CODE TECH™ (channel)
227 subscribers
42 photos
1 video
8 files
21 links
“Any fool can write code that a computer can understand. Good programmers write code that humans can understand.” – Martin Fowler

Channel ➻ @h_programming
Group ➻ @h_programmers_group
Bot ➻ @h_gramBot
Download Telegram
Escape sequence for special characters
---------------------------------------

🤗 ሰላም programmers
ዛሬ በ string ዉስጥ የተለየ ትርጉም ስላላቸዉ አንዳንድ character 'ኦች እናያለን : : ትኩተት!

በቀደም ያየነዉ back slash ወይም በሌላ ስሙ escape sequence character ከ special character 'ኦች (n, t, f, r) በፊት ሲመጣ በ string ዉስጥ የተለየ ትርጉም ይኖረዋል : : ለለምሳሌ አዲስ መስመር ለማስጀመር ሊሆን ይችላል, የ አራት space ክፍተት እንዲኖር ለማድረግ ወይም cursor 'ኡን ወደ መጀመሪያዉ ቦታ ለመመለስ,...,etc.

1⃣ New Line (\n) - ይህን አዲስ መስመር ለማስጀመር እንጠቀምበታለን : :

⚜ ምሳሌ : -

print("Code\nTech")

ከላይ ባለዉ string ዉስጥ ያለችዉ የ \n ምልክት ምክንያት "Tech" የሚለዉ የ string 'ኡ አካል በ አዲስ መስመር print ይደረጋል : :

እንደዚ 👇

Code
Tech


2⃣ tab (\t) - ይህን ደሞ አራት space ለማስገባት እንጠቀምበታለን : :

⚜ ምሳሌ :-

print("Code\tTech")

Result:
Code Tech

3⃣ Formfeed (\f) - ይህን ደሞ አዲስ መስመር ላይ የላይኛዉ string እስከሚያልቅበት ድረስ ገባ ብሎ ለመፃፍ እንጠቀምበታለን : :

⚜ ምሳሌ : -

print("Code\fTech")

Result:
Code
Tech


4⃣ Carriage return (\r) - ይህ ደሞ cursors 'ኡን ወደነጀመሪያዉ መስመር ለመመለስ እንጠቀምበታለን : :

⚜ ምሳሌ : -

print("Tech Tech\rCode")

Result:
Code Tech

Note: ከላይ ያየናቸዉን escape sequence character 'ኦች print ማረግ ብንፈልግ ባለፈዉ እንዳየነዉ ከነሱ በፊት ሌላ back slash ማስገባት አለብን : :

⚜ ምሳሌ : -

print("new line \\n")
print("tab \\t")
print("formfeed \\f")
print("carriage return \\r")


Result:

new line \n
tab \t
formfeed \f
carriage return \r




📣 @h_programming
❓ @h_programmers_group
📩 @h_grambot
identifiers
------------------

በ python identifiers የምንላቸዉ ማንኛዉንም የ data type ለመወከል (assign ለማረግ) የሚጠቅሙ የ letter, የ number እና የ underscore (_) ስብስቦች ናቸዉ : :

አንድን identifier ለ ሆነ data type ለመወከል assignment operator ( = ) 'ን እንጠቀማለን : :

⚜ ምሳሌ : -
x = 5
st = "code tech"

.
.
ከላይ ባለዉ ምሳሌ ላይ የምታዩአቸዉ x እና st identifier ናቸዉ : : ይህ 👉 = ምልክ ደሞ assignment operators ይባላል : :

Identifier 'ኦች የግዴታ ሊያሟሏቸዉ የሚገቡ ነገሮች

🔻 ከታች ያሉት ነገሮች የግዴታ መከተል አለብን ያን ካላረግን syntax error ስለሚሆን የ code 'አችንን ዉጤት ማየት አንችልም : :

🛑 Identifier 'ኦች በ letter ወይም በ underscore መጀመር አለባቸዉ : : (ቁጥር መጀመሪያ መምጣት የለበትም)

_sum, sum, sum1......

🛑 በ key word ወይም reserved word 'ኦችን እንደ identifier መጠቀም አንችልም : :
Note: key word የምንላቸዉ የ python የሆኑ ቃላት ናቸዉ : : ለምሳሌ: try, except, in, is, import, for, if, elif, else, not, True, False......( ከታች በ photo እለቅላቹዋለሁ )

else = 5 ❌
True = 6 ❌

🛑 An identifier can be of any length.

🛑 Python case sensitive በመሆኑ የተነሳ ለምሳሌ area, Area, እና AREA ሶስት የተለያዩ identifier ናቸዉ : :

Identifier ስንፅፍ የሚመከሩ ነገሮች

🔻 ከታች ያሉት ነገሮች ግዴታ ባይሆኑም code 'አችንን የሚያነቡ ሰዎች በቀላሉ አንብበዉ እንዲረዱት ስለሚያግዝ ብንተገብረዉ አሪፍ ነዉ : :

🟠 የሚወከለዉን ነገር የሚገልፅ ቃል (descriptive word) ብንጠቀም ለምሳሌ area, length, sum, result....

🟠 መጠቀም የፈለግነዉ Identifier ከ አንድ በላይ ቃል ካለዉ በ ቃላቶቹ መሀል underscore (_) ምስገባት ወይም አንዱ ቃል አልቆ ሌላኛዉ ሲጀምር አዲስ የጀመረዉን ቃል የመጀመሪያ ፊደል capital letter ማረግ : :

ልክ እንደዚ 👇

number_of_data = 15
OR
numberOfData = 15

❓ ጥያቄ

ከሚከተሉት ዉስጥ identifier መሆን የሚችሉትን እና የማይችሉትን ለዩ !

ሀ/ 1st_num
ለ/ first num
ሐ/ num1
መ/ _1num
ሠ/ *num_1
ረ/ import

© credit: iboy (code tech member)

#share_and_support_us


📣 @h_programming
❓ @h_programmers_group
📩 @h_grambot
👆እነዚህ የ python key word ናቸዉ : : እነዛህን እንደ identifier መጠቀም አይችልም 🚫 : :
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Using Python to Perform Mathematical Computations

Python 'ን የተለያዩ የሂሳብሰ ስራዎችን ለመስራት መጠቀም እንችላለን : : ለምሳሌ: ለመደመር, ለመቀነስ, ለማባዛት, ለማካፈል, ቀሪ ለማግኘት,....., e.t.c.

ይህን ለማድረግ የምንጠቀማቸዉ operators የሚከተሉት ናቸዉ : :

1) Addition ( + )
በ maths ትምርት እንደምናዉቀዉ ይሄን operator ተጠቅመን ሁለት ቁጥሮችን መደመር እንችላለን : :

Sample code:

print(11 + 10)

Result:
21

ሌላዉ የዚ operator ጥቅም; ሁለት string 'ኦችን concatinate (ወደ አንድ ማምጣት) ነዉ : :

Sample code:

print("Code" + "Tech")

Result:
CodeTech

2) Subtraction ( - )

ሁለት ቁጥሮችን ለማቀናነስ የሚጠቅም operator ነዉ : :

Sample code:
print(22 - 1)

Result:
21

⚠️ ይህን operator ለ string መጠቀም አይቻልም!

3) Multiplication ( * )

ሁለት ቁጥሮችን ለማባዛት ይህን operator እንጠቀማለን : :

Sample code:
print(3 * 7)

Result:
21

⚠️ ይህም operator ለ string አያገለግልም : :

3 ) Float division ( / )

ይህ ደሞ ሁለት ቁጥሮችን ለማካፈል እንጠቀምበታለን : :

በዚ operators ቁጥሮችን ስናካፍል መልሱ የሚመጣዉ በ float type (በ ነጥብ) ነዉ : :

Sample code:
print(10 / 2)
print(5 / 2)

Result:
5.0
2.5

4) integer division ( // )

ይህም ቁጥርችን ለማካፈል ነዉ የምንጠቀምበት operator ሲሆን ከ ላይኛዉ የሚለየዉ ይሄ መልሱን የሚያመጣዉ በ int type (ያለ ነጥብ) ነዉ : :

Sample Code:
print(10 // 2)
print(5 // 2)

Result:
5
2

5) Exponentiation ( ** )

ይህ ደሞ የሆነ ቁጥር the power of የ ሆነ ቁጥር ለማድረግ ይጠቅማል : :

Sample code:
print(3 ** 2) #3 the power of 2

Result:
9

3) Remainder operator ( % )

ቀሪን ለማግኘት የምንጠቀምበት operator ነዉ : :

Sample code:
print(5 % 2)

Result:
1


📣 @h_programming
❓ @h_programmers_group
📩 @h_grambot

😉 key 🔑

📣 = channel
❓= ጥያቄ
📩 = ሀሳብ/አስተያየት
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
What will be the result of the following code?

print(2 + 6 / 2 - 1 // 9 * 2 ** 3 % 4)

⚠️ Please do this by yourself. Don't use any IDE ❗️
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🥇 @Esyael
🥈 @danie_ye21

The reward : -
👏👏👏👏👏👏
input function
-------------------------

🤗 ሰላም ዉድ የ code tech ቤተሰቦች, ዛሬ አንዳንድ ቀለል ያሉ function 'ኦችን እናያለን : : ትኩረት!

1) input() function

input() function 'ን ተጠቅመን ከ console ላይ የፈለግነዉን ነገር መዉሰድ እንችላለን : : ወይም በሌላ አገላለፅ ከ user ( ከ ተጠቃሚ ) የፈለግነዉን ነገር መቀበል እንችላለን : :

input function አንድ argument ይቀበላል : :

input ካልን በኋላ ቅንፍ እንከፍታለን ከዛ ተጠቃሚዉ ስለሚያስገዉ ነገር 'ሚያብራራ string እንፅፋለን ከዛም ቅንፋን እንዘጋዋለን : :

⚜ ምሳሌ : -
name = input("what is your name? ")
print("hey " + name + " how are you?")


ለምሳሌ ከላይ ያለዉ code ከ ተጠቃሚዉ ስም ይጠይቃል : : ለምሳሌ ተጠቃሚዉ henok ብሎ ቢያስገባ; hey henok, how are you? ብሎ ይመልሳል ማለት ነዉ : :

ልክ እንደዚ 👇

what is your name? henok
hey henok, how are you?



Next 🔜 int() function
int() function

❓int ምንድን ነው 🤔
በመጀመሪያ int ማለት integer ማለት ነው : :

ለምሳሌ : -
12 int ነው
-1int ነው
0 int ነዉ
0.0, 1.2, 12.8 እነዚ ግን int አይደለም ምክንያቱይ መሀል ላይ ነጥብ አለ : እነዚ ነጥብ ያለባቸዉ ቁጥሮች float ተብለዉ ይጠራሉ : :

ስለዚህ ነጥብ ያለው ቁጥር integer አይደለም : : ባጭሩ integer ማለት ነጥብ የሌለዉ ማንኛዉም ቁጥር ማለት ነው : :

❓ ስለዚህ int የሚባለውን function ለምን እንጠቀመዋለን

🔺 int() function 'ን ተጠቅመን #float ቁጥርን ወደ integer ወይም string 'ን ወደ integer መቀየር እንችላለን : :

⚜ ምሳሌ-1
float = 12.5

👆ይህ float ቁጥር ነዉ

👇 ወደ int ለመቀየር

int(float)

እንለዋለን ከዛ ከነጥቡ በስተ ቀኝ ያሉትን ያጠፍቸው እና ወደ int ይቀይረዋል

ስለዚህ

ስለዚህ 12 ይመጣል

ወደ integer ከተቀየረ በኋላ screen ላይ እንዲይ ለማረግ : -

print(int(float))

⚜ ምሳሌ-2
float_str = '12.3'

ከላይ እንዳለዉ አይነት string ሆኖ ነገር ግን ቁጥር የያዘ ከሆነ int() function 'ን ተጠቅመን ወደ integer መቀየር እንችላለን : :

ለመቀየር : -

int(float_str)

ወደ integer ከተቀየረ በኋላ screen ላይ እንዲይ ለማረግ : -

print(int(num))

Result:
12

⚜ ምሳሌ-3

int_str = '123'
ከላይ ያለዉ string ቢሆንም ነገር ግን በዉስጡ ቁጥር ብቻ ስለያዘ int() function 'ን መጠቀም እንችላለን : :

ለመቀየር : -

int(tech)

ወደ integer ከተቀየረ በኋላ screen ላይ እንዲይ ለማረግ : -

print(int(num))

Result:
123

©credit: iboy (CodeTech member)
float() function

🔺 ይህን function ተጠቅመን

☑️ integer 'ን ለምሳሌ (1, 5, 0, -2...)

☑️ string ሆኖ በዉስጡ integer ቁጥር የያዘ ለምሳሌ ( "1", "5", "-2",......)

☑️ string ሆኖ በዉስጡ float ቁጥር የያዘ ለምሳሌ ("0.0", "1.2", "-1.0",......)

..ወደ float ቁጥር መቀየር እንችላለን : :

Sample code - 1:
#integer 'ን ወደ float

x = float(1)
print(x)

result:
1.0

Sample code - 2:
#int_string 'ን ወደ float

x = float("1")
print(x)

result:
1.0

Sample code - 3:
#float_string 'ን ወደ float

x = float("1.0")
print(x)

result:
1.0
str()

🔺 ይህን function ተጠቅመን float ቁጥሮችን ወይም integer ቁጥሮችን ወደ string መቀየር እንችላለን : :

💡 የበለጠ ግልፅ እንዲሆን ከታች ያሉትን ምሳሌዎች ተመልከቱ !

Same code - 1:

x = str(1)
print(x)


Result:
"1"

Sample code - 2:

x = str(0.0)

Result:
"0.0"
eval()

ይህን function የሚቀበለዉ string ብቻ ሲሆን የሰጠነዉን string evaluate ከረገ ወይም ካሰላ በኋላ ወደ ቁጥር ይቀይራል : :

⚜ ምሳሌ_1 : -

x = eval("2 + 1.0")
print(x)

Result:
3.0

⚜ ምሳሌ_2 :-

x = eval("2 + 3")
print(x)

Result:
5

ሌኛዉ የ eval() function ጠቀሜታ አንድን #int_string ወደ #integer መቀየር ነዉ : :

⚜ ምሳሌ_3 : -

x = eval("21")
print(x)

Result:
21

📝Note: #int_string ማለት string ሆኖ ነገር ግን በዉስጡ integer ቁጥርን ብቻ የያዘ ማለት ነዉ : : ለምሳሌ: "1", "-5", "0",.....

በተጨማሪም eval function 'ን ተጠቅመን #float_string 'ን ወደ #float መቀየር እንችላለን : :

⚜ምሳሌ_4 : -

x = print("2.1")
print(x)

Result:
2.1

📝Note: #float_string ማለት string ሆኖ ነገር ግን በዉስጡ flaot ቁጥርን ብቻ የያዘ ማለት ነዉ : : ለምሳሌ: "2.0", "1.1", -2.6",......



ወይም አንድን #float_string ወደ float ለመቀየር እንእንጠቀምበታለን : :

ለምሳሌ:


Sample code - 2:
x = eval("2")
print(x)

Result:
2



🔥"Knowledge is power"🔥


#Stay@home
@h_programming
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሺ ሰዎች አስከዛሬ ያስተማርኳችሁን ተጠቀማችሁ የምትሰሯት ሁለት ቀለል ያሉ #challenge 'ኦች ይዜላቹ መጥቻለዉ : : ትኩረት!

Challenge_1: ከተጠቃሚ radius ተቀብሎ area እና circumference አስልቶ ለተጠቃሚዉ የሚያሳዉቅ python code ፃፉ : :

Challenge_2: ከ ተጠቃሚ width እና length ተቀብሎ area እና perimeter አስልቶ ለተጠቃሚዉ የሚያሳዉቅ python code ፃፋ : :


በትክክል ለሚመልሱ ሰዎች እንደተለመደዉ ስጦታ ተዘጋጅቷል : :

መልካም እድል!
ብዙዎቻቹ መልስ እየላካቹልኝ አደለም : : 😔

እሺ ፍንጭ ልስጣቹ....

ይሄን challenge ለመስራት የምትጠቀሟቸዉ function 'እች : :

#input() - ከ ተጠቃሚ radius, length, እና width ለመቀበል : :

#eval() - የተቀበላቹትን ወደ ቁጥር ለመቀየር : :

#print() - የሚመጣዉን መልስ console ላይ እንዲታይ ለማረግ : :

Challenge 'ኦቹን ለመስራት የምትጠቀሟቸዉ formula

3.14 * radius * radius (የ circle 'ኡን area ለማግኘት)

2 * 3.14 * radius (የ circle 'ኡን circumference ለማግኘት)

length * width (የ rectangle area ለማግኘት )

2 * (length + width) (perimeter ለማግኘት)

....እነዚን ፍንጮች ተጠቅማቹ መስራት እንደምችሉ ተስፋ አረጋለዉ : :

#እባካቹ_ቢያንስ_ሞክሩ

መልሳችሁን 👉 @h_grambot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM