ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.83K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
እንዴትም
----------
እንዴት ናችሁ ላላችሁን
አለን አንደምጥ ስቀን
በማይለቅ ጉንፋን ታፍነን
የማያልቅ ንፍጥ ተናፍጠን
የማያልቅ ነፍጥ ተናፍጠን
ወደራሳችን ደግነን
...
እንዴት ናችሁ ላላችሁ
እንዴት እንመልስላችሁ
'አለን' ለማለት ፈርተን
ያለን መስሎን የሌለን
የሌለን መስሎን አለን
አይባል ነገር ለሰው
አንዴት ናችሁም ያሉን
መቼም ያለን መስለን ነው
...ምን ሊውጠን ልንል ስንል
ምን ልንውጥ ነው 'ምንል
ምኑን እንዴት ነህ ይባላል
ሊጥ መጥለቂያ የራስ ቅል

ሰይፈ ተማም 2009
#ሰይፈተማም #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ
Forwarded from Getz_mag
Forwarded from Events Ethiopia (Events Ethiopia Bot 🤖)
Much Needed Conversations - Art vs. Artist
📅 Sunday October 11, 2020 at 7 PM
📍 IG Live
🙏 @KeTsenat

Join us this week as we discuss Art vs. Artist - should we differentiate between the two?

@ketsenatmagazine
@eventsethiopia
ጀንበር ሳትጠልቅ

እንባ ስታቀሪ፣
በሰቆቃ ስትሞሸሪ፣
ሰላም እየጠማሽ ፣
ባለመኖር መኖር እየተቆራመድሽ፣
አለሁኝ አትበይኝ
ቆፈን ሲገርፍሽ፣
ጠኔ ሲፈጅሽ፣
የነፃነት አየር አጥቢያ ምትናፍቂ፣
በዛሬ ውጥን
ኦና አልባ መንገድ ላይ የምትሳቀቂ፣
ታድያ ለምንድን ነው ?
ደህና ነኝ እያልሽኝ ወሬ የምትሰብቂ፣
መአልቱ ሌሊቱ
እንደ ሰጋር ፈረስ እየነጎደ፣
ጎህ ይቀዳል አትበይ
በፅልመት ተውጧል እየተራመደ።
ህመምሽ ህመሜ
በደሙ ጠበል እያጠመቀኝ፣
ምድር ቆቧን ሳ'ጥል
መለኮት በመጣ ቅኔውን እንዲቀኝ።

ሀብታሙ ፍቃዴ (የጁ)

#ሀብታሙ_ፍቃዴ #ግጥምሲጥም
ዕድሜ ለጨረቃ

የቀትሯ ፅሃይ ግዜዋን ጠብቃ
ምሽጓን ስትመሽግ ከኔ ተደብቃ
አዕዋፍ ጥለውኝ ጎጇቸው ሲሰፍሩ
ሰዎች በየቤቱ
በሳቅ በጨዋታ ፈንድቀው ሲዳሩ

ብኩኑ ብቸኛው 'የት ደረስክ' የሚለኝ
ጠያቂ የሌለኝ
ብቻየን ወጥቼ በሀሳብ ዋትቼ
ሳልተኛ ተኝቼ በህልም አለም ሞቼ
በብርድ ስንሰፈሰፍ በውርጭ ስንቃቃ
ዕድሜ ለጨረቃ
ከሰዎች ተሽላ መጣች ተደብቃ

የሀሳብ ባትሞላም አብልታ አጠጥታ
ጭንቀትን ተጋርታ
ዕድሜ ለጨረቃ
ስቃ አሳሳቀችኝ ብርሀንን ዘርግታ።

#ዮሃንስ_ጋሻው #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ
1. አንድ ሰው ፈጣሪውን የማይፈራ
2. ሰውን የማያፍር (ህሊናው የማይከብደው)
3. ህግን የማያከብርና፤ቢያጠፋ እንኳን ከህግ ተጠያቂነት ሊያመልጥ የሚችልበት መንገድ እንዳለ የሚያስብ ከሆነ።
ወዳጄ #አጥፍቶ_ጠፊ ነው ይህ ሰው!
ማናችንንም ከነዚህ ገመዶች አንዱ ነው፤ ከጥፋት መንገድ መልሶ የያዘን። እዚ ምድር ላይ እኚህ #ሶስቱ_ገመዶች የተበጠሱበት ሰው፤ እጅግ አደገኛ #ፍረት_ነው ሚሆነው። ማለቴ እራሱ ላይ እንኳን ሳይቀር በቀላሉ አደጋ ሊጥል ይችላል ይህ አይነት ሰው። እኔ ቢያንስ አንዱ እንደቀረው እርግጠኛ ካልሆንኩት ሰው ጋር በምንም ተአምር አብሬ ለመስራት ፍቃደኛ አይደለሁም። ከመቃብር በላይ፤ በህያዋን አለም ስትኖር ከሰዎች ጋር ከሶስቱ በአንዱ ገመድ ነው ልትተሳሰርና ልትግባባ የምትችለው። በአንድ አጋጣሚ ማንነቱ እስኪገለጥ እንጂ፤ እኚ ሶስቱን በጥሶ ሚኖር ሰው ፤ #ሁኔታና #ስፖንሰር_ያጣ_አጥፍቶ_ጠፊ_ነው። ሰው #ሃይማኖቱ፣ብሄሩ፣የኑሮው ሁኔታ፣የትምህርት ደረጃው ምንም ይሁን ፈጣሪውን የማይፈራ፣ህሊናውን የማያፍር፣ህግን የማያከብር ከሆነ፤ ዳግመኛ ሊያገናኛችሁ የሚችል ነገር ከዚህ ሰው ጋር ፈጽሞ አይስፈልግም። ለዚ ምስኪን ሰው #ስጦታ እንጂ #ብድር እንዳትሰጡት፤ እናንተም እንዳትበደሩት ተጠንቀቁ። #አላህን_ፍራ/ #ስለ_እግዚአብሄር፣ በህግ አምላክ አልያም ለዘመድ ወዳጆችህ እነግርብሃለሁ የማይባል ሰው #በጣም_አደገኛ_ፍጥረት ነው። #ከኖራችሁ_አይቀር ከቻላችሁ ሶስቱም ገመድ ይኑራችሁ፤ ካልሆነ ግን #ቢያንስ አንዱን አስቀሩ። እኚ ሶስቱ ከተበጠሱብህ ግን #በአራዊትና በሰው መሃል ያለውን ልዩነት ነው በሂደት እያጣህ ምትሄደው። እንደ ተቋም፤ የሞቱና በከባድ የህይወት ልምምድ ውስጥ አልፈው የደነዘዙ ህሊናዎችን የማነቃቃት ስራ በትውልድ መሃል እንሰራለን።
Forwarded from Jafer Books 📚 (Zee - Se)
የመጻሕፍት ሕብረ - ቀለም ::
Forwarded from Esubalew Abera N.
ትዝታሽን_ለእኔ፣_ትዝታዬ_ለአንቺ_ኂሳዊ_ንባብ_በማርቆስ_ዘመንበረ_ልዑል.pdf
1.6 MB
ትዝታሽን ለእኔ፣ ትዝታዬ ለአንቺ ኂሳዊ ንባብ በማርቆስ ዘመንበረ ልዑል
ያ ዕድሜ ላይ

ሰው በተሰበሰበበት
ወይን ጭስ ጨዋታ
ዳንስ ሴት እስክስታ
ዳንኪራ ሁካታ ቡንቧታ
ግርግር ጫጫታ ነገር
ማኪያቶ የቆንጆ ሴት ከንፈር ሲቀራርብ
ተፈለኩ ብዬ
ሰው ጠራኝ ብዬ
ራሴን ገፍትሬ
ራሴን ቀጥሬ
ወደ ቤቴ ምበር
ጫማዬን ከበሬ የ ምወረውር
ከአልጋዬ ትራሴ ስር
ቀዝቃዛ ሙዚቃ ነገር
ከፍቼ ከራሴ ሃሳብ የምቀበር ።
(ያ ዕድሜ ላይ ። )
____
ሰው ሁሉ ጓጉቶ
መንገድ ጉዞ ተዘጋጅቶ
ስንቅ ተዘጋጅቶ
ጠጅ ተይዞ
ቆሎ ተይዞ
ባጋጣሚ ምክነያት
ባለቀ ሰዓት
ጉዞ ተሰርዟል !! ሲባል
ፈገግ የሚያስብለኝ

(ያ ዕድሜ ላይ )
....
ብዙ የፈረሱ ህልሞች _ ከአመድ የገቡ
ከምስጥ ጉድጓድ የጠበቡ
ሰው እየቀነስኩ
ሰው እየቀነሰኝ
አነስኩ ስል ገዝፌ የምገኝ ____( ያ ዕድሜ ላይ )

_
ሴት ቀጥሬ
ከወንበሬ ስትደርስ _ ተነስቼ ስሜ
ከወጠራት ልብስ _ዳሌ
ይልቅ ህልሟ የሚስበኝ
(ያ ዕድሜ ላይ )

ትርጉም በሌላት ዓለም _ ትርጉም የምፈልግ
የክብ ጉዞ የምስብ
ጠፍቼ _ስለመገኘት_ የማስብ
(ያ ዕድሜ ላይ )
_
የሲሲፈስን ርግማን _ኑሮዬ አርጌ የተቀበልኩ
ለራሴው እርድ _ ቢላ ስዬ ያቀረብኩ
በሞቱት የምቀና መኖር የሚያስፈራኝ
_
(ያ ዕድሜ ላይ )
_
ብናኝ መሆኔ የገባኝ
አዋራ መሆኔ የገባኝ
'አውራ ነኝ' የምል
__
ከመሞት ይልቅ
መኖር የሚያስፈራኝ
ሰው ያረገው የሚያስጠላኝ
ራሴው ያደረኩት የሚያስጠላኝ
በትልቁ ተጋድሜ
ትንሹ ነገር የሚያስፈራኝ
_
(ያ ዕድሜ ላይ )
_
የራሴን ህይወት ማሳመር ባልችል
ለማበላሸት የማላንስ
(ካደረኩት ይልቅ
የማደርገው የሚያጓጓኝ
የማያጓጓኝ
ይቅር እንዴ ?
ላርገው እንዴ ?
ልሂድ እንዴ ?
ልምጣ እንዴ ?
ላግባ እንዴ ?
ልውለድ እንዴ ?
ልሙት እንዴ ?
የሚያስብለኝ የማያስብለኝ
(ያ ዕድሜ ላይ )

1ዱ ጌታቸው

#1ዱ #ግጥምሲጥም #ግጥማዊቅዳሜ