CODE TECH™ (channel)
227 subscribers
42 photos
1 video
8 files
21 links
“Any fool can write code that a computer can understand. Good programmers write code that humans can understand.” – Martin Fowler

Channel ➻ @h_programming
Group ➻ @h_programmers_group
Bot ➻ @h_gramBot
Download Telegram
The winner is:
M.AMANUEL

👏👏 for his effort
🤗ሰላም ሁላችሁም
ባለፈው በለቀቅነው poll መሰረት አብዛኞቻችሁ Absolute beginner ስለሆናችሁ ከ introduction እንጀምራለን ፀጥ ብላቹ ተከታተሉ እሽሽሽ...🤫

@h_programming
@h_programmers_group
📌ትውውቅ(Introduction)፡

ፕሮግራሚንግ(Programming) ምንድነው❓
┄┄┉┉•═════•┉┉┄┄

➠ስለ ፕሮግራሚንግ ምንነት ከማየታችን በፊት ፕሮግራም እራሱ ምን ማለት እንደሆነ ማየት ጠቃሚ ነው: :

❖ ፕሮግራም(program) - ፕሮግራም ማለት ኮምፒውተር ሊረዳቸው የሚችላቸው የተለያዩ ትእዛዞች ሰብሰብ ነው: : እነዚህን ትእዞዞች(Codes) ተጠቅመን ኮምፒውተራችን 💻 የሆነ ስራ እንዲሰራልን ማዘዝ እንችላለን: :

💡ፕሮግራሚንግ(Programming) - ወደ ፕሮግራሚንግ ስንመጣ ደሞ ፕሮግራሚንግ ማለት ፕሮግራም የመጻፍ እና ለኮምፒውተራችን የምንፈልገውን ትእዛዝ የማሳለፍ ሂደት ነው: :

➡በአሁን ሰአት እየተጠቀምንባቸው ያሉ የተለያዩ መተግበሪያዎቸ(applications) የ ፕሮግራሚንግ ውጤቶች ናቸው: :

በቀጣይ ስለ programming language እናያለን: :

ማንኛውም አይነት ሀሳብ ወይም ጥያቄ ካላችሁ በ @h_gramBot 📩 በኩል አድርሱን.....

✍ @h_programming
📌Programming language📌

Programming language ማለት ከ ኮምፒዉተር ጋር ሊያግባባን የሚችል program ለመፃፍ የሚጠቅም ቋንቋ ማለት ነው: :


👨‍💻Computer ላይ የምንጭናቸው ማንኛውም አይነት የ ዳታ አይነቶች ለምሳሌ: photo, video , software....ሌሎችም የሚቀመጡት Mechine language በሚባል 0 እና 1 ቁጥሮች በያዘ የኮምፒውተር ቋንቋ ነው: : ለምሳሌ 10 ቁጥርን ከ keyboard ⌨ ብናስገባ ኮምፒዉተራችን የሚረዳውና የሚያስቀምጠው ወደ እንደዚህ አይነት ቁጥሮች ቀይሮ ነው 👉 010001010...እነዚህ አይነት ቁጥሮች Machine language በመባል ይጠራሉ: :

Machine Language
━━━━━━━━━━━━━
Machine language ማለት computer 💻 ሊረዳው የሚችል የኮምፒውተር ቋንቋ ነው: : የሚጠቀመውም 0 እና 1'ን ብቻ ነው: : ለምሳሌ 33 በ Machine language 00100001 ነው: :

➠ ነገር ግን ለኛ ለሰዎች Machine language'ን ለማንበብና ለመረዳት ከባድም አሰልቺም በመሆኑ ምክንያት በ Machine language program መፃፍ የማይታሰብ ነው: :

➠ በዚም ምክንያት ሰዎች አንብበው ሊረዱት የሚችል program መፃፊያ ቋንቋ(programming language) ለመፍጠር ጥረት መደረግ ተጀመረ: :
ይህ ጥረትም ለ Assembly language መፈጠር ምክንያት ሆነ: :

Assembly Language
━━━━━━━━━━━━━━
✅ Assembly language ሰዎችንና computer'ን በመጠኑም ቢሆን ያቀራረበ ቋንቋ ነው: :

✅ Assembly language ከ Machine language አንፃር ለማነበብና ለመረዳት በመጠኑም ቢሆን ቀለል ያለ programming language ነው: :

✅ Assembly language የእንግሊዝኛ ፊደላትን የያዙ አጫጭር ቃላቶችን ይጠቀማል። ለምሳሌ: ADD, MUL, MOV, INC, POP, PUSH, SUB, DEC,....,e.t.c

✅ እነዚህ Assembly language ላይ ያሉ አጫጭር ቃላት(instructions) mnemonic( ሜሞኒክ) ተብለው ይጠራሉ።

✅ Assembly language እና Machine language ባንድ ላይ low-level programming language በመባል ይጠራሉ: :

✅ Assembly language ከ Machine language አንፃር ለ ሰው ልጅ ቋንቋ ቀረብ ያለ ነው አልን እንጂ እሱም ቢሆን ለ መማንበብ እና ለመረዳት ያን ያህል የቀለለ አልነበረም: :

✅ በዚህም ምክንያት እስካሁን ካየናቸው የተሻለና ለማንበብ ለመፃፍ የበለጠ የቀለለ አዲስ programming language አስፈለገ: :

High-level Programming language
━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
➻ በፈረንጆቹ ወደ 1950ዓ.ም ላይ ለ ሰውልጅ ቋንቋ እጅግ የቀረበ, እንግሊዘኛ ቋንቋ መሳይ ለማንበብ , ለመረዳት እና ለመፃፍ ቀላል የሆኑ programming language'ኦች መሰራትና ወደ ገበያ መውጣት ጀመሩ: : እነዚህ programming language'ኦች high-level programming language በመባል ይታወቃሉ: :

➻ አሁን ባለንበት ዘመን ከ 100 በላይ High-level programming language'ኦች ይገኛሉ: : ከነዚህ ውስጥ ታዋቂዎቹ:
C, C++, C#, Java, COBOL, FORTRAN, Python, PHP …ይገኙበታል: :


For any questions or suggestions use the bot @h_gramBot

Channel ➠ @h_programming
Group ➠ @h_programmers_group
🚦በቀጣይ ስለ High-level programming language እናያለን: :

🙏እስከዛው የ ቻናላችንን link ለወዳጆ ያጋሩ: :

ለማጋራት ይሄን በተን ተጠቀሙ👇
━━━━━━━━━━━━━━━━━
#Quiz_1
━━━━━━━━━━━━━━━━━
እስከዛሬ ስለ programming የለቀቅናቸው ትምህርቶች በደንብ እንደገባችሁና ከኛ ጋር እንደሆናችሁ ለማለጋገጥ ከታች ጥያቄዎች አስቀምጠናል : :

😊እንዳትኮራረጁ ሸፍናችሁ ስሩ‼️
━━━━━━━━━━━━━━━━━
1⃣ ኮምፒውተራችን የፈለግነውን ስራ እንዲሰራልን የሚያስችል የትእዛዞች ስብስብ የሆነው የቱ ነው ❓
Anonymous Poll
40%
ሀ/ Programming
4%
ለ/ Mnemonic
52%
ሐ/ Program
4%
መ/ Algorithm
👍1
2⃣ ለ computer ትእዛዞችን የመፃፍ እና የማስተላለፍ ሂደት ምን ተብሎ ይጠራል❓
Anonymous Poll
13%
ሀ/ Ordering
2%
ለ/ Typing
84%
ሐ/ Programming
2%
መ/ Writing
👍1
3⃣ ከሚከተለት ዉስጥ የ Machine language የሆነው የቱ ነው❓
Anonymous Poll
9%
ሀ/ MOV, ADD, SUB.......
75%
ለ/ 00100001
6%
ሐ/ print, input, float.....
9%
መ/ ሁሉም
4⃣ እንደ ADD, MUL, MOV, INC, POP, PUSH, SUB, DEC ያሉ mnemonic(ሜሞኒክ) የሚባሉ አጫጫር ቃላትን የሚጠቀመው የ programming language አይነት የቱ ነው❓
Anonymous Poll
15%
ሀ/ Machine language
7%
ለ/ C++
11%
ሐ/ Python
67%
መ/ Assembly language
5⃣ High - level programming language የሆነው የቱ ነው?
Anonymous Poll
9%
ሀ/ Assembly language
10%
ለ/ Machine language
78%
ሐ/ Java
4%
መ/ None of the above
6⃣ Low-level programming language የሆኑት የትኞቹ ናቸው❓
Anonymous Poll
9%
ሀ/ Python & PHP
10%
ለ/ C & C++
78%
ሐ/ Assembly and Machine language
4%
መ/ Java & JavaScript
7⃣ ለማንበብ ለመረዳትና ለመፃፍ ቀላል የሆነዉ የ programming language አይነት የቱ ነው❓
Anonymous Poll
79%
ሀ/ High - level programming language
21%
ለ/ Low - level programming language
እንዴት ነው ጥያቄዎቹን ሰርታቹ ጨረሳቹ?
እስከ ነገ ማታ ጊዜ አላችሁ ሁላችሁም እንድትሰሩ እንፈልጋለን: :

‼️❕‼️❕‼️❕‼️❕‼️
━━━━━━━━━━━━━━━━━
አንዳንድ የ telegram አፓች ላይ እንደዚ አይነት ሚሴጅ ሊያመጣ ይችላል 👉 this message is not supported.
እንደዚህ የሚሆንባችሁ plus latest version ተጠቀሙ: :

ከታች የ Plus➕ messenger latest version እለቃለሁ አውርዳቹ ተጠቀሙ: :

@h_programming

👇👇👇👇👇👇👇👇👇
org.telegram.plus_16318.apk
29.2 MB
━━━━━━━━━━━━━━━━━
Plus Messenger
━━━━━━━━━━━━━━━━━
❖Version: 5.14.0. 3 (16318)
❖Last Updated: Feb 6, 2020
❖Size: 29.23MB
ሰላም ሰዎች 👋
ዛሬ ባለፈው ለለቀቅናቸው ጥያቄዎች ትክክለኛ መልሶቻቸውን እነግራችኋለው: :

1⃣ ሐ

2⃣ ሐ

3⃣ ለ

4⃣ መ

5⃣ ሐ

6⃣ ሐ

7⃣ ሀ

አብዛኞቻቹ በትክክል ሰርታቹታል ጎበዞች 👏👏👏👏👏
⚜እስኪ የደፈናቹ ( 7/7) 🔱
══════◄••❀••►══════

እስከዛሬ በለቀቅናቸው ትምህርቶች ስለ:
✦ program
✦ programming
✦ programming language:
➢ low level and
➢ high level
በቂ እውቀት እንዳገኛቹ ተስፋ አረጋለሁ: :
ከዚ በኋላ በሚኖረን ቆይታ ከ high-level programming language'ኦች ዉስጥ አንዱ ስለሆነው ስለ PYTHON የምናይ ይሆናል: :
አብሮነታችሁ አይለየን🙏

For any contact 👉 @h_gramBot
•
•
•
══════◄••❀••►══════
🇵 🇾 🇹 🇭 🇴 🇳
━━━━━━━━━━━━
📌ትዉዉቅ ከ python ጋር..
━━━━━━━━━━━━━━━━━
Python ባለፈዉ ካየናቸዉ የ high level programming language'ኦች ዉስጥ አንዱ ሲሆን በአሁኑ ሰአት ተወዳጅነት እያገኘ የመጣ የኘሮግራሚን ቋንቋ ነዉ: :

Python'ን የተፈጠረዉ በ 1995 Guido van Rossum በተባለ ሰዉ ነበር : : ከጊዜ ወደ ዜ እያደገና እየተሻሻለ የመጣና አሁን ላ ይ በጣም ታዋቂ የሆነ high level programming language ነዉ::

ባለፈዉ ስለ high level programming language ስናይ በአለም ላይ እጅግ ብዙ high level የሆኑ languages እንዳሉ አይተናል ለማስታወስ ያህል Java, Java script C, C++, FORTRAN, PHP, Python...etc. ታዲያ ከነዚ ሁሉ programming languages Python'ን የመረጥንበት ምክንያት ለአፃፃፍ ቀላል በመሆኑ በ አሁኑ ሰአት ተፈላጊና በሁሉም ቦታዎች በ ኢንዱስትሪዎች በ ተለያዩ የሳይንስና የ ቴክኖሎጂ ተቋማት በብዛት አገልግሎት እየሰጠ ያለ በጣም አሪፍ programming language በመሆኑ ነው: : በተለይ ደሞ አብዛኞቻቹ ጀማሪዎች ስለሆናችሁ python ደሞ ለጀማሪዎ በጣም ጥሩ በመሆኑ ለናንተ ስለ python'ን ብናስተምር ዉጤታማ ታሆናላችሁ ብለን ስላሰብን ነው python'ን የመረጥንበት ምክንያት::

እስኪ እንደተስማማችሁ like 👍 በማረግ አሳዩን: :

✍ @h_programming
👋 ሰላም የተከበራቹ የ 💻 CODE TECH ቤተሰቦች : :

ዛሬ Python'ን ለመማር ስለሚያስፈልጉ ነገሮች እንነጋገራለን : : ሁላችሁም ቢሆን Python programming language የመማር ፍላጎት ዋነኛዉ ነገር ቢሆንም፤ አንዳንድ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ማሟላት ይኖርባችኋል: :

የሚያስፈልጉ ነገሮች.....
➢ ከቻላቹ computer ቢኖራችሁ በጣም አሪፍ ነዉ....
➢ ከሌላችሁ ግን ችግር የለዉም በ smart phone'አችሁ መጠቀም ትችላላችሁ : :

Python'ን ጨምሮ ሌሎችንም programming languages በcomputer ላይ ወይም በ smart phone ላይ ለመፃፍ ሁለት አይነት tools እንጠቀማለን....

✔️ Text editor
✅ Integrated development environment (IDE)


1⃣ Text editor
Text editor የምንላቸው code ለመፃፍ ብቻ የሚያገለግሉ ናቸዉ : : በ text editor የፃፍነዉን Code run ማድረግ እና የሚመጣዉን ነገር ማየት አንችልም: :

Example; sublime text, Notepad, Notepad ++, Aton,...etc.

2⃣ Integrated Development Enviroment (IDE)
የምንላቸው ደግሞ code'ኡን እየፃፍን run ማድረግ የምንችልበት ነው።

Example; net beans, Ecliplse, Pycharm, IDLE,...etc.