ወርቃማ ንግግሮች
16.6K subscribers
1K photos
210 videos
54 files
3.29K links
ሰው የለበስክ ሰው እንጂ ልብስ የለበስክ ሰው አትሁን.. ሰውነት የአለም ምርጡ ጌጥህ እሱ ነውና።

አስተያየት እንቀበላለን.. @Golden_SpeechBot

https://youtube.com/channel/UCgP-E0miz3BhJ0YAGJ2zCHg
Download Telegram
ልክ በዛሬዋ ቀን

ያን ቀን ማታ ነቢ ሰዐወ ከሀረም ቅጥር ግቢ ውስጥ ከካዕባው አጎራባች ተኝተዋል። መልዐኩ ጅብሪል እሳቸው ከተኙበት ስፍራ ቁሞ እግራቸውን መታ አድርጎ ተሰወረ።

ነቢ ብድግ አሉ።
ዙርያቸውን ቢቃኙ ምንም ሊያዩ አልቻሉም። ዳግም ወገባቸውን ከመሬት አሳርፈው አሸለቡ። መልዐኩም ዳግም መጥቶ የነቢን እግር መታ በማድረግ እራሱን ሰወረ።

ዳግም ብድግ አሉ። ዙርያቸውን ቢቃኙም ምንም ሊያገኙ ባለመቻላቸው ቀን ሲንከራተት የዋለ ገላቸውን ለማሳረፍ ዳግም ተመልሰው ተኙ።

መልዓኩ ለሶስተኛ ግዜ ብቅ አለ። ነቢ በእንቅልፍ ጭልጥ ብለዋል። እግራቸውን መታ አደረገው...እሳቸውም ብንን ብለው ከተኙበት ተቀመጡ።

መልዐኩም ጡንቻቸውን ይዞ አቆማቸው። ከወደ መስጅዱ መውጫም ይዟቸው ይሄድ ጀመር። ነቢ ይከተሉታል...
ከመስጅዱ ሲወጡ ደጅ ላይ አንድ ፍጥረት ቁሟል።

ለአይን ይማርካል፣ የፈረስ ቅርፅ ቢኖረውም ቁመቱ ከአህያ ትንሽ ከፍ ይላል። ወገቡ ላይ ተገጥመው የሚታዩት ሁለቱ ክንፎቹ ውበቱን አድምቀውታል።

ነቢ ከተዘጋጀላቸው መጓጓዣ ወደታቀደላቸው ስፍራ ሊጓዙ ግና ለመውጣት ቢጠጉ ፍጥረቱ/ቡራቅ ተርበተበተ፣ ተንዘፈዘፈ፣ ተንቀጠቀጠ...እንዲያው ተወራጨ። እንዴታ! ነቢን ሊጭን ነዋ! እድል ቀንቶታላ! እንዴት አይወራጭ?

ሁናታውን ሲመለከት የነበረው ጅብሪልም፦«አደብ ግዛ እንጂ! እንዲያው በነቢ ነው እንዴ እንዲህ እምትሆን? የሱን ያህል ክቡር በጀርባክ ተሸክመህም አታውቅም።» ብሎ ወቀሰው። አልተረዳውማ!

ነቢ ከቡራቁ ተቀመጡ። ጎዞው ተጀምሮ ቡራቁም በየእርምጃው አድማሳቱን ያቋርጥ ጀመር። ከመሀል መንገድ ከአሸዋማው ስፍራ ከዘንባባዎች አውድማ ቡራቁ ቆመ።

«ሙሀመድ ሆይ! እዚህ ጋ ውረድ ና ስገድ» ብሎ በውድቅቱ ሌሊት ጂብሪል አዘዛቸው፤ ነቢም ወርደው ሰገዱ።

«ይህን ስፍራ ታውቃለህ?» ጂብሪል ጠየቃቸው።
«አላውቀውም/አላህ ይወቅ» ብለው መለሱለት ውዴ።
«ይህ ስፍራ የስሪብ ይባላል፤ ጠይባ» ብሎ ነገራቸው።

ጉዞው ቀጠለ፤ ከአድማስ አድማሱን እየነጎዱ ከአንድ በረሀ ደረሱ። ቡራቁ ቆመ።

«ሙሀመድ ሆይ! እዚህ ጋ ውረድ ና ስገድ» ብሎ በውድቅቱ ሌሊት ጂብሪል አዘዛቸው፤ ነቢም ወርደው ሰገዱ።

«ይህን ስፍራ ታውቃለህ?» ጂብሪል ጠየቃቸው።
«አላውቀውም/አላህ ይወቅ» ብለው መለሱለት ነቢ።
«ይህ ስፍራ መድየን ይባላል። ሙሳ ከተቀመጠባት ጥላ ስር ነው የሰገድከው» ብሎ ጎዞውን ቀጠሉ።

ቡራቁ ይከንፋል፤ ከመቅፀብት ብዙህ ሺህ ኪሎሜትሮችን ይምዘገዘጋል። ቡራቁ ድንገት ቆመ፤ ከርቀት ህንፃዎች ይታያሉ ስፍራው ጭር ብሏል።

«ሙሀመድ ሆይ! እዚህ ጋ ውረድ ና ስገድ» ብሎ በውድቅቱ ሌሊት ጂብሪል አዘዛቸው፤ ነቢም ወርደው ሰገዱ።

«ይህን ስፍራ ታውቃለህ?» ጂብሪል ጠየቃቸው።
«አላውቀውም/አላህ ይወቅ» ብለው መለሱለት ውዴ።
«ይህ ስፍራ ቤተልሔም ይባላል። እዚህ ነቢ ዒሳ ተወልዷል።» ብሎ ነገራቸው።

ወደ ከተማዋ ተጉዘውም ከመግብያዋ ገብተው ከአቅሳው ቅጥር ግቢ ጅብሪል ነቢን ይዞ ብቅ አለ። ቡራቁን ከአንድ ድንጋይ ሽንቁር ሸብ አድርጎ የነቢያቱን ንጉስ ከመስጅዱ ይዞት ዘለቀ።

ለክብር እንግዳው አቀባበል ልያደርጉ ነብያት ከመስጅዱ ተሰብስበዋል። ኢብራሂም፣ ዒሳ፣ ሙሳ...በናፍቆት ይጠባበቁት ነበር።

መስጅዱ በነብያት ተሞልቷል፣ ጂብሪል ለነቢ ኢማምነት አዛን ለማድረግ ያን ቀን ተወፍቆ አዛን አደረገ። ነብያቱም ከነቢ ጀርባ ተሰልፈው ለመስገድ እድል ቀንቷቸው ከኋላው አረሙ።

ልክ ሰላቱ ሲጠናቀቅ ጀብሪል በሁለት እቃዎች ወተት እና ጠጅ ይዞላቸው መጥቶ ያማርጣቸው ጀመር።
ነብይህም ሳያንገራግሩ ወተቱን መረጡ።
ተፈጥሮን ለመረጠው ነብይ ጂብሪልም ያበስረው ጀመር።

ብዙም ሳይቆዩ ከመስጅደል አቅሳ ጅብሪል ይዟቸው ወጣ። ደጅ ላይ የተዘጋጀውን ሚዕራጅ/ማረግያ ተመለከቱ። ውበቱ ፈጥረታትን ሁሉ ይልቃል፤ እዝያ ላይ ነቢን መልዐኩ አስቀመጣቸው።

ሚዕራጁ ተንቀሳቀሰ፤ ጉዞ ወደ ሰማየ-ሰማያት....ጂብሪል ከነቢ ጋ የመጀመርያውን ረጅም ጉዞ አላህ ወፍቆት ያጣጥመው ጀመር።

የታችኛውን ግዛተ አለም ከኋላቸው ትተው ወደ ላይ መጠቁ፤ ሰማይ ተደረሰ። ወደ ሰማየ-አለሙ መዝለቅያ በር አለ።

ይህ በር ባቡል ሐፈዛ/የጠባቅያን በር በመባል የሚታወቅ ሲሆን የስፍራው አዛዥም ኢስማዒል ይሰኛል። ከስሩ 12 ሺህ የመግብያው ጠባቅያን ይገኛሉ።

ጅብሪል እደጅ ሁኖ አንኳኳ።

«ማን ነው?» ከወደ ውስጥ ሁኖ ጠባቂው ጠየቀ።
«ጂብሪል ነኝ» ብሎ መልዐኩ መለሰ።
«ከማን ጋር ነህ» ጠየቀው ጠባቂው።
«ከሙሀመድ» ጂብሪል መለሰለት።
«እዚህ እንዲመጣ ተጠርቶ ነው?»
«አዎን» ብሎ ጂብሪል መለሰለት።
«እንኳን ደህና መጣ! መልካም አመጣጥን መጥቷል» ብሎ ተቀበለው።

በሩ ተከፈተ፤ ነቢ ከጅብሪል ጋ ዘልቀው ሲገቡ አደም ቁሟል።
«ሂድ ሰላም በለው፤ይህ አባትህ አደም ነው» ብሎ ጅብሪል ነቢን አዘዘ።

ነቢን ሂደው ቢዘይሩት አደምም፦«እንኳን ደህና መጣህ መልካም ነብይ እና መልካም ልጄ» ብሎ ተቀበላቸው። ዋ አደም! ነቢን ያየህ ቀን ምንኛ ታደልክ!

ትተውት አለፉ።
ገና ሰማዩን ተሻግረው ሳያልፉ የግመል አፍ ይመስል ከፊታቸው የተገጠመላቸው ሰዎች በእጆቻቸው የድንጋይ ፍሞችን ይዘው ይጎርሱ'ና ከመቀመጫዎቻቸው ሲወጣ ተመለከቱ።

ነቢ ግራ ተጋብተዋል፤ ትዕይንቱ ግራ አጋብቷቸዋል...
ወደ ጉዞ ባልደረባቸው ዞር ብለው፦«ምንድናቸው እነዚህ?» ብለው ጠየቁት።
«የየቲሞችን ንብረት በይዎች ናቸው» ብሎ መለሰላቸው፣

ትተው አለፏቸው።
ብዙም ሳይርቁ አንጀታቸው በውሀ ጥም የተቃጠሉ ግመሎችን ይመስል የሚተረማመሱ ቦርጫም ሰዎችን ነቢ ተመለከቱ። የሚተረማመሱበት መንገድም የፈርኦናውያኑ ጎዳና ላይ ነው። ጀሀነም VIP...

ነቢ ቆም አሉ።
«እነዚህስ ምንድናቸው...?» ብለው ነቢ ጠየቁት።
«እነዚህ ወለድ በይዎች ናቸው» ብሎ መለሰላቸው።

ትተው አለፉ።
ጥቂት እንደተጓዙ በጡቶቻቸው ቁልቁል የተንጠለጠሉ እንስቶችን ተመለከቱ። ምን ጉድ ይሆን!

«እነ ማን ናቸው?» ብለው ጠየቁት ነቢ።
«ባሎቻቸው ላይ ማግጠው ከሌላ የሚወልዱ ዝሙታውያን እንስቶች ናቸው» ብሎ መለሰላቸው።

ትተው ሰማየ-አድማሳቱን እያቆራረጡ ከሁለተኛው ሰማይ ደጃፍ ላይ ተከሰቱ። ጅብሪል ሊካድም ወገቡን ያሰረ ይመስላል። በሩን አንኳኳ።

«ማን ነው?» ከወደ ውስጥ ሁኖ ጠባቂው ጠየቀ።
«ጂብሪል ነኝ» ብሎ መልዐኩ መለሰ።
«ከማን ጋር ነህ» ጠየቀው ጠባቂው።
«ከሙሀመድ ጋ ነኝ» ጂብሪል መለሰለት።
«እዚህ እንዲመጣ ተጠርቶ ነው?»
«አዎን» ብሎ ጂብሪል መለሰለት።
«እንኳን ደህና መጣ! መልካም አመጣጥን መጥቷል» ብሎ ተቀበለው።

ከሰማዩ ግዛት አብረው ሲገቡ የአጎታሞች ልጆች ሁለተኛ ሰማይ ላይ ቁመዋል። ያሕያ እና ዒሳ ዱንያ ላይም አብረው ያሳልፉ ነበር።

«እነኝያ ያሕያ እና ዒሳ ናቸው ሰላም በላቸው» ብሎ ጂብሪል ነገራቸው።
ነቢም ሰላምታ አቀረቡ።

«እንኳን ደህና መጣህ አንተ መልካሙ ነብይ! አንተ መልካሙ ወንድም » ብለው ለነብይህ ክብር እጅ ነሱ።

ጉዞው ቀጠለ፤ የሰማዩን አድማሳት በቅፅበት እያቆራረጡ ከሶስተኛው ሰማይ መዳረሻ ደጃፍ ላይ ቆሙ። ጂብሪል ቀደም ብሎ በሩን አንኳኳ።

«ማን ነው?» ከወደ ውስጥ ሁኖ ጠባቂው ጠየቀ።
«ጂብሪል ነኝ» ብሎ መልዐኩ መለሰ።
«ከማን ጋር ነህ» ጠየቀው ጠባቂው።
«ከሙሀመድ ጋ ነኝ» ጂብሪል መለሰለት።
«እዚህ እንዲመጣ ተጠርቶ ነው?»
«አዎን» ብሎ ጂብሪል መለሰለት።
«እንኳን ደህና መጣ! መልካም አመጣጥን መጥቷል» ብሎ ተቀበለው።
ነቢ በሩን ዘልቀው ከሰማዩ ገፅ ብቅ ሲሉ እፊቱ የሞላች ጨረቃን እሚመስል ሰው ተመለከቱ።

«ማን ነው ይሄ?» ብለው ጠየቁ።
«ይኼ ዩሱፍ ነው የያዕቁብ ልጅ፤ ሰላም በለው» ብሏቸው ነቢ ሰላም አሉት።

ዩሱፍም በነቢ የመዘየርን እድል እያጣጣመ፦«እንኳን ደህና መጣህ መልካም ነብይ፤ መልካም ወንድም» አላቸው።

ከላይ ተናፍቀዋልና ቁሞ ለማውጋት ግዜ የላቸውም፤ ነቢ ትተውት ወደ ሰማየ ሰማያቱ ግዛት ይመጥቁ ጀመር።

አራተኛ ሰማይ ደርሰዋል፤ ሰማይቱ የከውኑን ብርሀን ልታስተናግድ በሯ በመልአኩ ተንኳኳላት ከፋች ጠባቂው ከደጃፉ ቆመ።

«ማን ነው?» ከወደ ውስጥ ሁኖ ጠባቂው ጠየቀ።
«ጂብሪል ነኝ» ብሎ መልዐኩ መለሰ።
«ከማን ጋር ነህ» ጠየቀው ጠባቂው።
«ከሙሀመድ ጋ ነኝ» ጂብሪል መለሰለት።
«እዚህ እንዲመጣ ተጠርቶ ነው?»
«አዎን» ብሎ ጂብሪል መለሰለት።
«እንኳን ደህና መጣ! መልካም አመጣጥን መጥቷል» ብሎ ተቀበለው።

አንድ ሰው ይታያል ነቢ ማንነቱ ግልፅ አልሆነላቸውም። ጅብሪል ጠጋ ብሎ ኢድሪስ መሆኑን አውግቷቸው በሰላምታ አስተዋወቃቸው።

የአራተኛውን ሰማይ ወለል ትተው የአምስተኛውን ግዛት በብርሀን ሊያደምቁ ነቢ ህዋውን ያቆራርጡ ጀመር። ከደጃፉ ሲቀርቡም ጂብሪል ለኪድማ ጠጋ ብሎ በሩን አንኳኳ።

«ማን ነው?» ከወደ ውስጥ ሁኖ ጠባቂው ጠየቀ።
«ጂብሪል ነኝ» ብሎ መልዐኩ መለሰ።
«ከማን ጋር ነህ» ጠየቀው ጠባቂው።
«ከሙሀመድ ጋ ነኝ» ጂብሪል መለሰለት።
«እዚህ እንዲመጣ ተጠርቶ ነው?»
«አዎን» ብሎ ጂብሪል መለሰለት።
«እንኳን ደህና መጣ! መልካም አመጣጥን መጥቷል» ብሎ ተቀበለው።

ዘልቀው ሲገቡ ከሰማዩ ገፅ ላይ አንድ ሰው ቁሟል። የፀጉሩ መሸበት ከፂሙ መርዘም ጋ ተደምሮ ግርማ ሞገስን አላብሶታል። እጅግ ውብ ነው።

«ማን ነው ይኼ?» ብለው ጠየቁት።
«ይኼ በህዝቡ ዘንድ ይወደድ የነበረው ሀሩን ነው፤ ሰላም በለው» ብሎ አስተዋወቃቸው።

ሀሩን በነቢ ተዘይሮ ደስታው ወደር ቢያጣ፦«ሰላም ባንተ ላይ ይሁን፤ አንተ መልካም ነቢይ መልካሙ ወንድም» ብሎ አከበረ።

ጎዞው ቀጠለ።
ሰማያት ነቢን እየሸኙ ነቢን ይቀባበሉ ይዘዋል። ስድስተኛው ሰማይ እድል ደርሶት በነቢ ወለሉ ሊረገጥ በሩ ተንኳኳለት።

«ማን ነው?» ከወደ ውስጥ ሁኖ ጠባቂው ጠየቀ።
«ጂብሪል ነኝ» ብሎ መልዐኩ መለሰ።
«ከማን ጋር ነህ» ጠየቀው ጠባቂው።
«ከሙሀመድ ጋ ነኝ» ጂብሪል መለሰለት።
«እዚህ እንዲመጣ ተጠርቶ ነው?»
«አዎን» ብሎ ጂብሪል መለሰለት።
«እንኳን ደህና መጣ! መልካም አመጣጥን መጥቷል» ብሎ ተቀበለው።

የሰማዩን ገፅ ገና ከመርገጣቸው ጂብሪል ጠጋ ብሎ፦«ይኼ ወንድምህ ሙሳ ነው የዒምራን ልጅ፤ ሰላም በለው» ብሎ ጂብሪል አስተዋወቃቸው።

ነቢ ሰላም ሲሉት፦«እንኳን ደህና መጣህ መልካም ነብይ መልካም ወንድም »አላቸው።
ነቢ እላይ ቀጠሮ አላቸው ተቻኩለዋል ጉዞ ለመቀጠል ሙሳን ትተውት ሲያልፉ ያለቅስ ጀመር።

«ምን ገጠመህ...?» ተብሎ ቢጠየቅ...
«ትናንት ከኔ በኋላ የተላከው ነብይ ከእኔ ኡመት በላይ ህዝቦቹን አስከትሎ ጀነት ሊገባም አይደል እንዴ! » አለ።

ነቢ ጉዞ ቀጠሉ።
የአላህን ምሉእ የእጅ ስራ ጥበባት እየተመለከቱ ከሰባተኛው ሰማይ ደጃፍ ደረሱ።

«ማን ነው?» ከወደ ውስጥ ሁኖ ጠባቂው ጠየቀ።
«ጂብሪል ነኝ» ብሎ መልዐኩ መለሰ።
«ከማን ጋር ነህ» ጠየቀው ጠባቂው።
«ከሙሀመድ ጋ ነኝ» ጂብሪል መለሰለት።
«እዚህ እንዲመጣ ተጠርቶ ነው?»
«አዎን» ብሎ ጂብሪል መለሰለት።
«እንኳን ደህና መጣ! መልካም አመጣጥን መጥቷል» ብሎ ተቀበለው።

ነቢ ከሰማዩ ግዛት ዘልቀው ሲገቡ አንድ ትልቅ ቤት ተመለከቱ። እመግብያው ላይ አንድ አዛውንት በወንበር ተቀምጠዋል።

ነቢ ጠየቁ፦«ይህ የት ነው? ሰውዬውስ ማን ነው?»
«ይኼ በይተል ማዕሙር ይባላል፤ ዙርያን በቀን 70 ሺህ መላዕክት እየገቡ ይጎበኙታል። አንዴ የጎበኙት መላዕክቶች ዳግም ለመጎብኘት እድሉን አያገኙም። ይኼ ደግሞ አባትህ ኢብራሂም ነው፤ ሰላም በለው » ብሎ ጠቆማቸው።

ነቢ ሰላም ሲሉት ኢብራሂምም፦«እንኳን ደህና መጣህ፤ ውድ ልጄ ውዱ ነቢ» ብሎ ተቀበላቸው። ነቢ ሳይቆዩም ተሰነባብተው ጎዞ ወደ ላይኛው አለም ቀጠሉ።

ሰማያቱን በሙሉ ወደ ታች ትተው ህዋውን ሲመጥቁ ከሲድረቱል ሙንተሀ ደረሱ።
ሲድረቱል ሙንተሃ ማለት...




Sefwan Sheik Ahmedin
የሆነ ቀን ከፒያሳ ወደ መገናኛ በመሄድ ላይ ሳለን አንዲት ወጣት ለምን ታየኛለህ?" ብላ የሆነ ሰዉዬ ላይ ጮኸች። ጭራሽ እሱ ካልወረደ አልሄድም ብላም እሪ አለች። ከብዙ ክርክር በኋላ ሰዉዬው እየሳቀ ወረደ። ለምን እንዲህ እንዳለች ልጅቷን ጠየቅናት።
" ባለፈው አንዱ እንዲህ አይቶኝ ነው አፍዞኝ ይዞኝ የሄደው ። ከዚያም የጆሮና የአንገት ወርቄ ሳይቀር፤ ያለኝን ገንዘብ ጭምር ከባንክ አውጥቼ ከሠጠሁት በኋላ ነው ሌላ ቦታ ላይ የነቃሁት።" አለች።
ይህች ልጅ ከዚያች ክስተት በኋላ ደጋግሞ የሚያያት ሰው ሁላ ያስፈራታል ማለት ነው።
ለሁሉም ግን ዝምብሎ ሰው ላይ ማፍጠጥ ልምድ የሆነባችሁ 'ሞኞች' ተጠንቀቁ እሺ።

በነገራችን ላይ የዚህ ዓይነት ወሬ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማችን በጣም ተስፋፍቷል። ጉዳዩ ለባለታሪኮቹ ተጨባጭ እውነት ሲሆን ለሰሚው ግን ተረት ተረት ዝባዝንኬ ሆኖ ሲሳለቁበት ይታያል።

እስቲ እርስዎ ገጠመኝዎን ይንገሩን። በዚህ ዓይነቱ ወሬስ ምን ያህል ያምናሉ። ሀሳብዎን መጋራት ፈለግን።
~•

~ የሻባን ጨረቃ ሰማዩን አጊጦልን ተራውን ለረመዳን ሊያስረክብ ሁለት ጁምዓ ወይም 15 ቀናት ይቀሩናል።

~ ነፍሳችንም በአመቷ ልትታደስና ልትሰክንልን ቀርባለች አላህ በሰላም ያድርሰን።

=• ሸጋ ጁምዓ ይሁንላችሁ •=

Ibnu Mohammed
አጋራችሁን በማሳነስ እናንተ አትተልቁም!

ለፍቅረኛሞች፣ ለእጮኛሞች፣ በተለይም ለባለትዳሮች . . .

በጓደኝነት ግንኙነት፣ በስራው መስክ፣ በንግዱ አለም፣ በፖለቲካው መድረክም ሆነ በማንኛውም ማሕበራዊ መስክ ውስጥ አጠገቡ ያሉትን ሰዎች ትንሽነት እንዲሰማቸው በማድረግ እሱ ትልቅ የሆነ ሰው ታይቶ አይታወቀም! በፍጹም!!! በፍቅር ግንኙነትም ሆነ በተለይም በትዳር አጋርነት እውነታው ይኸው ነው፡፡

የአጋራችሁን ጥሩ ጎን ማየት፣ እንደሚችሉ መናገር፣ መልካም መልካሙን ማንሳትና ማደናነቅ፣ ማበረታታት፣ እናንተ የማትችሉትንና እነሱ የሚሳካላቸውን ነገር በግልጽ በማመን ማውጣት፣ ስለስኬታቸው ማንሳት . . . ትልቅ ያደርጋችኋል እንጂ አያሳንሳችሁም፡፡

ከዚህ በተቃራኒ የምታስቡ ከሆነና እነሱ እንደማይችሉ፣ ትንሽ እንደሆኑ፣ እንዳልተሳካላቸው፣ እንደምትበልጧቸው . . . የምታስቡና የምትናገሩ ከሆን ሁኔታው መጀመሪያውኑ ከአናሳነታችሁ ጋር የምትታገሉት እናንተው እንደሆናችሁ አመልካች ነው፡፡

Dr.eyob
የአዛውንቱ ማስታወሻ

ለአቅመ አዳም ስደርስ ማግባት እመኝ ነበር'ና በርግጥም ደርሼ አገባሁ። ግና ትዳር ያለ ልጆች አይጥምም ነበር። ልጅ ተመኘሁ፤ ልጆችንም ወለድኩም።

ለኔም ለልጆቼም ሚበቃን ቪላ እንዲኖረን ተመኘሁ። ተግቼ ሰርቼ ገንዘብ ያዝኩ'ና ቪላውን ገነባሁ።

ልጆቼ አድገው ጎረመሱ። ልድራቸው እና የልጅ ልጅ እንዲያሳዩኝ ተመኘሁ፤ በርግጥም ዳርኳቸው።

ግና አሁን ሰውነቴ ይደክም ጀመር፤ እድሜዬም ስራ ትቼ ቤት እንድቀመጥ ያስገድደኝም ያዘ። ስራዬን ሰው ተክቼ ቤት ጠቅልዬ ለመግባት ተመኘሁ፤ በርግጥም ቤት ገባሁ።

ያኔ ስራ አጥ ሆኜ ቤት እውል እንደነበረ ሁላ በተመሳሳይ መልኩ በስተርጅናዬም ላይ ቤት መዋል ጀመርኩ።

ግና ምኞት አሁንም ያማልለኝ ይዟል።

ቁርአንን መሐፈዝ ተመኘሁ፤ ግና አዕምሮዬ ዝሏል።
የሱና ፆሞች ላይ ለማተኮር ተመኘሁ፤ ግና ጤንነቴ ከድቶኝ ኑሯል።
የለይል ሰላት ላይ ለመበርታት ወሰንኩ፤ ግና እግሮቼ ሊሸከሙኝ ተሳናቸው።

ነቢዩ ﷺ  ያሉት ነገር አሁን ገባኝ።

5 ነገር ሳይቀድምህ በ5 ነገር ተጠቀም
- ወጣትነትህን እርጅና ሳይቀድምህ
- ጤንነትህን በሽታ ሳይቀድምህ
- ሀብትህን ድህነት ሳይቀድምህ
- ነፃ ግዜህን የግዜ እጥረት ሳይገጥምህ
- ህይወትህን ሞት ሳይቀድምህ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
~ ○ የሟችና አልቃሽ አስገራሚ ገፅታ ○~

አንድ ቀን አላህን በጣም የሚያመልክ ሰው ወደ ሞት እየተቃረበ መጣ በዙሪያው ያሉ ቤተሰቦቹ ማልቀስ ጀመሩ...ከዛም ይህ ሊሞት የተቃረበ ሰው ለቤተሰቦቹ "ቁጭ አድርጉኝ " አላቸው ደግፈው አስቀመጡት ..ከዛም ወደ አባቱ ዞረና ለምን ታለቅሳለህ ብሎ ጠየቀው አባቱም አንተን ማጣቴ ከአንተ በኋላ ብቸኛ መሆኔ ነው የሚያስለቅሰኝ ብሎ መለሰ ..ወደ እናቱም ዞረና እናቴ ለምንድነው የምታለቅሺው አላት እናትየውም "የልጅ ማጣት መሪር ሀዘን ነው የሚያስለቅሰኝ " አለችው ..ወደ ሚስቱ ዞረና ባለቤቴ ምንድነው የሚያስለቅስሽ አላት እሷም " የአንተን መልካም ነገር ስለማጣ ፤ወደሌላ ስለምከጅል ሸክም ስለምሆን ነው አለችው ወደ ልጆቹም ዞረና ምንድነው የሚያስለቅሳችሁ አላቸው እነሱም " ካሁን በኋላ ወደ የቲምነት ወደ ውርደትና ደጋፊ ወደማጣት ስለምንጓዝ አሉት....ይህን ሁሉ ከሰማ በኋላ በጣም አለቀሰ ቤተሰቦቹም ለምን ታለቅሳለህ አሉት እሱም ሁላችሁም ለኔ ብላችሁ ሳይሆን ለራሳችሁ ጥቅም ነው የምታለቅሱት ከናንተ ውስጥ ...ለጉዞዬ መርዘም ለስንቄ ማነስ የሚያለቅስልኝ የለም??....ከናንተ ውስጥ ከዚህ በኋላ መኝታዬ ለብቻዬ አፈር ለመሆኑ የሚያለቅስልኝ የለም ?? ከናንተ ውስጥ ከዚህ በኋላ ስለሚጠብቀኝ አስደንጋጭ ጥያቄዎች የሚያለቅስልኝ ሰው የለም ?? ከናንተ ውስጥ የአለማት ጌታ ፊት መቆሜን አስታውሶ የሚያለቅስልኝ የለም ??......አለና በፊቱ ወደቀ ቢያንቀሳቅሱትም ህይወቱ አልፋለች 💔💔😭
መልዕክተኛው ሰዐወ ተቀምጠው ንግግር ያደርጋሉ። ዙርያቸውን ከበው የተቀመጡ የመልዕክተኛው ሰዐወ ባልደረቦች በተመስጦ እና በስስት የመልዕክተኛውን ንግግር እያዳመጡ ነው። ፍፁም እርጋታ ፍፁም ስክነት ስፍራው ላይ ሰፍኗል።

ድንገት ከየት መጣ ያልተባለ አንድ አይሁድ ዘሎ ወደ መሀል በመግባት ነቢን ሰዐወ በሀይል አናቃቸው።
‹‹ሙሀመድ ሆይ! ገንዘቤን መልስልኝ፤ ድሮም ገንዘብ ተበድሮ መጥፋት የዘራችሁ ነው ›› ብሎ ጮኸባቸው።

ይህ ሰው በርግጥ ብድር ለነቢ ሰዐወ አብድሮ ነበር፤ ግና መክፈያ ግዜው አልደረሰም። ሰሀባው የነቢን መታነቅ ሲመለከት በጥድፍያ ሰይፉን መዘዘ፦‹‹ነቢ እባክዎን ይህን አንገት ልቀንጥሰው ይፍቀዱልኝ›› አለም።

ነቢ ሰዐወ ሰከኑ፣ ታገሱ፣ ንዴታቸውን ዋጡ፣ እንዲህም አሉ፦‹‹በስርዐት ብሩን እንዲጠይቀኝ ለርሱ ንገረው፤ ለኔ ደግሞ ብድሬን እንድመልስ ምከረኝ እንጂ አንገት መቁረጥን ምን አመጣው!››

የሁዲው ተናገረ፦‹‹በዝያ በዕውነት በላከህ ጌታ እምላለሁ፤ ብድሬን ልጠይቅህ አልመጣሁም። መክፈያ ግዜውም አልደረሰም። ብዙ ሰለልኩህ፣ ብዙ ፈተንኩህ ግና ያ በኦሪት ይወራለት የነበረው ነቢይ አንተ ሁነህ አገኘሁህ። ትዕግስተኛ ስለመሆንህ ኦሪት ነገረኝ። ዛሬ ልፈትንህ ሽቼ በአክባሪዎችህ ፊት አነቅኩህ ትዕግስትህን ተመለከትኩ።

እነሆ! የአላህ መልዕክተኛ መሆንህን እመሰክራለሁ። የነበረብህንም እዳ ለነዳያን ትመፀውተው ዘንድም ይቅር ብያለሁ ››

ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም
0ረብ ሃገር ያላችሁ ወገኖች !
~

1- ቤተሰቦቻችሁን እርዱ። መሆንም ያለበት ነው። ግን ድጋፋችሁ የሚጠቀሙበት እንጂ የሚጎዱበት እንዳይሆን ተጠንቀቁ። ለአጉል ሱሶች የሚጠፋ አይሁን።
2- ራሳችሁን አትርሱ። ተቀማጭ ይኑራችሁ። ዛሬ ሰው ተጨካክኗል። እድሜ ልካችሁን ስትልኩ ኖራችሁ በህመም የወደቃችሁ እለት የሚያነሳችሁ እንኳ ላይኖር ይችላል።
3- ብድር ስትሰጡ በሚገባ ተዋዋሉ። መካካድ በዝቷል። አማና የምታስቀምጡበትንም ለዩ።
4- በማይረቡ ሰበቦች የሚወጡ ወጭዎችን ቀንሱ።
5- ጥሩ ክፍያ አላገኘንም እያላችሁ ለወራት ያለ ስራ አትቀመጡ።
6- "አገባሻለሁ" ለሚሉ ጩልሌዎች የዘመናት ጥሪታችሁን አሟጣችሁ አትስጡ። ለትዳር ሲባል ገንዘብ መውጣቱ ችግር የለውም። ገንዘባችሁን እንጂ እናንተን በማይፈልጉ ሰዎች አትሸወዱ ማለቴ ነው።

=
የቴሌግራም ቻናል
https://t.me/IbnuMunewor
Forwarded from Qidmiya Letwhid
በቀላሉ እጅግ ጠቃሚ ቻናሎች ተቀላቀሉ
👇👇
ነሺዳ + መንዙማ = ዘፈን

በየአመቱ ረመዷን ጠብቀው ይህን ኢስላማዊ  የሚል ቅብ ቀብተው የሚለቁ አሉ  ረመዳንን በመንዙማና በነሺዳ  ሞቅ ሞቅ ለማድረግ ያስባሉ 

የሚያስቀውና የሚያሳዝነው እነኚህ መንዙማ እና
ነሺዳ ከታዋቂ ዘፋኞች ሳይቀር  ግጥም
እየሰረቁ ነው የሚሰሩት ግን አንሳሳት ሁላችንም ቆም ብለን ልናስብበት ይገባል መንዙማ በማዳመጥ
ወደ አላህ የምንቃረብ አይምሰለን
ፆመኛ ሆነን የሽርክ መንዙማ እየሰማን እንዴት
          ወደ አላህ እንቃረባለን
ረመዷን ላይ መንዙማ ከረመዷን ውጪ ዘፈን??

ኢስላማዊ ስለተባለ ብቻ አናሰልመውም 
ረመዳን የቁርአን ወር ነው ።
ረመዳን የኢባዳ ወር ነው ።
ረመዳን የዚክር ወር ነው ።
አላህ ከምንም ግዜ በላይ
የምናስታውበት የምንለምንበት
የምናመሰግንበት ወር ነው


ረሱል ሰለላሁአለዪሂ ወሰለም
የወደደ እኮ  እነሱን ነው ሚከተለው።
ሱናቸውን ነው በአቅሙ ልክ እግር በእግር የሚከተለው እንጂ በሳቸው ስም እየነገድ ኪሱን እየሞላ ኡማውን ኢስላማዊ የሚል ስም ሰይሞ በዘፈን አያጠምም

አላህ ይምራን አላህ ከአውቆ አጥፊዎች አያድርገን

ሼር በማድረግ አሰራጩት
a.k
ቻናሉ ተቀላቀሉ👇👇
t.me/tdar_ina_islam
t.me/tdar_ina_islam
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ስናፈጥር የምንለው ዱአ ለመሸምደድ እንዲመች ቀለል ባለ መልኩ የተዘጋጀ ነው ቪዲዮውን

ሼር አድርጉት ይህ ነገር የማያውቁ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ

ሼር
ቻናሉ ተቀላቀሉ👇👇
t.me/tdar_ina_islam
t.me/tdar_ina_islam
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ዩሱፍ
መጃሊሱ ሽህሪ ረመዷን.apk
383.6 MB
「𑁍📲አዲስ አፕ | ተለቀቀ 𑁍」

╭┈⟢🎁የረመዷን ስጦታ

│❏መጃሊሱ ሸህሪ ረመዷን

ሊሸይኺል ዑሰይሚን
╰─────────────────╯   
🎙የደርሱ አቅራቢ:-
├─┈┈┈
│✑አቡ ዐብዲላህ ኢብኑ ኸይሩ
╰──────────────
╭⧿⧿⛉
├⎙አሁኑኑ ዳውንሎድ በማድረግ │ይጠቀሙ!

┝ለሌሎችም ሼር በማድረግ የአጅሩ │ተቋዳሽ ይሁኑ!
╰───────────
╭╼╺╼╺╼╺╼╺╼ ╺╼╺╼
┢⎘  ለመሰል ስራዎች ይቀላቀላሉን

🖇http://t.me/Yusuf_App1
╰─╼╺╼╺╼╺╼╺╼╺╼╺╼
በተፈጥሮ እንግዳ ቸኮላ ነው በር በር ነው የሚያየው ከመቀመጣቸው ይልቅ ለመሄድ ለመሰናበት ይቸኩላሉ።

ረመዷናችንም እንግዲህ እንዲሁ ነው። እንግዳችን እንደቸኮለ ነው። ነፍሶቻችሁን አንድሱ ፣ ቁርዓን አንብቡ ፣ ጉድለቶቻችሁን ሙሉ ፣ ስግደታችሁን አስረዝሙ ፣ የሱና ሰላትን ስገዱ ፣ ዱዓአችሁንም በማብዛት ፣ ነፍሶቻችሁን በማፃንት የረመዳንን ህይወት ለልባችሁ አድርጉ።

ዛሬ ረመዷን ⑦ ነው።
بسم الله الرحمن الرحيم

{ وَٱلۡعَصۡرِ }
{ إِنَّ ٱلۡإِنسَـٰنَ لَفِی خُسۡرٍ }
{ إِلَّا ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّـٰلِحَـٰتِ وَتَوَاصَوۡا۟ بِٱلۡحَقِّ وَتَوَاصَوۡا۟ بِٱلصَّبۡرِ }
[Surah Al-asr ]


ሰለፎች ተገናኝተው ሲለያዩ ከላይ ያለው ማለትም
Surah Al-asr  አንደኛው  ላንደኛው በየተራ ይቀሩት ነበር ።

ግን ዛሬ ላይ ይህን የሰለፍች መንገድየተረሳ
የተዘነጋ ይመስላል
ከኛ ውስጥ አንዳችን ለጓደኛችን ይህን ሱራ
አስቁመን ብንቀራለት  ስቆብን ሁላ ሊያልፍ ይችላል
አልያም ድምፅ ያምራል ብሎ ያሾፍብናል

ለዚህ ሁሉ ምክንያት ግን👇
1/ ዲናዊ የሆኑ እውቀቶችን ካለመገንዘብ
2/ ለቁርአን ያለን ክብር የወረደ ስለመሆኑ
3/ የቀልባችን መድረቅ
4/ጓደኝነታችን ለአላህ ብሎ የተዋደዱ ከሚባሉት
ውስጥ የማይመደብ እና ለጥቅም የተገናኘን ስለመሆኑ እንዲሁ ለዱኒያዊ አላማ የተገናኝን
       በመሆኑ ነው
ሼር ሼር
ቻናል t.me/tdar_ina_islam ተቀላቀሉ
ይህ ግሩፕ የሸኻችንን ሸኽ ያሲን ሙሳን
ለማሳከም የተከፈተ ነው 
በዚህ በተከበር ወር ከኸይር ስራ ልንሰላች
አይገባም  ይህ እንደ ተራ ነገር ቆጥረነው
scroll አድርገን ልናልፈው ፈፅሞ ተገቢ አይደለም

ተቀላቀሉ 👇👇👇
t.me/+FCoJ8Aqxga1mZmI0
t.me/+FCoJ8Aqxga1mZmI0
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM