ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.8K subscribers
847 photos
55 videos
20 files
397 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
ስቆሽሽ በጊዜ እንቅልፍ የጣላችሁ
ምነው ዛሬ ደርሶ ፊንፊን ያላችሁ
ነገ ዛሬ
ዛሬ ሲቻል ለነገ አልኩ
ነገም ደርሶ ነገን አከልኩ
ከነገወዲያም ደሞ መቶ
ነገ ሊባል ሰበብ ሞልቶ
ነገ ሲባል ተጎትቶ
በነ ነገ ነገር ተወግቶ
ባንዱ ነገ ውስጥ ተካቶ
እቅድ ተገኘ ሞቶ
እምጽ አምጵጽ
#seifetemam
ግጥም ሲጥም:
ቀና ልብ
ያልቀጠረውን ሰው ናፍቆ የሚጠብቅ
በውድቅት ለሊት ጨረቃን የሚሞቅ
ካለም ብርሃናት ላይ ወዳጁን የሚስል
በወደደው መጠን መውደዱን 'ሚያክል
በደም እና በ'ምነት በተስፋ የጸና
ልብስ ይኸውልሽ በፍቅር የቀና
#seifetemam
እውነቱን ልንገርሽ
(በ ሰይፈ ተማም)
እውነቱን ልንገርሽ
ከራሴ አስበልጬ አንቺን የምወደው
እያለሽ ናፋቂ
እየሄድሽ አድናቂ
ተራግመሽ መራቂ
ልቤን ብጠላ ነው
እውነቱን ልንገርሽ
ከራሴ አስበልጬ አንቺን እምወድሽ
ከፋት ብሎ ሚያምጥ
ሳቀች ብሎ ሚያገጥ
ኖረሽ የማይወዛ
ሄደሽ የማይከሳ
ሆኜ ብገኝልሽ
አንቺን የምወደው አብልጬ ከራሴ
አይንሽን ለማየት ጨረር እማይፈራ
አለሽበት ሊደርስ መንገድ ሚሰራ
ጣትሽን ለመንካት ጣቱን ሚሰዋ
ቃልሽን ለመስማት መናኝ እስከ ህዋ
የሆነው አካሌን ብትጠላው ነፍሴ
ከማንም አብልጬ አንቺን የወደድኩኝ
የወደድሽው ሁሉ...
በፍቅር አሳቦ
ቅናትን ሰብስቦ
ቢያስጨንቀኝ ከቦ
(አንቺን ከማስበለጥ) አማራጭ አጣሁኝ
ህዳር ፳፬፣ ፪፼፯ ዓም
#seifetemam
ወዳጄ
ጠጥቶ ጠጥቶ ጠጥቶ
ውሃም ይሁን ጠላ ተግቶ ተግቶ
ግድግዳ ይጠጋል
አጥር ይደገፋል ጀርባ ለሰው ሰጥቶ
አጥር ስር ማስለቀስ ህቅም እንኳን ሳይለው
ሊከልል ይጥራል
የሰውነቱ አካል ሆኖበት ማፈሪያው

(ጋሼ Seife ...አስለቃሽህ ወዳጅህን ጠምጄዋለሁ ዛሬ)
የጌታነህ ልጅ
ሐምሌ 22, 2009
ያልቃሽ አዋጅ

በዚህ ፊት አምላኪ በበዛበት አለም

ፊት እንደመቧጠጥ ታላቅ ግድፈት የለም
#ፍሰሃ
እጅ-አዙር
አዬ አጤው ቴዎድሮስ እጅግ ተታለለ
በነጭ መያዝን ውርደት እንዳላለ
ልቡን አጀገነ ያችን ጥይት ሊውጥ
በማን ተሰራና በ'ጁ ያለው ሽጉጥ
#seifetemam
ግጥምጥም
የሰበራችሁትን እገጥማለሁ ብዬ
ያጣመማችሁትን አቀናለሁ ብዬ
እኔው ተሰብሬ እኔው ተጣምሜ
ማቅናቴም መግጠሜ
በማዝመም ማዝገሜ
አወይ ግጥም ጥሜ
#seifetemam
ዋጋ የለሽም
ምክንያቴን ሁሌም ተረጂው
ቢለይብሽም መንገዴ
ተመን የለኝም ላንቺ
ከቶም አልልሽ ውዴ
በዚች ኮተታም አለም
ኦና ቤቴን ካሻሽም
ውድነት ቢያረክስሽ እንጂ
አንቺስ ዋጋ የለሽም
#seifetemam
መስታወተ ጓደኛ
ጓደኛ ሲሆን መስታወት
'ራስን 'ሚያሳይ ሲያዩት
አንዳ'ንዱ ግን ይለያል
የ'ራሱን ምስል ሲያሳዩት
ጓደኛዬ ይህ ነው ይላል
#seifetemam
ለ አባባ ተስፋዬ 1
'ዛሬ አበባዎች
የነገ ፍሬዎች'
ብለው ከጠሯቸው ስንቶቹ ረገፉ?
ለሳሎን ጌጥነት ስንቶች ተቀጠፉ?
እርሶስ ፍሬ ሆነው ተዘርተው አለፉ::
#seifetemam
ለአባባ ተስፋዬ 2

ያኔ...

የፕላስቲክ ኮዳ የሞባይል ካርዱ
መንገድ ሳይከመር
መስኮትና ጣሪያው በዲሽ ሳይወረር
አንድ ቲቪ ብቻ ላንድ ሙሉ ሰፈር
አንድ ቲቪ ቻናል ላንድ ሙሉ ሃገር
አንድ ሰው ብቻውን ስንቱን ያስቆም ነበር?

ኋላ ላይ...

እንደ'ውቀት ፍሬ ልጅ ሁሉ እድሜ በላ
እንደ አዳም ባነነ ጩጬ ና ፈልፈላ
ገባው እንደሌሉ አባባ ተስፋዬ
ከስክሪኑ ኋላ
ፎገሩኝ እያለ ተካቸው በሌላ

ከዛም...

ቴሌቭዥኑም ከስቶ እንደእንጀራ ሳሳ
ገብስ ወረረው ፈልቶ የአበባውን ማሳ
ልጅ ባገሩ በዝቶም ልጅ ሁላ ተረሳ
(በአካል ተከስቶም) ለአባባ ተስፋዬ ጠፋ የሚነሳ

ከዛም በኋላ...

ለገዢው መደብ ጦር ተሰለፉ ልጆች
ለአባይ ዘመሩ ጮሁ ለታጋዮች
'ብሔር ብሔረሰቦች'

ከ'ዛ በኋላም በኋላ...

እነዛን ተወዝዋዥ እጆች
እስኪዘክራቸው ታሪክ
እስኪገኝ የአባባ ምትክ
አዋቂው እንደ ልጅ ይጃጃል
ልጅም ይቅበጥ በአዋቂ ልክ
ማንም ለማንም አይነሳ
እራሱን ያክብር ዘመኑ
'1' እና '0'ን ቀምሩ
የ'1' እና '0' ነው ቀኑ
በሉ ልጆች ደህና ሁኑ
ደህና ሁኑ ደህና ሁኑ
#seifetemam
ለማፍቀር ቀጠሮ

ሸትታ 'ምትገለማ
መርቅዛ 'ምትገማ
ወፍፋ ያበደች
ጨርቋን ጥላ የሄደች
ማንነቷን ስታ
ከሆነው ተጣልታ
ካልሆነው ተጣብታ
ያልሆነውን ሽታ
ማስመሰል አብዝታ
በመክሰም ለማበብ
በመግደል ለማከም
በምታደክም አለም
ውዴ አንቺን ልወድሽ
'ሚገባ አይደለም
...
... ... ስለዚህ
...
በናርዶስ ምዓዛሽ የዝች ቅርናት አለም ሽታዋ ከጠፋ
ወይ ሰናይ ፀባይሽ አሽሏት እንደሆን እንዳትቀር ወፍፋ
ማስመሰሏን ከሳ
እራሷን ስትሆነው ደግሞ ተመልሳ
ቀጠሮ ስላለኝ ያንግዜ ልወድሽ
አለሜን አክምያት እንዳይረፍድ ባክሽ
#seifetemam
የገጣችን ታዳሚዎች ሆይ
ከስር በተቀመጠው ማግኛ (link) ከ9500 በላይ ወዳጆች ያሉትን የ ፌስቡክ ገጣችንን ትጎበኙት ዘንድ ተጋብዛችኋል https://www.facebook.com/gitemsitem/