Great Ethiopian Run (ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ)
6.05K subscribers
2.46K photos
190 videos
6 files
276 links
Official Great Ethiopian Run Telegram Channel.

Call 0116635757 for more details.
Download Telegram
የ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. 23ኛውን ውድድር ምዝገባ ነገ ይጀመራል

አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም.

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ እሁድ መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚካሄደውን የ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ሩጫ ውድድር ምዝገባ ዛሬ በይፋ አስጀምራል።

ይህ በየዓመቱ ለሴቶች ብቻ የሚዘጋጀው ሩጫ በቦሌ አትላስ ሆቴል አቅራቢያ በሚገኘው የተለመደ ስፍራ መነሻ እና መድረሻውን በማድረግ የ5 ኪሎ ሜትር ውድድሩን ያካሒዳል። ውድድሩ የኢትዮጵያ ሴቶችን ስኬት በማብሰር እና ለሌሎች ተምሳሌት በማድረግ 23 ዓመታትን ተጉዟል።

ዛሬ በህያት ሬጀንሲ በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የተወከሉ የስራ ሃላፊዎች፣ የመገናኛ ብዙኃን ባለሞያዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የውድድሩ አምባሳደር አትሌት መሰረት ደፋር ተገኝተዋል።

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዋና ስራ አስኪያጅ ዳግማዊት አማረ፣ በውድድሩ ላይ የሴቶችን ተሳትፎ ከዚህም በላይ ማሳደግ እና ማስፋፋት እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። ዳግማዊት ሲናገሩ "የውድድሩን መመዝገቢያ ዋጋ ለሁሉም ሰው ተደራሽ እንዲሆን በማሰብ፣ ተመጣጣኝ ለማድረግ የምንችለውን ሁሉ እያደረግን ነው" ብለዋል። ኤም-ፔሳ (M-Pesa) መተግበሪያውን ተጠቅመው ለሚመዘገቡ የ15% ቅናሽ ፤ እንዲሁም ዳሽን ባንክ በሱፐር አፑ ለሚመዘገቡ የ10% ቅናሽ እንዳዘጋጁም አያይዘው ተናግረዋል።

የስያሜ አጋር የሆነውን ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በመወከል የብራንድ እና ኮሙኒኬሽን ክፍል ሃላፊ የሆኑት ሔርሜላ ይልማ በበኩላቸው፡ "እንደ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ፣ የሴቶችን ጥንካሬ የምናንጸባርቅበት፣ ድምፃቸውን የምናሰማበት እና ስኬታቸውን የምናከብርበት የዚህ ዓመታዊ ውድድር ዋና ስፖንሰር በመሆናችን ትልቅ ኩራት ይሰማናል። ጠንካራ አጋርነታችንም ወደፊት እንደሚቀጥል ላረጋግጥ እወዳለሁ" ብለዋል።

የዘንድሮው ውድድር በዲ.ኬ.ቲ ኢትዮጵያ (DKT Ethiopia) የቀረበውን ‘በመላ ኑሪ - በኮንፊደንስ ሩጪ’ የሚል የውድድር መልዕክት ይተላለፍበታል። በመክፈቻው ላይ ንግግር ያደረጉት የዲ.ኬ.ቲ. ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አዲቲያ ፑትራ "ዲ.ኬ.ቲ. ኢትዮጵያ የውድድሩ የመልዕክት አጋር በመሆኑ ደስታ ይሰማዋል። ‘በመላ ኑሪ - በኮንፊደንስ ሩጪ’ የሚለው መሪ ቃል፣ በቂ ግንዛቤ ያለው፣ የስነ-ተዋልዶ ጤና ምርጫ በራስ መተማመንን እና ዕድሎችን ይፈጥራል የሚለውን ዕምነታችንን ያንጸባርቃል። በኢትዮጵያ ያልተሟላ የቤተሰብ ምጣኔ ፍላጎት አሁንም እንደ ፈተና ቢቀጥልም፣ ይህ አጋርነት የጤና ግንዛቤን ከማህበረሰብ ተሳትፎ ጋር ለማስተሳሰር ይረዳል" ብለዋል።

ለ23ኛው ዓመት የ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ሩጫ ምዝገባ የካቲት 14 ቀን 2018 ዓ.ም. በኤም-ፔሳ፣ በዳሽን ሱፐር አፕ እና በአራት የሳፋሪኮም ሱቆች ይጀምራል። የዘንድሮው የውድድር መመዝገቢያ ዋጋ 590 ብር ነው። ውድድሩ በሳፋሪኮም፣ ኤም-ፔሳ፣ ዲ.ኬ.ቲ. ኢትዮጵያ፣ ዳሽን ባንክ፣ አክቲቭ (Aktive)፣ የአየርላንድ ኤምባሲ፣ ዩኒሴፍ (UNICEF)፣ ፋብ ውበት ሳሙና፣ ቶፕ ውሃ፣ ህያት ሬጀንሲ፣ ኢ.ቲ.ቪ እና አፍራን ሆስፒታል አጋርነት የተዘጋጀ ነው።
12👍2
ቅዳሜን በቆንጆ ሁኔታ ያሳለፍንበትን ሩጫችን ላይ በድጋሚ ለመገኘት አሁኑኑ ይመዝገቡ!🤩

ለቀጣይ ሩጫችን ምዝገባ ላይ ነን!📣

እንጦጦ ፓርክ ሲቢኢ ሩጫ

#EntotoCBERun #GreatEthiopianRun #EntotoPark
👍51
በአምስት ቀናት 10ሺህ ሴቶች ለ2018 የሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ሩጫ ተመዘገቡ

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ሩጫ 10,000 የውድድር ቦታዎች መያዛቸውን አስታወቀ።

ምዝገባ በተጀመረ የመጀመሪያ ሳምንት ከ60በመቶ በላይ ተሳታፊዎች መመዝገባቸውን በመጥቀስ ከጠቅላላው 16,000 የውድድር ቦታዎች ውስጥ አሁን የቀሩት 6,000 ቦታዎች መሆኑን ገልፅዋል።

በየዓመቱ ለሴቶች ብቻ የሚዘጋጀውና እሁድ መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. ሊከናወን የታቀደው ይህ ውድድር ዘንድሮ 23ኛ ዓመቱን ያከብራል። ውድድሩ በኢትዮጵያ ውስጥ የሴቶችን ስኬት በማክበር ረገድ እየተጫወተ ባለው ሚና እና የውድድር ቀን ባለው ልዩ ድባብ ምክንያት በተሳታፊዎች ዘንድ ተጠባቂ ቀን ሆኗል።

የዘንድሮው የውድድር መልዕክት ‘በመላ ኑሪ ፤ በኮንፊደንስ ሩጪ’ (‘Live Smart - Run Confident’) የሚል ነው። ይህ መልዕክት ሴቶች ህይወታቸውን በእውቀት እና በዕቅድ በሚመሩ የጤና ውሳኔዎች ላይ እንዲመሰርቱ በማሰብ በዲኬቲ ኢትዮጵያ አማካኝነት የቀረበ መልዕክት ነው።

ምዝገባው ለቀሩት 6,000 ቦታዎች በ 590 ብር ክፍያ ክፍት ሆኖ ይቀጥላል።

ተሳታፊዎች በዲጂታል መንገድ በ ኤም-ፔሳ (M-Pesa) እና በ ዳሽን ሱፐር አፕ (Dashen SuperApp)፣ ወይም በአካል በ ሳፋሪኮም ሱቆች (ፍየል ቤት ፣ አራት ኪሎ ፣ መገናኛ እና ጀሞ) እንዲሁም በ ዳሽን ባንክ ቅርንጫፎች (ፒያሳ ፣ ጣና መርካቶ እና ልደታ) መመዝገብ ይችላሉ።

የሴቶችን ተሳትፎ ለማበረታታት በየመተግበሪያዎቻቸው ለሚመዘገቡ ኤም-ፔሳ የ15% እንዲሁም ዳሽን ባንክ የ10% ቅናሽ እያደረጉ ይገኛሉ።

በተጨማሪም የተማሪነት መታወቂያ ማቅረብ ለሚችሉ ተማሪዎች የ30% ልዩ ቅናሽ በታላቁ ሩጫ አማካኝነት ተዘጋጅቷል።
15
ነፃነት ፣ ድል ፣ ጀግንነት፣ ኩራት ፣… በዓድዋ!

እንኳን ለ130ኛው የዓድዋ ድል በዓል አደረሳችሁ!

#Adwa #GreatEthiopianRun #Ethiopia #AfricanVictory
14👍8🔥2👏1
አትሌት መሰረት ደፋር ለ16ሺህ ሴቶች 5ኪ.ሜ. ሩጫን ከ’35 ደቂቃ በታች’ የማጠናቀቅ ፈተናን አቀረበች፡፡

ከተለያዩ የስራ ዘርፎች የተመረጡ ተምሳሌት ሴቶች የውድድሩ አንድ አካል በመሆን ስኬታቸው የሚወደስበት ፕሮግራም በሩጫው ቀን ይከናወናል።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሚያዘጋጀውና መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. ለሚካሄደውና 16,000 ሴቶች ለሚሳተፉበት የ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. የሩጫ ውድድር ልምምድ ቀጥሏል። የሁለት ጊዜ ኦሊምፒክ የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቷ የውድድሩ አምባሳደር መሰረት ደፋር ሴቶች አስቀድመው እንዲለማመዱ እና እንዲሮጡ ለማበረታታት ዓመታዊውን የ’35 ደቂቃ በታች’ ፈተና ይፋ አድርጋለች።

ተሳታፊዎች ይህንን ግብ እንዲመቱና በስፖርት የዳበረ ዘመናዊ የአኗኗር ዘይቤን እንዲለማመዱ ለመርዳት፣ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለ4 ተከታታይ ሳምንታት የሚቆይ የስልጠና መርሃ ግብር በማከናወን ላይ ነው። ስልጠናው በሙያዊ አሰልጣኞችና አሯሯጮች (pace-makers) የሚታገዝ ሲሆን፣ በመሰረት ደፋር የአራት ሳምንታት የልምምድ ምክሮች የታጀበ ነው።

እንዳለፉት ዓመታት ሁሉ የውድድሩ መነሻና መድረሻ በቅርቡ እድሳት በተደረገለት ቦሌ አትላስ አካባቢ የሆነው ይህ ውድድር ከስፖርታዊ እንቅስቃሴ ባለፈ የሴቶች ስኬት የሚዘከርበት ፣ ስራቸው የሚነገርበት እና ዕውቅና የሚያገኝበት እንዲሁም አንዳቸው ሌላቸውን የሚያበረቱበት ልዩ መድረክ ሆኖ ለ22 ዓመታት ቀጥሏል።

ዘንድሮም በ‘ተምሳሌት ሴቶች’ (Icons Women) መሐከል የሩጫ ውድድር የሚከናወን ሲሆን፣ የአሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማት በስማቸው ለመረጡት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ይለገሳል። በ23ኛው ዓመት ሩጫ ውድድር ላይ ከስምንት የተለያዩ ዘርፎች የተመረጡ ታዋቂ እና ተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ይሳተፋሉ። ዘርፎቹም፦ ከኪነጥበብ፣ ከበጎ አድራጎት፣ ከመምህራን፣ ከሰራ አመራሮች፣ ከሚዲያ ባለሙያዎች፣ ከስራ ፈጣሪዎች፣ ከጤና ባለሙያዎች እና ከማህበራዊ ሚድያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች የተውጣጡ ናቸው። በዚህም መሰረት፦ ሉላ ገዙ፣ እማሆይ ዜና ማርያም፣ ሊያ ሳሙኤል፣ ቤተልሄም ደሴ፣ መቅደስ ሙሉጌታ (መቅዲዬ) እና ቤቲ ጂ በውድድሩ ላይ በተምሳሌት ሴቶች ዘርፍ ከሚሳተፉ ባለሞያዎች መካከል ጥቂቶቹ ናቸው።

ለውድድሩ የተመዘገቡ ተሳታፊዎች ከመጋቢት 2 እስከ 4 ቀን 2018 ከአለም ሲኒማ ጋር ቲሸርታቸውን መውሰድ እንደሚችሉም ታውቋል፡፡ ውድድሩ በሳፋሪኮም፣ ኤም-ፔሳ፣ ዲ.ኬ.ቲ (DKT)፣ ዳሽን ባንክ፣ አክቲቭ (Aktive)፣ የአየርላንድ ኤምባሲ፣ ዩኒሴፍ (UNICEF)፣ ፋብ የውበት ሳሙና፣ ቶፕ ውሃ፣ ህያት ሬጀንሲ፣ ኢቲቪ እና አፍራን ሆስፒታል አጋርነት ይዘጋጃል።
9👍9
ጋዜጣዊ መግለጫ

የ23ኛው ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪ.ሜ ሩጫ የቅድመ-ውድድር ጋዜጣዊ መግለጫ በእቴጌ መነን የልጃገረዶች ትምህርት ቤት በደመቀ ሁኔታ ተካሄደ

እሁድ መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. የሚካሄደውን የ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች  ኪ.ሜ. የጎዳና ላይ ሩጫ አስመልክቶ፤ የመጨረሻው የቅድመ-ውድድር ጋዜጣዊ መግለጫ ዛሬ በታሪካዊው እቴጌ መነን የልጃገረዶች ትምህርት ቤት ተካሒዷል።

በዝግጅቱ ላይ የውድድሩ አምባሳደር የሆነችው አትሌት መሰረት ደፋር እና የቀድሞ የትምህርት ቤቱ ተማሪ የነበሩት ታዋቂዋ ፖለቲከኛ ወ/ሮ ብርቱካን ሚደቅሳ እንዲሁም ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

"ሴቶች በዓላማ ጠንክረው ከሰሩ ያሰቡበት ደረጃ መድረስ ይችላሉ፤ እናንተ ለሀገር ተስፋዎች ናችሁና በርቱ" ስትል አትሌት መሰረት ደፋር በመድረኩ ላይ ንግግር አድርጋለች።

ሌላው በመድረኩ ላይ ንግግር ያደረጉት የአ.አ. ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰግደው ኃ/ጊዮርጊስ "እቴጌ መነን ወደ ትክክለኛ ማንነቱ የተመለሰ ታሪክ ሆኗል ፤ ጎበዝ፣ አስተዋይ እና የወደፊቷ ኢትዮጵያ መሪ የሆኑ ሴቶች እየተማሩበት ነው። ስፖርት በጤና እና ስነምግባር የበለፀገ ማህበረሰብን ይፈጥራል ዛሬ አብረን የተሳተፍንበት እንቅስቃሴ የዚህ ማሳያ ነው። መጋቢት 13 የሚኖረው ሩጫ ከምንም በላይ አብሮነታችንን የምናሳይበት እንዲሆን አብረን እንሰራለን" ብለዋል።

የቀድሞ የፖለቲካ ሰው ብርቱካን ሚደቅሳ ቀደም ሲል ይማሩበት በነበረው በዚህ ትምህርት ቤት ተገኝተው ለተማሪዎቹ እና ለመምህራኑ ንግግር ያደረጉ ሲሆን፣ ለአሁኑ ትውልድ ተማሪዎች ማበረታቻ እንዲሆን አዲስ ካሳተሙትን 'መመለስ' የተሰኘ መጽሐፍ የተወሰነ ክፍልን በማንበብ የራሳቸውን ታሪክ ከማጋራታቸው ባሻገር መፅሐፋቸውን በስጦታነት ለት/ቤቱ አበርክተዋል።

በልዩ ዝግጅቱ ማጠቃለያ ላይ በትምህርት ቤቱ ተማሪዎች መሀከል ጠንካራ የፉክክር መንፈስ የታየበት የዱላ ቅብብል የሩጫ ውድድር የተካሄደ ሲሆን፣ ይህም በውድድሩ ዋዜማ በትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ዘንድ ልዩ መነቃቃትን ፈጥሯል።

ስለ የ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች  ኪ.ሜ. አጠቃላይ መረጃ

* የውድድሩ ቀን፦ እሁድ መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም።
* መነሻ እና መድረሻ፦ ቦሌ አትላስ ሆቴል አካባቢ።
* ተሳታፊዎች፦ 16,000 ሴቶች፣ ከ150 በላይ ጠንካራ ተፎካካሪ አትሌቶች እና ከ25 ተምሳሌት ሴቶች።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ለ23 ዓመታት ያለማቋረጥ ሲያካሂደው የቆየው ይህ ውድድር፣ ዘንድሮም "በመላ ኑሪ በኮንፊደንስ ሩጪ" በሚል የውድድር መልዕክት በደመቀ ሁኔታ ለመካሄድ ዝግጅቱን አጠናቋል።
👍1210
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1447ኛው ዒድ አል-ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ዒድ ሙባረክ!

#GreatEthiopianRun
👍83
የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚንስትር ክብርት ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚገኘውን የካንሰር ህሙማን ማዕከል ጎበኙ።

መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም. ከሚካሄደው የ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ሩጫ አስቀድሞ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ የሚገኘውን የካንሰር ህሙማን ማዕከል ላይ ጉብኝት ተደርጓል። 

በጉብኝቱ ከዶ/ር ኤርጎጌ በተጨማሪም የአዲስ አበባ ሜዲካል ኮሌጅ ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ብርሀኑ ደስይበለው እና የአክቲቭ መስራች ኤሌ አኒሰን ተገኝተዋል።

‘AKTIVE AGAINST CANCER’ በዘንድሮ 2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ውድድር ላይ ሴቶች የካንሰር ህመምን ቀድሞ ለመከላከል ሩጫን በማዘውተር ጤናቸውን ይጠብቁ ዘንድ መልዕክታቸውን ያስተላልፋሉ።

ዛሬም በጉብኝቱ ላይ ዶ/ር ኤርጎጌ "የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር እንደዚህ ያሉ ትብብሮችን ሁልጊዜ ይደግፋል ፤ ይህ ለኢትዮጵያ ሴቶች ትልቅ ትርጉም አለው ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ. ዉድድር ሴቶችን የሚያበረታታ መድረክ ነው" በማለት ገልፀዋል።

ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ ለካንሰር ማዕከሉ ያደረገውን ድጋፍ በማመስገን ንግግር ያደረጉት የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ብርሀኑ ሰንደቅ "ከታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ስለ ካንሰር ግንዛቤ ለመፍጠር ብዙ ተስፋ አለን" ብለዋል።

ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ሩጫ ካንሰርን ለመከላከል ብሎም በማገገም ሒደት ውስጥ ባለው ጠቀሜታ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን ለመስራት የሚችልበትን ስምምነት ለአራት ተከታታይ አመታት ከአክቲቭ አጌንስት ካንሰር ጋር ፈፅሟል።

የ2018 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5ኪ.ሜ.  ነገ መነሻ እና መድረሻውን ቦሌ አትላስ በማድረግ ለ23ኛ ጊዜ ይከናወናል።
7👍5