ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.8K subscribers
847 photos
55 videos
20 files
397 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
Forwarded from Events Ethiopia (Events Ethiopia Bot 🤖)
The Africa Energy Generation Prize
📅 September 15, 2020
📍 Online
🙏 Events

#AEGP2020

https://en.energy-generation.org/aegp2020


Applications are open until September 15th

The Africa Energy Generation Prize aims to reward young African talents who have an innovative  project  or idea  in the energy, health or agribusiness sectors.

The proposed projects must promote, in these sectors, access to essential services for as many people as possible with the potential of having a concrete impact on the socio-economic development of the
continent.
@eventsethiopia
'ቃሌ ይሁን እዳዬ'

ችግኝ ብቻ አይደም
ቃሌንም ተክላለው
በለም አፈርሽ ላይ በአረንጓዴ
ቀለም ህይወት ከትባለው
ሊጠፋ የማይችል የነገ ተስፋዬን
ምድርሽ ላይ አሰፍራለው
እመኝኝ እማማ መውደዴን
ለመግለፅ ቃላት ባልደረድር
ስላ'ንቺ ለማዜም ባልጫወት ክራር
የሠራሁት ባይኖር ስምሽን
ለማስጠራት
ባንዲራሽን ይዤ ባላውለበልብም
ከተራራሽ አናት
እህ ብለሽ ስሚኝ ስላለፈው
ሳይሆን ስለ አሁኔ ላውራሽ
እንደ አክሱም የሚቆም
ዘመን የማይሽረው
እንደ ላሊበላ እልፍ የሚጎበኘው
እንደ ፋሲሉ ግንብ ታሪክን ነጋሪ
ነበርን አስታዋሽ ያለፈን ዘካሪ
እንደ አባ ጅፋር እንደ ውቡ ቤትሽ
በየሀገሩ እንዳሉ የታሪክ ቅርሶችሽ
ተቀማጭ የሚሆን የሚችል
ሊያስጠራኝ
እኔም ከቃሌ ጋር እተክላለው
ችግኝ
እናማ እማማዬ
ከባንዲራሽ አናት በአሀዱ ቀለም
ትርጉም በሚሠጠው በቃላት
ሲሰየም
ደምቆ በሚታየው በዛ ውበት አዘል
ከማሪያም መቀነት ከቀለማት
መሀል
በአረንጓዴ ቀለም በጥቁር ሸራሽ
ላይ
አሻራዬ ያርፋል ለትውልድ የሚቆይ
በጥቁሩ ሸራሽ ላይ ሲከትም
ቀለሜ
በምተክለው ችግኝ ይሰየማል ስሜ
ግና......
የምተክለው ችግኝ እልፍ አእላፍ
ሆኖ ከየትም ቢበቅልም
ባብቃዩ በእኔ እንጂ በሌላ
አይጠራም
ስለዚህ አበባዬ እናት ሀገር ቤቴ
ልክ እንደ ችግኜ የትም ተተክዬ
ከየትም ብበቅልም
ካ'ንድ አንቺ በስተቀር
ከጦቢያዬ ሌላ መጠሪያ የለኝም
ለምልሚልኝ እማ አንቺን ለማለምለም ምክንያት አያሻኝም
መጠሪያ ከሆንሽኝ ስምሽን
ካገኘሁኝ ሌላን አልፈልግም
እና....እንደነገርኩሽ
ከቃሌ ጋር እንጂ ከቃሌ ለይቼ
ችግኜን አልተክልም
ለምን ያልሽኝ እንደው
ምናልባት ተስቶኝ ችግኜን ብረሳም
ቃሌ እዳ ሆኖ ከቶ አይፈቅድልኝም
ፀንቶ ለመቆየት ከሱ የተሻለ
ማሰሪያ አላገኝም
ስሚኝ እናት አለም
በእምነት ካ'ንቺ እንድቆይ ችግኜን
ተክዬ
ቃሌም አብሮ ይተከል እንዲሆን
እዳዬ።።


(ሸዊት ሂርጶ)
#ሸዊት_ሂርጶ #ግጥምሲጥም #አረንጓዴስነግጥም #አረንጓዴአሻራ
_ ሶስትነት _

ፍቅሬ አንቺ ማለት
በንፁህ ሴትነት
የገለፅሽልኝ
ታላቁን ቅኔ፣ የውሃን ሶስትነት
የሶስቱን አንድነት።

ፈሳሽ ፣ ተን (አየር)፣ በረዶ ።

እውነቴን ነው ምልሽ ....
ውዴ በየቅስፈታቱ ፣ እስትንፋሴ ሚፈልግሽ
ጊዜ፡ ሁኔታ፡ ቦታ ፣ሁሉ የማይገድቡሽ
የውሃው አየር ነሽ ።

የፍቅሬን ፣ የእምነት ተክል
ለምልሞ እንዲበቅል
የቃልሽ ፈሳሽ ውሃነት ነው
ልቤን የሚያጠጣ፣ እንደህይወት ፀበል።

ናፍቆት ንሮ ንሮ
ነፍስ-ተስጋ እስኪያቃጥል
አንቺን በመቃተት፣ ሰውነቴ ሲግል
ብቸኝነት ሲያነድ፣ ሀሳቤን እስኪያዝል።
መምጣትሽ ዝናቡ፣ሁሌም ሰላም ያለው
ፍቅርን ስትሰጪ፣የሚያቀዘቅው
ያይኖችሽ እርጋታ፣
በረዶነትሽ ነበር፣ ሚነጥቀኝ ከቃጠሎው።

እውነቴን ነው ምልሽ ....
በረዶ ነበርሽ ድሮ፣ ጠንካራ ምትጨበጭ
አሁን እንደ ፈሳሹ፣ ሳትጨበጭ ምትገለጭ
ልቤ የማይከለክልሽ፣ ተን ሆነሽ ስትቀመጭ
ደስታ ማገኝብሽ ፣ ምናብ ሆንሽ ስትቀመጭ ።
እውነቴን ነው ምልሽ ....
ውዴ አንቺ ማለት
#ምናብ (ተን) የሆንሽ
የፍቅርን ስም የማታረክሽ
ፈሳሽ ፣ ተን ፣ በረዶ
በእውነትና በአለም ፣ ማገዶ
የምትሆኝ
አንዳድጊዜ ፈሳሽ ፣ አንዳንዴ በረዶ ።
_~\\~_____
ተን ፣ አየር ፣ ምናብ ... አንድ አርጌ ተጠቅሜዋለው ።
ውሃ በ3 ሁነት ሊገኝ የሚችል ልዩ ውህድ ነው ።
( ሮቤል .ታ )

#ሮቤል_ታ #ግጥምሲጥም #አረንጓዴስነግጥም #አረንጓዴአሻራ
ነገን ዛሬ እንትከል!

ዛሬ ህይወት ነገ ተስፋ
ምርጫ እያለ ከንቱ አይጥፋ!
ዛፍማ
ንፁህ እስትንፋስ ሰጥቶ
ጉልበት አበርትቶ
ሀሩርን መክቶ
ደመና ጎትቶ
ምድርን ይታደጋል፣ ድርሻውን ለይቶ።
እኛስ
ለህይወት ሳንራራ
ጥፋትን ስንሰራ
ጨርሶ ሲያመራ
ወደ እልቂት መከራ
ደርሰን አማራሪ፣ ቅጣት የምንፈራ።
በዚህ ድርቅ ሮሮ
ከጅ ወደአፍ ኑሮ
ክረምቱን አዛብተን
ወንዝ ጎርፍ ሞልተን
መከራ እየጠራን፣ እንዲሁ እናልቃለን።
ስለዚህ
ጠግበን እንድንበላ
መሬት አይከላ
ተፈጥሮን አናርክስ
በረከት እንድንቀምስ።
ትውልድን እናስብ
እጃችን ይሰብሰብ
ለጠፋው እርማት
ተስፋንም ለመዝራት
ዘብ መቆም ግድ ይላል፣ ሁሉም በያለበት።
ችግኞች እንተካ ሃይላችን ይሰብሰብ
ተሸናፊ አይኖርም ዘላቂ በማሰብ +
+
ከጥንት የወረስናት እያልን ስንመካ
የትውልድ ድርሻም መሆኗ ነው ለካ!
“ We didn’t inherit this land from our Ancestors,
Rather borrowed it from our children!“
ዮሐንስ ታደመ

#ዮሐንስ_ታደመ #ግጥምሲጥም #አረንጓዴስነግጥም #አረንጓዴአሻራ
መኖርህ ኖሯል ለመኖሬ በዕዝራ

የታላቅነት ትርጉሙ የገባህ
የትዕግስት ሊቅነት የተረዳህ
ፍጥረት ማስተማሪያ አንት እኮ ድንቅ ነህ
ከምድር ውስጥ ወጥተህ እንጣጥ ሳትል አድገህ
ጊዜህን ተጠቅመህ
ተፈጥሮን ታሳያለህ
ህይወት ነህ መድኃኒት
ምግብ ነህ ውበት
ቀለም ነህ መዓዛ
መች ይነገራል ጥቅምህ እንደዋዛ
የ'ለት እንጀራ ስጠን
ብለን ስንለምን
ዘንግተነው ከቶእንደምንኖር ተንፍሰን
ላፍታ ሳናስበው ከቶውኑ ረስተንተ
ለሆዳችን ለመንን ሳንባችንን ትተን
አየር እንደመዳብ ምግብን እንደወርቅ
ነው ብለን ስናረቅ
ኋላ የጠፋ እንደው ተመን የለው አየር

ትንፋሼ ትንፋሹ ፣ ትንፋሹ ትንፋሼ
የተፈጥሮን ቀመር ሀ ብሎ መፍቻዬ
ስረዳው የገባኝ ሆነልኝ ቁልፌዬ

ንቀን ኡፍ ያልነውን
ምን ያረጋል ብለን
እርሱ ግን ዘረቶበት ህይወትን ለነፍሱ
እንካችሁ ይለናል እናንተም ተንፍሱ

ሰይፈ በአማርኛ መፃፍ ግን ዝገት ነው
እቺን ዲሊት አድርገው

ከቃለት በላይ ነህ ላቅ ያልክ ስጦታ
ከፈጣሪ ቀጥሎ በትንፋሽ ነፍስ የምትዘራ
አንድ አንተ ብቻ ነህ የምትኖር በዝምታ
አኖርኩ ብለህ የማት ኮራ

እንደነገረኛ
እኔ ስኖር አይደል እሱስ መኖሩ
ትንፋሽ ባላወጣ ምን ይውጠው ነበር
ፍጥረት ባይሞት ባይፀዳዳ ምን ይበላ ነበር
እንደነገሩ
Newton እና ያሬድ ውለታህ አለባቸው
ፍሬህን ባትጥቸል ትሏ ባትንጠላጠልህ
ከየትስ ሊያመጡት እንዴት አባታቸው

ቁምነገሩ
ትልቅ ነው ሚስጥሩ
አለም እንዴት ሰረች በጥልቅ ማስተማሩ
እኔነትን ትቶ አንድ ላይ ካደሩ
መናበብ ከቻሉ አንድ ላይ ካበሩ
ሁሉም ይገለፃል ድንጋዩን ካፈሩ

ለነገሩ
ላውራ ቢል ማን ሊያዳምጠው
አኖርኩህ ቢል ማን ሊያምነው

ግን አፍ ቢኖረው እንዲህ የሚል ይመስለኛል
ዝረኝ አየር ልዝራ
አብላኝ እንዳበላህ
አጠጣኝ እንደለማ
ቁረጠኝ እንዳስጠልልህ
አቃጥለኝ እነዳሞቅህ
ፍጨኝ እነዳክምህ
ፍለጠኝ፣ቀንጥሰኝ፣ላጠኝ፣ገነጣጥለኝ
ተንፍስልኝ ልተንፍስልህ
አኑረኝ ላኑርህ
ልሁን ላንተ የእድሜህ ልክ ባርያህ

#ዕዝራ #ግጥምሲጥም #አረንጓዴስነግጥም #አረንጓዴአሻራ
ብዙ reaction ያገኙ ተወዳዳሪዎችን የምንመርጥ ሲሆን ድምጽ የመስጫው ጊዜ የሚያበቃበትን ቀን ከማሳወቃችን በፊት የግጥም ቤተሰቡን በመጋበዝ እነዚህን ጽሁፎች እንጋራ ለወደድነውም ድጋፋችንን እናሳይ!
🤫ሽልማቱ ምን እንደሆነ እስካሁን አልተነገረም። ብቻ ግን ብዙ ነው!
Forwarded from Tibeb Be Adebabay-TBA
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Tibeb be adebabay 2020 Digital Art Festival:

brought to you by a dedicated team of 11 Partners, 10 Art Groups, 64 Artists and a dedicated project management team.

Thank you all for making this unique digital art festival come true and we hope it inspires many!

#Challenges and #Prizes coming your way, stay tuned!

Find our pages and channels:
Facebook Page: https://www.facebook.com/Tibeb2020
Telegram: t.me/Tibeb_Be_Adebabay
Instagram: instagram.com/tibeb_be_adebaba_2020/
Twitter: twitter.com/TibebBe
Youtube: youtube.com/channel/UCmvDcNWiv8oNpzL7elz1fag/featured
Website: http://tibebbeadebabay.org
Find out more: tibebbeadebabayethio@gmail.com
or
+251983320317

#tibebbeadebabay2020 #digitalArt #artfestival #digitalartfestival #artinaddis #tba
Forwarded from LinkUp Addis
AWiB will host its monthly event series on 03 August 2020 at Hilton Hotel. The event will be titled Arts: Film and the Ethiopian Culture. To register go to: https://bit.ly/2Qma0UM @linkupaddis
Forwarded from Tibeb Be Adebabay-TBA
Meet Chewata Awaqi - ጨዋታ አዋቂ if you haven't already!

They have prepared something special for Tibeb be Adebabay 2020 online art festival.

They will bring you first-ever Alternate Reality Game (ARG), a 360' interactive networked narrative that uses the real world as a platform and employs trans-media storytelling to deliver a story that may be altered by players' ideas or actions. This 360' interactive experience will run on all platforms (analog, digital, and physical) and will use all existing channels (website, Facebook, YouTube, telegram, zoom, voice and text messages).

Get ready and stay tuned!

Facebook Page: https://www.facebook.com/Tibeb2020
Telegram: t.me/Tibeb_Be_Adebabay
Instagram: instagram.com/tibeb_be_adebaba_2020/
Twitter: twitter.com/TibebBe
Youtube: youtube.com/channel/UCmvDcNWiv8oNpzL7elz1fag/featured
Website: http://tibebbeadebabay.org

#tibebbeadebabay #digitalart #digitalartfestival #artinaddis #tba
ዛሬን ልስጣት

ዛሬውን ተነፍጎ ሕልሙን ለተቀማ

ቁራሽ ለተራበው ፍቅርን ለተጠማ

ግዜ ስለት ወግቶት እድሜውን ላደማ

ለዛ ምስኪን ወጣት ስለ ተስፋ ላውጋው

የፀለመ አለሙን በፈገግታ ላንጋው

መውደድ ልመፅውተው በልቤ ልጠጋው

ሴትነቷ ከሽፎ ለነተበ ትልሟ

ገላዋን ቸርችራ ለተረፋት አፅሟ

በረንዳ ላሰሰው ብርድ ለገረፈው

ጠኔ ላስጨነቀው ምቾት ለወረፈው

ኗሪ ላሽሟጠጠው ሂያጁ ለዘረፈው

ለሆዷ ጥያቄ ለጠፋባት መልሷ

ስጋዋ ለጎዳት ላሰቃያት ነፍሷ

ብቻዋን ላለችው ለተበዳይ ወጣት

ፍቅር ለታረዘች መገፋት ለቀጣት

ትላንትን ቢያቅተኝ እስቲ ዛሬን ልጣት

ውርጭ ላበደነው በሀሩር ለተቆላ

በእናት በአባት ናፍቆት መኖሩን ለጠላ

እፍኝ ቆሎ አጥቶ ፍዳውን ለበላ

ልጅነት ለራቀው ለተጎዳው ጨቅላ

ሰው ሆኜ ሰው ላርገው

ትላንቱን ባልመልስ ዛሬን ልታደገው

ሁለት እጅ የሆነው

በአንዱ ለመቀበል በአንዱ ለመስጠት ነው።

ተፃፈ በማርስ መላው

#ማርስ_መላው #ግጥምሲጥም
'እኔ ማን ነኝ?' የሚለውን ጥያቄ ለራሳችሁ ጠይቁና በአንድ ቃል ወይም ሐረግ ብቻ መልሱን አቀብሉን። በአዲሱ አደባባይ በኢንተርኔት አማካኝነት በሚካሄደው የዚህ አመት የ ጥበብ በአደባባይ ኦንላይን ፌስቲቫል ላይ መልሳችሁን ግጥማችን ውስጥ ተካትቶ ታገኙታላችሁ።

መልሳችሁን ከስር ባለው
Show Comments በሚለው ቁልፍ በጽሁፍ አድርሱን ወይም እራሳችሁን በቪድዮ በመቅረጽ መልሱን ብቻ በመናገር #ግጥምሲጥም ብላችሁ በማንኛውም የማህበራዊ ሚድያ በኩል አጋሩን።

ማን ነሽ? - ማን ነህ? - ማን ናችሁ?

በአንድ ቃል ወይም ሐረግ ብቻ በመመለስ ቃልና ሃሳብ አቀብሉን - አብረን ግጥም እንጻፍ። ምናልባትም ብዙ ሰው በማሳተፍ ቀዳሚው የሚሆን ግጥም አብረን እንፈጥር ይሆናል።

ተመስገኑልን!

#ግጥምሲጥም #ጥበብበአደባባይ #ስነ_ግጥም #ሙዚቃ #gitemsitem #tibebbeadebabay #poetry #music #Yisaacandfriends #digitalartfestival #artinaddis #tba

http://tibebbeadebabay.org/
Forwarded from Tibeb Be Adebabay-TBA
Meet Echoing Cities, if you haven't
already!

A collective founded by young enthusiastic architects who are alumni of EiABC, led by Bemnet Demissie and Yasmin Abdu. Having come a long way with #TibebBeAdebabay since its inception.

They have a creative project planned for you and to be implemented with you.

Stay tuned and join the creative community.

Facebook Page: https://www.facebook.com/Tibeb2020
Twitter: twitter.com/TibebBe
YouTube: youtube.com/channel/UCmvDcNWiv8oNpzL7elz1fag/featured
Website: http://tibebbeadebabay.org

#tibebbeadebabay #digitalart #digitalartfestival #artinaddis #tba
Forwarded from Events Ethiopia (Events Ethiopia Bot 🤖)
ኑ ጭቃ እናቡካ vertual art camp
📅 Sep 15, 2020
📍 🌐 Zoom and Telegram
🙏 Josh

"ኑ ጭቃ እናቡካ በቤትዎ "
ልጆችዎን ሲያስመዘገቡ ለትምህርቱ አስፈላጊ የሆኑ ልዩ ልዩ ቁሶችን ለልጆችዎ ይወስዳሉ። ትምህርቱ online ቢሆንም አሳታፊ እና ሙሉ ብሙሉ ተግባራዊ ነዉ።
አድራሻ :22 ድንበሯ አካባቢ
።።። ።። 0911659487 / 0911447443
@eventsethiopia
Forwarded from Tibeb Be Adebabay-TBA
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
WHO AM I

Everything is constantly moving, constantly changing. Through all this movement who we are and become is constantly altered. Our culture and lifestyle, the plants and animals, the cars and the buildings, our food and drinks and our artistic expressions of all these are always moving and changing.

TELLING MIGRATING STORIES

Tell your story, tell our migrating stories through your #art and #creativity.

Follow us:

Facebook Page: https://www.facebook.com/Tibeb2020

Twitter: twitter.com/TibebBe

YouTube: youtube.com/channel/UCmvDcNWiv8oNpzL7elz1fag/featured

Website: http://tibebbeadebabay.org

#tibebbeadebabay #digitalart #digitalartfestival