ተ ስ ፋ
ኩሽያ ፑዴ ዴንቲቴ (እጃችሁን ወደላይ አንሱ)
ቤሳ ቤሳ ቤሳ ቤስቴ ቤሳ
(አሳይ አሳዪ አሳይ እናሳይ አሳዪ)
ነጋሁ ይለኛል ሊመሽ
ይመሻል ደግሞ እስከሚነጋ
ትንሽ ተስፋ ብዙ አለው ዋጋ
ጨረቃ ጀምበር ናት ማታ
የልቤ እሳት የልቤ ፍም
አልጠፋችም ዛሬን ባትነድም
ነገ ምን ሊያመጣ ባላውቅም
ተስፋን ይዣት አለቅም
እልፍ ሲሄድ እልፍ ይመጣል
እልፍ ወስዶ እልፍን ይሰጣል
ለአመስጋኝ ሰው ላጣም ላገኘው
ተስፋን ስንቅ አርጎ ይይዛታል
ብርርርርርርር ይላል ልቤ ገና
ሁሉን አልፎ ቀና
ይበራል ልቤ ወቶ ከላይ
ተስፋው ነው ከሰማይ
የያዝኩት ወድቆ ቢረግፍም ብንን
ብ ን ን ት ን ን
የቀናው ጥምም
ቢልም እድል ካልሆነው ጋር ዝምም
ዝምም ምንም
እጁ የለም ምንም
ምሰጠው እነሳለሁ ደግሜ
ነገን ቀድሜ
ስወድቅም እነሳለሁ ደግሜ
ደግሜ ደግሜ ደግሜ
ራሴን ሸልሜ
ፍሬ ከአፈር ይወድቃል
ቀን ጠብቆ ኖሮ
ከዚያዝ ትንሽ ፍሬ ዛፍ ይነቃል
ላባ ቀለም ይነክራል
የጠቢብ ሰው ሥራ
በትንሽ ብራና አገር ይመክራል።
ግንበኛ የናቀው ድንጋይ
ማዘኑን ይተው ተመርጧል
ሊውል ከመዓዘኑ ላይ
መዳን አለ በስቃይ
መጥፋት አለ በደስታም
መልካም ብቻ እርሱ የባረከው ሰማይ
ውሸታም ዓለም በውሸት ቀለም ሥዕል ሥሎ
በውሸት ምሎ
ነጋሁ ይለኛል ሊመሽ
ይመሻል ደግሞ
©️ሮፍናን
ኩሽያ ፑዴ ዴንቲቴ (እጃችሁን ወደላይ አንሱ)
ቤሳ ቤሳ ቤሳ ቤስቴ ቤሳ
(አሳይ አሳዪ አሳይ እናሳይ አሳዪ)
ነጋሁ ይለኛል ሊመሽ
ይመሻል ደግሞ እስከሚነጋ
ትንሽ ተስፋ ብዙ አለው ዋጋ
ጨረቃ ጀምበር ናት ማታ
የልቤ እሳት የልቤ ፍም
አልጠፋችም ዛሬን ባትነድም
ነገ ምን ሊያመጣ ባላውቅም
ተስፋን ይዣት አለቅም
እልፍ ሲሄድ እልፍ ይመጣል
እልፍ ወስዶ እልፍን ይሰጣል
ለአመስጋኝ ሰው ላጣም ላገኘው
ተስፋን ስንቅ አርጎ ይይዛታል
ብርርርርርርር ይላል ልቤ ገና
ሁሉን አልፎ ቀና
ይበራል ልቤ ወቶ ከላይ
ተስፋው ነው ከሰማይ
የያዝኩት ወድቆ ቢረግፍም ብንን
ብ ን ን ት ን ን
የቀናው ጥምም
ቢልም እድል ካልሆነው ጋር ዝምም
ዝምም ምንም
እጁ የለም ምንም
ምሰጠው እነሳለሁ ደግሜ
ነገን ቀድሜ
ስወድቅም እነሳለሁ ደግሜ
ደግሜ ደግሜ ደግሜ
ራሴን ሸልሜ
ፍሬ ከአፈር ይወድቃል
ቀን ጠብቆ ኖሮ
ከዚያዝ ትንሽ ፍሬ ዛፍ ይነቃል
ላባ ቀለም ይነክራል
የጠቢብ ሰው ሥራ
በትንሽ ብራና አገር ይመክራል።
ግንበኛ የናቀው ድንጋይ
ማዘኑን ይተው ተመርጧል
ሊውል ከመዓዘኑ ላይ
መዳን አለ በስቃይ
መጥፋት አለ በደስታም
መልካም ብቻ እርሱ የባረከው ሰማይ
ውሸታም ዓለም በውሸት ቀለም ሥዕል ሥሎ
በውሸት ምሎ
ነጋሁ ይለኛል ሊመሽ
ይመሻል ደግሞ
©️ሮፍናን
👍4
Forwarded from Andu Getachew .( Poems ) ግጥሞች (Andu Getachew)
ከፍላጎቴ በላይ ምን ጠላት አለኝ ?
ከመንፈግ ውጭ ምን ሃይል አለሽ ?
.
(ይኸው ራሴን ወሰድኩብሽ። )
.
ስስ ነኝ ፤ በእቅፍሽ ባይሆንልኝ_ ምናለ በፀሎትሽ ብታስቢኝ
ደረቅ ነሽ፤ ከአብሮነታችን_ ብቸኝነቱ ነው የሚያድንሽ ?
.
በአለም ካሉ ጠጣሮች እንደ ሰው ልብ አላየሁ
አስቸገርኩ አይደል ወድጄሽ ?
አስቸገርኩ አይደል ጠርቼሽ ?
................ድባቴሽን ቀምቼሸ ?
................ሰቆቃሽን ቀምቼሽ?
...............ብቸኝነትሽን ቀምቼሽ ?
አስቸገርኩኝ አይደል ?
.
(ይኸው ራሴን ወሰድኩብሽ !) .
.
.
እኔማ _ ሴጣኔም ለምዶኝ
ህመሜም ለምዶኝ
ሰማይ ሜዳው ለምዶኝ
እንዴት 'መሰሌ' ሰው ጋር ተገፋፋው፣ ብዬ አንጂ የእውነት
ሰለቸኝ ወደ የትም የማይሄድ ዝምድና መጎተት ..
.
.
ምናልባት
ምናልባት
የመንገዱ መብዛት ይሆናል እንዳንገናኝ ያረገን
የአማራጭሽ መብዛቱ ይሆናል አማራጭ ያሳጣሽ
.
(ይኸው ራሴን መሰድኩብሽ።)
.
..
ድሮም ከፍላጎቴ በላይ ምን ጠላት አለኝ
ከመንፈግ ውጭ ምን ሃይል አለሽ
.
(ይኸው ራሴን ወሰድኩብሽ )
ከመንፈግ ውጭ ምን ሃይል አለሽ ?
.
(ይኸው ራሴን ወሰድኩብሽ። )
.
ስስ ነኝ ፤ በእቅፍሽ ባይሆንልኝ_ ምናለ በፀሎትሽ ብታስቢኝ
ደረቅ ነሽ፤ ከአብሮነታችን_ ብቸኝነቱ ነው የሚያድንሽ ?
.
በአለም ካሉ ጠጣሮች እንደ ሰው ልብ አላየሁ
አስቸገርኩ አይደል ወድጄሽ ?
አስቸገርኩ አይደል ጠርቼሽ ?
................ድባቴሽን ቀምቼሸ ?
................ሰቆቃሽን ቀምቼሽ?
...............ብቸኝነትሽን ቀምቼሽ ?
አስቸገርኩኝ አይደል ?
.
(ይኸው ራሴን ወሰድኩብሽ !) .
.
.
እኔማ _ ሴጣኔም ለምዶኝ
ህመሜም ለምዶኝ
ሰማይ ሜዳው ለምዶኝ
እንዴት 'መሰሌ' ሰው ጋር ተገፋፋው፣ ብዬ አንጂ የእውነት
ሰለቸኝ ወደ የትም የማይሄድ ዝምድና መጎተት ..
.
.
ምናልባት
ምናልባት
የመንገዱ መብዛት ይሆናል እንዳንገናኝ ያረገን
የአማራጭሽ መብዛቱ ይሆናል አማራጭ ያሳጣሽ
.
(ይኸው ራሴን መሰድኩብሽ።)
.
..
ድሮም ከፍላጎቴ በላይ ምን ጠላት አለኝ
ከመንፈግ ውጭ ምን ሃይል አለሽ
.
(ይኸው ራሴን ወሰድኩብሽ )
👍1
ይሰለቻል
ከአፍንጫዬ ጠርዝ ላይ
የደረቀ ንፍጥ መቅረፌ
ለሰው ይቀፍፋል እንዴ
ጉድፌን ከሰው መግደፌ?
ልቤን ሲመታ ማድመጤ
ብሶብኝ በመደንገጤ
ከምት ላላመልጥ ድባቴ
ከሞት አምልጬ መሞቴ
ኧረ ሰለቸኝ እቴ
ዓይኔም ከቂጥ ጋር
ሲፎካከር
ዓይን አር ይዞ ሲዞር
ሰውን ያስከፋል ይሆን?
ታከተኝ ለሰው መጠንቀቅ
ሰለቸኝ እራሴን መንጠቅ
ባይተነፈስስ ቢቀር
ተብሎ አይተው ዓየር
ነጻ ፈቃድ ከተሰጠኝ
ምነው ዋጋ የሚያስከፍል
የፈቀድኩትም ሲፈቅደኝ
የቀፈፍኩትም ሳይቀርፈኝ . . .
የሚበላኝን ጫጫታ
ላይዳብስ ለማያክልኝ
የገባሁበት ኤጭታ
መኖሬ ነጸብራቅ እንጂ
እያጣ የመኖር ኖታ
ቅኝት የሳተ ድም ድም
ድንብር የሳተ ዝም ዝም
ይሄንን ይሆን ያለችው
ሸዋ ስ'ተርት 'ግም ለግም'?
ሁሉ ተሳካ እንኳ ቢባል
ይሰለቻል ትግል ሲግል
ከማሸነፍ ለማይዘልል
ከዛስ?
ቀጣዩ ትንፋሽ እስኪሳብ
ህይወት ቅጽበቷ ሲሳብ
ለግብ የገባ ግብግብ
ሞት ለማይጠግብ ሳንባ
ሳብ ዓየር ና ከእኔ ግባ
ምታ ልብ በምትህ አንባ
አምባ ሂድ ከኑሮ ደባ
ከዛስ?
ሰው አሸን ሆኖ በዙሪያህ
ውስጡን ሊሸሸው
ሲያሻው
ደስታውን ካንተ ሲያስስ
ከአፍንጫህ ጠርዝ ላይ
ንፍጥህን ይነቅፋል
እንደ ዓይንህ ጉድፍ
. . . ይሰለቻል!
አቻ መቆያ ፍለጋ
በእድፍ መግፈፊያ መዳፌ
መሃላዎች አስደግፌ
ሳድል ማረጋገጫ
ስንቱን እየረገጥኩኝ
ስንቱን ማምለጤን እንጃ
እሺ ቢረጋገጥስ
እርግጥ ቢል ነገር ሁሉ
አይሰለች ይሆን መተንፈስ
ስንት ንጋቶች ናቸው
አዲስ ቀናት የሚባሉ?
ይሰለቻል መጠየቅ
ያስጠይቃል ደሞ መልሱ
ልብ ለምን ይመታል
መውደድ በሆነ ጓዙ
. . .
ኧረ ምንድነው እሱ?
እሺ ሁሉም ተመለሰ
. . . ግን ከዛስ?
መታመምን የለመደ
ምን ይውጣል
ሳግ ከሄደ?
ለሰው የሚበጅ መንገድ
አንድ ፍሬ ቃል ላይፈልቀኝ
ምን ይጠቀማል ማንስ
የግሉ አድርጎ ቢፈቅደኝ
ምን ልሰራለት ይህ ዓየር
ዝምብሎ 'ሚተነፈሰኝ
ለእናቴስ ምን ላ'ረግላት
ከህመም የተነጠለ
ያለኝ ይመስል በረከት
አሳምሜያት ምድር ድረስ
ዓየር ስቤ እስከማለቅስ
ልቧን በጥያቄ
አውልቄ
መውደጃ ማቄን አጥልቄ
አድጌም የሷው ሰቀቀን
በአፌ አትሜ ደግነቷን
ያልተባረኩ ስሜ ልቧን
መታመምን የለመደ
ምን ይውጣል
ሳግ ከሄደ?
. . .አቦ ስሰለች!
©️ ሰይፈ ተማም
ከአፍንጫዬ ጠርዝ ላይ
የደረቀ ንፍጥ መቅረፌ
ለሰው ይቀፍፋል እንዴ
ጉድፌን ከሰው መግደፌ?
ልቤን ሲመታ ማድመጤ
ብሶብኝ በመደንገጤ
ከምት ላላመልጥ ድባቴ
ከሞት አምልጬ መሞቴ
ኧረ ሰለቸኝ እቴ
ዓይኔም ከቂጥ ጋር
ሲፎካከር
ዓይን አር ይዞ ሲዞር
ሰውን ያስከፋል ይሆን?
ታከተኝ ለሰው መጠንቀቅ
ሰለቸኝ እራሴን መንጠቅ
ባይተነፈስስ ቢቀር
ተብሎ አይተው ዓየር
ነጻ ፈቃድ ከተሰጠኝ
ምነው ዋጋ የሚያስከፍል
የፈቀድኩትም ሲፈቅደኝ
የቀፈፍኩትም ሳይቀርፈኝ . . .
የሚበላኝን ጫጫታ
ላይዳብስ ለማያክልኝ
የገባሁበት ኤጭታ
መኖሬ ነጸብራቅ እንጂ
እያጣ የመኖር ኖታ
ቅኝት የሳተ ድም ድም
ድንብር የሳተ ዝም ዝም
ይሄንን ይሆን ያለችው
ሸዋ ስ'ተርት 'ግም ለግም'?
ሁሉ ተሳካ እንኳ ቢባል
ይሰለቻል ትግል ሲግል
ከማሸነፍ ለማይዘልል
ከዛስ?
ቀጣዩ ትንፋሽ እስኪሳብ
ህይወት ቅጽበቷ ሲሳብ
ለግብ የገባ ግብግብ
ሞት ለማይጠግብ ሳንባ
ሳብ ዓየር ና ከእኔ ግባ
ምታ ልብ በምትህ አንባ
አምባ ሂድ ከኑሮ ደባ
ከዛስ?
ሰው አሸን ሆኖ በዙሪያህ
ውስጡን ሊሸሸው
ሲያሻው
ደስታውን ካንተ ሲያስስ
ከአፍንጫህ ጠርዝ ላይ
ንፍጥህን ይነቅፋል
እንደ ዓይንህ ጉድፍ
. . . ይሰለቻል!
አቻ መቆያ ፍለጋ
በእድፍ መግፈፊያ መዳፌ
መሃላዎች አስደግፌ
ሳድል ማረጋገጫ
ስንቱን እየረገጥኩኝ
ስንቱን ማምለጤን እንጃ
እሺ ቢረጋገጥስ
እርግጥ ቢል ነገር ሁሉ
አይሰለች ይሆን መተንፈስ
ስንት ንጋቶች ናቸው
አዲስ ቀናት የሚባሉ?
ይሰለቻል መጠየቅ
ያስጠይቃል ደሞ መልሱ
ልብ ለምን ይመታል
መውደድ በሆነ ጓዙ
. . .
ኧረ ምንድነው እሱ?
እሺ ሁሉም ተመለሰ
. . . ግን ከዛስ?
መታመምን የለመደ
ምን ይውጣል
ሳግ ከሄደ?
ለሰው የሚበጅ መንገድ
አንድ ፍሬ ቃል ላይፈልቀኝ
ምን ይጠቀማል ማንስ
የግሉ አድርጎ ቢፈቅደኝ
ምን ልሰራለት ይህ ዓየር
ዝምብሎ 'ሚተነፈሰኝ
ለእናቴስ ምን ላ'ረግላት
ከህመም የተነጠለ
ያለኝ ይመስል በረከት
አሳምሜያት ምድር ድረስ
ዓየር ስቤ እስከማለቅስ
ልቧን በጥያቄ
አውልቄ
መውደጃ ማቄን አጥልቄ
አድጌም የሷው ሰቀቀን
በአፌ አትሜ ደግነቷን
ያልተባረኩ ስሜ ልቧን
መታመምን የለመደ
ምን ይውጣል
ሳግ ከሄደ?
. . .አቦ ስሰለች!
©️ ሰይፈ ተማም
❤2🔥1
Forwarded from Bruh Club
The Arts Mailing List newsletter – 17th Jan 2022 is out now!!!!!
https://bit.ly/3qupGIC
The place for Ethiopian creatives to find opportunities and apply
This week we are featuring the fascinating work of Biniyam Kassahun https://www.instagram.com/biniyam_almaz/
@artsmailinglist
https://bit.ly/3qupGIC
The place for Ethiopian creatives to find opportunities and apply
This week we are featuring the fascinating work of Biniyam Kassahun https://www.instagram.com/biniyam_almaz/
@artsmailinglist
SEIGE
Down on one knee
I grab the earth below
The Land of the free
Me, the invader, Shining in armor
Steel mesh and
Helm under my arm
Sword on my hip
For i came to do harm.
My eyes in the sun light
I hear the noise behind
Of men ready for a fight.
a touch on my shoulder
I Turned my eyes
To a field in smolder.
Loud sound to my left
My captain of wars
Right wing man I kept.
"It is time my king"
Time to plunder and kill
death and fire to bring.
"Aye" I replied
With A look of bravery
From my soul I lied.
I reach for my helm
Red feathers and steel
From the devil's realm.
I turn to my men...
Lined up and waiting
"Do it" I said
To my captain nodding.
A roar he let out
Sounds quickly followed
From the lions snout.
The men now heed
I mount my friend
My steed of stampede.
I draw my father's razor
Sharp as pythons fangs
Old, man flesh grazer.
Go home the coward
Leave my place of war
anywhere but forward
for my war drums are now blowing.
the loud thunderous roar of my nations blood flowing.
Down on one knee
I grab the earth below
The Land of the free
Me, the invader, Shining in armor
Steel mesh and
Helm under my arm
Sword on my hip
For i came to do harm.
My eyes in the sun light
I hear the noise behind
Of men ready for a fight.
a touch on my shoulder
I Turned my eyes
To a field in smolder.
Loud sound to my left
My captain of wars
Right wing man I kept.
"It is time my king"
Time to plunder and kill
death and fire to bring.
"Aye" I replied
With A look of bravery
From my soul I lied.
I reach for my helm
Red feathers and steel
From the devil's realm.
I turn to my men...
Lined up and waiting
"Do it" I said
To my captain nodding.
A roar he let out
Sounds quickly followed
From the lions snout.
The men now heed
I mount my friend
My steed of stampede.
I draw my father's razor
Sharp as pythons fangs
Old, man flesh grazer.
Go home the coward
Leave my place of war
anywhere but forward
for my war drums are now blowing.
the loud thunderous roar of my nations blood flowing.
👍1
with thoughts of his and hers,
they all think, they all dread,
who to glory and who will lose their head.
Their Eyes slow in blinking,
single sweat from their faces
and their Shields connecting,
With the song of my steel, helms are worn and hoorah is roared.
HOORAH!! HOORAH!!
Men once still now hastily moving .
Take all and show no mercy,
for king and country, cleave and burry.
Here, here, for king and country show no fear,
make way my entry, go and make all mine.
To the gods do look up and from your heels do spring,
long live this life,
long live the king.
©️OKEANOS
Art by Brenda Erickson
#Art_to_Earth #ጥበብ_ለምድር
@gitemsitem @tibeb_be_adebabay_2021
they all think, they all dread,
who to glory and who will lose their head.
Their Eyes slow in blinking,
single sweat from their faces
and their Shields connecting,
With the song of my steel, helms are worn and hoorah is roared.
HOORAH!! HOORAH!!
Men once still now hastily moving .
Take all and show no mercy,
for king and country, cleave and burry.
Here, here, for king and country show no fear,
make way my entry, go and make all mine.
To the gods do look up and from your heels do spring,
long live this life,
long live the king.
©️OKEANOS
Art by Brenda Erickson
#Art_to_Earth #ጥበብ_ለምድር
@gitemsitem @tibeb_be_adebabay_2021
Forwarded from don (Natty)
This is my first release, wanted to do it right here. Hope you enjoy! 💙
🔥1
ነፋስማ ገፍቶሽ ነበር - ከአውሎ ጋር ተመሳጥሮ
እየታጠፍሽ እረታሽው - ሰገደልሽ ተሽከርክሮ
አወይ አንቺ!
ሞትን በዳንስ የምትረቺ።
©️ ሠይፈ ወርቅ
እየታጠፍሽ እረታሽው - ሰገደልሽ ተሽከርክሮ
አወይ አንቺ!
ሞትን በዳንስ የምትረቺ።
©️ ሠይፈ ወርቅ
❤3👍2
ስጠኝ ትራጀዲ
[ፀሎት ለትራጀዲው ጌታ]
--------------------------------
አምላክ ሆይ ፀሎት ነው ስማ
ከልጅህ ዘንድ ብርቱ ልመና
ስጠኝ ትራጀዲ
ስጠኝ ማጣት መቸገር
መች ትቶኝ ሄዶስ ቀድሞ ነገር
እንዲሁ ነው ነገሩን
የፍራቻ የሥጋቴን
ስጠኝ ትራጀዲ ለጥበብ ግብአት ይሁነኝ
''ደክሞኛል መኖር ላለመሞት
በህይወት ከርሞ ለመቆየት
ፈቅ እማይል ከ ፈቀቅታ
ሠርክ ሮሮ ሁሌ ዋይታ"
እያልኩ:- ፈፅሞ አላማርርህም
ይሁነኝ ትራጀዲ ለጥበብ ስንቅ
ኑሮ'ንዲህ ነው ለገጣሚ የሚናፈቅ
በምቾት ውስጥ የታል ጥበብ
የታል ግጥም?
ሁሉ ነገር አንድ ቀለም
ለትየባ ምን ሊጠቅም?
ምን ረብ አለ እማግኘት ውስጥ?
ከሀብት ወዲያ ወደየት ለውጥ?
ሁሉ ቆመ ጥበብ የታል
ከሉክ ደረት ምን ይውላል
የደላው ግን ግጥም ያውቃል?
ለሙት መታሠቢያ ሚፃፍግጥም
ጥበብ ሊባል ይቻለዋል?
ኤድያ
ቲሽ
ማግኘት
ቢላሽ
ግን እንጃልኝ ፤
ግን እንጃልን
ሀሳብ ያልቃል የደላኝ ቀን
አምላኬ ሆይ አደራህን
ጣለው ከህይወቴ አሽቀንጥረህ
ወዲያ በልልኝ ምቾት ብሎ ነገር
ችግሬ አርምሞን ያምጣ
አስቦ በማስፈር ልመር
ልግጠም የት-አባቱ
ይህ ነው የኔ ጊዜ
ፅፌ ሳረቅ የለፋሁት
አድማጭ ሳገኝ የደም-ወዜ
ችግር ማጣት ምን ቢጠላ
ለገጣሚ መልኩ ሌላ
አቆይልኝ ድህነቴን
ልግጠምበት ደስ ይለኛል
ድሎት ክፉ ከመክሊቴ ያርቀኛል
ምቾት ክፉ ይነጥቀኛል
አቦ [ልግጠም] ይሻለኛል︎! ።
© ዘር:ታዬ
[ፀሎት ለትራጀዲው ጌታ]
--------------------------------
አምላክ ሆይ ፀሎት ነው ስማ
ከልጅህ ዘንድ ብርቱ ልመና
ስጠኝ ትራጀዲ
ስጠኝ ማጣት መቸገር
መች ትቶኝ ሄዶስ ቀድሞ ነገር
እንዲሁ ነው ነገሩን
የፍራቻ የሥጋቴን
ስጠኝ ትራጀዲ ለጥበብ ግብአት ይሁነኝ
''ደክሞኛል መኖር ላለመሞት
በህይወት ከርሞ ለመቆየት
ፈቅ እማይል ከ ፈቀቅታ
ሠርክ ሮሮ ሁሌ ዋይታ"
እያልኩ:- ፈፅሞ አላማርርህም
ይሁነኝ ትራጀዲ ለጥበብ ስንቅ
ኑሮ'ንዲህ ነው ለገጣሚ የሚናፈቅ
በምቾት ውስጥ የታል ጥበብ
የታል ግጥም?
ሁሉ ነገር አንድ ቀለም
ለትየባ ምን ሊጠቅም?
ምን ረብ አለ እማግኘት ውስጥ?
ከሀብት ወዲያ ወደየት ለውጥ?
ሁሉ ቆመ ጥበብ የታል
ከሉክ ደረት ምን ይውላል
የደላው ግን ግጥም ያውቃል?
ለሙት መታሠቢያ ሚፃፍግጥም
ጥበብ ሊባል ይቻለዋል?
ኤድያ
ቲሽ
ማግኘት
ቢላሽ
ግን እንጃልኝ ፤
ግን እንጃልን
ሀሳብ ያልቃል የደላኝ ቀን
አምላኬ ሆይ አደራህን
ጣለው ከህይወቴ አሽቀንጥረህ
ወዲያ በልልኝ ምቾት ብሎ ነገር
ችግሬ አርምሞን ያምጣ
አስቦ በማስፈር ልመር
ልግጠም የት-አባቱ
ይህ ነው የኔ ጊዜ
ፅፌ ሳረቅ የለፋሁት
አድማጭ ሳገኝ የደም-ወዜ
ችግር ማጣት ምን ቢጠላ
ለገጣሚ መልኩ ሌላ
አቆይልኝ ድህነቴን
ልግጠምበት ደስ ይለኛል
ድሎት ክፉ ከመክሊቴ ያርቀኛል
ምቾት ክፉ ይነጥቀኛል
አቦ [ልግጠም] ይሻለኛል︎! ።
© ዘር:ታዬ
👍4❤1
Forwarded from ሀቅ Music Crew
👨👩👧👧 ሰላም ውድ ቤተሰቦች
እንደቃላችን መሰረት እንደ ጅምር ቅምሻ
"ሀቅ" የተሰኝ የሙዚቃ አልበም ይዘንላችሁ ልንቀርብ ዝግጅታችንን ጨርሰናል።
በቅርቡ ይጠብቁን
2014/2022
#newalbumalert #newethiopianhiphopalbum #fyp #AtniHAQ #OmmieHaq #HAQmusic #comingsoon #alert
@Haqcrew
እንደቃላችን መሰረት እንደ ጅምር ቅምሻ
"ሀቅ" የተሰኝ የሙዚቃ አልበም ይዘንላችሁ ልንቀርብ ዝግጅታችንን ጨርሰናል።
በቅርቡ ይጠብቁን
2014/2022
#newalbumalert #newethiopianhiphopalbum #fyp #AtniHAQ #OmmieHaq #HAQmusic #comingsoon #alert
@Haqcrew
Forwarded from LinkUp Addis
The 11th edition of Gitem Sitem Open Mic Circle is happening at Shifta on 02 February 2022. The event will feature several talented poets and artists. Doors will open at 6:00pm and show starts at 6:30pm. Entrance fee is ETB 50.
Have you tried our brand new app: https://bit.ly/3Fqrpno
@linkupaddis
Have you tried our brand new app: https://bit.ly/3Fqrpno
@linkupaddis
👍1