This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
እንኳን ደስ አላችሁ!!!
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ በ 2017 ዓ.ም ሲካሄድ በነበረው የባንኮች የእግር ኳስ ውድድር አሸናፊ በመሆን የዋንጫ ባለቤት ሆኗል፡፡
ለመላው የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ማህበረሰብ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እንወዳለን፡፡
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን
#globalbankethiopia #champions #football

የውድድር ዓመቱ ኮኮብ ተጫዋች እና ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ተጨዋች #ማርቆስ_ወልዴ ሆኗል።
Audio
ተወዳጁ አሃዱ ሬዲዮ የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያን የዋንጫ ድል በስፖርት ዘገባው እንዲህ አድርጎ ሸፍኖታል፡፡
ለአዲሱ የቦርድ ሥራ አመራር አባላት የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር ተካሄደ
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አዲስ ለተመረጡ የቦርድ ሥራ አመራር አባላት የእንኳን ደህና መጣችሁ እና ሥራ የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ሰኔ 09 ቀን 2017 ዓ.ም በባንኩ ዋናው መስሪያ ቤት አካሂዷል፡፡
ባንኩ ከዚህ በፊት ይስተዋሉ የነበሩ የአሰራር ክፍተቶችን በማረም እና ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ በማስቀጠል በማይናወጥ የእድገት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው የገለጹት የግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተስፋዬ ቦሩ፤ አዲሶቹ የቦርድ አባላት ከባንኩ የማኔጅመንት አባላት ጋረ በመቀናጀት የባንኩን ራዕይ እውን ማድረግ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
ባንኩን ላለፉት ዓመታት በብቃት በማገልገል እዚህ ደረጃ ላደረሱት የቀድሞ የቦርድ አመራር አባላት ዶ/ር ተስፋዬ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
አዲሶቹ የቦርድ ሥራ አመራር አባላት አቶ ዮሴፍ ጌታቸውን በቦርድ ሰብሳቢነት እንዲሁም ዶ/ር ዮናስ ሀጎስን ምክትል ሰብሳቢ በማድረግ መርጧል።
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ለአዲሶቹ የቦርድ አባላት መልካም የሥራ ጊዜ እንዲሆንላቸው ይመኛል፡፡
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!

ግሎባል ቱር በሽረ እንደስላሴ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ተካሄደ።
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች እና አጠቃላይ የባንኩን ነባራዊ ሁኔታ ለደንበኞቹ የሚያስተዋውቅበት "ግሎባል ቱር" የተሰኘውን መርሃግብር በሽረ እንደስላሴ ከተማ በሚገኘው ቅርንጫፍ በተለያዩ ዝግጅቶች ሰኔ 14 ቀን 2017 ዓ.ም በድምቀት አካሂዷል።
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ ስሙን የሚመጥን አገልግሎት በመላው የሀገራችን ክፍል እየሰጠ መሆኑን በመርሃ ግብሩ ወቅት ባደረጉት ንግግር የገለፁት የኮርፖሬት ባንኪንግ ቺፍ ኦፊሰር አቶ ሳህለሚካኤል መኮንን አዳዲስ የቴክኖሎጅ ግኝቶችን በማካተት ለደንበኞች ምቹ፣ ፈጣንና አስተማማኝ አገልግሎት ለመስጠት በሙሉ አቅም እየሰራን ነው ብለዋል።
በሽረ የተከፈተው ቅርንጫፍ በአካባቢው ማህበረሰብ ዘንድ ተመራጭ የሆነ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን በአፅንኦት የገለፁት ቺፍ ኦፊሰሩ የሚስተካከሉ ክፍተቶች ካሉም በፍጥነት ለማረም ዝግጁ ነን ብለዋል።
የባንኩን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ምን እንደሚመስል የመወያያ ርዕስ ያቀረቡት ደግሞ የደንበኞች ግንኙነት መምሪያ ዳይሬክተር አቶ መሠረት አሰፍ ናቸው።
በቀረበው የመወያያ ርዕስ አስመልክቶ ከንግዱ ማህበረሰብ ለተነሱ አስተያየት እና ጥያቄዎች በባንኩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
የሽረ እንደስላሴ ከተማ ንግድ ም/ቤት ፕሬዘዳንት መምህር ፍስሃ ገብሩ በበኩላቸው ከተማዋ ከፍተኛ የንግድ ማዕከል መሆኗን ገልፀው ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያም የንግድ ማህበረሰቡን በሙሉ አቅም ለማገልገል ወደ ከተማችን ስለመጣችሁ በም/ቤቱ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ወደፊትም ከባንኩ ጋር አብረን ልንሰራባቸው በሚቻል ምቹ ሁኔታዎች ዙሪያ ውይይት ለማድረግ ቢሮው ዝግጁ መሆኑን ፕሬዘዳንቱ ገልፀዋል።
በግሎባል ቱር የተሳተፉ የንግዱ የማህበረሰብ ክፍሎች በበኩላቸው ከባንኩ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በመርሃ ግብሩ የኮርፖሬት ባንኪንግ ቺፍ ኦፊሰር አቶ ሳህለሚካኤል መኮነን፣ የማርኬቲንግ እና ኮምዩኒኬሽንስ ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ፍቃዱ፣ የደንበኞች ግንኙነት መምሪያ ዳይሬክተር አቶ መሠረት አሰፍ፣ የምዕራብ ዲስትሪክት ዳይሬክተር አቶ ሠለሞን ግርማ፣ የሽረእንደስላሴ ከተማ ንግድ ም/ቤት መምህር ፍስሃ ገብሩ እንዲሁም የንግዱ የማህበረሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
ግሎባል ቱር በቀጣይም በተለያዩ ከተሞች እንደሚካሄድ ይጠበቃል።