CODE TECH™ (channel)
227 subscribers
42 photos
1 video
8 files
21 links
“Any fool can write code that a computer can understand. Good programmers write code that humans can understand.” – Martin Fowler

Channel ➻ @h_programming
Group ➻ @h_programmers_group
Bot ➻ @h_gramBot
Download Telegram
Getting started with python
----------------------------------------------

🤗 ሰላም ሰዎች ዛሬ ባለፈዉ በሰጠናችሁ tools ማለትም በ IDLE ወይም በ Pydroid ተጠቅመን ቀለል ያሉ code 'ኦችን መፃፍ እንጀምራለን : : ትኩረት!

ባብዛኛዉ አዲስ programming language በምንጀምርበት ጊዜ የመጀመሪያ ስራችን የሚሆነዉ hello word የሚለዉን string #console ላይ ወይም screen ላይ እንዲታይ ማረግ ነዉ : : ሁሉም programming language 'ኦች ይህን ለማድረግ የተለያየ መንገድ አላቸዉ : : በ python 3 ይህን ለማድረግ የምንፅፈዉ code የሚከተለዉን ይመስላል 👇

print("hello word")
ㅤㅤወይም
print('hello word')

ሌላ ምሳሌ: welcome to python የሚለዉን string console ላይ እንዳታይ ለማረግ : -
print("welcome to python")
ㅤㅤㅤወይም
print('welcome to python')

ባጠቃላይ የምንፈልገዉን ነገር ስክሪን ላይ ለማዉጣት ከላይ ያየናትን #print() function እንጠቀማለን : ስክሪን ላይ እንዲታይ የምንፈልገዉን ነገር በቅንፎቹ መሀል መፃፍ ይኖርብናል : : ይህ በቅንፎቹ መሀል የሚፃፈዉ ነገር #argument ወይም #parameter የሚባል ሲሆን የ ቅንፍ ምልክትቹ ደሞ #parenthesis የማለት እንጠራቸዋለን : :

💪 Challenge :

የሚከተሉትን string 'ኦች screen ላይ እንዲታዩ አርጉ : :

1) code tech
2) python's syntax is very easy.
3) He said, "I love coding."
4) He said, "python's syntax is very easy."

መልሶቻችሁን በ @h_grambot 🤖 በኩል ወይም @h_programmers_group 👥 ላይ መላክ ትችላላችሁ : :

😋 ቀድመዉ በትክክል ለሚመልሱ 3 ሰዎች ልዩ ሽልማት 🎁 ተዘጋጅቷል!

#stay_home
#stay_safe

✍ @h_programming
🔥 Boooooooooom 🔥
It's Over!
🥇🥇🥇🥇🥇

The winner is:
@KinGNaH

👏👏 for his effort

ሰላም ሰዎች ዛሬ ባለፈዉ በሰጠኋችሁ ጥያቄ ላይ እንነጋገራለን : :

💡 Correction
--------------------------

1⃣ print("code tech")

OR

print('code tech')

2⃣ print("python's syntax is very easy.")

OR

print('python\'s syntax is very easy.')

3⃣ print('he said, "I love coding."')

OR

print("he said, \"I love coding.\"")

4⃣ print("he said, \"python's syntax is very easy.\"")

OR

print('he said, "python\'s syntax is very easy."')

OR

print("he said, \"python\'s syntax is very easy.\"")

OR

print('he said, \"python\'s syntax is very easy.\"')


🔺 በቀደም የሰጠኋችሁ ጥያቄ መልስ ይሄን ይመስላል : : አብዛኞቻችሁ አንደኛዉን በትክክል ሰርታችኋል ምክንያቱም በዉስጡ ምንም quotation mark አልያዘም ስለዚህ በቀላሉ double quote ( " " ) ወይም single quote ( ' ' ) ተጠቅማችሁ በቀላሉ መስራት ትችላላችሁ : : አብዛኞቻችሁ የቀሩትንም (2, 3, 4) አንደኛዉን በሰራችሁበት መንገድ ለመስራት እየሞከራችሁ እንደነበር እገምታለሁ በዛም ምክንያት syntax error እንዳጋጠማችሁ.....

🔺 በ python የተለያዩ አይነት data types (የ data አይነቶች) አሉ : : ለምሳሌ : - integer, float, string, list, tuple,...,etc. አብዛኞቹን ወደፊት የምናያቸዉ ቢሆንም ለዛሬ ግን ከ ጥያቄያችን ጋር ስለሚያያዝ ስለ #string እንነጋገር : :

🔺 በ python-3 ማንኛዉም በ single quote (' ') ወይም በ double quote(" ") መካከል ያለ ነገር #string ይባላል : :

ለምሳሌ:- "this is a string", 'this is a string'

🔺 ስለዚህ single quote እና double quote የተፃፈዉ ነገር string መሆኑን ለማመልከት እንጠቀማቸዋለን : : ከ ሁለቱ አንዱ እንደፍላጎታችን መጠቀም እንችላለን ነገር ግን አንዳንዴ አንዱን ብቻ መጠቀም የሚኖርብን ሁኔታ ሊኖር ይችላል : : በ string 'ኡ ላይ single quote ካለ መጠቀም የምንችለዉ double quote 'ን ብቻ ይሆናል : : በ string ዉስጥ double quote ካለ ደሞ መጠቀም የምንችለዉ single quote 'ን ብቻ ይሆናል : :

⚜ ምሳሌ-1: -
That's is my code.

🔺 ከላይ ባለዉ string ዉስጥ single quote ስላለ የምንጠቀነዉ double quote 'ን ነዉ : : Like 👇

"That's is my code."

⚜ምሳሌ-2:
He said, "I love coding."

🔺 ከላይ ባለዉ string ላይ ደሞ double quote ስላለ መጠቀም የምንችለዉ single quote 'ን ነዉ : : Like 👇

'He said, "I love coding."'

🤔 ነገር ግን ሁለቱም ማለትም single quote 'ም double quote 'ም string ዉስጥ ካሉስ ❓

🔺 ሁለቱም ካሉ ደም ከነሱ በፊት back slash ( \ ) በማስገባት interpreter 'አችን እንዳያነባቸዉ ማለትም እንደሌሉ እንዲቆጠሩ ማድረግ እንችላለን : :

⚜ምሳሌ-3:
He said, "That's is my code."

🔺 እንደምታዩት ከላይ ባለዉ string ዉስጥ single quote 'ም double quote 'ም አሉ ስለዚህም ከላይ ያለዉን መንገድ እንጠቀማለን : :

"He said, \"That\'s my code.\""

OR

'He said, \"That\'s my code.\"'


✍ @h_programming
❓@h_programmers_group
📩 @h_grambot
Another challenge :

print the following texts on the console.

1⃣ \ this is back slash.
2⃣ \n this is new line.
3⃣ \t this is tab.
4⃣ \\\n code tech.

☣️☣️☣️☣️☣️☣️☣️☣️☣️

እንደተለመደዉ መልሳችሁን በ @h_grambot ወይም @h_programmers_group ላይ ላኩ!
💡 Correction 👆
-----------------------------
1⃣ print("\\")
2⃣ print("\\n")
3⃣ print("\\t")
4⃣ print("\\\\\\n")

ከዚ በፊት እንዳየነዉ single quote እና double quote በ string መሀል ሲመጡ ከነሱ በፊት back slash (\) እናስገባለን : :

🤔 ነገር ግን እራሱ back slash print ማድረግ ብንፈልግስ ❓

ይህን ማድረግ ብንፈልግ ደሞ print እንዲደረግ ከምንፈልገዉ back slash ( \ ) በፊት ሌላ back slash ማስገባት ይኖርብናል : :

⚜ ምሳሌ : -
\ this is back slash

👆ይሄን print ለማድረግ👇

print("\\this is back slash")

ብዙ ከሆኑስ❓

ብዙ ቢሆኑ ለምሳሌ 3 back slash ያለበትን string print ለማረግ ከ እያንዳንዱ back slash በፊት ሌላ back slash በማስገባት ያለ error print ማድረግ እንችላለን : :

⚜ምሳሌ: -
\\\ code tech

👆👇

print("\\\\\\ code tech")
👍1
🎲 Get ready for the quiz 'Code tech Quiz 3'

ይህ quiz የተዘጋጀዉ በ ቻናላችን በየጊዜዉ የምንለቃቸዉን ትምህርቶች subscriber 'ኦች ምን ያህል እንደገባቸዉ እና ምን ያህል እየተከታተሉን እንደሆነ ለማረጋገጥ ነዉ : :

ፈተናዉን ከመውሰዳችሁ በፊት እስከዛሬ የተማርነዉን ክለሳ ብታረጉ ጥሩ ይመስለኛል : :

11 ጥዬቄዎች ተዘጋጅተዋል ለእያንዳንዱ ጥያቄ አንድ አንድ ደቂቃ አላችሁ : :

መልካም እድል !

🖊 11 questions
⏱ 1 minute per question

ዝግጁ ስትሆኑ ይህን👇 በተን ተጫኑት ወደፈተናዉ ይወስዳችኋል : :
Escape sequence for special characters
---------------------------------------

🤗 ሰላም programmers
ዛሬ በ string ዉስጥ የተለየ ትርጉም ስላላቸዉ አንዳንድ character 'ኦች እናያለን : : ትኩተት!

በቀደም ያየነዉ back slash ወይም በሌላ ስሙ escape sequence character ከ special character 'ኦች (n, t, f, r) በፊት ሲመጣ በ string ዉስጥ የተለየ ትርጉም ይኖረዋል : : ለለምሳሌ አዲስ መስመር ለማስጀመር ሊሆን ይችላል, የ አራት space ክፍተት እንዲኖር ለማድረግ ወይም cursor 'ኡን ወደ መጀመሪያዉ ቦታ ለመመለስ,...,etc.

1⃣ New Line (\n) - ይህን አዲስ መስመር ለማስጀመር እንጠቀምበታለን : :

⚜ ምሳሌ : -

print("Code\nTech")

ከላይ ባለዉ string ዉስጥ ያለችዉ የ \n ምልክት ምክንያት "Tech" የሚለዉ የ string 'ኡ አካል በ አዲስ መስመር print ይደረጋል : :

እንደዚ 👇

Code
Tech


2⃣ tab (\t) - ይህን ደሞ አራት space ለማስገባት እንጠቀምበታለን : :

⚜ ምሳሌ :-

print("Code\tTech")

Result:
Code Tech

3⃣ Formfeed (\f) - ይህን ደሞ አዲስ መስመር ላይ የላይኛዉ string እስከሚያልቅበት ድረስ ገባ ብሎ ለመፃፍ እንጠቀምበታለን : :

⚜ ምሳሌ : -

print("Code\fTech")

Result:
Code
Tech


4⃣ Carriage return (\r) - ይህ ደሞ cursors 'ኡን ወደነጀመሪያዉ መስመር ለመመለስ እንጠቀምበታለን : :

⚜ ምሳሌ : -

print("Tech Tech\rCode")

Result:
Code Tech

Note: ከላይ ያየናቸዉን escape sequence character 'ኦች print ማረግ ብንፈልግ ባለፈዉ እንዳየነዉ ከነሱ በፊት ሌላ back slash ማስገባት አለብን : :

⚜ ምሳሌ : -

print("new line \\n")
print("tab \\t")
print("formfeed \\f")
print("carriage return \\r")


Result:

new line \n
tab \t
formfeed \f
carriage return \r




📣 @h_programming
❓ @h_programmers_group
📩 @h_grambot
identifiers
------------------

በ python identifiers የምንላቸዉ ማንኛዉንም የ data type ለመወከል (assign ለማረግ) የሚጠቅሙ የ letter, የ number እና የ underscore (_) ስብስቦች ናቸዉ : :

አንድን identifier ለ ሆነ data type ለመወከል assignment operator ( = ) 'ን እንጠቀማለን : :

⚜ ምሳሌ : -
x = 5
st = "code tech"

.
.
ከላይ ባለዉ ምሳሌ ላይ የምታዩአቸዉ x እና st identifier ናቸዉ : : ይህ 👉 = ምልክ ደሞ assignment operators ይባላል : :

Identifier 'ኦች የግዴታ ሊያሟሏቸዉ የሚገቡ ነገሮች

🔻 ከታች ያሉት ነገሮች የግዴታ መከተል አለብን ያን ካላረግን syntax error ስለሚሆን የ code 'አችንን ዉጤት ማየት አንችልም : :

🛑 Identifier 'ኦች በ letter ወይም በ underscore መጀመር አለባቸዉ : : (ቁጥር መጀመሪያ መምጣት የለበትም)

_sum, sum, sum1......

🛑 በ key word ወይም reserved word 'ኦችን እንደ identifier መጠቀም አንችልም : :
Note: key word የምንላቸዉ የ python የሆኑ ቃላት ናቸዉ : : ለምሳሌ: try, except, in, is, import, for, if, elif, else, not, True, False......( ከታች በ photo እለቅላቹዋለሁ )

else = 5 ❌
True = 6 ❌

🛑 An identifier can be of any length.

🛑 Python case sensitive በመሆኑ የተነሳ ለምሳሌ area, Area, እና AREA ሶስት የተለያዩ identifier ናቸዉ : :

Identifier ስንፅፍ የሚመከሩ ነገሮች

🔻 ከታች ያሉት ነገሮች ግዴታ ባይሆኑም code 'አችንን የሚያነቡ ሰዎች በቀላሉ አንብበዉ እንዲረዱት ስለሚያግዝ ብንተገብረዉ አሪፍ ነዉ : :

🟠 የሚወከለዉን ነገር የሚገልፅ ቃል (descriptive word) ብንጠቀም ለምሳሌ area, length, sum, result....

🟠 መጠቀም የፈለግነዉ Identifier ከ አንድ በላይ ቃል ካለዉ በ ቃላቶቹ መሀል underscore (_) ምስገባት ወይም አንዱ ቃል አልቆ ሌላኛዉ ሲጀምር አዲስ የጀመረዉን ቃል የመጀመሪያ ፊደል capital letter ማረግ : :

ልክ እንደዚ 👇

number_of_data = 15
OR
numberOfData = 15

❓ ጥያቄ

ከሚከተሉት ዉስጥ identifier መሆን የሚችሉትን እና የማይችሉትን ለዩ !

ሀ/ 1st_num
ለ/ first num
ሐ/ num1
መ/ _1num
ሠ/ *num_1
ረ/ import

© credit: iboy (code tech member)

#share_and_support_us


📣 @h_programming
❓ @h_programmers_group
📩 @h_grambot
👆እነዚህ የ python key word ናቸዉ : : እነዛህን እንደ identifier መጠቀም አይችልም 🚫 : :
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Using Python to Perform Mathematical Computations

Python 'ን የተለያዩ የሂሳብሰ ስራዎችን ለመስራት መጠቀም እንችላለን : : ለምሳሌ: ለመደመር, ለመቀነስ, ለማባዛት, ለማካፈል, ቀሪ ለማግኘት,....., e.t.c.

ይህን ለማድረግ የምንጠቀማቸዉ operators የሚከተሉት ናቸዉ : :

1) Addition ( + )
በ maths ትምርት እንደምናዉቀዉ ይሄን operator ተጠቅመን ሁለት ቁጥሮችን መደመር እንችላለን : :

Sample code:

print(11 + 10)

Result:
21

ሌላዉ የዚ operator ጥቅም; ሁለት string 'ኦችን concatinate (ወደ አንድ ማምጣት) ነዉ : :

Sample code:

print("Code" + "Tech")

Result:
CodeTech

2) Subtraction ( - )

ሁለት ቁጥሮችን ለማቀናነስ የሚጠቅም operator ነዉ : :

Sample code:
print(22 - 1)

Result:
21

⚠️ ይህን operator ለ string መጠቀም አይቻልም!

3) Multiplication ( * )

ሁለት ቁጥሮችን ለማባዛት ይህን operator እንጠቀማለን : :

Sample code:
print(3 * 7)

Result:
21

⚠️ ይህም operator ለ string አያገለግልም : :

3 ) Float division ( / )

ይህ ደሞ ሁለት ቁጥሮችን ለማካፈል እንጠቀምበታለን : :

በዚ operators ቁጥሮችን ስናካፍል መልሱ የሚመጣዉ በ float type (በ ነጥብ) ነዉ : :

Sample code:
print(10 / 2)
print(5 / 2)

Result:
5.0
2.5

4) integer division ( // )

ይህም ቁጥርችን ለማካፈል ነዉ የምንጠቀምበት operator ሲሆን ከ ላይኛዉ የሚለየዉ ይሄ መልሱን የሚያመጣዉ በ int type (ያለ ነጥብ) ነዉ : :

Sample Code:
print(10 // 2)
print(5 // 2)

Result:
5
2

5) Exponentiation ( ** )

ይህ ደሞ የሆነ ቁጥር the power of የ ሆነ ቁጥር ለማድረግ ይጠቅማል : :

Sample code:
print(3 ** 2) #3 the power of 2

Result:
9

3) Remainder operator ( % )

ቀሪን ለማግኘት የምንጠቀምበት operator ነዉ : :

Sample code:
print(5 % 2)

Result:
1


📣 @h_programming
❓ @h_programmers_group
📩 @h_grambot

😉 key 🔑

📣 = channel
❓= ጥያቄ
📩 = ሀሳብ/አስተያየት
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
What will be the result of the following code?

print(2 + 6 / 2 - 1 // 9 * 2 ** 3 % 4)

⚠️ Please do this by yourself. Don't use any IDE ❗️
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🥇 @Esyael
🥈 @danie_ye21

The reward : -
👏👏👏👏👏👏
input function
-------------------------

🤗 ሰላም ዉድ የ code tech ቤተሰቦች, ዛሬ አንዳንድ ቀለል ያሉ function 'ኦችን እናያለን : : ትኩረት!

1) input() function

input() function 'ን ተጠቅመን ከ console ላይ የፈለግነዉን ነገር መዉሰድ እንችላለን : : ወይም በሌላ አገላለፅ ከ user ( ከ ተጠቃሚ ) የፈለግነዉን ነገር መቀበል እንችላለን : :

input function አንድ argument ይቀበላል : :

input ካልን በኋላ ቅንፍ እንከፍታለን ከዛ ተጠቃሚዉ ስለሚያስገዉ ነገር 'ሚያብራራ string እንፅፋለን ከዛም ቅንፋን እንዘጋዋለን : :

⚜ ምሳሌ : -
name = input("what is your name? ")
print("hey " + name + " how are you?")


ለምሳሌ ከላይ ያለዉ code ከ ተጠቃሚዉ ስም ይጠይቃል : : ለምሳሌ ተጠቃሚዉ henok ብሎ ቢያስገባ; hey henok, how are you? ብሎ ይመልሳል ማለት ነዉ : :

ልክ እንደዚ 👇

what is your name? henok
hey henok, how are you?



Next 🔜 int() function
int() function

❓int ምንድን ነው 🤔
በመጀመሪያ int ማለት integer ማለት ነው : :

ለምሳሌ : -
12 int ነው
-1int ነው
0 int ነዉ
0.0, 1.2, 12.8 እነዚ ግን int አይደለም ምክንያቱይ መሀል ላይ ነጥብ አለ : እነዚ ነጥብ ያለባቸዉ ቁጥሮች float ተብለዉ ይጠራሉ : :

ስለዚህ ነጥብ ያለው ቁጥር integer አይደለም : : ባጭሩ integer ማለት ነጥብ የሌለዉ ማንኛዉም ቁጥር ማለት ነው : :

❓ ስለዚህ int የሚባለውን function ለምን እንጠቀመዋለን

🔺 int() function 'ን ተጠቅመን #float ቁጥርን ወደ integer ወይም string 'ን ወደ integer መቀየር እንችላለን : :

⚜ ምሳሌ-1
float = 12.5

👆ይህ float ቁጥር ነዉ

👇 ወደ int ለመቀየር

int(float)

እንለዋለን ከዛ ከነጥቡ በስተ ቀኝ ያሉትን ያጠፍቸው እና ወደ int ይቀይረዋል

ስለዚህ

ስለዚህ 12 ይመጣል

ወደ integer ከተቀየረ በኋላ screen ላይ እንዲይ ለማረግ : -

print(int(float))

⚜ ምሳሌ-2
float_str = '12.3'

ከላይ እንዳለዉ አይነት string ሆኖ ነገር ግን ቁጥር የያዘ ከሆነ int() function 'ን ተጠቅመን ወደ integer መቀየር እንችላለን : :

ለመቀየር : -

int(float_str)

ወደ integer ከተቀየረ በኋላ screen ላይ እንዲይ ለማረግ : -

print(int(num))

Result:
12

⚜ ምሳሌ-3

int_str = '123'
ከላይ ያለዉ string ቢሆንም ነገር ግን በዉስጡ ቁጥር ብቻ ስለያዘ int() function 'ን መጠቀም እንችላለን : :

ለመቀየር : -

int(tech)

ወደ integer ከተቀየረ በኋላ screen ላይ እንዲይ ለማረግ : -

print(int(num))

Result:
123

©credit: iboy (CodeTech member)