ ማለት ነዉ : :

ለምሳሌ በቀደም የሰጠኋችሁን challenge_1 ለመስራት የምትፅፋት algorithm ይሄን ሊመስል ይችላል 👇

1) ከተጠቃሚ radius መቀበል
2) የተቀበልነዉን radius ተጠቅመን area መፈለግ : : area ለመፈለግ ይህን formula መጠቀም radius * radius * 3.14
3) ዉጤቱን ማሳወቅ

ስለዚህ እንደዚ አርገን algorithm እንፅፋለን : : በመቀጠል የፃፍነዉን algorithm በቀላሉ ወደ code መቀየር እንችላለን : :

ከዚ በኋላ በዚ channel ላይም ሆነ ሌላ ቦታ problem ሲያጋጥማችሁ በቀጥታ code ወደመፃፍ ከመግባት ይልቅ problem 'ኡን እንዴት መስራት እንደምንችል በማሰብ የሚመጡልንን ሀሳቦች በቅደም ተከተል መፃፍ ዉጤታማ እንድንሆን ትልቅ ድጋፍ ያረግልናል : :

Algorithm መፃፍ ማለት የጥያቄዉን 50% መስራት ማለት ነዉ ::

Algorithm በ natural ቋንቋ ማለትም በ ሰዉ ቋንቋ ወይም በ pseudocode ሊፃፍ ይችላል : :

Note: pseudocode ማለት የ natural language እና programming code ቅልቅል ማለት ነዉ : :





@h_programming
CODE TECH™ (channel) pinned «World of Tech በዚ ቻናል ላይ ስለ : - 💢 HTML 💢Javascript 💢 Python 💢 Hacking ቀለል ባለና ግልፅ በሆነ መንገድ መማር ትችላላቹ : : እባካቹ ተቀላቀሉ.. 👇👇 https://t.me/reprograms»
Variables & Literals

#Variable ማለት identifier ማለት ነዉ : : #Literal ማለት ደሞ አንድ variable ላይ የሚወከለዉ ነገር ማለት ነዉ : :

x = 2

⚜ ለምሳሌ ከላይ ባለዉ ምሳሌ ላይ 'x' variable ስትሆን '2' ደሞ literal ነች : :

🔺 በ python ሁልጊዜም ቢሆን variable በግራ በኩል የሚቀመጥ ሲሆን literal ደሞ በቀኝ በኩል መቀመጥ አለበት : : 👇

x = 3 ✅
3
= x ❌

🔺 አንዴ አንድን literal በሆነ variable ከወከልን በኋላ variable 'ኡን በመጠቀም የተለያዩ ነገሮችን ማረግ እንችላለን : :

⚜ ምሳሌ : -

x = 1

ከላይ ባለዉ ምሳሌ ላይ እንደምታዩት '1' ቁጥር በ 'x' ተወክላለች : : ስለዚህ '1' ቁጥርን print ማረግ ብንፈልግ x 'ን ተጠቅመን print ማረግ እንችላለን : : ልክ እንደዚ 👇

print(x)

✨ ሌሎችንም ነገሮች የ literal 'ኡ የተወከለበትን variable በመጠቀም ማከናወን ይቻላል : :

⚜ለምሳሌ : -

y = x + 1

እንደምታዉቁት 'x' የወከለችዉ '1' ቁጥርን ነዉ : : ስለዚህ x + 1 የሚመጣዉ '2' ነዉ : : ስለዚህ 'y' ማለት '2' ነዉ ማለት ነዉ : :

🌐 ባጠቃላይ variable በየትኛዉም ቦታ የ literal 'ኡን ቦታ በመተካት ማገልገል ይችላል : :

🔅 ሁሉንም የ python data type ( የ ዳታ አይነቶች ) እንደ literal መጠቀም ማለትም በፈለግነዉ variable መወከል እንችላለን : :

ከነዚህ የ python data types መካከል 3 'ቱን (string, integer, እና float) 'ን አይተናል : : በቀጣይ ከነሱ በተጨማሪ ያሉ የ python የ data አይነቶችን ለማየት እንሞክራለን : :

#ሰናይ_ቀን




@h_programming
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Data types in python

በ python variable ላይ ልንወክላቸዉ የሚችሉ ወይም literal መሆን የሚችሉ የ data አይነቶች የሚከተሉት ናቸዉ : :

ከዚ በፊት 3 'ቱን(string, integer እና float) 'ን ስላየን 4 ብዬ እጀምራለሁ : :

4⃣ List

List ማለት የተለያዩ የ data አይነቶችን በዉስጡ የያዘ የ data type ስብስብ ነዉ : :

✔️ List ዉስጥ ያሉ እያንዳንዱ data type 'ኦች በ comma (,) የተለዩ ናቸዉ : :

✔️ እንዲሁም list በ square bracket ( [ ] ) የተዘጋ ነዉ : :

⚜ ምሳሌ : -

[1, "codeTech", 1.0]

🔺 ለምሳሌ ከላይ የምትመለከቱት list የሚባለዉን data type ነዉ : : እንደምትመለከቱት በዉስጡ 3 ነገርችን ይዟል እነሱም integer(1), string("codeTech"), እና float(1.0) : : እነዚህም element 'ኦች በ comma( , ) ተለይተዋል : :

🔘 Empty list: empty list ማለት በ ዉስጡ ምንም የሌለዉ ሊስት ማለት ነዉ : : ልክ እንደዚ 👇

[]

🔘 list 'ኦችን ወደ አንድ list መቀየር

በ python 3 ሁለት ወይም ከዛ በላይ የሆኑ list 'ኦችን ወደ አንድ list ለመቀየር የ መደመር ምልክትን ( + ) እንጠቀማለን : :

⚜ ምሳሌ : -

["code"]
["tech"]

🔺 ለምሳሌ ከላይ የምታዩአቸዉን ሁለት list 'ኦች ወደ አንድ list ለመቀየር : -

["code"] + ["tech"]

...እናረጋለን, ዉጤቱም እንደዚ 👇 ይሆናል

["code", "tech"]

🔘 አንድን list የተደጋገመ ለማረግ

ይህን ለማረግ የ ማባዛት ምልክት ( * ) 'ን እንጠቀማለን : :

["code", "tech"]

🔺ለምሳሌ ከላይ ያለዉ list ሁለቴ እንዲደጋገም ብፈልግ በ 2 አባዛዋለሁ : : ልክ እንደዚ 👇

["code", "tech"] * 2

በዉጤቱም ይህን 👇 አገኛለሁ...

["code", "tech", "code", "tech"]

🌐 ባጠቃላይ እንዲደጋገም በፈለግነዉ ቁጥር ልክ እያባዛን የተደጋገመ list መስራት እንችላለን : :

ስለ list ይቀጥላል....


@h_programming
CODE TECH™ (channel)
Data types in python በ python variable ላይ ልንወክላቸዉ የሚችሉ ወይም literal መሆን የሚችሉ የ data አይነቶች የሚከተሉት ናቸዉ : : ከዚ በፊት 3 'ቱን(string, integer እና float) 'ን ስላየን 4 ብዬ እጀምራለሁ : : 4⃣ List List ማለት የተለያዩ የ data አይነቶችን በዉስጡ የያዘ የ data type ስብስብ ነዉ : : ✔️ List ዉስጥ ያሉ…
....የቀጠለ

☑️ አንድ list ዉስጥ የሚገኙ element 'ኦች የየራሳቸዉ መለያ ቁጥር አላቸዉ : : ይህንንም መለያ ቁጥር "index" እንለዋለን : :

☑️ የመጀመሪያዉ list ዉስጥ የሚገኝ element index 'ኡ '0' ሲሆን 2 'ተኛዉ ላይ የሚገኘዉ element ደሞ index 'ኡ '1' ነዉ : : 3, 4 ... እያለ ይቀጥላል : :

"ጠጅ በብርሌ : ነገር በምሳሌ" እንዲሉ አበዉ እስኪ በምሳሌ ለማየት እንሞክር ...

⚜ ምሳሌ : -

[0, 1, 2, "codeTech"]

🔺 ለምሳሌ ከላይ በምታዩት list ዉስጥ index 0 ላይ የሚገኘዉ element 0 ነዉ : index 1 ላይ የሚገኘዉ ደሞ 1 ነዉ : index 2 ላይ የሚገኘዉ ደሞ 2 ነዉ : የመጨረሻዉና index 3 ላይ የሚገኘዉ ደሞ "codeTech" ነዉ : :

☑️ index 'ን በመጠቀም የተለያዩ ነገሮችን ማረግ እንችላለን ለምሳሌ: -

✔️ አንዴ የፈጠርነዉን list አባላቶቹን መቀየር
✔️ ከ አንድ list ዉስጥ element 'ኦችን ቆርጦ ለማዉጣት : :

...e.t.c

ለዛሬ ከላይ የጠቀስናቸዉን ለማየት እንሞክር : :

1⃣ አንዴ የተፈጠረን list አባላቶች መቀየር

በምሳሌ እንየዉ...👇

x = [1, 3, 3, 4, 5]

🔺 ከላይ የምታዩት list 'x' በሚባል variable ተወክሏል : : ለምሳሌ በ list 'ኡ ዉስጥ index 1 ላይ የሚገኘዉን element ማለትም 3 'ትን በ 2 መቀየር ብንፈልግ እንዚ 👇 እናረጋለን

x[1] = 2

እንደምታዩት መጀመሪያ list 'ኡ የተወከለበትን variable እንፅፋለን( እኔ የሰራሁት list የተወከለዉ በ 'x' ስለሆነ x ብዬ ፅፌአለሁ)

:> በመቀጠል square bracket እንከፈታለን ( [ )

:> ከዛ በመቀጠል መቀየር የፈለግነዉን የ list element የሚገኝበትን index እንፅፋለን (እኔ መቀየር የፈለኩት element index 1 ላይ የሚገኘዉን ማለትም 3'ን ስለሆነ 1 ብዬ ፅፌአለሁ )

:> በመቀጠል የከፈትነዉን square bracket እንዘጋዋለን ( ] )

በዚ መሰረት index 1 ላይ ያለዉን element ቀየርኩት : : የተቀየረዉም list ይሄን ይመስላል 👇

[1, 2, 3, 4, 5]

2⃣ ከ አንድ list ዉስጥ element 'ኦችን ቆርጦ ለማዉጣት...

ይህንንም በ ምሳሌ እንየዉ 👇

x = [1, 2, 3, 4, 5]

ለምሳሌ ከዚህ list ዉስጥ ከ 2 እስከ 5 ( 5'ን ሳያካትት) ቆርጠን ለማዉጣት ብንፈልግ እንደዚ እናረጋለን 👇

x[1: 4]

:> እንደምታዩት መጀመሪያ list 'ኡ የተወከለበትን variable እንፅፋለን( እኔ የሰራሁት list የተወከለዉ በ 'x' ስለሆነ x ብዬ ፅፌአለሁ)

:> በመቀጠል square bracket እንከፈታለን ( [ )

:> ከየት ጀምሮ ነዉ መቁረጥ የምንፈልገዉ ? index 'ኡን እንፅፋለን: : (እኔ መቁረጥ የፈለኩት ከ 2 ጀምሮ ስለሆነ 2 የምትገኝበትን index ማለትም 1'ን ፅፌአለሁ)

:> በመቀጠል ሁለት ነጥብ እናረጋለን( : )

:> እስከየት ነዉ መቁረጥ የፈለግነዉ ? index እንፅፋለን (እኔ መቁረጥ የፈለኩት እስከ 5 ስለሆነ 5 የምትገኝበትን index ማለትም 4'ን ፅፌአለሁ)

:> በመቀጠል የከፈትነዉን square bracket እንዘጋለን ( ] )


ጥያቄ ካላቹ ግሩፕ ላይ ጠይቁን!


@h_programming

(I typed this fast in my 5.5 inch mobile, if any mistakes I am sorry)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM