ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.83K subscribers
842 photos
55 videos
20 files
394 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሁሌ ድምቀታችን አስቱ እንዲህ በድንገቴ ተጋባዥነት የግጥም ግጥሚያችንን አፍታ አድምቆልን ነበር።
የላላ መቀነት ተፈቶ ያልተፈታ
የነተበ ማተብ የፈዘዘ እውነታ
የትውልድ ስብራት በአፍ እየታበየ
ነገን አሳቢ ነፍስ እውነት አለ ወይ?

ኋላ ቀረች አሉኝ ሀገር ተጎትታ
ጉልበት እንደከዳው ፈረስ ተንኮታኩታ
ሰንሰለት ጠፍሮ ይጎተጉተኛል
የምትረግጪበትን አስተውይ ይለኛል
ይወተውተኛል የፊቴን እንዳይ
እግር ሳይራመድ ወደፊት አለ ወይ?

ሰው'ነት ያልገባው እኛነት ይሰብካል
ግራው ስለት ይዞ ቀኙ ይዘረጋል
እኔነት አስክሮት ጦቢያዬ ይለኛል
የበግ ለምድ ከላዩ ደርቦ ደራርቦ
በተኩላ ጥርሶቹ ይጠቀጥቀኛል
ደሞ ሀገሬ እያለ ውስጤን ያቆስለኛል
በደም የጠገበ ፊቱን የማያይ
እውነት የእናት ነገር ሀገር ያውቃል ወይ?

አያውቅም አያውቅም አልገባውም ፍፁም
የእትብቱ ማደሪያ ዕንቁ አፈር መሆኑን ከቶ አልተረዳውም
እኔ የሚሉት ዛር የተጠናወተው
ሆ ብሎ የወጣ የነገ ያልገባው
ህሊናው ከአእምሮው የተነነበት
ሙት መንፈስ ነው መሪው

አንተ ግን ልብ በል ንቃ የኔ ትውልድ
ለለኮሰህ ሁሉ እሳት ሆነህ አትንደድ
ታሪክህን ጠብቅ...
ያለህን እወቀዉ
የፊደል ገበታ ሀ ብለህ የጀመርከው
ከራስ በፊት ሀ'ገር ስለሚቀድም ነው

©️ዮርዳኖስ

https://t.me/Wordgasm
👍1
The British Council in Ethiopia presents a roundtable dicussion on Performance Art in Ethiopia.
The programme will also include Live Performance like Poetry, Music, and Painting.

📍Shifta
📆Thursday, March 10, 2022
5:30pm - 8:00pm
ነገ አርብ ደግሞ አራት ኪሎ ኢኽላስ ህንጻ በሚገኘው ዋልያ ቡክስ 'ወደ ግጥም' እንትመም
👍4
Forwarded from Addis Powerhouse
ዳኞቻችን የቃላት እመቤቶቻቸውን መርጠዋል። እርሶስ ለመምረጥ ዝግጁ ኖት?

Our judges have picked their winners. Are you ready to choose yours?

A submission with the most number of likes will become Addis Powerhouse’s 2022 የቃላት እመቤት and win printed paintings from Kuku Pencil’s gallery.

Go to ✍🏾 Addis Powerhouse to see the top 6 feminist writing submissions, and vote for (like) your የቃላት እመቤት!
Forwarded from Afromile
Book a the camping trip to Chebera Churchura by Tobiya Hiking via Afromile and get a 7% discount on the all-inclusive ticket. Contact 0941151575 to book the ticket. @afromile
👍1
Forwarded from LinkUp Addis
The next edition of Shifta Concert will take place at Shifta Foods on Wednesday 23 March 2022 featuring RASS. Doors will open at 7:00pm, and entrance is ETB 150. @linkupaddis
Wag 1 Arts is hosting the 3rd edition of its Open Mic event, a music, comedy amd ppetry event on Sunday 27 March 2022 at Karibu Bar and Restaurant. Doors will open at 3:00pm. Admission to this event is Free of charge.
@linkupaddis
አታውቂም?

ጓደኛ መስታወት የኔነት ነጸብራቅ:
በሩቅም እያለ ከልብ ውስጥ የማይርቅ:
ጓደኛ ፈውስ ነው የሚስጥሬ አለም:
እንደ ብቸኝነት ከቶ የወጋኝ የለም:
እኔ አንቺን ካጣው ሞቴ ነው አታውቂም?
:
ኦ ኦ ኦ ትችላለህ አትበይኝ አልችልም ግድየለም:
አጉል ተስፋ አትስጪኝ ድጋሜ አልታመም:
ብቸኝነት ጎድቶኝ መቼም አላገግም:
አስበሽዋል...ሊያውም በድጋሜ ስጎዳ ስሰበር:
ምን የሚሉት ቁስል ወይ ላይድን ወይ ላይ ሽር:
አረ ወይኔ....ልቤ ላይ ሲወጣ እንዴትስ ሊረሳ:
ሰው የማጣት ቁስል ዘላቂ ጠባሳ::

ይድናል አትበይኝ ጊዜውን ጠብቆ:
ትዝታ እያለበት ቁስል መቼ ደርቆ:
ይታያል ብለሽ ነው ሰውን ያጣ አለም:
አንድም ባዶ ሸክም:
ሌላም
በቁሙ የሞተ መሆኑን አታውቂም???

© ሚኪ ሳ.
👍32🤮1
ኧረ 'ኔስ አላይም ደጁን!

ይመጣል ነፋሱን መስሎ
ይሄዳል ናፍቆቱን ጥሎ።
ከዝናብ ፣ ከሰንበት ጋራ፥
መጠበቅ ነው የእኔስ ስራ።
እረፍትሽ ይሉኛል ሰዎች ፥ ዓርብ ዕለት ቤቴ ስገባ፣
ቅዳሜ አለ ቀጠሮ ፥ የእኩያ ፌሽታ ስብሰባ፤
ኧረ እኔስ አላይም ደጁን ፥ አልወጣም ቤቴን ለቅቄ፣
አለኝ የምናፍቀው ፥ አለኝ ከሰው ደብቄ፤
አለኝ የምጠብቀው ፥ አለኝ ትዝታ አሙቄ።
ኧረ 'ኔስ አላይም ደጁን!

ቅዳሜ ገበያ ነበር ፥ ስሜው የወጣሁ ከቤት፣
እሁድ በተስኪያን ልንሄድ ፥ ላስገባ ጥላ ለስለት።
አብሮነት ታደልን ብለን ፥ ጎጆችን ቀና ፣ ሰመረ፥
እሁድ ምሳ ሰዓት ላይ ፥ ቤታችን ጥሪ ነበረ።
ከሸመትኩት ከገበያው፥ አልቀረኝ ቄጤማ ፣ ጡንጅት
ለምስጋና የሚሆነን ጧፍ ሻማውን አረሳሁት።

ቀረች ብሎ ወጣ ከቤት ሊጠብቀኝ ከመንገድ፣
ከሩቅ ሁኘ ነው ያየሁት ሲፈልገኝ የእኔን መውደድ።
ፈገግ አልኩኝ ጥርሴ ጠራው ከአስፓልት ማዶ፣
መጥቶ አቀፈኝ የገበያ ሸክሜን ወስዶ።
እሱን ሳገኝ ያልገዛሁት ትዝ እያለኝ፣
'እፎይ.. አንተን ሰጥቶ ገላገለኝ!'
በል ሂድ አልኩት ፥ ገዝተህ አምጣ፣
ተመልሼ ከምወጣ፤
ቡና አፍልቼ ምሳ አቅርቤ ልጠብቅህ
ብቻ እንዳትቆይ ስሞትልህ?!

ቤቱን ሰንዳ ፥ ሰንዳ...ሰንዳ፣
ሁሉ ቀርቦ ቀረብኝ ዕዳ።
አንድ ...ሰዓት
ሁለት ሰዓት ፣ሶስት ..ልቤ ፈራ፣
በዚያው ቅጽበት ስልኬ ጠራ፤
'ሄሎ?'
"ሀሎ ..ወርቃማ ጥላ የያዘ ሰው..
መንገድ ሲያቋርጥ..." ሞተ ብሎ ጨረሰው ።

ኧረ እኔስ አላይም ደጁን..
ይሄን መርጦ ወሳጁን።

ሰው ስለት ይበላል እንጂ ፤ ፈጣሪን አረሳስቶ፣
እግዜሩም ይቀማል እንዴ፥ የሰው ዋጋ ገምቶ ።

እንግዳውም በሰንበት ፥ ተሸኘ እንደታሰበው፣
ወርቅ ጥላዬን ለስለት ፥ እልል ተባለ ሳስገባው።
ጡንጅቱ ቤቴን አጠነ ፥ ወግ ነው አሉ በባህሉ ፣
ሻማናጧፍ ለፍታት በየተራ ተቃጠሉ፤
እምባ የለሽ ሐዘኔን መጠበቄን አበቀሉ።

ኧረ እኔስ አልሄድም ደጁ፣
ቢፈልግ ይውሰደኝ እንጂ
እግዜር በረጅም እጁ።

© አስካለ ልቅና
👍63