CODE TECH™ (channel)
227 subscribers
42 photos
1 video
8 files
21 links
“Any fool can write code that a computer can understand. Good programmers write code that humans can understand.” – Martin Fowler

Channel ➻ @h_programming
Group ➻ @h_programmers_group
Bot ➻ @h_gramBot
Download Telegram
Built in functions in python 👆
-------------------------------------------
1, Do U want to shape and guide Ur life by getting lessons of hope, comfort, courage, etc?
...........................................
2, Do U want to build up your psychological make up and shape Ur thought patterns?
...........................................
3, Do U need words of advice, encouragement, confidence and strength?
...........................................
4, Moreover, Do U want to make Ur life delicious?
____
As long as ur answer is "Yes", please join this chanal 👉"QOUTES AND PROVERBS" now!
How interesting it is!
............................................
"If I have some time to talk to my friends, I never miss time to read sayings which are everlasting advices in my life."
Link - @Cqoute_proverb
- @Gqoute_proverb
----------------------------------------------
⁣ㅤㅤ🇵 🇾 🇹 🇭 🇴 🇳
══════◄••❀••►══════

💻PROGRAMMING STYLES

የምንፅፈው #code ተቀባይነት እንዲኖረዉ የሚያስችለዉ ዋነኛዉ ነገር #በትክክል_መስራቱ ቢሆንም ነገር ግን ሌሎች programmer’ኦች ያለ code’ኡ ፀሀፊ ድጋፍ በትክክል አንብበው የሚረዱት, የሚጠቀሙት እና የሚያሻሽሉት መሆን መቻል አለበት፡፡ ይህም ሊሆን የሚችለዉ #good_programming_style ስንከተል ነዉ : :

ስለዚህ Programming Style ማለት የprogram’ኣችን #ገፅታ(አፃፃፍ) ምን እንደሚመሰል ይገልፅልናል : :

✅ በ ጥሩ የ programming አፃፃፍ ( በ Good programming style) የተፃፈን code ማንኛዉም ሰዉ በቀላሉ አንብቦ መረዳት ይችላል : :

✅ ነገር ግን በ መጥፎ የ programming አፃፃፍ ( በ Bad programming style) የተፃፈን code ሌላ ሰዉ ለማንበብ ለመረዳትና ለማስተካከል ቢሞክር ከባድ ነዉ የሚሆነዉ : :

የ ጥሩ programming አፃፃፍ ( Good programming style ) መገለጫዎች

🔆 በprogram’ኣችን ውስጥ ቁዋሚ የሆነ programming style መጠቀም : :

⚜ለምሣሌ⚜፡
#Code1 - print(“Programming Styles deal with what program looks like.”)

#Code2 - print('Programming Styles deal with what program looks like.')


ከላይ እንደሚታየዉ #Code1- ላይ 👉 Programming Styles deal with what program looks like. 👈 የሚለዉ text በ ሁለት double quote መካከል የሚገኝ ሲሆን | #Code2 ላይ ደሞ በ ሁለት single quote መካከል ይገኛል : :

ሆኖም ግን #code1 እና #code2 የ ሚሰሩት ስራ ተመሳሳይ ነዉ : : ሁለቱም 👉 Programming Styles deal with what program looks like. 👈 የሚለዉን string screen ላይ እንዲታይ ያደርጋሉ : :

ምክንያቱም በ python #double_quote(" ") እና #single_quote(' ') ተመሳሳይ አገልግሎት ያላቸዉ በመሆኑ ነዉ : : ነገር ግን ለዉጥ የለዉም ብለን ሲፈልገን በ double quote ሲፈልገን በ single quote መፃፍ ተገቢ አይደለም በ single quote ከጀመርን በዛዉ መቀጠል | በ double quote ከ ጀመርንም በ ዛዉ መቀጠል አለብን : :

🔆 code'አችን ላይ operator የምንጠቀም ከሆነ በ2ቱም የoperator side ላይ አንድ አንድ space መተው : :

⚜ለምሳሌ⚜:-
4 + 10 * 2 / 5 ✔️(good p.s)
4+10*2/5 ❌(bad p.s)

#Note: operator የምንላቸዉ (+, -, /, //, *, **.…ወደፊት በስፋት እናያቸዋለን)

🔆 በprogram’ኣችን መጀመሪያ ላይ ጠቅላላ የprogram’ኡን #ዓላማ, #key feautures እና የሚጠቀማቸው ልዩ ልዩ መንገዶች በ #comment መልክ መግለፅ (ስለ comment በቀጣይ እንመጣበታለን)

✍ @h_programming

#share #share
Comment
••••••••••••••••••••••••••

በፕሮግራሚንግ ውስጥ አንድ ዋና እና ጠቃሚ የሆነ ነገር ቢኖር ኮዳችንን ኮመንት ማድረግ ነው::

ኮመንት ማድረግ ማለት ኮዳችንን ለሚያነቡ ሰዎች ስለ ኮዳችን ቀላል ማብራርያን ወይም መረጃን የምንሰጥበት መንገድ ነው:: ይህ ኮመንት የተንዛዛ መሆንም የለበትም በቀላሉ ማስተላለፍ የፈለግነውን መልእክት በአጭሩ መግለፅ አለብን::

ኮዳችንን ኮመንት ማድረግ ጠቀሜታው ኮዳችንን ለሚያነቡ ሌሎች ሰዎች ብቻ ሳይሆን እኛም ተመልሰን ከጊዝያት ቡሀላ ኮዳችንን እንዳንረሳው እና በቀላሉ እንድናስታውስ ያግዘናል::

ማስታወሻ:-
ፕሮግራማችንን run በምናረግበት ጊዜ ኮመንት ያደረግነው ነገር excute አይደረግም ማለትም ለተጠቃሚዎች አይታይም::

ከታች በምስሉ እንደምትረዱት ኮመንት እንደተፃፈ የምታውቁት ኮዱን ከከፈታችሁ ብቻ ነው::

📌 የ ኮመንት አይነቶች

1⃣ line comment (ባለ አንድ መስመር ኮመንት)

ከአንድ መስመር ያልበለጠ ኮመንት line comment በመባል ይጠራል : :
line comment ለመፃፍ በ መሰላል ምልክት(#) እንጀምራለን ይቺ የመሰላል ምልክት pound sign (#) ትባላለች : :

⚜ ምሳሌ :
#this is line comment

2⃣ Pharagraph comment ( ባለ ብዙ መስመር ኮመንት )

ከአንድ መስመር በላይ የሚሆን ኮመንት pharagraph comment በመባል ይታወቃል : : pharagraph ኮመንት ለመፃፍ በ ሶስት #single_quote እንጀምርና comment ከፃፍን በኋላ በ ሶስት #single_quote እንዘጋዋለን : :

⚜ምሳሌ:
'''
this is paragraph comment
this is paragraph comment
'''


©CodeIT
⁣Format of different types of comment.
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
እስኪ እየተከታተላችሁን እንደሆነ like 👍 በማረግ አሳዩን !
🙌 ሰላም ሰዎች !
ዛሬ ስለ Errors in programming (በ programming ዉስጥ ሊያጋጥሙን ስለሚችሉ ስህተትች) እናወራለን : : ትኩረት !!!

Errors in Programming

Program በምንፅፍነት ጊዜ የተለያዩ አይነት Errors ( ስህተቶችን ) ልንሰራ እንችላለን : : እነዚህን ስህተቶች ካልተስተካከሉ በስተቀር የ program'ኦችንን ዉጤት ማየት አንችልም : : ስለሆነም ስህተቱ የተፈጠረበትን ቦታ ፈልጎ ማስተካከል የግድ ነዉ : :

Type of programming errors

3 አይነት የ error አይነቶች አሉ : : እነሱም : -

1) Syntax Error

የመጀመሪያዉ syntax error በመባል ይጠራል : :

🔺 በአፃፃፍ ስህተት ምክንያት ወይም የ programming አፃፃፍ ህግን ባለመከተል የሚፈጠር የ error አይነት ነዉ : : ሁሉም programming language'ኦች የየራሳቸዉ የአፃፃፎ ስርአት አላቸዉ ይህን የአፃፃፍ ስርአት ያልተከተልን እንደሆነ syntax error ይፈጠራል ማለት ነዉ : :

ለምሳሌ : -
print("code tech"

🔺 ይህን 👆 python code run ለማረግ ብንምክር አሺ አይልም ምክንያቱም በትክክል አልተፃፈም : : ይህም syntax error 'ን ያስከትላል : :

ከላይ ያለዉ code ተስተካክሎ ሲፃፍ : -
print("code tech")

🔺 ይህ የ error አይነት ቀለል ያለ እና በቀላሉ ሊስተካከል የሚችል ነዉ : :

🔺 Syntax error በሚፈጥረበት ጊዜ interpreter'አችን error 'ኡ የተፈጠረበትን ቦታ እና የተፈጠረዉን የ error አይነት እንዲሁም ለምን እንደተፈጠረ የሚገልፅ መልእክት ያሳየናል : :

በቀጣይ ስለ : -
2) Run Time Error
3) Logical Error
እናያለን : :

መልካም ቀን !

@h_programming
@h_programmers_group
👍2
Image: Syntax Error በሚፈጠርነት ጊዜ interpreter 'አችን የሚያሳየን መልእክት ይሄን ይመስላል 🔺
የቀጠለ...

2) Run Time Error

ይህ የ error አይነት የፃፍነዉን program run ካረግን ነኋላ ተጠቃሚዉ ወይም user 'ኡ በሚያስገባዉ ነገር ምክንያት ሊፈጠር የሚችል የ error አይነት ነዉ : :

⚜ ምሳሌ : -
num = float(input("enter the number: "))
print(num)

ለምሳሌ ከላይ የምታዩት code ከተጠቃሚ decimal ቁጥርን ተቀብሎ, አጠጋግቶ የሚመልስ ነዉ : : ለምሳሌ ተጠቃሚዉ 3.8 ቢያስገባ 4 'ን ይመልሳል ማለት ነዉ : : ነገር ግን ይህ code በትክክል ሊሰራ የሚችለዉ user 'ኡ ቁጥር ብቻ ሲያስገባ ነዉ ቁጥር ያሎነ ነገር ለምሳሌ A 'ን ቢያስገባ error ይፈጠራል ይህም የ error አይነት run time error ይባላል : :

🔺 ልክ እንደ syntax error ሁሉ ይህም የ error አይነት በሚፈጠርበት ጊዜ interpreter 'አችን ስህተቱ የተፈጠረበትን ቦታ, የተፈጠረበትን ምክንያት እና የ error 'ኡን አይነት የያዘ መልእክት ያሳየናል : :

🔺 run time error 'ን የምናስተካክለዉ try-except block 'ን በመጠቀም ነዉ : ማለትም ለምሳሌ ተጠቃሚዉ ቁጥር ያሎነ ነገር ሲያስገባ "እባክዎን ቁጥር ብቻ ያስገቡ! " የሚል መልዕክት ወይም የተሳሳተ ነገር እንዳስገቡ የሚገልፅ መልዕክት እንዲያሳይ በማድረግ ለማስተካከል መሞከር አስፈላጊ ነዉ : :

Next 🔜 Logical error

@h_programming
❔ጥይቄ 👉 @h_programmers_group or @h_grambot
👍2
Image: Run time error በሚፈጠርነት ጊዜ interpreter 'አችን የሚያሳየን የ error መልእክት ይሄን ይመስላል 🔺
3) Logical Error

🔺 ይህ የ error አይነት ከሌሎቹ የ error አይነቶች አንፃር ስህተቱን ለማግኘትና ለማስተካከል ትንሽ ከበድ ያለ የ error አይነት ነዉ : :
ይህም የሆነበት ምክንያት interpreter 'አችን እንደ error ስለማያየዉ ስህተቱ የተፈጠረበትን ቦታ ሊነግረን ስለማይችል ነዉ : :

🔺 Logical error ተፈጠረ የሚባለዉ የ ፃፍነዉ code የምንፈልገዉን ዉጤት ሳያመጣልን ሲቀር ወይም እንዳሰብነዉ ሳይሆን ሲቀር logical error ተፈጠረ ይባላል : :

⚜ ምሳሌ : -
ከተጠቃሚ ቁጥር ተቀብሎ ቁጥሩ prime number ከሆነ #True ካልሆነ ደሞ #False ብሎ የሚመልስ code ብንፅፍ እና ስንሞክረዉ በትክክል ባይሰራ (ለምሳሌ 121 ሰተነዉ True ብሎ ቢመልስ) logical ስህተት ሰርተናል ማለትነዉ ስለዚህም ወደ code 'አችን ተመልሰን የሰራነዉን ስህተት ፈልገን 🔍 ማስተካከል ካልሆነም ደሞ እርዳታ መጠየቅ ተገቢ ነዉ : :

#stay home,
#stay safe

📣 @h_programming
❔@h_programmers_group
📩 @h_grambot
🔆 ማሳሰቢያ: ከላይ በተለያዩ ምሳሌዎች የ ተጠቀምናቸዉ code 'ኦች የ python 3 መሆናቸዉን እንድታዉቁ እንፈልጋለን : :

ባጠቃላይ በዚ ቻናል የምንማረዉ ስለ python 3 ሲሆን እሱን ከጨረስን በኋላ ሌሎች programming language የምንጀምር ይሆናል : :

አብሮነታችሁ አይለየን! ፍላጎት ይኑራችሁ! ጠያቂ ሁኑ!
ከቤት አቱጡ!
ኢትዮ-Students.apk
4.1 MB
🎲ኢትዮ-Students የተማሪዎች መተግበሪያ

⭐️ይህ አፕ ጥቅሙ ተማሪዎች እርስ በእርሳቸው እንዲነጋገሩና እንዲወያዩ News Feed አለው እናም በየጊዜው የሚለቀቁ የትምህርት ፋይሎችን ለማዉረድም ሆነ ለመልቀቅ በጣም አመቺና ተማሪዎች በቀላሉ በስልካቸዉ ላይ በመጫን በትምህርታቸዉ ተጠቃሚ ለማድረግ የተሰራ መተግበሪያ ነዉ

👉በተለይም በዚህ አስከፊ ወረርሺኝ ጊዜ ተማሪዎች በትምህርታቸዉ እንዳይጐዱ ይህን መተግበሪያ በመጠቀም መወያየትም ሆነ ሀሳብ መለዋወጥ የሚያስችል መተግበሪያ ነዉ

❇️ እናም ተማሪዎች ይሄን መተግበሪያ በመጠቀም በቀላሉ ከትምህርታቸዉ ጋር መገናኘት እንዲችሉ ተደርጎ የተዘጋጀ መተግበሪያ ነዉ
Getting started with python
----------------------------------------------

🤗 ሰላም ሰዎች ዛሬ ባለፈዉ በሰጠናችሁ tools ማለትም በ IDLE ወይም በ Pydroid ተጠቅመን ቀለል ያሉ code 'ኦችን መፃፍ እንጀምራለን : : ትኩረት!

ባብዛኛዉ አዲስ programming language በምንጀምርበት ጊዜ የመጀመሪያ ስራችን የሚሆነዉ hello word የሚለዉን string #console ላይ ወይም screen ላይ እንዲታይ ማረግ ነዉ : : ሁሉም programming language 'ኦች ይህን ለማድረግ የተለያየ መንገድ አላቸዉ : : በ python 3 ይህን ለማድረግ የምንፅፈዉ code የሚከተለዉን ይመስላል 👇

print("hello word")
ㅤㅤወይም
print('hello word')

ሌላ ምሳሌ: welcome to python የሚለዉን string console ላይ እንዳታይ ለማረግ : -
print("welcome to python")
ㅤㅤㅤወይም
print('welcome to python')

ባጠቃላይ የምንፈልገዉን ነገር ስክሪን ላይ ለማዉጣት ከላይ ያየናትን #print() function እንጠቀማለን : ስክሪን ላይ እንዲታይ የምንፈልገዉን ነገር በቅንፎቹ መሀል መፃፍ ይኖርብናል : : ይህ በቅንፎቹ መሀል የሚፃፈዉ ነገር #argument ወይም #parameter የሚባል ሲሆን የ ቅንፍ ምልክትቹ ደሞ #parenthesis የማለት እንጠራቸዋለን : :

💪 Challenge :

የሚከተሉትን string 'ኦች screen ላይ እንዲታዩ አርጉ : :

1) code tech
2) python's syntax is very easy.
3) He said, "I love coding."
4) He said, "python's syntax is very easy."

መልሶቻችሁን በ @h_grambot 🤖 በኩል ወይም @h_programmers_group 👥 ላይ መላክ ትችላላችሁ : :

😋 ቀድመዉ በትክክል ለሚመልሱ 3 ሰዎች ልዩ ሽልማት 🎁 ተዘጋጅቷል!

#stay_home
#stay_safe

✍ @h_programming
🔥 Boooooooooom 🔥
It's Over!
🥇🥇🥇🥇🥇

The winner is:
@KinGNaH

👏👏 for his effort

ሰላም ሰዎች ዛሬ ባለፈዉ በሰጠኋችሁ ጥያቄ ላይ እንነጋገራለን : :

💡 Correction
--------------------------

1⃣ print("code tech")

OR

print('code tech')

2⃣ print("python's syntax is very easy.")

OR

print('python\'s syntax is very easy.')

3⃣ print('he said, "I love coding."')

OR

print("he said, \"I love coding.\"")

4⃣ print("he said, \"python's syntax is very easy.\"")

OR

print('he said, "python\'s syntax is very easy."')

OR

print("he said, \"python\'s syntax is very easy.\"")

OR

print('he said, \"python\'s syntax is very easy.\"')


🔺 በቀደም የሰጠኋችሁ ጥያቄ መልስ ይሄን ይመስላል : : አብዛኞቻችሁ አንደኛዉን በትክክል ሰርታችኋል ምክንያቱም በዉስጡ ምንም quotation mark አልያዘም ስለዚህ በቀላሉ double quote ( " " ) ወይም single quote ( ' ' ) ተጠቅማችሁ በቀላሉ መስራት ትችላላችሁ : : አብዛኞቻችሁ የቀሩትንም (2, 3, 4) አንደኛዉን በሰራችሁበት መንገድ ለመስራት እየሞከራችሁ እንደነበር እገምታለሁ በዛም ምክንያት syntax error እንዳጋጠማችሁ.....

🔺 በ python የተለያዩ አይነት data types (የ data አይነቶች) አሉ : : ለምሳሌ : - integer, float, string, list, tuple,...,etc. አብዛኞቹን ወደፊት የምናያቸዉ ቢሆንም ለዛሬ ግን ከ ጥያቄያችን ጋር ስለሚያያዝ ስለ #string እንነጋገር : :

🔺 በ python-3 ማንኛዉም በ single quote (' ') ወይም በ double quote(" ") መካከል ያለ ነገር #string ይባላል : :

ለምሳሌ:- "this is a string", 'this is a string'

🔺 ስለዚህ single quote እና double quote የተፃፈዉ ነገር string መሆኑን ለማመልከት እንጠቀማቸዋለን : : ከ ሁለቱ አንዱ እንደፍላጎታችን መጠቀም እንችላለን ነገር ግን አንዳንዴ አንዱን ብቻ መጠቀም የሚኖርብን ሁኔታ ሊኖር ይችላል : : በ string 'ኡ ላይ single quote ካለ መጠቀም የምንችለዉ double quote 'ን ብቻ ይሆናል : : በ string ዉስጥ double quote ካለ ደሞ መጠቀም የምንችለዉ single quote 'ን ብቻ ይሆናል : :

⚜ ምሳሌ-1: -
That's is my code.

🔺 ከላይ ባለዉ string ዉስጥ single quote ስላለ የምንጠቀነዉ double quote 'ን ነዉ : : Like 👇

"That's is my code."

⚜ምሳሌ-2:
He said, "I love coding."

🔺 ከላይ ባለዉ string ላይ ደሞ double quote ስላለ መጠቀም የምንችለዉ single quote 'ን ነዉ : : Like 👇

'He said, "I love coding."'

🤔 ነገር ግን ሁለቱም ማለትም single quote 'ም double quote 'ም string ዉስጥ ካሉስ ❓

🔺 ሁለቱም ካሉ ደም ከነሱ በፊት back slash ( \ ) በማስገባት interpreter 'አችን እንዳያነባቸዉ ማለትም እንደሌሉ እንዲቆጠሩ ማድረግ እንችላለን : :

⚜ምሳሌ-3:
He said, "That's is my code."

🔺 እንደምታዩት ከላይ ባለዉ string ዉስጥ single quote 'ም double quote 'ም አሉ ስለዚህም ከላይ ያለዉን መንገድ እንጠቀማለን : :

"He said, \"That\'s my code.\""

OR

'He said, \"That\'s my code.\"'


✍ @h_programming
❓@h_programmers_group
📩 @h_grambot
Another challenge :

print the following texts on the console.

1⃣ \ this is back slash.
2⃣ \n this is new line.
3⃣ \t this is tab.
4⃣ \\\n code tech.

☣️☣️☣️☣️☣️☣️☣️☣️☣️

እንደተለመደዉ መልሳችሁን በ @h_grambot ወይም @h_programmers_group ላይ ላኩ!
💡 Correction 👆
-----------------------------
1⃣ print("\\")
2⃣ print("\\n")
3⃣ print("\\t")
4⃣ print("\\\\\\n")

ከዚ በፊት እንዳየነዉ single quote እና double quote በ string መሀል ሲመጡ ከነሱ በፊት back slash (\) እናስገባለን : :

🤔 ነገር ግን እራሱ back slash print ማድረግ ብንፈልግስ ❓

ይህን ማድረግ ብንፈልግ ደሞ print እንዲደረግ ከምንፈልገዉ back slash ( \ ) በፊት ሌላ back slash ማስገባት ይኖርብናል : :

⚜ ምሳሌ : -
\ this is back slash

👆ይሄን print ለማድረግ👇

print("\\this is back slash")

ብዙ ከሆኑስ❓

ብዙ ቢሆኑ ለምሳሌ 3 back slash ያለበትን string print ለማረግ ከ እያንዳንዱ back slash በፊት ሌላ back slash በማስገባት ያለ error print ማድረግ እንችላለን : :

⚜ምሳሌ: -
\\\ code tech

👆👇

print("\\\\\\ code tech")
👍1