ግጥም ሲጥም - Gitem Sitem
1.79K subscribers
847 photos
55 videos
20 files
397 links
የዘመናችንን ቀለም ያሳያሉ ያልናቸውን የዚህ ትውልድ የስነ ግጥም ውጤቶችን እንጋራ - እናጋራ።
ለማካፈል የፈለጋችሁትን በGitem_Sitem ፣ gitemsitem@gmail.com የጸሃፊ ስም እና ርዕስ አክላችሁ ላኩልን።

We are all about sharing this generation's poetry. Please email us your pieces gitemsitem@gmail.com
Download Telegram
ጥቅምት 5 የፊታችን አርብ ከ11 ጀምሮ
"ቃል ና ሀሳብ" የስነ-ፅሁፍ ምሽት
ቦሌ ሚካኤል ከሩዋንዳ ኤምባሲ ዝቅ ብሎ ታክሲ ማውረጃው ጋር
"ጓዳ ስጋ ቤት"..በገጣሚያን እና ደመቅ ባለ ልዩ ዝግጅት ይጠብቃችኋል ።
ለበለጠ መረጃ
0987367513

@Gitem_Sitem
@gitemsitem
1👍1
Forwarded from LinkUp Addis
Tune in to LinkUp Addis's Instagram page starting Monday 18 October 2021 and join our live shows every evening.
We will be livestreaming LinkUp Addis's original shows live on Instagram.
@linkupaddis
« ያልተመለሰ አንጓ ..!
---

መቃብሩን አቀፍኩ ፣ ሳምኩት መቃብሩን
መለየትን አየኹ ፣ አየኹ የሞት በሩን
አየኹ የሞት ጥላ ፣ አየኹ የሞት ጉዝጓዝ
አንቺን ተከናንቦ ፣ ሣቅ ወደ'ኔ ሲጓዝ ።

ለሚል ታካች ገላ...!

አፈር አንከባሎ ፣ ወደ ሞት ቁልቁለት
አፈር ሰውነትን ፣ አፈር ኹን ያለ ዕለት
«ተው» የማይባል ሞት ፣ ቁም የማይባል ቀን
በእንባ ስንጠብቀው
በሣግ ስንጠብቀው ፣ በሣቅ ሰነጠቀን ።

አጀብ ነው አንቺዬ..!

ሕይወት ‟ግብረ - መልኩ” ፣ ካንቺ መለያየት
የመኖር ‟ጣር - ልኩ” ፣ ካንቺ መወያየት
ተወዲያ ተወዲህ ፣ ቁሞ መተያየት
እንደ ገሳ ግምጃ ፣ እንደ ቀትር ጀንበር
አልገለጥ አለ
መኖር ማለት ኹሉ ፣ መሞት እንደ ነበር ።

አልገለጥ አለ
በቀን በሸፈነው
በጋረደው መዝገብ ፣ በሸሸገው በኩል
ፈጣሪው 'ራሱ
እስከ'ሚሆን ድረስ ፣ ሞት ከሚለው እኩል ።

©️ሶሎሞን ሽፈራው

@GitemSitem
👍2
Forwarded from አድማስ Book Delivery (Mele😋)
አታንብብ
ምክንያቱም
ማንበብ ጥርጣሬን ይፈጥራል እምነትን ይሸረሽራል (ያላወቅነው በተገለጠልን ቁጥር የማናቀው እንደሚሰፋ ስለምንረዳ የያዝነውን መጠራጠር እንጀምራለን)

ምክንያቱም
ማንበብ ያፈላስፋል (የ 'ለምን' ጥያቄን ይደረድራል)

ምክንያቱም
ማንበብ ያሳብዳል(...)

ምክንያቱም
ማንበብ ከማህበረሰብ ያስገልላል...

ምክንያቱም
ማንበብ ከሃይማኖት አስተምህሮ ያቃቅራል (ስታነብ የበለጠ ማወቅ ስለምትፈልግ በማመን የሚታለፉ ረቂቅ ሃሳቦችን በጥልቀት ለማወቅ በሚደረግ ትግል የእምነት ሚዛን ይዛኘፋል ለዚህም ነው ያወቁ ያነበቡ ሰዎች ለኑፋቂ ወይም ለክህደት የተጋለጡ የሚሆኑት)

ዝም ብለህ አንብብ!

ቢያንስ ጥያቄህ ምክንያታዊ እንዲሆንና የማይወላወል የፀና አቋም እንዲኖርህ ንባብን ምርጫህ አድርግ!
ከንባብ ለመራቅህ ምክንያት አትደርድር🙌

ማንበብ የሚፈልጉት መጽሐፍ ካለ ያናግሩን ቅርብ ከሆኑ በአካል ራቅ ካሉ በፖስታ ቤት ያሉበት እናደርሳለን!
ለስምንተኛው ክፍት መድረካችን የሚቀርበውን አዘጋጃችሁ?
ብታቀርቡ በደስታ ብትታደሙም በአክብሮት እንቀበላችኋለን - እናንተ ብቻ ኑልን!

የፊታችን ረቡዕ 12 ሰዓት ላይ ምዝገባ እንጀምርና ልክ 12:30 ሲሆን እስከ 2:30 የሚቆየው ዝግጅታችን ይጀምራል

ሐያት ሆስፒታል አካባቢ በሚገኘው ሽፍታ Shifta እንተያይ

@PoeticSaturdays @aradaet

@LinkUpAddis @Ramapicture

@FebenFancho @SeifeTemam @Mcholmes


#gitemsitem #LinkUpAddis #PoeticSaturdays #feben_fancho #Arada #Shifta #Poetry #artinaddis #poetrylovers
Love hated to wake up in the morning
He hated the sun and the light it brings
New days scared him
So I would wake him up everyday
Before the sun did
From her evil eye
To shield
And I always rocked
His anxiety to bed
I sang lullabies
The kind that would make
His fear sleep
I loved his demons
Before he knew them
And tamed
Their anger
And told them to be kind
The only thing I did wrong is
While I was focused on him
I forgot me and my demons
That escaped
My leash
And beat him to death
And all this time
I thought he was at peace
All this time I thought angels
Were singing in his dreams
All this time
I was killing him bit by bit
Love and it's potion
With no antidotes.

©️Feben Fancho
2
Here is a new book to hype your winter...
Forwarded from Natna books
All was normal, Hailu knew without looking, he could understand the body's silent language without the help of machinery. Years of practice had taught him how to decipher what most patients couldn't articulate. These days were teaching him more: that the frailty of our bodies stems from the heart and travels to the brain. That what the body feels and thinks determines the way it stumbles and falls.

Novel by Ethiopian-American writer Maaza Mengist.
https://t.me/thebookworm23
#የአርምሞ_ፅዋ

አንዲት ኮኮብ
መሬት መሀል ብትወድቅም
የብርሀኗ አክሊለል አያስፈነድቅም

ከደብራችን ቅጥር ውበት እንድናስስ
በፀሎት ምህላ ቀናቱን እንቀድስ

የነብሳችን አፀድ ሂወት እንድታምጥ
ልክ እንደቡድሀ ዝምታን እናድምጥ

የውበት ነፀብራቅ ልብን የሚያርደው
ዝምታ ላይ አለ ምላስ ሳይቀይደው
ኑ እናጣጥመው የአርምሞን ፅዋ
ሩህ ያጠረቃል አካል እየሰዋ

©️ አዲብ

@Tufaw_muhe

@Am_in_love

@GitemSitem
Forwarded from Tibeb Be Adebabay-TBA
ጥበብ ተመልሷል!
ፌስቲቫሉ በሕዳር 19 ተከፈተ!

አርብ ህዳር 17, 2014; ለ2014 የጥበብ ኦንላይን እና የጥበብ በአደባባይ ፌስቲቫል ለሚሳተፉ አርቲስቶች የግብአት ክፍለ-ጊዜ ተዘጋጅቶ አልፏል።
የዚህ ክፍለ ጊዜ ዋና ትኩረት አርቲስቶቻችን እና የፈጠራ ባለሙያዎቻችን እንዴት ተመልካች አሳታፊ፣ ጭብጥ እና ተሟጋች ተኮር፣ የፕሮጀክት በጀትን ማስተዳደር፣ የግምገማ ቴክኒኮችን እና የፕሮጀክት ፅንሰ-ሀሳቦችን እና የፈጠራ እይታዎችን መፍጠር አና መጠቀም እንደሚችሉ በለጠ ያለ ግንዛቤ እና እውቀትን ለመስጠት የታለመ ነበር።

ከዚህም በተጨማሪ አርቲስቶች ከጥበብ የቀድሞ ተሳታፊዎች ጋር በሃሳብ እና የልምድ ልውውጥ አካሄደዋል::

ለተሳተፉት ሁሉ እናመሰግናለን!

Tibeb is back!
Festival opened on 28 November!

On Friday, Nov 26, 2021; we hosted an input session for 2021 participating artists of Tibeb Online & Tibeb be Adeababay art festival.

The main focus of this session was giving more insight & knowledge to our artists and curators on how they can curate an interactive, audience-engaging, theme and advocacy-oriented, managing project budget, evaluation techniques, and redefinition of project concepts.

It was then followed by an experience sharing session from Tibeb alumni with a networking & idea exchange session.

Thanks to everyone involved!
👍1