ባንክ ኦፍ አሜሪካ በኢትዮጵያ ከሩጫ ጋር እያሳደገ የሚገኘው አጋርነት አካል አድርጎ የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. የስያሜ አጋር ሆነ
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከባንክ ኦፍ አሜሪካ ጋር እያሳደገ የሚገኘው አጋርነት አካል ሆኖ፣ ዓመታዊው ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ውድድርም አዲስ የስያሜ ስፖንሰር (presenting sponsor) እንደሚኖረው ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡ በህዳር ወር 2018ዓ.ም. የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መታወቂያ የሆነው የ10ኪ.ሜ. የጎዳና ሩጫ የስያሜ አጋር (Presenting Partner) እንደሚሆን ያሳወቀው ባንኩ፣ የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ.ን መጨመሩ የበለጡ ሰዎችን ወደረዥም ርቀት ሩጫ ለማምጣት የያዘውን ተልዕኮ እንዲያሰፋ እና በማህበረሰቡ ዘንድ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ እንዲያጠናክር ያስችለዋል፡፡
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ሶስቱም ትልልቅ የሩጫ ሁነቶች (events) ፤ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ.፣ የልጆች ሩጫዎች እና የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ውድድሮች ላይ ባንክ ኦፍ አሜሪካ አዲሱ የስያሜ አጋር (Presenting Partner) ይሆናል።
ማህበረሰብን ያስቀደመ መርሆን መሰረት ያደረገው አጋርነት በርካታ ግቦችን ለማሳካት አቅዷል፡፡ ባንክ ኦፍ አሜሪካ በ10ኪ.ሜ. እና የልጆች ሩጫዎች ላይ ነፃ ተሳትፎዎችን በገንዘብ በመደገፍ የተሳታፊነትን ተደራሽነት የማስፋት ግብን ያግዛል፡፡ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ቀጣዩን የሯጮች ትውልድ የማበርታት ተልዕኮም ከባንኩ ልጆች እና ወጣቶች በስፖርት እንዲሳተፉ የበለጡ እድሎችን ከማቅረብ ዓለምአቀፍ ስትራቴጂ ጋር ይዛመዳል፡፡ ባንክ ኦፍ አሜሪካ በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለሚዘጋጁ ውድድሮች የሚውሉ ቴክኖሎጂዎችን ለማዘመን የሚያስችል ሀብትም ያቀርባል፤ ይህም በተራው የተሳታፊዎች ቁጥር ይበልጥ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ፣ ባንክ ኦፍ አሜሪካ የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. አዲሱ የስያሜ አጋር መሆኑን ይፋ ሲያደርጉ ‹‹ባለፉት ሀያ ዓመታት የልጃገረዶች እና ሴቶች ዓመታዊ ሩጫችንን ለማሳደግ ብዙ ወጪ ፈሰስ አድርገናል፡፡ አሁን በባንክ ኦፍ አሜሪካ የአጋርነት ድጋፍ ደግሞ የበለጡ እድሎች ይከፈቱልናል፡፡ ባንክ ኦፍ አሜሪካ ለሩጫዎቻችን እና በሩጫዎቻችን አማካይነት ልናገለግላቸው ለምንሻው ማህበረሰቦች እንዲሁም ከሴቶች እና ልጆች ጋር ላሉን ሰፊ ስራዎች አብረውን ለመስራት ላሳዩት ቁርጠኝነት ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ›› ብለዋል፡፡
በማርች 8 ከሚከበረው ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን ጋር ተያይዞ የሚዘጋጀው የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ባለፈው እሁድ 23ኛ ውድድሩን ሲያደርግ፣ ከ12ሺህ የበለጡ ተሳታፊዎችም ውድድሩን አጠናቅቀዋል፡፡ ከኢትዮጵያ የፖሊቲካ፣ ቢዝነስ እና ባህል ህይወት ብዙ ስመ-ጥር እንስቶችን እንዲሁም በኢትዮጵያ እያገለገሉ የሚገኙ በርካታ የውጪ አምባሳደሮችን የሚያሳትፈው ውድድር ተካፋዮቹ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ሴቶችን ስኬቶች ለማክበር ሲሰባሰቡ የተለየ አይነት የህብረት ስሜት እንዲሰማቸው እንደሚያደርግ ተስተውሏል፡፡
የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ሩጫ አምባሳደር እና የጥንድ የኦሊምፒክ 5000ሜ ሻምፒዮኗ መሰረት ደፋር በእሁዱ ውድድር ወቅት ስትናገር ‹‹ይህ ውድድር ሁሌም የተለየ ነው፡፡ በሁሉም የማህበረሰቡ ክፍሎች ወስጥ የሚገኙ ሴቶችን ስኬቶች ለማክበር እና ለሌሎቾ ሴቶች ስኬታማ የመሆን በራስ መተማመንን ለመስጠት አስደናቂ መድረክ ነው፡፡ ሁሌም በየዓመቱ እኛን ሴቶችን ማነሳሳት አይሳነውም›› ብላለች፡፡
ባንክ ኦፍ አሜሪካ አዲስ እና ጠለቅ ያለ የደንበኛ ግንኙነትን የመፍጠር፣ የቡድን አጋሮችን የማሳተፍ እና በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዘላቂ የኢኮኖሚ ተፅዕኖን የማገዝ እንቅስቃሴው አካል አድርጎ በስፖርት ውስጥ ካሉ እጅግ ታዋቂ ብራንዶች ጋር በአጋርነት ይሰራል፡፡
ባንክ ኦፍ አሜሪካ ዓለምአቀፋዊውን የብርታት መድረኩን በኢትዮጵያ ሁለቱም ውድድሮች - በአፍሪካ ትልቁ የጎዳና ሩጫ በሆነው የኖቬምበሩ ዓለምአቀፍ የ10ኪ.ሜ. እና የመጋቢቱ የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. - ላይ ከሚወዳደሩ የቀጣይ ትውልድ ሯጮች ጋር በማስተሳሰር ስፖርት እንዴት ዕድሎችን ሊፈጥር እንደሚችል እና ሰዎች እና ማህበረሰቦችን እንደሚያዋህድ ማሳየቱን ቀጥሏል፡፡
ባንክ ኦፍ አሜሪካ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር ካለው አጋርነት ባሻገር በሩጫ፣ እግር ኳስ እና ጎልፍ ከዓለም አቀፍ ብራንዶች እና ሁነቶች ጋር በአጋርነት ይሰራል፡፡ እነዚህም Boston Marathon presented by Bank of America፣ Bank of America Chicago Marathon እና Chicago Distance Series፣ የ2026 የፊፋ ዓለም ዋንጫ፣ የአሜሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ሁሉም 27 የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድኖች እንዲሁም በጎልፍ የማስተርስ ውድድር እና Augusta National Women’s Amateur ናቸው፡፡
ከመጋቢት 2019 (March 2027) ጀምሮ ባንክ ኦፍ አሜሪካ ከአፍሪካ ትልቆቹ የሴቶች-ብቻ ሩጫ ውድድሮች አንዱ የሆነው ውድድር የስያሜ አጋር (Presenting Partner) ይሆናል። ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከባንክ ኦፍ አሜሪካ ጋር እያሳደገ የሚገኘው አጋርነት አካል ሆኖ፣ ዓመታዊው ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ውድድርም አዲስ የስያሜ ስፖንሰር (presenting sponsor) እንደሚኖረው ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡ በህዳር ወር 2018ዓ.ም. የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መታወቂያ የሆነው የ10ኪ.ሜ. የጎዳና ሩጫ የስያሜ አጋር (Presenting Partner) እንደሚሆን ያሳወቀው ባንኩ፣ የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ.ን መጨመሩ የበለጡ ሰዎችን ወደረዥም ርቀት ሩጫ ለማምጣት የያዘውን ተልዕኮ እንዲያሰፋ እና በማህበረሰቡ ዘንድ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ እንዲያጠናክር ያስችለዋል፡፡
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የአዲስ አበባ ሶስቱም ትልልቅ የሩጫ ሁነቶች (events) ፤ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10ኪ.ሜ.፣ የልጆች ሩጫዎች እና የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ውድድሮች ላይ ባንክ ኦፍ አሜሪካ አዲሱ የስያሜ አጋር (Presenting Partner) ይሆናል።
ማህበረሰብን ያስቀደመ መርሆን መሰረት ያደረገው አጋርነት በርካታ ግቦችን ለማሳካት አቅዷል፡፡ ባንክ ኦፍ አሜሪካ በ10ኪ.ሜ. እና የልጆች ሩጫዎች ላይ ነፃ ተሳትፎዎችን በገንዘብ በመደገፍ የተሳታፊነትን ተደራሽነት የማስፋት ግብን ያግዛል፡፡ የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ቀጣዩን የሯጮች ትውልድ የማበርታት ተልዕኮም ከባንኩ ልጆች እና ወጣቶች በስፖርት እንዲሳተፉ የበለጡ እድሎችን ከማቅረብ ዓለምአቀፍ ስትራቴጂ ጋር ይዛመዳል፡፡ ባንክ ኦፍ አሜሪካ በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለሚዘጋጁ ውድድሮች የሚውሉ ቴክኖሎጂዎችን ለማዘመን የሚያስችል ሀብትም ያቀርባል፤ ይህም በተራው የተሳታፊዎች ቁጥር ይበልጥ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ፣ ባንክ ኦፍ አሜሪካ የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. አዲሱ የስያሜ አጋር መሆኑን ይፋ ሲያደርጉ ‹‹ባለፉት ሀያ ዓመታት የልጃገረዶች እና ሴቶች ዓመታዊ ሩጫችንን ለማሳደግ ብዙ ወጪ ፈሰስ አድርገናል፡፡ አሁን በባንክ ኦፍ አሜሪካ የአጋርነት ድጋፍ ደግሞ የበለጡ እድሎች ይከፈቱልናል፡፡ ባንክ ኦፍ አሜሪካ ለሩጫዎቻችን እና በሩጫዎቻችን አማካይነት ልናገለግላቸው ለምንሻው ማህበረሰቦች እንዲሁም ከሴቶች እና ልጆች ጋር ላሉን ሰፊ ስራዎች አብረውን ለመስራት ላሳዩት ቁርጠኝነት ላመሰግናቸው እፈልጋለሁ›› ብለዋል፡፡
በማርች 8 ከሚከበረው ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን ጋር ተያይዞ የሚዘጋጀው የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ባለፈው እሁድ 23ኛ ውድድሩን ሲያደርግ፣ ከ12ሺህ የበለጡ ተሳታፊዎችም ውድድሩን አጠናቅቀዋል፡፡ ከኢትዮጵያ የፖሊቲካ፣ ቢዝነስ እና ባህል ህይወት ብዙ ስመ-ጥር እንስቶችን እንዲሁም በኢትዮጵያ እያገለገሉ የሚገኙ በርካታ የውጪ አምባሳደሮችን የሚያሳትፈው ውድድር ተካፋዮቹ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ሴቶችን ስኬቶች ለማክበር ሲሰባሰቡ የተለየ አይነት የህብረት ስሜት እንዲሰማቸው እንደሚያደርግ ተስተውሏል፡፡
የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ሩጫ አምባሳደር እና የጥንድ የኦሊምፒክ 5000ሜ ሻምፒዮኗ መሰረት ደፋር በእሁዱ ውድድር ወቅት ስትናገር ‹‹ይህ ውድድር ሁሌም የተለየ ነው፡፡ በሁሉም የማህበረሰቡ ክፍሎች ወስጥ የሚገኙ ሴቶችን ስኬቶች ለማክበር እና ለሌሎቾ ሴቶች ስኬታማ የመሆን በራስ መተማመንን ለመስጠት አስደናቂ መድረክ ነው፡፡ ሁሌም በየዓመቱ እኛን ሴቶችን ማነሳሳት አይሳነውም›› ብላለች፡፡
ባንክ ኦፍ አሜሪካ አዲስ እና ጠለቅ ያለ የደንበኛ ግንኙነትን የመፍጠር፣ የቡድን አጋሮችን የማሳተፍ እና በሀገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ዘላቂ የኢኮኖሚ ተፅዕኖን የማገዝ እንቅስቃሴው አካል አድርጎ በስፖርት ውስጥ ካሉ እጅግ ታዋቂ ብራንዶች ጋር በአጋርነት ይሰራል፡፡
ባንክ ኦፍ አሜሪካ ዓለምአቀፋዊውን የብርታት መድረኩን በኢትዮጵያ ሁለቱም ውድድሮች - በአፍሪካ ትልቁ የጎዳና ሩጫ በሆነው የኖቬምበሩ ዓለምአቀፍ የ10ኪ.ሜ. እና የመጋቢቱ የቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. - ላይ ከሚወዳደሩ የቀጣይ ትውልድ ሯጮች ጋር በማስተሳሰር ስፖርት እንዴት ዕድሎችን ሊፈጥር እንደሚችል እና ሰዎች እና ማህበረሰቦችን እንደሚያዋህድ ማሳየቱን ቀጥሏል፡፡
ባንክ ኦፍ አሜሪካ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር ካለው አጋርነት ባሻገር በሩጫ፣ እግር ኳስ እና ጎልፍ ከዓለም አቀፍ ብራንዶች እና ሁነቶች ጋር በአጋርነት ይሰራል፡፡ እነዚህም Boston Marathon presented by Bank of America፣ Bank of America Chicago Marathon እና Chicago Distance Series፣ የ2026 የፊፋ ዓለም ዋንጫ፣ የአሜሪካ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና ሁሉም 27 የአሜሪካ ብሔራዊ ቡድኖች እንዲሁም በጎልፍ የማስተርስ ውድድር እና Augusta National Women’s Amateur ናቸው፡፡
❤6👏6👍2
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች የ4 ሚሊዮን ብር የገንዘብ ድጋፍ አበረከተ
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
መጋቢት 17 ቀን 2018 ዓ.ም.
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ‘ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ’ በተሰኘው የ2018 ሶፊማልት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አለምአቀፍ 10ኪ.ሜ. የበጎ አድራጎት ዘመቻው አማካኝነት ያሰባሰበውን 4 ሚሊዮን ብር በቼሻየር ኢትዮጵያ መናገሻ ቢሮ በተከናወነ ደማቅ ስነ-ስርዓት ለተመረጡ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች አስረክቧል።
በዘንድሮው የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ-ግብር ድጋፍ የተደረገላቸው ተቋማት ቼሻየር ኢትዮጵያ፣ ተስፋ ማህበራዊና ልማት ማህበር ፣ የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ማህበራት ፌደሬሽን እና እዘነት አካል ጉዳተኞች ህፃናት እና ወላጆች መርጃ ድርጅት በኢትዮጵያ ናቸው።
በርክክብ ስነ-ስርዓቱ ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ባስተላለፉት መልዕክት "ዛሬ ማዕከሉን ተገኝቼ በመጎብኘቴ በጣም ደስ ብሎኛል ፤ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከስፖርታዊ እንቅስቃሴው ባሻገር ህዝብን ከማስተሳሰር ባለፈ፣ ችግረኞችን ለመርዳት የሚያደርገው ጥረት ለሌሎችም አርአያ የሚሆን ተግባር ነው።በቀጣይም ሌሎች በርካታ ተቋማትን ማገዛችንን እንቀጥላለን" ብለዋል።
አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ በበኩሉ "ይህን 'ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ’ ዘመቻን ስንጀምር ዓላማችን ስፖርታዊ ውድድሩ ለወገኖቻችን መድረሻ እንዲሆን ነበር። ዛሬ ላይ በየአመቱ ተጠናክሮ መቀጠሉ አስደሳች ነገር ነው። ከምንሰበስበው ገንዘብ በላይ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶቹ በሚሰጠው ትኩረት ትልቅ ኩራት ይሰማኛል" ሲል ገልጿል።
በዕለቱ በግላቸው ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ላሰባሰቡና ለዘመቻው ስኬት ጉልህ አስተዋፅኦ ላበረከቱ ግለሰቦች ልዩ ዕውቅና ተሰጥቷል። ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ወደፊትም ስፖርትን ከበጎ አድራጎት ጋር በማስተሳሰር ማህበራዊ ግዴታውን መወጣቱን እንደሚቀጥልም በዚሁ ወቅት ተገልጿል።
ይህ ‘ሌሎችን ለመርዳት እሮጣለሁ’ የተሰኘው ዘመቻ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ውድድርን ከማዘጋጀት ባሻገር ማህበራዊ ኃላፊነቱን ከሚወጣባቸው መንገዶች ዋነኛው ሲሆን፤ ከተጀመረም 20 ዓመታትን አስቆጥሯል። ባለፉት ሁለት አስርተ ዓመታት ውስጥ ብቻ ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ ከተለያዩ ድርጅቶችና ግለሰቦች በማሰባሰብ ለተለያዩ ተቋማት ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል። ዘመቻው ከገንዘብ ድጋፍ ባለፈ ተቋማቱ ተከታታይ የድጋፍ ምንጭና የመገናኛ ብዙኃን ሽፋን እንዲያገኙ በማድረግ ለህጻናት፣ ለሴቶች፣ ለአካል ጉዳተኞችና ለተፈናቃዮች የላቀ ፋይዳ ያለው ስራ ሲያከናውን ቆይቷል።

👍12❤3👏2
📌 የዚህ ወር እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫችን መጋቢት 26 ይካሔዳል - ሰኞ ማለዳ በሲቢኢ ብር ፕላስ ይመዝገቡ 📌
እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ✨
መጋቢት 26 / 2018ዓ.ም.
#EntotoCBERun #GreatEthiopianRun
እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ✨
መጋቢት 26 / 2018ዓ.ም.
#EntotoCBERun #GreatEthiopianRun
❤14
📌 ምዝገባ ተጀምሯል!!! ✍️
🗓 የዚህ ወር እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫችን መጋቢት 26 ይካሔዳል - በሲቢኢ ብር ፕላስ ይመዝገቡ📱
እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ✨
መጋቢት 26 ቀን 2018ዓ.ም. እንገናኝ!
#EntotoParkCBERun #GreatEthiopianRun

❤11
ውብ ቅዳሜን ከእኛ ጋር ያሳልፉ!🌟
እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ💫🏃♀️
ነገ - ቅዳሜ - መጋቢት 26 ቀን 2018ዓ.ም. እንገናኝ!
#EntotoParkCBERun #GreatEthiopianRun
እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ💫🏃♀️
ነገ - ቅዳሜ - መጋቢት 26 ቀን 2018ዓ.ም. እንገናኝ!
#EntotoParkCBERun #GreatEthiopianRun
❤8👍2
የ2018 ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በጅማ እሁድ ሚያዝያ 18 ቀን / 2018ዓ.ም. ይካሔዳል
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከቱሪዝም ሚኒስትር ጋር በመተባበር እያከናወነው ያለው የ'ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ' የስድስት ከተሞች ውድድር ዘንድሮ በደብረ ብርሃን እና ሐዋሳ የተከናወነ ሲሆን ፤ ቀጣይ አስተናጋጅ ከተማ ጅማ - ሚያዝያ 18 ቀን 2018ዓ.ም. ውድድሩን በድምቀት ታስተናግዳለች።
በ6 ከተሞች የሚካሔደው የ2018 ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ ተከታታይ ውድድር ሶስተኛዋ መዳረሻ የሆነችው ጅማ ለ2018 ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በጅማ ዝግጅቷን በማጠናቀቅ ላይ ትገኛለች።
ይህ ውድድር ወላጆች ልጆቻቸውን በተገቢው ጊዜ ክትባት እንዲያስከትቡ የሚያበረታታውን ‘ፖሊዮን በጋራ እናጥፋ’ የውድድር መልዕክት ይዞ ቀርቧል፡፡
የ15ኪ.ሜ.፤ የ5ኪ.ሜ እና የየህፃናት ሩጫዎችን ያካተተው ይህ ውድድር ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ከ10 የተለያዩ ሀገራት የተውጣጡ ዜጎችን እንደሚያሳትፍ ይጠበቃል። በ15ኪ.ሜ. ውድድሩ ላይ ከአዲስ አበባ እና ሌሎች ከተሞች ወደ ጅማ የሚጓዙ ከ90 በላይ ተሳታፊዎች የተመዘገቡ ሲሆን ፤ በ5ኪ.ሜ. ውድድሩ ላይ ከጅማ እና አካባቢው አትሌቶች እንዲሁም ከ4000 በላይ የጤና ሯጮች ይሳተፋሉ።
ሩጫው ከሚካሔድበት ቀን ሚያዝያ 18 አስቀድሞ ባለው ቅዳሜ የሚድሮክ ሆራይዘን ፕላንቴሽን የቡና እርሻ ጉብኝት እና የ5ኪ.ሜ. የእግር ጉዞ እና ሌሎች የጉብኝት እና የመዝናኛ ዝግጅቶች ተካተውበታል።
የዘንድሮውን ውድድር ስኬታማ ለማድረግ ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በአጋርነት እየሰሩ የሚገኙት ውድድሩን እና ጅማ ከተማን ለማድመቅ የተዘጋጁት ኢትዮ ቴሌኮም፣ ቴሌብር፣ ቱሪዝም ሚኒስቴር፣ ሮተሪ ኢትዮጵያ፣ ፔፕሲ፣ ዳሽን ባንክ፣ ሚድሮክ ሆራይዘን፣ ቶፕ ውሃ፣ ኃይሌ ሆቴልና ሪዞርት እንዲሁም አፍራን ሆስፒታል ናቸው፡፡

❤15👍7
የ2018 ኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በጅማ ቡናን ከሩጫ ጋር አስተሳስሮ ተከናወነ
የ"ልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ" (Discover Ethiopia Classics) ውድድር አካል የሆነው የ2018 የኢትዮ ቴሌኮም ታላቁ ሩጫ በጅማ ዛሬ ጠዋት በጅማ ከተማ ተካሄደ።
በውድድሩ ላይ ከ4,000 በላይ የሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች እንዲሁም ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ሰዎች ተሳትፈዋል። ውድድሩን የጅማ ከተማ ከንቲባ አቶ ጣሃ ቀድር እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና ታዋቂ ግለሰቦች በክብር እንግድነት ተገኝተው አስጀምረውታል።
የዘንድሮው ውድድር "ፖሊዮን በጋራ እናጥፋ" (End Polio Now) የሚል መልዕክትን በማስተላለፍ ለጤና ግንዛቤ ትልቅ ትኩረት የሰጠ ነበር።
ከአባ ጅፋር ቤተመንግስት ተነስተው በከተማው መሃል ፈረንጅ አራዳ ፍፃሜያቸውን ባደረጉት የ15 ኪሎ ሜትር የጤና ሯጮች ውድድር በወንዶች ጃፈር ጀማል እና በሴቶች የግሌ እሸቱ አንደኛ በመውጣት አሸንፈዋል።
በአትሌቶች መካከል በተደረገው የ5 ኪሎ ሜትር ውድድር በወንዶችብሩክ ዘለቀ ፣ ኦሊፈን ዲባባ እና ማዲ ሪዳ ከአንድ እስከ ሶስት በመውጣት ሲያሸንፉ ፤ በሴቶች ዝናሽ ግዛው ቀዳሚ ስትሆን ማርሸት መላኩ እና ሊና አብዱ ተከታትለው ገብተዋል።
ዕድሜያቸው ከ16 እና ከ11 ዓመት በታች ለሆኑ ህፃናት የተዘጋጀው ውድድር በልዩ ሁኔታ የተከናወነ ሲሆን፣ የወደፊት ተተኪ እና ተስፈኛ አትሌቶች ታይተውበታል። በሁሉም የዕድሜ ክልል ላሉት ታዳጊዎችም ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ከአጋር ድርጅቶቹ ጋር በመሆን ልዩ ልዩ ሽልማቶችን አበርክቷል።
ጅማ የዘንድሮው የልወቅሽ ኢትዮጵያ ክላሲክስ የሩጫ ተከታታይ ውድድር ሶስተኛ መድረሻ ስትሆን፣ ቀጣዩ ውድድር በሯጮች መፍለቂያዋ በቦቆጂ ከተማ ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም (May 24, 2026) ይካሔዳል።

👍4❤3