ብጣሽ ወረቀቶች
208 subscribers
18 photos
2 videos
9 files
10 links
Yohana
ግጥም ለምንወድ ሁላችን
For any comment @eawiiii
Download Telegram
"አቤት" ብሎ ዞረ ከኋላ ድምጽ ሰምቶ
መገረምም መደንበርም ቃጣዉ
ከ ሁለት አመት በፊት የሞተችዉን ፍቅረኛዉን ፊቱ ቆማ እያያት ነዉ።
ምን ማድረግ እንዳለበት ግራ ገባዉ
ደስታም ግርታም ተሰማዉ።
ሮጦ ሄዶ አቀፋት።
"ልጄ..... ወዴት ነዉ 'ምትሮጠዉ"
የሚለዉ የእናቱ ድምጽ ከምናቡ አናጠበዉ^

አቢ
💔2😢1💘1
ምን ይሆን የተሰማት ግን
ገብርኤል ሲያድናት ኢየሉጣን ከእሳት
ልጇስ ቂርቆስ ምን ያህል ቢያምን ነዉ
እሳቱስ ለመግባት እንዲያ የደፈረዉ
የሶስት አመት ጨቅላ እናቱን 'ሚመክረዉ

ታላቁ ትልቅ🔥


በረከታቸዉ ይደርብን


አሜን @eawiiii
39
ብጣሽ ወረቀቶች pinned «ምን ይሆን የተሰማት ግን ገብርኤል ሲያድናት ኢየሉጣን ከእሳት ልጇስ ቂርቆስ ምን ያህል ቢያምን ነዉ እሳቱስ ለመግባት እንዲያ የደፈረዉ የሶስት አመት ጨቅላ እናቱን 'ሚመክረዉ ታላቁ ትልቅ🔥 በረከታቸዉ ይደርብን አሜን @eawiiii»
ሁሉም ያማርራል
ሁሉም ይማረራል
ሀገር እሱ መሆኑን
ዘንግቶ ነዉ መሰል
"የዚች ሀገር ነገር"
እያለ ይዉላል!

የሀገሬ ጉልበት ግን ጥንካሬዉ

@eawiiii
4
አንድ ጸጉሩ ጨበሬ የሆነ ልጅ "normal" ቁርጥ ከተቆረጠ ጓደኛዉ ጋር ፊት ለፊቴ ካለዉ "hotel" በር ላይ ቆመዉ እያወሩ ነዉ። አስተናጋጆች መሰሉኝ፡ትንሽ ቆይቶ ሶስት ሴቶች በጎናቸዉ አለፉ ጨበሬዉ ልጅ ድምጹን ጮክ አድርጎ "አንቺ" ? ብሎ ሲጣራ ሶስቱም ዞረዉ አዩትና መንገዳቸዉን ቀጠሉ።ጨበሬዉ ልጅ ወደ ጓደኛዉ ዞሮ ከልቡ የደስታ ሳቅ።ምን እንደሆነ አልገባኝም።ለከፋም መሰለኝ መገመት አቃተኝ።ይባስ ብሎ "hotel" ከተከፈተዉ ሙዚቃ ጋር መዝለል ጀመረ፡ጓደኛዉም ተከተለዉ ወዲያዉ ደግሞ አቆሙ። ሳቁ ግን አልቆመም፡ይነጋገሩና ደሞ ይስቃሉ።
ፍቅር ወይስ እብደት?
እኝዳይጋባብኝ ፈርቼ አይኔን ነቀልኩ።
ምኑን እንደፈራዉ ባላቅም
ፍቅሩን ወይስ ዕብደቱን??
ከ'ነሱ የተወሰነ እርምጃ ራቅ ብሎ ደግሞ አጠር ያለ እድሜዉ 35 የሚገመት ሰዉዬ የሴት መቀመጫ ያያል።አይኑን ከልጅቷ ሳይነቅል አስተናጋጁን ጠርቶ ማዉራት ጀመረ።ምን ውስጥ ነዉ ያለሁት በስመ አብ አሁን መሮጥ ነዉ ያለብኝ🏃‍♂️ ሆ...።

ምን ማድረግ እንዳለብን አይደለም
ምን እንደሆንን 'ራሱ አናዉቅም!

Real ትዝብት

አቢ @eawiiii
12:19 ግብተ ጸሀይ በኋላ
🔥3
Check out our TikTok Account

tiktok.com/@btashwereqet
🔥1
ብጣሽ ወረቀቶች pinned «Check out our TikTok Account tiktok.com/@btashwereqet»
ዛፉ ለሰው ወንዙ ለሰው
ተራራዉ ለሰው እንስሳዉ ለሰው
አየሩ ለሰው ውሀው ለሰው
የምድሩ ለሰው የሰማዩም ለሰው
የሰዉ ለሰው የአምላኩ ለሰው
ይሄ ሁሉ ሆኖ የሰው
እንዴት ያቅተዋል ለራሱ መሆን ሰው

Yohans
🔥6
ብጣሽ ወረቀቶች
Video
https://vm.tiktok.com/ZS4k1oR6M/ This post is shared via TikTok Lite. Download TikTok Lite to enjoy more posts: https://www.tiktok.com/tiktoklite
🔥3
ሰንበት ክቡር

እንኳን አደረሳቹ🙏
🙏3
ብንሰለቻችም ልብ ለልብ ብንራራቅ
ብንጎነታተልም እርስ በእርስ ብንናናቅ
እሁድ እሁድ ብቻ እንታረቅ


8:37 PM አቢ
🤔31
የማይሆን እየሆነ
የሚሆን የማይሆነው
የማይደረግ የሚያደርግ
የሚደረግ የማያደርግ
ሰው ያልሆነ ሰው ስላለ ነው

ሰው!?

Yohans
🔥4
በማሰብ ነገ እንደሚኖር
የነገን ዛሬ እንደመቅበር
የለም ቅስም የሚሰብር
አይታወቅ እንጂ ዛሬን ሲኖር

ዮሀንስ
6👏1